Awusa.com

Awusa.com A resource and advocacy center for the art, history, culture, ethnography and current affairs of Afa
(1)

በዓለማችን ዉስጥ  ያሉ 10 ትላልቅ ተራሮች እነዚህ ናቸዉ 👇1ኛ. የኤቨረስት ተራራ፡ 8,848.86 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል/ቻይና2ኛ. K2 ተራራ  ፡ 8,611 ሜትር  የሚገኘዉ ካራ...
04/10/2025

በዓለማችን ዉስጥ ያሉ 10 ትላልቅ ተራሮች እነዚህ ናቸዉ 👇

1ኛ. የኤቨረስት ተራራ፡ 8,848.86 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል/ቻይና
2ኛ. K2 ተራራ ፡ 8,611 ሜትር የሚገኘዉ ካራኮራም፣ ቻይና/ፓኪስታን
3ኛ. ካንቺንጁንጋ ተራራ 8,586 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል/ህንድ
4ኛ. ሎተሴ ተራራ 8,516 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል/ቻይና
5ኛ. ማካሉ ተራራ 8,485 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል/ቻይና

6ኛ. ቾ ኦዩ ተራራ 8,188 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል
7ኛ. ዳውላጊሪ ተራራ 8,167 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል
8ኛ. ምናስሉ ተራራ 8,163 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል
9ኛ. ናንጋ ፓርባት ተራራ 8,126 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ፓኪስታን
10ኛ. አናፑርና ተራራ 8,091 ሜትር የሚገኘዉ ሂማላያስ፣ ኔፓል

ከደሴ አሰብ ወደብ 513 ኪሎ ሜትር ብቻ ይርቃል !በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን አሰብ በወሎ ክፍለገር ስር ነበር የሚተዳደረው ።አውሳ አውራጃ የአሁኑ አፋር ክልልንና የቀይ ባህር አፋር( አሰብ ...
03/10/2025

ከደሴ አሰብ ወደብ 513 ኪሎ ሜትር ብቻ ይርቃል !

በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን አሰብ በወሎ ክፍለገር ስር ነበር የሚተዳደረው ።አውሳ አውራጃ የአሁኑ አፋር ክልልንና የቀይ ባህር አፋር( አሰብ ወደብ ያለበት ቦታን )በከፊል ያጠቃልላል።

ልጅ እያሱን ለበርካታ አመታት ደብቀውና በክብር ጠብቀው በታማኝነት ያኖሩት የአውሳ (የአፋር) ሰዎች እንደሆኑ ይታወቃል 🙏

በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ በብዛት ጎልተው የሚታዩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች አሉ።የቱሪዝም መዳረሻዎች ብዛት በቁጥር ለመናገር ቢከብድም፣ አፋር ክልል ...
03/10/2025

በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ በብዛት ጎልተው የሚታዩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች አሉ።

የቱሪዝም መዳረሻዎች ብዛት በቁጥር ለመናገር ቢከብድም፣ አፋር ክልል የሚታወቅባቸው ዋና ዋናዎቹ መዳረሻዎች የሚከተሉት ናቸው። እነዚህ ቦታዎች በጂኦሎጂካል አፈጣጠር፣ በታሪክ እና በዱር እንስሳት ሀብታቸው ልዩ ናቸው።
ዋና ዋና የቱሪዝም መዳረሻዎች:
* ዳናኪል በረሃ (Danakil Depression):
* ይህ ቦታ ከባህር ወለል በታች የሚገኝ ሲሆን፣ በዓለም ላይ ካሉ በጣም ሞቃታማ ቦታዎች አንዱ ነው።
* ኤርታሌ እሳተ ገሞራ (Erta Ale Volcano): በዓለም ላይ በቋሚነት የቀለጠ የላቫ ሐይቅ ካላቸው ጥቂት እሳተ ገሞራዎች አንዱ ነው።
* ዳሎል (Dallol): በብዙ ዓይነት ቀለማት ያሸበረቁ የማዕድን ክምችቶች ያሉት የጂኦተርማል ቦታ ነው።
* የጨው ሐይቆች እና የጨው ማውጫዎች (Salt Lakes and Salt Flats): የጨው ንግድ የሚካሄድበት እና አስገራሚ መልክአ ምድር ያለው ቦታ ነው።
* አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ (Awash National Park):
* ይህ ፓርክ በአዋሽ ወንዝ ሸለቆ የሚገኝ ሲሆን፣ ለየት ያሉ አፍሪካዊ የዱር እንስሳት (እንደ ቅጠል አንበጣ፣ ጦጣ እና የተለያዩ አእዋፋት) መኖሪያ ነው።
* በፓርኩ ውስጥ የሆኑ ሙቅ ውሃ ምንጮች (Hot Springs) እና አዋሽ ገደል (Awash Gorge) ይገኛሉ።
* የታሪክና የፓሊዮአንትሮፖሎጂ ቦታዎች (Historical and Paleoanthropological Sites):
* ሐዳር (Hadar): ታዋቂዋ የጥንት ሰው አፅም ሉሲ (Lucy - Australopithecus afarensis) የተገኘችበት ቦታ ነው።
* አራሚስ (Aramis): አርዲ (Ardipithecus ramidus) የተባለው የጥንት ሰው አፅም የተገኘበት ቦታ ነው።
* የያንግዲ ራሳ ብሔራዊ ፓርክ (Yangudi Rassa National Park):
* ለአፍሪካ የዱር አህያ (African Wild Ass) መኖሪያነት የሚታወቅ ነው።
በተጨማሪም የአፋር ሕዝቦች ባህልና የአኗኗር ዘይቤ በክልሉ ውስጥ ሌላው ትልቅ መስህብ ነው።
እነዚህ ዋና ዋናዎቹ ቢሆኑም፣ በአፋር ክልል ውስጥ ሌሎች ሐይቆች (እንደ አፍዴራ ሐይቅ)፣ ፍልውሃዎች እና ሌሎች ትናንሽ መዳረሻዎች ይገኛሉ።

Afar Histories Gallery

መሪ ማለት ተፅኖ ፈጣሪ፤ ሰርቶ ሚያሳይ፣ ምሳሌ የሚሆን፣ የተናገረውን የሚፈጽም፣ የለውጥ አርአያ የሚሆን፣ የሚያዳምጥና አስተዋይ፣ ለውሳኔ የማይቸኩል እንዲሁም ሚዛናዊ አሰተሳሰብ ያለው ሰዎችን...
02/10/2025

መሪ ማለት ተፅኖ ፈጣሪ፤ ሰርቶ ሚያሳይ፣ ምሳሌ የሚሆን፣ የተናገረውን የሚፈጽም፣ የለውጥ አርአያ የሚሆን፣ የሚያዳምጥና አስተዋይ፣ ለውሳኔ የማይቸኩል እንዲሁም ሚዛናዊ አሰተሳሰብ ያለው ሰዎችን መረዳት የሚችል ውሳኔ የመወሰን አቅም ያለው በጋራና በተናጠል በመስራት ስኬት የሚያሰመዘግብ ነው!!

የለውጥ መሪ ሃጅ Awel Arba 🙏🙏.

የአሰብ ባለርስቶችReform ለብዙ ሀገራት ዕድገት አይነተኛ ሚና ተጫውቷል። ወደፊት በማሳትመው የትርጉም ስራ የዘመናዊ ቻይና ፈጣሪ የሚባለው ዴንግ ሾኦፒንግ የፈጠራቸው ሶስት  ሪፎርሞች  እን...
01/10/2025

የአሰብ ባለርስቶች

Reform ለብዙ ሀገራት ዕድገት አይነተኛ ሚና ተጫውቷል። ወደፊት በማሳትመው የትርጉም ስራ የዘመናዊ ቻይና ፈጣሪ የሚባለው ዴንግ ሾኦፒንግ የፈጠራቸው ሶስት ሪፎርሞች እንዴት በአሁኑ ሺ ጀምፒንግ እንደቀጠሉና እንደተሻሻሉ ታነቡታላችሁ።

ሪፎርም ድንቅቅቅቅቅቅቅ የሀገር ግንባታ መሳሪያም ነው።

ዴንግ Reform ካደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ተቋማዊ ሪፎርም/ Institutional Reform/ አንዱ ነው።

ተቋማዊ ሪፎርምን ለመምራት የሚያስችል ሀገራዊ ሪፎርም ዶር መኩሪያ ሀይሌ በሚመራው የፐብሊክ ሰርቪስ ኬሚሽን እንዲፈፀም ስራዎች ወደ ክልል ጭምር ተሰራጭተዋል።

በዚህ ሂደት የሪፎሩም ሆነ ሀገር በቀል የመሪነት ባህል ሳያንሳቸው ግን ከነሱ ውጭ የሆነ ሰው ምን እንደሚል ለማወቅ፣ በዚያውም እይታ የራሳቸውን የreform ስራ ለማከናወን እንዲችሉ ተጋብዤ በአፋር ሰመራ ተገኝቻለሁ። "ሌሎች ምን ይላሉ?" "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" እንዲሉ።

ይህ እይታ outsiders view መፈለግና መጠቀም ሰዎች ራሳቸውን እንዳያጋንኑና ደሴት እየሰሩ ግጭት እንዳይበራከት ያደርጋል። ይህ open minded ከመሆን የሚመጣ ነው። ስለሆነም ትዝብቶቼን ለመግለፅም የምችልበት አካባቢ ነው።

ለኔ አፋር ቤቴም፣ ጎሳዬም ነው። ቢሆንም ፈንጠር ብዬ በመኖር ያጠራቀምኳቸውን ዕውቀትና ልምድ የሩቅ ታዛቢ አድርገውኛል። ይህን ለማካፈል እንዲሁም ድሮ የማውቀውና አሁን ያሉ ልዩ ልዩ ባህሪያትን እንድረዳ ዕድል ፈጥሮልኛል።

ለዚህም ምስጋናዬ የላቀ ነው። ጋባዤ የቀድሞ ጎበዝ ተማሪዬና የአሁኑ የቢሮ ሀላፊ Macammad Acmaad, እንዲሁም በእርጋታቸውና የአመራር ችሎታቸው ብዙዎች የሚያደንቋቸው Elema Abubakar እና Idris Mohamed

በልባችሁ ውስጥ ያለው የሪፎርም ስራ ፍላጎትና ጥረት ላነሳሳ መጥቼ እኔንም አነሳስቶኛል።

የክልሉ ፕሬዝዳንት ሀጂ አወል አርባ በፕሮግራሙ መጨረሻ የየዘርፉ አመራሮች ጋር በተደረገው ርክክብ ተገኝተው የሰጡት መልዕክትና አቅጣጫ reform ላይ የሰጣችሁት ትኩረት ማሳያ ነው። በክልሉ ውስጥ የሲቪል ሰርቪሱ ሪፎርም የሚለውጣቸውና የሚያስቀጥላቸው ባህሎች ይኖራሉ።

ይህ ሪፎርም ለአፋር ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ ለውጥ የሚያመጣ፣ ኢንቨስትመንት በመሳብ በክልሉ ያሉ ፀጋዎች ተቋዳሽ እንደሚያደርገን እምነቴ የፀና ነው።

ኑሩልኝ።

ሰመራ
መስከረም 21/2018
የናንተው ተስፋዬ ይመር

01/10/2025

የስልክ ባትሪ ቶሎ የሚያልቅበት ምክንያቶች እና መፍትሄዎች !

~ የስልክዎ ባትሪ በፍጥነት የሚያልቅበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከዚህ በታች የተለመዱ ምክንያቶችን እና ለእያንዳንዳቸው መፍትሄዎችን ዘርዝረናል ።

~ ምክንያቶች ~

📌brightness ☀️: የስክሪን (brightness) በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ ሲል ባትሪ በፍጥነት ይጨርሳል።

📌 አፕሊኬሽኖች: ከበስተጀርባ የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች(background -running )፣ በተለይም ብዙ ዳታ የሚጠቀሙ መተግበሪያዎች ባትሪን ይጎዳሉ።

📌 እንደ wifi ,Cellular data ያሉትን ብዙን ጊዜ ማብራት: የስልክዎ ኔትወርክ ደካማ በሆነበት ቦታ ስልኩ የተሻለ ሲግናል ለማግኘት ስለሚጥር ባትሪ በፍጥነት ያልቃል።

📌 ሁሌም GPS ON ማድረግ: የጂፒኤስ አገልግሎት ሲበራ እና ለተለያዩ አፕሊኬሽኖች ሲጠቀሙበት ብዙ ባትሪ ስለሚጨርስ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር Off ማድረግ ።

📌 ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ስልካችሁ ሲያገኝ :ስልክዎን ለከፍተኛ ሙቀት ማጋለጥ የባትሪውን ጤና ይጎዳል።

- መፍትሄዎች -

🎯 የስክሪን brightness ይቀንሱ : የስልኮዎን ስክሪን ብሩህነት በራስ-ሰር እንዲስተካከል (Auto Brightness) በማድረግ ወይም እራስዎ በመቀነስ የባትሪ ዕድሜን ማራዘም ይችላሉ።

🎯ከበስተጀርባ የሚሰሩ አፕሊኬሽኖችን ይቆጣጠሩ: ከስልኮዎ Settings ውስጥ ወደ Battery ክፍል በመግባት የትኛው አፕሊኬሽን ብዙ ባትሪ እየበላ እንደሆነ ማየት ይችላሉ። የማትጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች ከበስተጀርባ እንዳይሰሩ መዝጋት (Force Stop) ወይም ማስወገድ (Uninstall)።

🎯 ስልኩን መጠቀም በማይፈልጉበት ጊዜ Wi-Fi እና Bluetooth ያጥፉ። ስልኩን ለጥሪ ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ ኢንተርኔት ሞባይል ዳታ መዝጋትም ባትሪ ይቆጥባል።

🎯 የጂፒኤስ አገልግሎትን ያጥፉ : ቦታን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን (location services) የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን መገደብ ወይም አስፈላጊ ካልሆነ ማጥፋት።

🎯የባትሪ ቆጣቢ ሁነታን (Battery Saver Mode) ይጠቀሙ ብዙ ስልኮች የባትሪ ቆጣቢ ሁነታ አላቸው ።
ይህን ሁኔታ ማብራት አላስፈላጊ ሂደቶችን በመቀነስ ባትሪን ያቆጥባል።

🎯 ሁሌም ቢሆን ሰልካችሁ Update ሲያስፈልገው update ያድርጉ ይህም ለ ባትሪ እድሜ መርዘም አስተዋፅኦ ያደርጋል ።

ቦነስ Tip:- 🎯 ባትሪውን በትክክል ይሙሉት :
ሁሌም ወይም በተደጋጋሚ ስልክዎን እስከ 100% መሙላት እና ከ 20% በታች እንዲወርድ ማድረግ ባትሪውን ይጎዳል። ባትሪውን ከ20% በላይ እና ከ80% በታች ማድረግ ይመከራል።

የምስራቅ አፍሪካ ወንበዴ ሃይል ማስተንፈስ ግድ ነው!! ==============================ይሄ ሽማግሌ ቡድን በሱዳን ጦርነት ውስጥ አንድ ሙሉ ክፈለ ጦር አሰግብቶ ከተለያዩ ወታደ...
01/10/2025

የምስራቅ አፍሪካ ወንበዴ ሃይል ማስተንፈስ ግድ ነው!!
==============================

ይሄ ሽማግሌ ቡድን በሱዳን ጦርነት ውስጥ አንድ ሙሉ ክፈለ ጦር አሰግብቶ ከተለያዩ ወታደራዊ አዛዦች ጋር በማጣመር ከአልቡርሃን ጎን እየተዋጋ ይገኛል። ሶማሊያ ውስጥም ሰላዬች እና ወታደራዊ መኮንኖች በመላክ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲዋጉ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። የሶማሌ ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እርቅ ሲያወርድ እብሪተኛ ሻዕቢያ ገልበጥ አለና አልሸባብ ማስታጠቅ እና ማጠናከር ጀመረ። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ሽፍቶች ስም ከኤርትራ ወታደሮች እያስገባ በሃገራችን ሽብር እያካሄደ ይገኛል እናም ይሄን አሸባሪ ሃይል እያለ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ በሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው።

በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮምያ፣ አፋር እና አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ የቤት ለቤት አሰሳ ተካሄዶ ሰላዬች እና ቅጥረኛ እየተለዩ ወደ እስር ቤት የመላክ ስራ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሻዕቢያ ሰላዬች በተለያየ ተቋም ውስጥ ስላስገባ ምንጠራ ማካሄድ አለበት። (ሚዲያ፣ ባንክ፣ ንግድ፣ ትራስፖርት፣ ፖሊሲ፣ ወታደር ቤት፣ በተለይ ኦፕሬሽን ክፍል ውስጥ ያሉትን፣ መረጃ እና ደህንነት ውስጥ ያሉትን፣ ጅቡቲ ሹፌሮች) ሁሉንም መዋቅሮች መፈተሽ። ማንም የመኪና ሹፌር ካሜራ ይዞ ትግራይ፣ አፋር እና ከጅቡቲ ጀምሮ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ፣ ልዩ ኦፕሬሽን በመላው ሃገሪቱ ያስፈልጋል። በግልጽ ሻዕቢያ ከኢትዮጵያ ድንበር በሁለት ቀን ውስጥ ወታደሮች ለቃቅሞ ማስወጣት ይኖርበታል፣ ከዛላምበሳ፣ ባድመ፣ ኢሮብ አካባቢ አይኑን ሳያሽ ለቆ መሄድ ይኖርበታል። ጥጋበኛ ሻዕቢያ እምቢ ካለ? አስመራ እና ሳዋ ድረስ ሄደን ማስተንፈስ ግዴታችን ይሆናል።

ከዚህ የሽፍታ ቡድን ጋር እየታሹ ዘለአለም መኖር ስልችት ብሎናል። ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት ደሞ ሲያስጠላ!! እነሱ ብቻ ብልጥ፣ እነሱ ብቻ አድራጊ ፈጣሪ፣ እነሱ ብቻ የስለላ አቅም እንዳላቸው የሚያስቡት አንበርክኮ ማሳየት ያስፈልጋል። ሻዕቢያ የታሪክ እስረኛ ነው እናም ራሱ ላይ ታሪክ ሰርቶ የመጨረሻ ዘመኑን ማሳየት ያስፈልጋል። ሻዕቢያን የሚተካ ኤርትራ መንግስት የማዘጋጀት ስራ መረሳት የለበትም።

ትግራይን ራት የሚያበሉት ጀነራል! በዛን ሰሞን ህወሃት በአማራ ክልል የመብራት ቋሚ ብረት ተክላ መብራቱ ቋሚው ያለበትን የአማራ ክልል ትልቀ ከተማ ተሻግሮ በትግራይ አንዲት ሚጢጢ ከተማ ላይ ...
30/09/2025

ትግራይን ራት የሚያበሉት ጀነራል!

በዛን ሰሞን ህወሃት በአማራ ክልል የመብራት ቋሚ ብረት ተክላ መብራቱ ቋሚው ያለበትን የአማራ ክልል ትልቀ ከተማ ተሻግሮ በትግራይ አንዲት ሚጢጢ ከተማ ላይ ይበራ ነበር። አሉ!

በዚህ ሁኔታ የተበሳጩት የአማራ ከልሉ ወጣቶች ማታ ማታ እየጠበቁ የመብራቱን ገመድ ይቆርጡት ነበር።

ይሄኔ የወቅቱ ባለስልጣናት የኤሌክትሪክ ገመዱ እንዳይቆረጥ ጥበቃ አቆሙ!

ጥበቃው ስራ ነው እና ቢበሰጨውም እየጠበቀ ያድራል።

በአንዱ ማታ የጥበቃው ጓደኛ በአጠገቡ ሲያልፍ የኤሌክትሪክ ብረቱን ደገፍ ብሎ በጨለማ ወስጥ ቆሞ ይመለከተዋል ይሄኔ ለካስ ስራውን አልሰማ ኖሮ

“በዚህ ጨለማ ምን ትሰራለህ ?” ብሎ ይጠይቀዋል። ሰውየውም በቁጨት

“እሰቲ ተወኝ ወዳጄ ትግራይን ራት እያበላሁ ነው!” ብሎ ይመልስለታል!

እነሆ ይሄ ጨለማ ወስጥ ቆማችሁ እራት አብሉኝ የሚባለበት ዘመን አለፈ።

ነገር ግን ትግራይንም ኤርትራንም ራት ካላበላሁ የሚሉ ጀነራል መጡ!!

ትህትናው ጥሩ ነበር ነገር ግን አባቴ ለራስዎ ጨለማ ውስጥ ቆመው ትግራይ እና ኤርትራን ራት ካላበላሁ ማለት የጤና ነው ? ብላችሁ ጠይቁልኝ እና በጣም ነው እንዴ ኤርትራ እና ትግራይን መጠበቅ የፈለጉት ? የሚለውንም ጨምሩልኝ! ሆ!

አቶ ጌታቸው ምን አሉ?📌" ሻዕብያ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ቢገጥም ጦርነቱ ከኤርትራ ራቅ አድርጎ በደቡባዊ የትግራይ ክፍል ( በራያ ) ቢሆንለት ደግሞ አማራ ክልል ላይ ለማድረግ ነው። ይህ እ...
30/09/2025

አቶ ጌታቸው ምን አሉ?

📌" ሻዕብያ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ቢገጥም ጦርነቱ ከኤርትራ ራቅ አድርጎ በደቡባዊ የትግራይ ክፍል ( በራያ ) ቢሆንለት ደግሞ አማራ ክልል ላይ ለማድረግ ነው። ይህ እንዳይሳካ እኔ ሁለንተናዊ ትግል አደርጋለሁ "

📌"ኤርትራውያን በጣም ብልሆች ናቸው። የፌደራል መንግስትን በቀጥታ የመዋጋት የሰው ኃይል ብልጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ። ስለዚህ፣ ሀገሪቱን ለማናጋት በድንበራቸው ማዶ ያሉ 'ጠቃሚ ሞኞችን' (useful idiots) መጠቀም ይፈልጋሉ። አሁን ያለው የህወሓት አመራር ለማድረግ እየሞከረ ያለው፣ ከፌደራል መንግስት ይመጣል ብለው ከሚያስቡት እውነተኛ ወይም ምናባዊ ስጋት እራሳቸውን ለማዳን፣ ከኤርትራውያን ጋር ህብረት መፍጠር ይቻል እንደሆነ ማየት ነው።"

📌‟...ማንም ወደደው ወይም ጠላው፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደዱትም ጠሉት ከ 135 ሚሊዮን በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የባህር በር ተዘግቶበት መውጫ መግቢያ እየለመነ አይኖርም፤ መኖርም የለበትም...”

አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የቀድሞው የCNN እና ሮይተርስ ጋዜጠኛ ጂም ስቴንማን በሚያዘጋጀው "Global Power Shift" ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ

የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይልን ለማጠናከር የፌዴራል ፖሊስ ቁርጠኝነት 👇በአፋር ክልል የሰሜን ምስራቅ ሚሌ ፈጥኖ ደራሽ እና የኮንትሮባንድ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያዎች ካምፕ በዛሬው ዕለት ተመር...
29/09/2025

የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይልን ለማጠናከር የፌዴራል ፖሊስ ቁርጠኝነት 👇

በአፋር ክልል የሰሜን ምስራቅ ሚሌ ፈጥኖ ደራሽ እና የኮንትሮባንድ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያዎች ካምፕ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።‎

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ÷ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ በጀግንነት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

ተቋሙ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ለማጠናከር በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ÷ ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

‎የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው÷ ፌደራል ለግዳጅ በተሰማራባቸው አካባቢዎች የተለያዩ ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን የሚያስችል አቅም ገንብቷል።

ሰራዊቱ ከጀግናው የአፋር ሕዝብ እና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን ሰላም እና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

ፌደራል ፖሊስ የሎጂስቲክስ አቅሙን ለማሳደግ ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ እያስረከበ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ ናቸው።

የሚሌ ፈጥኖ ደራሽ መምሪያና የኮንትሮባንድ ቁጥጥር መምሪያ ካምፕ በራስ አቅም እና ወጪ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉንም አመልክተዋል፡፡

ሰበር ዜና: የህወኃት ዕቅድ በአማራ ክልል‼️መነሻውን በራያ ያደረገው የህወኃት ፋኖ በወሎ እና በህወኃቱ ኮሎኔል ንጉሴ የተመራው ታጣቂ ኃይል የሚችል ከሆነ መዳረሻውን ነድፏል ከእጃችንም ገብቷ...
27/09/2025

ሰበር ዜና: የህወኃት ዕቅድ በአማራ ክልል‼️

መነሻውን በራያ ያደረገው የህወኃት ፋኖ በወሎ እና በህወኃቱ ኮሎኔል ንጉሴ የተመራው ታጣቂ ኃይል የሚችል ከሆነ መዳረሻውን ነድፏል ከእጃችንም ገብቷል፡፡

ከዚህ በፊት በስውር የነበረው የህወኃት እጅ በቀጣይ ከፋኖ ጀርባ ሆኖ ሁሉንም ሎጅስቲክና ቴክኒካል ድጋፍ ወሳኝ ቦታ ላይ ሰርጂካል ኦፕሬሽን የሚሰራ ቲም በማስገባት
1. ጋሸናን
2. ደብረዘቢጥን
3. ጋይንትን
4. እብናትን
5. በለሳን
6. ደጎማን
7. ጎንደርን

ቆርጦ ወልቃይትን በፍጥነት መያዝ ነው ሲል ወታደራዊ መረጃዬ አድርሶኛል፡፡

በአማራ ሕዝብ ሥም እየማለ!እየተገዘተ ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ ክልሉን የሚያተራምስ የወንበዴ ስብስብ የትም አይደርስ! እንደምታዩት በግራ ያለው ጽሁፍ የፋኖ አመራር ነው በቀኝ...
26/09/2025

በአማራ ሕዝብ ሥም እየማለ!እየተገዘተ ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ ክልሉን የሚያተራምስ የወንበዴ ስብስብ የትም አይደርስ! እንደምታዩት በግራ ያለው ጽሁፍ የፋኖ አመራር ነው በቀኝ ያለው ደግሞ የሻዕቢያ ሜዲያ ነው። ሁለቱም የሚያወሩት ግን አንድ አይነት ነው። የፋኖው መሪ አሰብን እንዳትሞክረው እኛ የሻዕቢያ ወኪሎች እየወጋንህ ነው በማለት ለመከላከያ መልክት እያስተላለፈ ይመስላል።

Adresse

Vienna

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Awusa.com erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Fördern

Teilen