Kersa Digital Army-East Hararghe

Kersa Digital Army-East Hararghe odeeffannoo sirrii fi maddoota amanamoo Addunyaan geenya.

08/08/2025
08/08/2025
15/04/2025
14/04/2025
11/04/2025

የመደመር እሳቤ ኃይል በማሰባሰብ መርህ ያምናል!

እንደ ፓርቲ የምንከተለው የመደመር እሳቤ ከርዕዮተ አለም ግትርነት ደዌ የተፈወሰ፤ የመሀል መንገድን የሚከተል፤ አካታችነት መገለጫው የሆነ እንዲሁም የሀገር በቀል ጥበብ ለሀገር በቀል ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን ግንባር ቀድም ምሳሌ የሆነ እሳቤ ነው፡፡

ከትላንት ውስጥ በጎ ነገሮችን ለመውሰድ የማይታክት፤ ዛሬን እንደ ወረት ወስዶ ነገን በትውልድ አይተኬ ሚና አስውቦ የተሻለች ሀገር መፍጠር እንደሚቻል አልሞ በመንቀሳቀስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ እመርታ ያስመዘገብንበት መንገድም ሆኗል፡፡

በእርግጥም የመደመር እሳቤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የነበረባትን ፖለቲካዊ ቁስል በአግባቡ ለማከም በእጅጉ የረዳን በዋናነትም በርዕዮተ አለም ግትርነት ምክንያት ትላንት አላስፈላጊ በሆኑ መካረሮች የከፈልናቸውን ዋጋዎች መዝኖ በአሰባሳቢ ሀገራዊ ትርክቶች ጸንተን ልዩነቶቻችን ተከብረው ኢትየጵያ በተባለች ውድ ጥላ ውስጥ በጋራ መኖር እንድንችል የጋራ አውድን የፈጠረ ነው፡፡

መደመር አንድ ጉዳይን በርእዮተ አለም ግትርነት ምክንያት እንሰዋለት፤ እንሙትለት፤ እንጋደልበት የሚል አቋም የለውም፡፡

ይልቁንስ እንምከርበት፤ እንወያይበት፤ እንማርበት፤ እንደራደርበት የሚለውን ከግራ ዘመምነት እና ከቀኝ አክራሪነት ያልተሰፋ የመሀል መንገድ ይከተላል፡፡

መደመር በርዕዮተ አለም ችንካር ውስጥ ተዘፍቆ ለአብሮ ሰራተኝነት ጉልበቱ የማይዝል፤ በሀሳብ ጎራ በጠላትነት ፈርጆ ማሰባሰብ ያለበትን አቅም የማይበትን፤ ለአሻጋሪ ሀሳቦች እና መፍትሄዎች ሁሉ እጁ የተዘረጋ የብርሀን መንገድ ነው፡፡

ለዚህም ነው መደመር መንገዳችን ሁለንተናዊ ብልፅግና መዳረሻችን ብለን ጉዞ የጀመርነው፡፡

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kersa Digital Army-East Hararghe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share