ሁሱ-Husu Page

ሁሱ-Husu Page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሁሱ-Husu Page, Digital creator, Dubai, Abu Dhabi.

30/04/2025

ጓደኝነት

30/04/2025
የነቢያት ሃይማኖትበአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤3፥19 አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَا...
18/04/2025

የነቢያት ሃይማኖት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

3፥19 አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

አላህ ዘንድ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፤ “ሃይማኖት” ማለት “ሀይመነ” ማለትም “አመነ” ወይም “ታመነ” ከሚል የግዕዝ ግስ የረባ ሲሆን “ማመን” ወይም “መታመን” ማለት ነው።
“ዲን” دِين ማለት ደግሞ “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርህ” ማለት ነው፤ “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፦ “ኢሥላም” إِسْلَٰم ፣ “ኢማን” إِيمَٰن እና “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው፤ “ኢሥላም” ማለት “አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ” ሲሆን “ኢማን” ማለት ግን “እምነት” ማለት ነው፤ “ኢሕሣን” ማለት “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፤ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው”፤ አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይሆናል፤ አላህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፤ ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ተቀባይ የለውም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት *“ኢስላም”* ብቻ ነው፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
3፥85 *”ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም”*፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

ነጥብ አንድ
“መልክተኞች”
አላህ መልክተኞቹን በግልጽ ማስረጃዎች ልኳል፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችን ወደ እነርሱ አውርዷል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን”*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ

ነብያችንም”ﷺ” ወደ መልክተኞቹ የተወረደውን ለሰዎች ሊገልጹ ቁርአን ወርዶላቸዋል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون

ነጥብ ሁለት
“ኢሥላም”
ኢሥላም ወደ ነብያት የተወረደው ጭብጥ ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “መታዘዝ”፣ “መገዛት”፣ “ማምለክ” ማለት ነው፤ አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ ኢሥላም ይባላል፤ የኢስላም አስኳሉ፦ “ላ ኢላሀ ኢላ አና” لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَ ማለትም “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚል ነው፤ የዓለማቱ ጌታ ወደ መልእክተኞቹ የሚያወርደው፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚል ቃል ነው፦
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም”፤ ፍሩኝም ማለትን አስታውቁ በማለት *ያወርዳል*፡፡ يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” እና አምልኩኝ በማለት ወደ እርሱ *የምናወርድለት* ቢኾን እንጅ *ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አውዱ ላይ ስንመለከተው ለነቢያችን”ﷺ” የወረደው እና ከእርሳቸው በፊት የወረደው መገሰጫ ይህ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚል ቃል ነው፤ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ብጤ ማለትም “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚል ነው፦
21፥24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ *ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው እና ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው* በላቸው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፡፡ ስለዚህ እነርሱ እምቢተኞች ናቸው፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ الْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ
40፥43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ብጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፡፡ ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው፡፡ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍ

ነጥብ ሦስት
“ወሕይ”
“ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሃ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው፤ ይህንን ወሕይ ወደ ነቢያት የሚያወርደው የዓርሹ ጌታ አላህ ነው፤ ይህንን ለማመልከት “አውሀይና” أَوْحَيْنَا “አወረድን” ብሎ ይናገራል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድን* ወደ አንተም *አወረድን*፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም”፤ ፍሩኝም ማለትን አስታውቁ በማለት *ያወርዳል*፡፡ يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሚን” مُّسْلِمُونَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ለዚህ አንድ አምላክ ፍጹም መታዘዝ ኢስላም ይሰኛል፤ ወደ ነቢያት የሚያወርደው ወሕይ እነሆ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚል ነው፤ ይህ እሳቤ በባይብል የፈጣሪ መለኮታዊ ቃል ቅሪት እንዲህ ተቀምጧል፦
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ *ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ* እዩ፤
ኢሳይያስ 45፥6 *ከእኔም በቀር አምላክ የለም*፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ *ከእኔም ሌላ ማንም የለም*።
ኢሳይያስ 45፥18 ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ *ከእኔም በቀር ሌላ የለም*።
ኢሳይያስ 45፥21 ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
ኢሳይያስ 45፥22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ *እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና* ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
ሆሴዕ13፥4 እኔ ግን ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ *ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም*፥ ከእኔም በቀር ሌላ መድኃኒት የለም።
ኢዮኤል 2፥27 እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ *ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ* እንደሌለ ታውቃላችሁ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

መደምደሚያ
ሚሽነሪዎች፦ “ኢስላም ከነብያችን”ﷺ” በፊት የለም” ብለው ለሰነዘሩት የተቃጣ ሴራና ደባ ከላይ የቀረቡት ነጥቦች በቂ ናቸው፤ ነብያት ሙሥሊም አይደሉም ማለት ሙሽሪክ ናቸው ብሎ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ሙሥሊም ማለት በአንድ አምላክ ምንነትና ማንነት ላይ ማንንም ምንንም ሳጋሩ የሚያመልክ ማለት ነውና።

ስለዚህ ከነብያችን”ﷺ” በፊት ሁሉም ነቢያት ያስተማሩት ኢስላምን ነው። ይህ የተውሒድ ትምህርት በመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ ሲሆን ወደ ነብያችን የተወረደ ነው፤ እርሱም በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው፦
20፥133 «ከጌታውም በኾነ ተዓምር አይመጣንምን?» አሉ *በመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸውምን*? وَقَالُوا لَوْلَا يَأْتِينَا بِآيَةٍ مِّن رَّبِّهِ ۚ أَوَلَمْ تَأْتِهِم بَيِّنَةُ مَا فِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ
26፥196 *እርሱም በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው*፡፡ وَإِنَّهُ لَفِي زُبُرِ الْأَوَّلِينَ
21፥24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ *ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው እና ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው* በላቸው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፡፡ ስለዚህ እነሱ እምቢተኞች ናቸው፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ الْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ

✍ ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ

Facebook ፦ ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም

ከ አፋር ክልል የምስጋና ወረቀት
16/04/2025

ከ አፋር ክልል የምስጋና ወረቀት

12/04/2025

Husu neg

ሁሱ ነኝ👇👇👇👇
11/04/2025

ሁሱ ነኝ
👇👇👇👇

Husu_neg
10/04/2025

Husu_neg

Address

Dubai
Abu Dhabi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሁሱ-Husu Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share