
09/07/2025
የፋይናንስ ጤንነት‼️
መቼስ የሂሳብ መዝጊያ ወቅትም አይደል? ፋይናንሶችን አለማስታወስ አለማመስገን አይቻልም።
በንግዱ አለም ያሉ ሰዎች የሰኔ 30 ቃለ ጉባኤ ሂሳብ መዝጊያ እና ባላንስ ሺት ጉዳይ ላይ ናቸው።
ጉዳዩ የንብረቶች (Assets)፣ የእዳዎች (Liabilities) እና የባለቤትነት ድርሻዎች (Equity) ጉዳይ ነው።
Assets = Liabilities + Equity
ቀመሩ በአማርኛ።
ንብረቶች = እዳዎች + የባለቤትነት ድርሻ። በሌላ አገላለፅ ድርሻ ማለት ንብረት ሲቀነስ እዳ ማለት ነው።
1. ንብረቶች (Assets) ንግዱ ያለው ዋጋ ወይም ሀብት።
2. እዳዎች (Liabilities)
አንድ ንግድ ድርጅት ለውጫዊ አካላት ያለበት የፋይናንስ ግዴታዎች ወይም ወጪዎች/እዳዎች ናቸው።
3. የባለቤትነት ድርሻ (Equity) - የባለቤቶች ድርሻ ወይም የባለአክሲዮኖች ድርሻ) ትርፉ ማለት ነው።
የፋይናንስ ጤንነት ጉዳይ ለነጋዴ የኅልውና ጉዳዩ ነው።
ሶስቱን ለይቶ ማወቅ እና በተጨባጭ በተግባር መመንዘር የአንድ ነጋዴ ግዴታ ነው።
ብዙ ውስብስ ነገር የለውም። (ወደ ኪስ የሚገባው ከሚወጣው ሲበልጥ ትርፍ ነው።)
ጥልቅ ዝርዝሩን አካውንታንቶቹ እና የፋይናንስ ባለሙያዎቹ ከመሰረቱ በጥሩ ክፍያ እንዲሰሩት መከታተል ነው። ይቺ ጊዜ የእነርሱ ናት!
በጣም ብቁ፣ አነቃቂ፣ ትጉህ እና ጠንቃቃ ፋይናንስ ባለሙዎች የድርጅቱ ግራ ክንፍ አጥቂዎች ነው። ቀኝ ክንፉ ካሽ ይባላል። ካሽ ፍሎው።
ካሽ ፍሎው ከብቁ ፋይናንስ ባለሙያ ጋር መኃል ተጫዎቹን (ስራ ፈጣሪውን) ውጤታማ ጤነኛም ያደርጉታል።