Ethio Vibe

Ethio Vibe Let's be the boss on time

01/09/2025

Celebrating my 3rd year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Hi በለኝ ስልከን በወስጥ መሰመር ....
10/07/2025

Hi በለኝ ስልከን በወስጥ መሰመር ....

ትራዎሬ አለምን ያስደመመ ውሳኔ ማሳለፉን ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል‼️የቡርኪናፋሶው የሽግግር ፕሬዚዳንት ትራዎሬ ቡርኪናፋሶ ከቀረጥ ነፃ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖራት ውሳኔ አሳልፈዋል።...
11/04/2025

ትራዎሬ አለምን ያስደመመ ውሳኔ ማሳለፉን ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል‼️

የቡርኪናፋሶው የሽግግር ፕሬዚዳንት ትራዎሬ ቡርኪናፋሶ ከቀረጥ ነፃ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖራት ውሳኔ አሳልፈዋል። "ህዝቤ በምዕራቡ ዓለም ኒኮሎኒያሊዝም እጅ ለረጅም ጊዜ ተሰቃይቷል" ያሉት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ አሁን በቡርኪናፋሶ ቀረጥ የሚባል ነገር አይኖርም ብለዋል።

ይህ ውሳኔያቸው ቡርኪናፋሶን ከዓለም ሀገራት ከቀረጥ ነፃ በመሆን የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል።

በዚህ ውሳኔያቸው በርካታ የዓለም ሀገራት የተደመሙ ሲሆን በዚህ ውሳኔ የተደመሙት የዓለም ቁጥር አንድ ባለሃብት የሆኑት ኤሌን መስክ ኢብራሂም ትራዎሬን በቅርቡ ሊያናግሩት እንደፈለጉ ከተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።
=======================

24/03/2025

ወፍረት የምቀንሱ የስፖርት አይነቶች part 2 😋

23/03/2025

ክብደት ለመቀነስ ጠቃሚ ምክሮች 😋

በሁለት አመታት ተአምር የሰራ መሪ !ትንሹ ሳንካራ ኢብራሂም ትራኦሬ   | ‹‹የእኔ ትውልድ የሆነው አፍሪካዊ አኅጉሪቱ ይህን ሁሉ ሀብት ታቅፋ እንዴት እንደደኸየች ሁሌም ይጠይቃል፡፡ዛሬም ድረ...
23/03/2025

በሁለት አመታት ተአምር የሰራ መሪ !
ትንሹ ሳንካራ ኢብራሂም ትራኦሬ

| ‹‹የእኔ ትውልድ የሆነው አፍሪካዊ አኅጉሪቱ ይህን ሁሉ ሀብት ታቅፋ እንዴት እንደደኸየች ሁሌም ይጠይቃል፡፡
ዛሬም ድረስ ባርነት ሊጫንብን ጥረት ይደረጋል፤››

ትንሹ ሳንካራ ኢብራሂም ትራኦሬ

ኢትዮጵያ ድሮን 🇪🇹ማምረት ጀመረች::በኢትዮጵያውያን እጆች የተሰሩ ሰው አልባ የሰማይ በራሪዎች ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ይመረቃሉ።የባ...
08/03/2025

ኢትዮጵያ ድሮን 🇪🇹
ማምረት ጀመረች::

በኢትዮጵያውያን እጆች የተሰሩ ሰው አልባ የሰማይ በራሪዎች ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ይመረቃሉ።

የባዳ ተለላኪ ባንዳዎች “ድሮን ምን ይሰራል?” የሚል ጽሁፍ እያዘጋጃችሁ ጠብቁን ::

08/03/2025

Just in ሰበር ዜና : ልክ እንዴ ቱርክ : ቻይና : አሜሪካ እና ኢራን ኢትዮጵያ የራሷን የድሮን ተክኖሎጂ አቅሟን መገባት የምያስችል ቁመና ላይ መድረሷን የምያሳይ Skywin የድሮን ማምረቻ ፋብሪካ አስመረቀች ::

Skywin dron 👉 Made in Ethiopia 🇪🇹

08/03/2025

የጠላት ተልዕኮ አስፈፃሚ ፈረሶች :: ምንም ያህል የፖለቲካ ልዩነት ብኖረንም ሀገር የጋራችን ናት ! መሪ ይመጣ ይሄዳል ግን ሀገር የእኔ ና ያንተ ለልጆቻችን የምናስረክባት ብቼኛ ቅርሳችን መሆኗን ልብ ልንል ይገባል ።

እንቁራሪቷ ኩሬ ውስጥ ሆና 'እዚያ ማዶ ያለው ከተማ ይቃጠላል' እያለች ትጨነቃለች።እንደ አጋጣሚ አንድ ሰው በአጠገቧ ሲያልፍ 'ወዳጄ ለፖሊስ ልትደውልልኝ ትችላለህ?' ትለዋለች...ሰውየውም ገ...
27/01/2025

እንቁራሪቷ ኩሬ ውስጥ ሆና 'እዚያ ማዶ ያለው ከተማ ይቃጠላል' እያለች ትጨነቃለች።

እንደ አጋጣሚ አንድ ሰው በአጠገቧ ሲያልፍ 'ወዳጄ ለፖሊስ ልትደውልልኝ ትችላለህ?' ትለዋለች...ሰውየውም ገርሞት 'ምን ሆንሽ ብዬ ነው የምደውውልልሽ?' ይላታል።

'ኧረ ባክህ እዛ ማዶ ሰደድ እሳት ተነስቷል ብለህ ደውል' አለችው።

ሰውየውም 'እሳቱ ያለው እዛማዶ አንቺ ምን አስጨንቆሽ ነው ደውል የምትይኝ?' አላት።

'አየህ እሳቱን እዚያ እያለ ካላቆምነው እዚህ ይመጣል። ያንዱ መቃጠል የኹላችን መቃጠል ሆኖ ካልተሰማን በኋላ መከራው ለኹላችን ይተርፋል" ትለዋለች።

ሰውዬውም አንቺ ያለሽው ውሃ ውስጥ እንዴት እሳቱ ያገኝሻል? አላት።

"እነዚያ ሰዎች እኮ እሳቱ ከባሰባቸው ውሃ ለመቅዳት ይመጣሉ። ያንጊዜ እኔን አብረው ጨልፈው ሊወስዱኝ ይችላሉ።" ስትል ትመልስለታለች።

"ቀልደኛነሽ" ብሏት ትቷት ይሄዳል.....

ወደ ማዶ አሻግረህ የምታየው የሌሎች ችግር አንድ ቀን ወደ አንተ ቤት ይገባል ...የሰዎችን ችግር እያይህ አትለፍ። የሰዎችን ችግር ስትፈታ የራስህን ችግር እያራክ መሆኑን ዕወቅ ❤
ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ
Via Haileyesus Desta

ትራኦሬ‼በ 2 አመት የፕሬዝዳንት ዘመኑ ኢብራሂም ትራኦሬ ለቡርኪና ፋሶ ምን ሰራ?1. የቡርኪና ፋሶ GDP ከ18.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 22.1 ቢሊዮን ዶላር እንድያድግ አድርጓል።2. ከዓለም ...
26/01/2025

ትራኦሬ‼

በ 2 አመት የፕሬዝዳንት ዘመኑ ኢብራሂም ትራኦሬ ለቡርኪና ፋሶ ምን ሰራ?

1. የቡርኪና ፋሶ GDP ከ18.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 22.1 ቢሊዮን ዶላር እንድያድግ አድርጓል።

2. ከዓለም አቀፍ ገንዘብ አበዳሪ እና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ገንዘብ አልተበደረም ድጋፍም አላገኘም::

3. የሚኒስትሮችን እና የፓርላማ አባላትን ደም እና ወዝ በ30% በመቀነስ የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ በ50% ጨምሯል።

4. የቡርኪና ፋሶን የሀገር ውስጥ ዕዳ ከፍሏል።

5. በቡርኪና ፋሶ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የቲማቲም ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን አቋቁሟል

6. የአገር ውስጥ የማቀነባበር አቅሞችን ለማሳደግ ዘመናዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ፋብርካ አስመርቋል።

7. እሴት ያልተጨመረበት የቡርኪና ፋሶ ወርቅ ወደ አውሮፓ እንዳይወጣ አድርጓል

8. የቡርኪና ፋሶ ሁለተኛ ግዙፍ የጥጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ገንብቷል።

9. አርሶ አደሮችን የእደ ጥበብ ስራ ለማበረታታት ለመርዳት ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ለዕደ-ጥበብ ጥጥ ማቀነባበሪያ ከፍቷል።

10. የብሪታንያ ህጋዊ ዊግ እና ጋውንን በአካባቢ ፍርድ ቤቶች እንዳይለብሱ በመከልከል የሀገረው ሰው ባህላዊ የቡርኪናቤ ልብሶችን እንድለብስ አበረታትተዋል።

11. ምርትና ምርታማነትን ለማሳደ እርሻ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አደርሶ አደሮች ከ400 ትራክተሮች፣ 710 የውሃ ፓምፖች እና 714 ሞተር ሳይክሎች በማከፋፈል ለግብርናውን ነማዘመን ስራ ሰርቷል።

12. የግብርና ምርትን ከፍ ለማድረግ ምርጥ ዘርና ሌሎች የእርሻ ግብአቶችን አቅርቧል።

13. የቡርኪና ፋሶን የቲማቲም ምርት ወደ ስልጣን ስመጣ ከነበረበት 315,000 ሜትሪክ ቶን በ2024 ወደ 360,000 ሜትሪክ ቶን አሳድጓል።

14. የሩዝ ምርት በ2022 ከነበረበት 280,000 ሜትሪክ ቶን በ2024 ወደ 326,000 ሜትሪክ ቶን አሳድጓል።

15. የፈረንሳይ ሚዲያን በቡርኪና ፋሶ አግዷል።

17. የፈረንሳይ ወታደሮችን ከቡርኪና ፋሶ አስወጥቷል።

18. መንግስታቸው አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት ነባሮቹን በማስፋት እና የጠጠር መንገዶችን ወደ አስፋልት ደረጃ እያሳደገ ነው።

ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ ተገለፀ******በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷ...
04/01/2025

ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ ተገለፀ
******

በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።

በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን የፋብካው ስራ አስኪያጅ አቶ አሊ ሁሴን ኡመር ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ ሁኔታ በአከባቢው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነባቸው ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉን የገለፁት አቶ አሊ ሁሴን፤ ከተፈጥሮ አደጋ በተጨማሪ በፋብሪካው ንብረት ላይ ስርቆት እንዳይፈጸም ከመከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና ከዞን ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የፋብሪካውን ንብረት ለማትረፍ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙ ተጠቅሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ አካባቢዎች ነዋሪዎችን የማራቅ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማስታወቁ ይታወቃል፡፡

በተለይም የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማስፈር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

Ebc

Address

Dubai

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Vibe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Vibe:

Share