04/06/2025
1. የዐረፋ ቀን መቼ ነው ?
ዐረፋ በእስልምና አቆጣጠር የመጨረሻ ወር የሆነው የዙልሂጃህ ወር 9ኛው ቀን ነው።
2. በዚህ ቀን አላህ ሱ.ወ ብዙ ሰዎችን ከጀሀነም እሳት ነፃ ያወጣል።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ከአረፋ ቀን የበለጠ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም። [ሰሂህ ሙስሊም 1348]
3. ሁጃጆች እና ዐረፋ ?
በዚህ ወር ሁጃጆች የአላህን ቤት ለመዘየር ከተላያዩ ዐለም ሀገራት ዘር ቋንቋ ሳይገድባቸው ይሰባሰባሉ። በዘጠነኛውም ቀን ሁጃጆች ከመካ ወጣ ብሎ በሚገኘው የዐረፋ ስፍራ ይሰበሰባሉ። ቀኑንም አላህን በመገዛት ፣ በማስታወስ፣ በመለመን፣ በመሰል ዒባዳዎች ያሳልፋሉ።
ዐረፋ ላይ መቆም ከሐጅ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው። ነብዩ ﷺ “ሐጅ ማለት ዐረፋ ነው” ማለታቸው ይህንን እውነታ ያሳያል።
"ሐጅ ማለት ዐረፋ ነው።" [ቲርሚዚ፣ 889 |
በዚህ ቀን አላህ የወፈቃቸው ሑጃጆች ሱብሂን ሚና ላይ ከሰገዱ በኋላ ፀሐይ ስትወጣ ተክቢራ፣ ዚክር እያደረጉ ወደ ዐረፋ ለኢባዳቸው ይጓዛሉ።
አላህ የሚመጣውን ሀጅ ይወፍቀን እና እንደ እኔ ይሄን ቦታ ለኢባዳ መዘየር ያልቻለ ምን ያድርግ ?
4. ሀጅ የማያረጉ አማኞች ቀኑን በምን ያሳልፋሉ ?
*. እለቱን በፆም ማሳለፍ
ይህን ቀን መፆም ያለውን ምንዳ አስመልክቶ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"የዐረፋ እለት የፆመ ሰው ያለፈውን አንድ አመት እና የሚመጣውን የአንድ አመት ወንጀሉን ያስምረታል ብየ እከጅላለሁ" ማለታቸው ተዘግቧል። (ሙስሊም)
*. ዱዐ ማድረግ
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ "በላጩ እና ምርጡ ዱዓ በአረፋ ቀን ውስጥ የተደረገ ዱዓ ነው" ብለዋል። [ቲርሙዚ ዘግበውታል] .........(በዱዐቹ አትርሱኝ)
N.B በዚህ ቀን የትኛው ዱዐ ነው ይበልጥ ተወዳጅ ?
ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ እኔም ከእኔ በፊትም የነበሩት ነብያት በዚህ ቀን የምንለው ይህን ዱዐ ነው:
لا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرُ،
ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም። አንድ ነው። አጋርም የለውም። ስልጣን የርሱ ብቻ ነው። ምስጋናም የሚገባው ለርሱ ብቻ ነው።
*. እውነተኛ ተውበትን ማድረግ
በዚህ ቀን አላህ (ሱ•ወ) ከእሳት ነጃ ካላቸው ሰዎች ያደርገን ዘንዳ ፤ ለክብሩ ተናንሰን፣ ለትእዛዙ እጅ ሰተን፣ ከልባችን እያለቀስን መሃርታውን ይቅር ባይነቱን እንዲሰጠን እየለመንን ከሰራናቸው ወንጀሎች በመጸጸት ወደ አላህ (ሱ•ወ) መመለስ ይገባል። ረሱል ﷺ "አላህ ከአረፋ ቀን የበለጠ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም።" ማለታቸው ይታወሳልና።
* በኸይር ነገር መሽቀዳደም
ከወንጀል መራቅ፣ ቁርአንን መቅራት፣ ሱና ሰላቶችን መስገድ፣ አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ)፣ ወላጆችን መርዳት፣ ድሆችን መመገብ፣ ዱዓን ማብዛት፣ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል በዚህ ቀናት ልንሽቀዳደምባቸው የምንችላቸው መልካም ስራዎች ናቸው።
ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
✍