Negarit - ነጋሪት

Negarit - ነጋሪት Negarit is a digital social media platform, providing news, information, insiders leaks and analysis for Ethiopian people.
(2)

Negarit is an independent and non partisan digital social media platform designed to inform, inspire and engage the people of Ethiopia. Reaching people through high-standard, high-quality and high impact multimedia content available in different formats such as youtube, facebook, twitter and other social media formats. Negarit recognizes and appreciates the efforts that citizens make each day in b

uilding a better Ethiopia for all people. Negarit strives to empower disadvantaged groups such as women, youth and people with disabilities etc. Working within collaboration of all people to enlighten, educate and strengthen citizens in order to expose corruption and to create unity between neighboring countries.

ሰበር መረጃበመጨረሻም ሻብያ አፈግፍጓል!ከሰሞኑ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር የተወያዩት የኤርትራ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ኦስማን ሳላህ፣ ኤርትራ በቀይ ባሕር ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመነጋገር መፍቀ...
26/09/2025

ሰበር መረጃ

በመጨረሻም ሻብያ አፈግፍጓል!

ከሰሞኑ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር የተወያዩት የኤርትራ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ኦስማን ሳላህ፣ ኤርትራ በቀይ ባሕር ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመነጋገር መፍቀዷል ተናግረዋል።

የኤርትራ መንግስት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ድርድር ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን በአቋሟ መጽናት ተከትሎ ለመደራደር ይሁንታውን ሰጥቷል።

የባህር በሩ ነገር ቁርጥ እየሆነ ነው !!ኢትዮጵያ ጉዳዩን ገፍታበታለች፡፡ የባህር በር ጥያቄዋን በሰሞንኛው የተመድ ጉባኤ ላይ በግልጽ አሳውቃለች፡፡ፕሬዝዳንት ታዬ በ80ኛው የተባበሩት መንግስ...
26/09/2025

የባህር በሩ ነገር ቁርጥ እየሆነ ነው !!

ኢትዮጵያ ጉዳዩን ገፍታበታለች፡፡ የባህር በር ጥያቄዋን በሰሞንኛው የተመድ ጉባኤ ላይ በግልጽ አሳውቃለች፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ቀይ ባሕርን እና ህንድ ውቅያኖስን የሰው ልጆች "የጋራ ቅርስ" ሲሉ በመግለፅ፣ ሁሉም ሀገራት እኩል ተደራሽነት እንዲኖራቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

አያይዘውም ከፍተኛ ባሕርን የሰው ልጅ የጋራ ቅርስ አድርጎ የሚገልጸው እና ሁሉንም ሀገራት በእኩልነት የመጠቀም መብትን የሚያረጋግጠው የዓለም አቀፍ ሕግ እውን መሆን አለበት ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዋዛ ቱርክሜኒስታን ተካሄዶ በነበረው ሶስተኛው የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ጉባኤ ላይ የተናገሩትን በማስታወስ፣ "አንድም ሀገር በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ምክንያት ከልማት ዕድሎች ሊገለል አይገባም" ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀይ ባሕርና በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለሚገኙ ሁሉም ሀገራት እኩል ልማትና ደህንነትን ለማረጋገጥ "ሁሉን አቀፍ አካሄድ" እንደምትከተል ገልፀው "ህጋዊ የፖሊሲ ግቧን በዲፕሎማሲያዊና በሰላማዊ ተሳትፎ እንደምታስቀጥል" ቃል ገብተዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛ ትልቅ የሕዝብ ብዛት ያላት እና ከፍተኛ የባሕር ንግድ ያላት እንደመሆኗ በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ ደኀንነት ላይ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ መግለፃቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ኢራን በአስቸኳይ ዜጎችን መፍታት እንዳለብሽ አሳስባለሁ !/ኢማኑኤል ማክሮን/‎‎‎የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለኢራን ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተሰማ ።‎‎እሮብ እለት ከኢራ...
25/09/2025

ኢራን በአስቸኳይ ዜጎችን መፍታት እንዳለብሽ አሳስባለሁ !/ኢማኑኤል ማክሮን/


‎የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለኢራን ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተሰማ ።

‎እሮብ እለት ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) በኩል ውይይት ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢራን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሶስት የፈረንሳይ ዜጎችን በአስቸኳይ እንድትፈታ አሳስበዋል ቴህራን የኒውክሌር ግዴታዋን ማክበር እንዳለባት እና ቴህራን የኒውክሌር ማበልፀግ በአለምአቀፋዊው ህግ ተገዢ የመሆን ግዴታዋን ማክበር እንዳለባት አሳስበዋል።

‎ማክሮን በ X ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ ላይ "ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ጋር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ተገናኝቻለሁ።እንደተገናኘን በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ ትኩረት ሰጠኋቸዉ ጥያቄዎች መካከልም በኢራን በእስር ላይ የሚገኙትን ሴሲል ኮህለር፣ ዣክ ፓሪስ እና ሌናርት ሞንቴርሎስ የተባሉትን ዜጎቻችን በዘፈቀደ የታሰሩና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈፀሙባቸዉ መሆኑን በመግለፅ በአስቸኳይ መፈታት እንዳለባቸው መግለፅ ነዉ" ሲል ጽፏል።

‎“ፈረንሳይ ልጆቿን በፍጹም አትተወም፤ አቋማችን ግልጽ ነው፤ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማግኘት የለባትም” ሲሉ የፈረንሳይን ጽኑ አቋም አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎ማክሮን ከጀርመን እና ከእንግሊዝ ጋር የተቀናጀ ዕርምጃ እንደሚወሰድ በማሳወቁ የኢራንን የኒውክሌር ተገዢ አለመሆንን ጉዳይ ገልፀው ኢራን የኒውክሌር ግዴታዎቿን ካላሟላች አዲስ ማዕቀብ እንደሚጣልባት ገልፀዋል ።

‎የድርድሩን አስፈላጊነትን በማጉላት የተያገሩት ማክሮን "እኛ የማንደራደርባቸውን ጥያቄዎች ለኢራን ፕሬዝዳንት በድጋሚ ግልፅ አድርጌአለሁ፡ በኢራን ውስጥ የIAEA ተቆጣጣሪዎች ፍተሻ እንዲያደርጉ፣ የበለፀጉ የቁሳቁስ ክምችቶችን በተመለከተ ግልፅነት የተሞላበት መረጃ እንዲሰጡ እና ድርድር እንዲጀምሩ ነግሬያቸዋለሁ " ብለዋል።

‎"ለአካባቢው ደህንነት, ለአለም መረጋጋት ሲባል ጥቂት ሰዓታት ብቻ በቀሩት አድል እንድትጠቀም እመክራለሁ ቀሪዉ ላስቀመጥናቸው ህጋዊ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት የኢራን ጉዳይ ነው ። ሲሉ ተናግረዋል በማለት የዘገቡት ሮይተርስ ኢንዲያ ቢታይም ናቸዉ ።

‎በታዴ የማመይ ልጅ

እናቱን አዝሎ የሚንቀሳቀሰው ቻይናዊ❤👌 በቻይና ሲቹዋን ግዛት የሚኖሩ አንድ የ51 ዓመት አዛውንት፣ ለእድሜ ባለጸጋ እናታቸው ያላቸውን የማይተመን ፍቅር እና እንክብካቤ በማሳየት የብዙዎችን ል...
24/09/2025

እናቱን አዝሎ የሚንቀሳቀሰው ቻይናዊ❤👌

በቻይና ሲቹዋን ግዛት የሚኖሩ አንድ የ51 ዓመት አዛውንት፣ ለእድሜ ባለጸጋ እናታቸው ያላቸውን የማይተመን ፍቅር እና እንክብካቤ በማሳየት የብዙዎችን ልብ ነክተዋል።

የ88 ዓመት እናታቸው ከወደቁ በኋላ ሽባ በመሆናቸው እና በዊልቸር ላይ እንዲንቀሳቀሱ በመገደዳቸው ምክንያት፣ ዓለማቸው እንዳይጠብ ወስነዋል። አዛውንቱ እናታቸውን አዘውትረው ወደተለያዩ ቦታዎች ይወስዳሉ። የሚጓዙበት ቦታም በዊልቸር ለመጓዝ አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜ፣ እናታቸውን በትከሻቸው ላይ በባህላዊ የጨርቅ ማዘያ በጀርባቸው ያዝሏቸዋል።

ይህ የፍቅር እና የልጅነት አብነት በመስመር ላይ “በጣም ታዛዥና መልካም ልጅ” የሚል ስያሜ አትርፎላቸዋል። በእሳቸው በኩል የሚታየው የማይናወጥ ፍቅርና እንክብካቤ ከቤተሰብ ጋር ሲሆን ምንም ዓይነት መንገድ ለመሄድ አስቸጋሪ እንዳልሆነ የሚያሳይ ልብ የሚነካ ማስታወሻ ሆኗል።

የእኚህ አዛውንት ታሪክ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፏል፤ እንዲሁም ለቤተሰብ ፍቅር እና እንክብካቤ ትልቅ ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል ሲል Menehariya ዘግቧል።

ከሻይ ቅጠል አምራችነት ወደ ፕሬዝዳንትነት !የ85 አመት አዛውንቱ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣናቸው በድጋሚ ተመልሰዋል።የናፈቀኝን ህዝብ በትጋት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ ህዝቡ ቢቻ አይደለም የናፈኩት...
24/09/2025

ከሻይ ቅጠል አምራችነት ወደ ፕሬዝዳንትነት !

የ85 አመት አዛውንቱ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣናቸው በድጋሚ ተመልሰዋል።

የናፈቀኝን ህዝብ በትጋት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ

ህዝቡ ቢቻ አይደለም የናፈኩት እኔም ደግ ዜጎቼም ናፍቀውኛል ሲሉ ነው ወደ ስልጣን በድጋሚ የተመለሱት የቀድሞ የማላዊ ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ የተናገሩት።

የዘመናት ተቀናቃኘቸው የሆኑትን የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ላዛሪየስ ቼኩዌራን በምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣናቸው ተመልሰዋል።

ላዛሪየስ ቼኩዌራም የምርጫውን ውጤት በጸጋ ተቀብለው ለሙታሪካ እንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከአመስት አመት በፊት ድራማ በመሰለው የፍርድ ውሳኔ ከስልጣናቸው ተነስተው እስር ላይ የቆዩት ሙታሪካ በድጋሚ ስልጣናቸው በምርጫ አግኝተዋል።

ከሰሞኑ በሀገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አብላጫ ድምጽ በማግኘት ወደ ስልጣናቸው የተመለሱት ሙታሪካ ህዝቡ የሚካስበት ትክክለኛው ሰአት ላይ ተገኝቻለሁ ብለዋል።

ሙታሪካ ከስልጣናቸው ከተነሱ ወዲህ የማላዊ ኢኮኖሚ ክፉኛ ተጎቶ መቆየቱን የተናገሩት የሀገሪቱ ሚዲያዎች የኑሮ ውድነቱ ህዝቡን ችግር ውስጥ አስገብቶት ቆይቷል ብለዋል።

ሙታሪካ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ስላላቸው የተበላሹ ነገሮች ለማስተካከል ጊዜ አይወስድባቸውም ሲሉም ጽፈዋል።

ከሻይ ቅጠል አምራች መንደር የተገኙት ሙታሪካ አሁን ላይ 85 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከሙስና እና የሀገሪቱን ሀብት በማባከን ስማቸዉ በተደጋጋሚ ይነሳል።

በ ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ፍልስጤምን ነፃ ለማውጣት "አለም አቀፍ ጦር" እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቀረቡ !የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እንደተናገሩ...
24/09/2025

የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ፍልስጤምን ነፃ ለማውጣት "አለም አቀፍ ጦር" እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቀረቡ !

የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እንደተናገሩት አለም አቀፋዊ ጦር በማቋቋም ፍልስጤምን ነፃ ለማውጣት እና በጋዛ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ለመከላከል እንዲገባ ጠይቀዋል።

በአሜሪካ እና በኔቶ የሚደገፉትን “ጨቋኝ አገዛዝ እና አምባገነንነት”ን የሚቃወሙ ሀገራት ኃይላቸውን አንድ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፣ “የዘር ማጥፋትን የማይቀበሉ ሀገራት ኃይለኛ ሰራዊት እንፈልጋለን… ፍልስጤምን ነፃ ማውጣት አለብን።

የፔትሮ ይግባኝ የኢንዶኔዥያ ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ 20,000 ወታደሮችን ለዚህ ሃይል ለማዋጣት ቃል በመግባት አስተጋብተዋል።

"የእስራኤል ውድ የሆነ የኢንቴል እና የሰለላ ሰነዶችን የያዘ በረከት እጃችን ገብቷል" _ ኢራንየኢራን የስለላ ድርጅት ሀላፊ ኢስማኤል ኻጢብ ምዕራባውያን ባለስልጣናት እና የእስራኤል ባለስልጣ...
24/09/2025

"የእስራኤል ውድ የሆነ የኢንቴል እና የሰለላ ሰነዶችን የያዘ በረከት እጃችን ገብቷል" _ ኢራን

የኢራን የስለላ ድርጅት ሀላፊ ኢስማኤል ኻጢብ ምዕራባውያን ባለስልጣናት እና የእስራኤል ባለስልጣናት ኢራን በወራሪዋ ግዛቶች ውስጥ በከፍተኛ ደርጃ የሳይበር ደህንነቱን በማለፍ ሰርጋ መግባቷን አምነው ለትልቅ ስኬቱ አድናቆታቸውን ገልፀዋል ብለዋል።

እሮብ ዕለት መከላከያን ለማስታወስ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ኢስማኤል ኻጢብ ኢራን ወደ ወራሪው ስርአት ስርጋ በመግባት በተያዙት መሬቶች ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችን ጠቅላላ መረጃ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይፋ አድርገዋል።

የኢራን የስለላ ድርጅት ሀላፊ ኢስማኤል ኻጢብ በተካሄደው የስለላ ኦፕሬሽን የተገኙ በረከቶችን መቀበላቸውን ገልፀው ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ የፈፀሙትን ባለሙያዎች አመስግነዋል።

እ.ኤ.አ. ኦገስት 2 ላይ የኢራን የስለላ ሰራተኞች በሰኔ ወር ውስጥ በእስራኤል ዘመቻ ውስጥ የተሳተፉ ተጨማሪ የእስራኤል የአየር ኃይል አብራሪዎች ፣ አዛዦች እና የድሮን ኦፕሬተሮችን ሙሉ መገለጫዎች አግኝተዋል።

እንደ ሪፖርቶቹ ከሆነ ግኝቱ የእስራኤላውያን አየር ሃይል ሰራተኞች ማንነታቸውን፣ የመኖሪያ ቦታቸውን፣ የስራ ክፍሎችን፣ የጦር ሰፈሮችን እና በሌሎች ወንጀሎች ውስጥ ያላቸውን ሚና ጨምሮ የተሟላ የግል ዝርዝሮችን የያዘ ነው።

የእስራኤል የዜና ማሰራጫዎች በቴሌቭዥን ስርጭት ወቅት ፊታቸውን ሲያደበዝዙ እንደታየው አገዛዙ የሰራተኞቹን ማንነት ለመደበቅ ጥብቅ ጥረት ቢያደርግም የስለላ ኦፕሬሽኑ በተሳካ ሁኔታ መደረጉን ታውቋል።

በጁን 13 የእስራኤል አገዛዝ በኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ኻቲብ የኢራን የስለላ ሰራተኞች የኒውክሌር ፋሲሊቲ ጋር የተያያዙ ሚስጥራዊ የሆኑ የእስራኤል ሰነዶችን እንዳገኙ ገልፀዋል።

"እነዚህ ሰነዶች እና ሌሎች የአገዛዙ ስትራቴጂካዊ መዝገቦች የሀገሪቱን የማጥቃት አቅም ያጎለብታሉ።"

የኢራን የስለላ ድርጅት ሀላፊ ኢስማኤል ኻጢብ ሰለሰነዶች ብዛት ለቀረበላቸው ጥያቄ "ይህ በጣም ትልቅ እድገት ነው ፣ እንዲያውም ከዚህ ቀደም ከተገኘው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰነዶች ጋር ሲነጻጸር ለመግለፅ በጣም ቃል ያጥራል።" ብለዋል።

ኢስማኤል ኻጢብ ንግግራቸው የኢራን ህዝብ ጦርነት ፈልጎ እንደማያውቅ ጠቁሟል። "በውጭ ኃይሎች የሚደገፉ ጠላቶች የኢስላሚክ ሪፐብሊክን ለመገልበጥ እና ለማፍረሰ ሙከራ ቢያደርጉም የሀገሪቱ ታማኝ ልጆች በድፍረት እና በክብር ጠብቀዋል" ብለዋል።

የኢራን የስለላ ድርጅት ሀላፊ ኢስማኤል ኻጢብ:-

"ለአያቶላ አሊ ካሜኔይ አስተዋይ አመራር ምስጋና ይግባውና ለታጠቁ ኃይሎች ጀግንነት ፣ የስለላ ማህበረሰብ ፣ የ14 ኛው አስተዳደር ተግባራት እና የህዝብ አንድነት የኢራን ጥንካሬ ተጠብቋል ።

“በሁለቱም በተጣሉ ጦርነቶች ወቅት ጠላቶች ስርዓቱን ለመጣል ታጣቂዎችና ተገንጣዮች በጥምረት በፂዮናዊያን እርዳታ ሙከራ ቢያደርጉም በአላህ እርዳታ ደኅንነቱ ጸንቷል”

ትራምፕ ሩሲያን "የወረቀት ላይ ነብር" ማለታቸውን ተከትሎ ሞስኮ ጦርነቱን እንደምትቀጥል አስታወቀች !የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድንገት ወደ ዩክሬን ያደረጉትን የአቋም ለ...
24/09/2025

ትራምፕ ሩሲያን "የወረቀት ላይ ነብር" ማለታቸውን ተከትሎ ሞስኮ ጦርነቱን እንደምትቀጥል አስታወቀች !

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድንገት ወደ ዩክሬን ያደረጉትን የአቋም ለውጥ እና ሩሲያን "የወረቀት ነብር" ብለው መፈረጃቸውን ተከትሎ ሞስኮ ጦርነቱን ከመቀጠል በቀር ምንም አይነት አማራጭ እንደሌላት አስታውቃለች። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዩክሬን በውጤታማነት ጦርነቱን ማሸነፍ እንደምትችል የትራምፕን አባባል በመቃወም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጥቃት "ጥቅማችንን ለማረጋገጥ እና ግቦቹን ለማሳካት" እንደምትቀጥል ረቡዕ እለት አስታውቀዋል።

ይህን እያደረግን ያለነው ለአሁኑም ሆነ ለወደፊት የአገራችን ሁኔታ ነው። ለብዙ ትውልዶች በማሰብ ጭምር ነው ስለዚህ ምንም ሌላ አማራጭ የለንም ሲሉ ከሩሲያ አር ቢ ሲ ሬዲዮ ጣቢያ ጋር ዲሞትሪ ፔስኮቭ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። ማክሰኞ ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከተገናኙ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አጋርነታቸውን ወደ ዩክሬን በይፋ ሲያደርጉ ታይቷል ።

ከሩሲያ ጋር ያለውን መቀራረብ ማብቃቱን የገለፁት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት “ሩሲያ ለሶስት አመት ተኩል ያለ አላማ ስትዋጋ የነበረችውን ጦርነት ለማሸነፍ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እውነተኛ ወታደራዊ ሃይል ቢኖራት ትጨርሰው ነበረ” ብለዋል። የሩሲያ ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀት ያስከተለ ሞስኮንም "የወረቀት ሌይ ነብር" እንድትመስል ያደረገ ነበር ብለዋል ሲል የዘገበው bisrat.fm ነው።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኦፕሬት የሚያደርገው ባይራክተር !"Akinci" የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን ይህ የአለማችን የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ስሪት የሆነ ድሮን ለ25 ሰአታት ካለማቛረጥ እየበረረ የ...
24/09/2025

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኦፕሬት የሚያደርገው ባይራክተር !

"Akinci" የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን ይህ የአለማችን የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ስሪት የሆነ ድሮን ለ25 ሰአታት ካለማቛረጥ እየበረረ የጠላትን ይዞታ መሰለል የሚችል ሲሆን ሲታዘዝም እስከ 1500 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሚሳኤሎችን በሆዱ ተሸክሞ የጠላትን ታርጌቶች ያደባያል።

ይህ ተአምረኛ ድሮን በአንድ ጊዜ 8 ሚሳኤሎችን ተሸክሞ እስከ 7500 ኪሎ ኪ.ሜትር እንደሚጓዝ የተነገረ ሲሆን ይህም ማለት ከኢትዮጵያ እስከ ደ/አፍሪካ እንደሚሆን ይገመታል።

ቱርክ ሰራሹ Akinci የተገጠመለት አይን የንስር በመሆኑ የሌዘር አይን ጠላትን አንድ ጊዜ ከተመለከተ በፍፁም ሊስተው አይችልም ተብሎለታል።

"ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣን  ያላቸው ሀገራት ቁጥር ከአምስት መብለጥ አለበት" _ ኤርዶጋንየጸጥታው ምክር ቤት አሰራሩ ላይ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲጵ ጣይብ ኤርዶ...
24/09/2025

"ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣን ያላቸው
ሀገራት ቁጥር ከአምስት መብለጥ አለበት" _ ኤርዶጋን

የጸጥታው ምክር ቤት አሰራሩ ላይ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን ጠየቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን የጠየቁት በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ሲሆን፤ ይህን ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው ተብሏል።

በምክር ቤቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣን ወይም ቬቶ ፓዎር ያላቸው ሀገራት ቁጥር ከአምስት መብለጥ አለበት ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ምክር ቤቱ ላለፉት አራት ዓመታት የሰላ ትችት ሲሰነዘርበት መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ተመድ ለተመሰረተበት ዓላማ መስራት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጸው፤ በዓለም የተወሰኑ ለውጦች መምጣት አለባቸውም ብለዋል፡፡

Via ጋዜጣ+

በአውሮፓ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የአየር ትራፊክ መጨናነቅ ልዩነቱን ተመልከቱ 👇ከጠቅላላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ትንሽ ጭንቅንቅ ይታያል እሱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።
24/09/2025

በአውሮፓ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የአየር ትራፊክ መጨናነቅ ልዩነቱን ተመልከቱ 👇

ከጠቅላላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ትንሽ ጭንቅንቅ ይታያል እሱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።

 ! በልምምድ ላይ እያለች ሞተች!አትሌት ሸዋረግ አለነ አማረ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየችበ2025 የስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ሸዋረግ አለነ አማረ፣ በአዲስ አበባ ል...
24/09/2025

! በልምምድ ላይ እያለች ሞተች!

አትሌት ሸዋረግ አለነ አማረ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

በ2025 የስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ሸዋረግ አለነ አማረ፣ በአዲስ አበባ ልምምድ ላይ እያለች ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተዘግቧል።

አትሌቷ ልምምድ ላይ ሳለች የድካም ስሜት ተሰምቷት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ህይወቷ ማለፉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ኑሮዋን በሜክሲኮ ያደረገችው አትሌት ሸዋረግ አለነ፣ ለልምምድ ወደ አዲስ አበባ መጥታ ነበር። አትሌቷ የቀድሞው አትሌት አለነ አማረ ልጅ ስትሆን፣ አባቷ ለ25 ዓመታት ያህል በአሜሪካ፣ ኒው ዮርክ ሲኖሩ እንደነበርም ታውቋል።

አትሌት ሸዋረግ ከስቶክሆልም ማራቶን በተጨማሪ በርካታ ታላላቅ ውድድሮችን አሸንፋለች። ከነዚህም መካከል፦

* ሜክሲኮ ሲቲ ማራቶን - 2012 እና 2014
* ሳንቲያጎ ደ ቺሌ ማራቶን - 2013 እና 2014
* ማራቶን ኢንተርናሽናል ላላ - 2014

ነፍስ ይማር!

©️Ethio Runner

Address

Addis Ababa
00000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Negarit - ነጋሪት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Negarit - ነጋሪት:

Share

Category