
10/03/2025
"አዎጅ" "አዎጅ" በል" የስማህ ላስማ አስማ"
የአማራ ክልል የአብክመ ፍርድ ቤት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደር
ስራተኞችን ጥቅም፣የስራ ልምድ፣ ሳያስከብር በቸልተኝነት
መመልከቱ የዘመኑን የፍትህ ደረጃ ምን ላይ እደደረስ የሚያሳይ
ነው። እኛ የፍ/ቤት የአስተዳደር ስራተኞች በአሽባሪነት የተፈረጅን
የማፊያ ስብስብ ወይንም የፖለቲካ ቀስቃሺ ፓርቲ ሳንሆን
እራበን፣ጠማን፣ በምንስራው ልክ ይከፈለን፣የስራችን ጥቅሙና
አግባብነቱ ይታወቅልን፣ እደማንኛውም የኢትዮጵያ የመንግስት
ስራተኞች ጥቅማችንና መብታችን ይከበርልን ብለን የምንጠይቅ
ሚስኪንና ሀገር ወዳድ፣ህዝብ አገልጋይ ዜጎች ነን።
ቢሆንም ግን የዳኞች አስተዳደር ጉባኤና የፍርድ ቤት ሺማምንቶች
የራሳቸውን ጥሩ ኑሮ ከነ ደመወዙ እየበሉ፣ለልጆቻቸው ቤታቸውን
እየስሩ፣ልጆቻቸውን እያስተማሩ የእኛን የመብት ጥያቄ በአግባቡ
መዝኖ አለመመለስ የስግብግብነት እጁን ያረዘመ የታወረ የፍትህ
ስርዓት ላይ እየዎኘን መሆኑን በግልፅ ያሳየናል።
በአጠቃላይ ከፍትህ ተቋም እየስራን ፍትህ ያጣን፣ ድምፃችን
የታፈነ፣ ብሎም የተረገጥን በመሆናችንና ፍርድ ቤት ማለት
በሚዛን የተወከለ ሁሉም እኩል የሚስፈርበት ቢሆንም የፍርድ
ቤት የአስተዳደር ስራተኞችን ስንመለከት ጥግ የሌለው በደል
እየደረስብን ይገኛል።
የአብክመ ፍርድ ቤት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደር ስራተኞች
የሞራላዊ ድሺቀት፣በኑሮ ማበሳቆል፣ የበይ ተመልካች
ማድረግ፣የመብት ጥያቄወችን ማፈንና መርገጡን " አዎጅ"
"አዎጅ" "አዎጅ" ብለን ቀስቅስን በጋራ በቃ ልንለው ይገባል!!
ስራችንን በቅንነት እየስራን መብታችንን እንጠይቅ። ለዳኞች ብቻ
የተቋቋመውን ኢትዮጵያዊ ግብረ ስናይ ድርጅት የሆነውን የፍርድ
ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቃህ ልንለው ይገባል።
"ፍትህን እየደገፍን ፍትህ እንጠይቃለን "