28/10/2025
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ምርጫውንና ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-
👉 ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ያለን ስርዓት የሚፈርስ አይደለም የሚያጠናክር ነው እንጂ፤ ምርጫን፣ በጀትን እና የወታደር እንቅስቃሴን የሚያስቆም ምክክር አንፈልግም፡፡
👉 መንግስት እንደመንግስት ስራውን እያከናወነ ግብዓት የሚሆኑ ሐሳቦች ይመጣሉ አልን እንጂ፤ መንግስት ስራውን አቁሞ፣ ምርጫ አቁሞ፣ በጀት ማፅደቅ አቁሞ፣ ፓርላማ ይበተን አላለም፡፡
👉 የሀገራዊ ምክከር ሂደቱ ከምርጫው በፊት ካለቀ እሰየው ግብዓት እንወስዳለን፤ ከዛ በኋላም ካለቀ ጥሩ ነገር ግን ምርጫውን የሚያስተጓጉል ነገር የሚፈጠር አይመስለኝም፡፡
👉 ሀገራዊ ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይካሄዳል፡፡
👉 መንግስት ምርጫውን ለማካሄድ በቂ አቅም አለው፤ ምርጫ የአንድ ፓርቲ ፍላጎት አይደለም የጋራ ነው፡፡
👉 ሐሳብ አለኝ በምርጫ መሳተፍ እፈልጋለሁ የሚል ፓርቲ በምርጫው መሳተፍ ይችላል፤ እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በፊት ከተደረጉት ምርጫዎች የበለጠ ግልፅ እና ተአማኒነት ያለው ነበር፤ 7ኛው ደግሞ ይሻላል፡፡
👉 ይህ ምክር ቤትም አሁን ያለው መልክ አይኖረውም ብዬ አስባለሁ፤ ብዙ ድምፆች ይገባሉ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ፣
👉 እንደ መንግስት እና ፓርቲ አማራጭ ድምፅ የሌለው ፓርላማ እንዲኖረን አንፈልግም፤ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ተዓማኒ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡