
23/07/2025
የከፋ የሚያደርጉ ነባር ቅርሶች
ክፍል #1
=================================
እንደሚታወቀው የሀገራችን የፖለቲካ ሹመት እና የአሜሪካን ዲቪ የማይደርሰው ይኖራል ተብሎ አይገመትም።
ሁለቱም ድንገት የሚከሰቱ ዕድሎች ናቸው ልዩነታቸው ያው ከሹመት ስትወርድና ወደአሜሪካን ከበረርክ በኃላ እንጂ አመጣጣቸው ድንገት ነው።
ማናችንም ብንሆን ሹመት የሚሰጠን ለመውረድ እንጂ እስከዘላለም አለመሆኑ ሀቅ ነው ስለዚህ አንድ ተሿሚ ከሹመት መውረዱን እርግጠኛ መሆን ያለበት የተሾመ ቀን እንጂ የወረደ ቀን አዲስ ሊሆንለት አይገባም ከሆነም ልክ አይደለም። ለዛሬ ድህረ ሹመት የሚገጥሙንን ሲወርዱ ስዋረዱ የየሚመጡ ገጠመኞችን ጀባ ልበላችሁ!
#በባለፈው በዓል እንኳን አደረሰህ ተብለው ከተላኩ አንድ ሺ አንድ ሜሴጆች መካከል በአሁኑ በአል አምስቱ ሰዎች ብቻ ይልኩልሀል እነሱም አባትህ; እናትህ; ወንድምህ እህትህ እና አንድ በስህተት መውረድህን ያልሰማ ሰው።
#ትናንት "ማቲ ወይም ማርክ" ብለው የሚጠሩህ ዛሬ መውረድህን ስላወቁ "ማቴዎስ ወይም ማርቆስ" ብለው ሙሉ ስምህን ይጠራሉ አይድነቅህ ትንሽ ስቆዩ "ማቶሳ ወይም ማርቆሳ" ማለታቸው አይቀርም የተለመደ ነው።
#የሞባይልህ ጥሪ ይናፍቅሀል ትናንት እናቱ ጥላው ገበያ እንደሄደች ህፃን ስጮህብን የነበረው ሞባይልህ ጥሪውን አቁሞ በሚስትህ ሞባይል ራስህ ደውለህ ጥሪውን አለመቀየሩን ታረጋግጣለህ ኖርማል ነው።
#በጣም የሚቀርቡህ ሰዎች መንገድ ላይ ሲያገኙህ "ወይኔ ቀፎ ቀይሬ የአንተ ስልክ የድሮው ቀፎ ላይ ቀርቶ ሳልደውልልህ" ይሉሀል የያዘው ቀፎ አንተ ከመሾምህ በፊት የገዛውን ነው። "ነው እንዴ" ብለህ እለፈው
#በእግርህ ስትሄድ ያዩህ ሰዎች "ወይኔ ምን ሆነህ ነው" ሲሉህ አትደንግጥ ምንም አልሆንክም ከአይኑ ነው!
#ምደባ ጥየቃ ደብዳቤ ይዘህ ሰው ሀብቶች ጋ ስትሄድ ለምን መጥተህ ነው ይሉሀል? የመጣሁበትን ታውቃለህ በል! ቀጥሎ የትምህርት ዝግጅትህን ይጠይቅና አጣርቼ ነግርሃለው ይልሀል። ምንም የሚያጣራው የለም ተመልሰህ ስትመጣ በአንተ ሙያ መደብ የለንም ይልሀል። አንተ መደብ አጣርተህ የመጣህ መሆኑን እያወቀ
#ሆቴል አንድ ቡናና ግማሽ ሊትር ውሃ ተጠቅመህ አታችመንት ይሁን ካሽ የሚልህ አስተናጋጅ በቅንነት መሆኑን ተረዳ መውረድህን አልሰማም::
#ልጆችህ ምን ሆኖ ነው ጋሼ ቤት መዋል አበዛ ሊሉህ ይችላሉ አትደንግጥ በሹመት ዘመን ያለህን ትርፍ ጊዜ በሙሉ ለእነርሱ አውለህ ከሆነ ኖርማል ይሆናቸዋል ያለበለዚያ ማስረዳቱ ከባድ ነው የዘመኑ ልጅ መልስ ስትሰጠው ሌላ ጥያቄ ማብዛቱ አይቀርም።
#ብሶት አናዛዥ ከአንተ ቀድሞ የወረደ ተሿሚ ያለወትሮው አንተ ጋ ደጋግሞ ሊመጣ ይችላል አታቅርበው የስራ ፈጠራ ሀሳብ አይነግርህ ተጨማሪ ብሶት ነው የሚጭንብህ።
#ከሹመትህ የወረድክ ቀን በሹመትህ ምክንያት የቀረቡህ ጓዶች በሙሉ እንዳትቀርቡ ተብለው ግልባጭ ስለሚደረግላቸው አትደንግጥ ትናንት የወረዱት ገጥሟቸው ነገ የሚወርዱትም ይገጥማቸዋል።
#ኃለቃ (ቦስ) የሚልህ ሾፌርህ "friend ሰላም ነው?" ካለህ "አለው friend እንዴት ነህ?" ብለህ በማዕረግህ መልስለት በቃ አንተን ማዕረግህ "friend" ሆኖ ቆይቷል። ይህም ማዕረግ የሚሠጥህ መልካም ኃለቃ ከሆንክ ነው አለበለዚያ የከፋም አለ።
ክፍል ሁለት ላይ መፍትሔውን ይዤላችሁ እመልስበታለሁ