29/11/2025
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ
👉 ክብረ በዓል: 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል።
👉 መሪ ቃል: በዋና ከተማዋ የተከበረው ክብረ በዓል "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ነው።
👉አካባቢ እና አላማ: ክብረ በዓሉ አራዳ ፓርክ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን፣ በብዝኃነት ደምቆ የኢትዮጵያውያንን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት የሚያጎላ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።
👉 ተሳታፊዎች: ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የሁሉም ክልሎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
👉 መልዕክት: ከንቲባዋ ክብረ በዓሉ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞን መሰረት መገንባት የሚያረጋግጥ እና በብዝሃነት ውስጥ ያለውን አንድነት የሚያጠናክር እንደሆነ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር እጅ ለእጅ ተያይዞ መትጋት እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።