WOLLO MEDIA

WOLLO MEDIA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from WOLLO MEDIA, Digital creator, Emirates, Dessie.
(7)

16/08/2026

❤❤😘

WOLLO MEDIA

16/08/2026

ኩሌ መጋሌዋ❤❤😘

WOLLO MEDIA

16/08/2026

ሸጋ ብቻ 👰👌

WOLLO MEDIA

16/08/2026

የወሎ ልጅ 🧒👌

WOLLO MEDIA

አምባሰል የአምባሰል ወረዳ በደቡብ ወሎ ዞን ስር ከሚገኙ ወረዳዎች  መካከል አንዱ ነው። አምባሰል በሰሜንየሀብሩና የጉባላፍቶ ወረዳ ፣ በደቡብ የተሁለደሬና የኩታበር ወረዳ ፣በምስራቅ የተሁለደ...
16/08/2026

አምባሰል

የአምባሰል ወረዳ በደቡብ ወሎ ዞን ስር ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው።

አምባሰል በሰሜንየሀብሩና የጉባላፍቶ ወረዳ ፣ በደቡብ የተሁለደሬና የኩታበር ወረዳ ፣በምስራቅ የተሁለደሬና በከፊል የሀብሩ ወረዳ እንዲሁም በምእራብ የደላንታና የተንታ ወረዳ ጋር ያዋሰናል፡፡

የወረዳው የቆዳ ስፋት 92 ሺህ 700 ሄ/ር ፤ወረዳው ውጫሌ ከተማን ጨምሮ በ25 ቀበሌዎች የተዋቀረ ነው፡፡ የወረዳው የአየር ንብረት ወይና ደጋ 50%፣ ደጋ 29.47% ቆላ 20.3%፣ውርጭ 0.4% ነው፡፡ የመሬት አቀማመጡ ወጣ ገባ 36%፣ ተራራማ 46%፣ ሸለቆ 12%፣ ሜዳማ 6% ነው፡፡

ወረዳው በሁለት ታላላቅ ተፋሰሶች የተከፈለ ሲሆን እነሱም የሚሌ አዋሽ ተፋሰስና የአባይ ተፋሰስ ናቸው፡፡

የአምባሰል ወረዳ አሁናዊ ገፅታ በከፊል፡-

በአምባሰል ወረዳ መ/ኮ ቢሮ
WOLLO MEDIA

ኮቱማ!!!ሽቱ ብሬ ከረሚሌ ዳማ፤ሸገናይ ወሎየ...በአንቻሮ በቃሉ ኮቱማ ኮቱማ፤አንች ብቅ ስትይ...በአንችው መጀን ብሎ....ይገለጥ የለም ወይ የወሎ ከራማ።እንደ ከሚሴዎች...እስኪ ሸብረክ በ...
16/08/2026

ኮቱማ!!!

ሽቱ ብሬ ከረሚሌ ዳማ፤
ሸገናይ ወሎየ...
በአንቻሮ በቃሉ ኮቱማ ኮቱማ፤
አንች ብቅ ስትይ...
በአንችው መጀን ብሎ....
ይገለጥ የለም ወይ የወሎ ከራማ።

እንደ ከሚሴዎች...
እስኪ ሸብረክ በይ...
በአንገት በወገብሽ ደግሞ ተደለቂ ፤
ፋጦ አቀበቱ ላይ...
አበጀሽ ተብለሽ በአገሩ ዱበርቴ እንድትመረቂ።

እስኪ ሰበር ሰካ...
እርም እርም ይበል እግርሽ መሬት ይምታ፤
ሸጋ ልጅ ሲደለቅ...
እንደ ዋርካ ቅጠል...
አሁንም አሁንም ጠንዝሎ ይረግፋል ያገሩ በሽታ።

በላይ በጥሙጋ ሳ-ፈ-ላ-ል-ግ-ሽ፤
ታቹን በጨፋ በር ሳ-ፈ-ላ-ል-ግ-ሽ፤
ላዩን በራህመቶ ሳ-ፈ-ላ-ል-ግ-ሽ፤
ቦርከና ወንዙ ዳር ተገኘ ዛ-ት-ሽ፤
የምወድሽዋ...
ወትሮም የውሃ ዳር ውብ ቄጤማ ነሽ፤
እስኪ ጠይቂያቸው....
የጉዝጓዝን ሃጃ ያውቃሉ እ-ና-ት-ሽ፤
መርሃባ በይኝ....
አንቺም ተጎዝጎዢ እኔም ል-ካ-ድ-ም-ሽ።

በካሊድ አል ረሻድ
WOLLO MEDIA

‎ወሎ ገሩ መጀን ‎የቁንጅና ንግስት ያቺ ወሎየዋ‎ሸጋ የሚያበቅለው ናፈቀኝ ቀየዋ‎ከልክ ያለፈ ነው አጃኢብ ነው አቦ‎እጇ ደምቆ ባ'ምባር እግሯ ደግሞ ባ'ልቦ‎አላውራው ይቅርብኝ ስለ ደግነቷን‎...
15/08/2026

‎ወሎ ገሩ መጀን
‎የቁንጅና ንግስት ያቺ ወሎየዋ
‎ሸጋ የሚያበቅለው ናፈቀኝ ቀየዋ
‎ከልክ ያለፈ ነው አጃኢብ ነው አቦ
‎እጇ ደምቆ ባ'ምባር እግሯ ደግሞ ባ'ልቦ
‎አላውራው ይቅርብኝ ስለ ደግነቷን
‎ለወግም አይመች ላላዩት ውበቷን
‎አርሂቡ ተብየ ብገባ ከቤትሽ
‎አምላክ ተጠቦበት ቢረታኝ ውበትሽ
‎ወሎ ገሩ መጀን እላለሁኝ እንጂ
‎ባንቺ አልመጀንም ምንም ብትቆነጂ
‎ለምን እንዳትይኝ ይረግፋል ቁንጅና
‎ደግሞ ባንቺ ፍቅር አልጨክንምና
‎ወሎም ገርነቱ አያረጅምና
‎አንቺን እንዲሠጠኝ ...
‎ወሎ ገሩ መጀን አልኩኝ እንደገና!!

WOLLO MEDIA

አንባር አልቦው ይቅር-           ማስጌጡም ይቅርበትአይኑረው ጠመንጃ - ሺ ገዳይ                        ተብሎ አይፎከርለትብቻ ወሎ ይሁን-                አያጣም ...
15/08/2026

አንባር አልቦው ይቅር-
ማስጌጡም ይቅርበት
አይኑረው ጠመንጃ - ሺ ገዳይ
ተብሎ አይፎከርለት
ብቻ ወሎ ይሁን-
አያጣም ሰው'ነት።

በሀዩ የደሴዙሪያዋ
WOLLO MEDIA

**ወሎየነት ውበት....እረ ደሴ ደሴ  ገራዶ ገራዶአለቀልሽ ልቤ  ተንዶ ተንዶ...ወልድያ ና ቆቦ ውጫሌ ውርጌሳየሸጋወች አገር ለምለሚቱ መርሳየሰጠሽኝ ፍቅር አለኝ አልረሳ... በየጁወች ቀየ ...
14/08/2026

**ወሎየነት ውበት....
እረ ደሴ ደሴ ገራዶ ገራዶ
አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ...
ወልድያ ና ቆቦ ውጫሌ ውርጌሳ
የሸጋወች አገር ለምለሚቱ መርሳ
የሰጠሽኝ ፍቅር አለኝ አልረሳ...

በየጁወች ቀየ በወሎየወች ቤት
ሃራ ጥጋጥጉን ብዙ ዱአ አለበት..

ይህ ሁሉ መኳኳል ምን ያደርግልሻል
ወሎየ ነኝ ብዝትይ ስሙ ይበቃሻል..
ወሎየነት ውበት....

WOLLO MEDIA

ሽንጧ ላይ ያረፈው ፀጉሯ ወርዶ ወርዶ፣የሚያንፀባርቀው ጥርሷ እንደበረዶ፣ወዲያ ማዶ ቆማ ባይኗ ብትጠቅሰኝ፣አረፈብኝ እና ፍቅሯም ቀሰቀሰኝ።ማራኪው ከንፈሯ ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፣የወሎ ልጅ ፍቅር ል...
14/08/2026

ሽንጧ ላይ ያረፈው ፀጉሯ ወርዶ ወርዶ፣
የሚያንፀባርቀው ጥርሷ እንደበረዶ፣
ወዲያ ማዶ ቆማ ባይኗ ብትጠቅሰኝ፣
አረፈብኝ እና ፍቅሯም ቀሰቀሰኝ።
ማራኪው ከንፈሯ ሳሙኝ ሳሙኝ ይላል፣
የወሎ ልጅ ፍቅር ልብ ያንቀዋልላል።

በአቡ ሰልማን
WOLLO MEDIA

Address

Emirates
Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WOLLO MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share