26/09/2025
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን ለኔ የደረሰች የስውሯ ማሪያም ።ለመላው አለም ትድረስ አሜን እልልልልልልልልልልልልል
ግንቦት 2017 አርብ ቀን ከስራ ስገባ ደህና ነበርኩ ድንገት ከምሽቱ 1 ሰአት አካባቢ እንደ ራስምታት ጀመረኝ ሰውነቴ በትኩሳት ተቃጠለ ሽፍንፍን ብዬ ለትንሽ ደቂቃ ተኛሁ እና ስነሳ ወዲያውኑ ጉሮሮዬ በቶንሲል ግጥም አለ ።በፊት ቶንሲል ሲነሳብኝ መጀመርያ ራስምታት አድሮ ጎንና ጎኑ ያብጣል ጨው ሎሚ ቁርንፉድ አፍልቼ ስጉመጠመጥ በተደጋጋሚ ሳጥበው ቶሎ ይቸወኛል። ከባሰ አሞክሳ እውጣለሁ ይተወኛል።የዛን ጊዜው ግን በጣም ይለያል።በአንድ ሌሊት መተንፈስ ሁሉ አቃተኝ ።በፊት የማደርገውን ሁሉ አደረኩ አልሆነም። ህመሙም ተለየ ሰውነቴ ተቃጠለ ውስጤን ግን ይበርደኛል ያንቀጠቅጠኛል ራሰምታቱ: ምራቄን መዋጥ ና አይኔን መግለጥአቃተኝ ።ህመሙ እየጨመረ መጣ ከሌሊቱ 9 ሰአት ሳልተኛ ሆነ ቤተሰብም ጭምር።ወደ ህክምና ለመሄድ ሌሊቱ አልነጋ አለኝ።ትዝ ሲለኝ የስውሯ ማሪያም የቅቤ እምነት አለኝ ጸበሏም ።እንደምንም ተነስቼ አንድ ኩባያ ጸበሏን መዋጥ እያቃተኝ ጠጣሁ ።እኔ የማልረባ ለጥያተኛ ልጇ በጆሮዬ ቅቤዋን በትንንሽ ቆንጥሬ እንድውጥ በሽኩታ መልእክት ውልብ አለኝ ።ደነገጥኩና እንደሰማሁት ድምጽ 3 ጊዜ በትንንሹ አድርጌ እንደምንም ዋጥኩት። በህመሙ ላይ እንቅልፍም አልተኛሁ ከሌሊቱ 11 ሰአት አካባቢ ትንሽ ቀለል አለኝ እና እንቅልፍም ወሰደኝ ቅዳሜ 2 ሰአት ስነቃ ህመሙ ቀንሶልኝ ።ግን ሰውነቴ ድቅቅ ብሏል ። በተኛሁበት ጸሎት አደረኩና ደግሜ ጸበሏን ጠጣሁ ።3 ሰአት ላይ ምግብ እንደምንም በልቼ ተመልሼ ተኛሁ ከቀኑ አምስት ሰአት ቤተሰቤ የሆኑ ሊጠይቁኝ ና ህክምና ሊወስዱኝ መጡ ቀሰቀሱኝ ስነቃ እራስ ምታቱ የለም ወድያ ሲያሰቃየኝ የነበረው ህመም ከድካም ና ትንሽ ትንሽ ስሜቱ በስተቀር የለም ።ጭራሽ ቤተሰቦቼን እስኪገርማቸው ስጋ ጠብሼ አብራቸው በላሁ ትንሽ ቆይቶ እውነት እውነት እላችኋለው ከታች የምትመለከቱት ከቀኝ ጎሮሮዬ ተናንቆኝ ከደም ጋር ፍቆኝ ዋጣ ደሙ ግን ለትንሽ ደቂቃ አልቆመም ።አሁንም ከግራ በኩል ጎሮሮዬ በጣም ፍቆኝ ተናነቀኝና መተንፈስ አቃተኝ ወደውጪ መውጣት አልቻለም ወደውስጥ እየቆረቆረኝ ገባ ና ደም አስተፋኝ 24 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቶንሲል አስመስላ ከጎሮሮዬ ውስጥ ያለን ችግር ፈነቃቅላ አወጣችልኝ ።እንደምታዩት አይደለም ትልቅ ነው መሀሉ አጥንት ነው ።ዳርዳሩ እንደ ስጋ ነው።እልልልልልልልል የኔ ስውሯ ማሪያም በስውር ያልፈታችልኝ የለም ። ለበሽተኛ :ለተቸገረና ለጎደለበት :ላዘነ ለተከዘ: ፍርድ ለተጓደለበት :ልጅ ላጣ: ለሁሉም ትድረስ የኔ አቻም የለሽ :የኔ ሰርክ አዲስ : የኔ ጽጌሬዳ : የኔ ደንጎለል: የሰማዩም የምድሩም እናት :የኔ ሳምራዊ :የኔ ብርሃን :ጌታችንን በድንግልና የወለድሽ ከወለድሽም በኋላ ማህተመ ድንግልናሽ ያልተለወጠ ክብርሽ ከፍፍፍ ይበል ።አንቺ ከተወለድሽ በኋላ እረፍት ያላገኘው ዲያቢሎስ እርርር ድብን ይበል ።