ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN

  • Home
  • Canada
  • Calgary, AB
  • ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN

ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN, Calgary, AB.

06/03/2025

እንኳን ወደ ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ በደህና መጡ! የአማራ ፋኖ ትኩስ የድል ዜናዎ፡፡ የአማር ህዝብ ተጋድሎ ሰኮቃ ደምጽ የሆነ ሚዲያ የአማራ ህዝብን ሰቀቃ የድል ጉዞ ከምንጩ ይዘግባል፡፡ .....

https://youtu.be/ABpRYomxm6Q
06/03/2025

https://youtu.be/ABpRYomxm6Q

ህልውናችን፣ ያለጊዜው በስልጣን ላይ የተገኘ መሪ፤ የኦሮሙማው ተልዕኮ ሰሜኑን መውረር ነው።እንኳን ወደ ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ በደህና መጡ! የአማራ ፋኖ ትኩስ የድል ዜናዎ፡፡ የአማር .....

https://youtu.be/KhJrQU3ZfMA
06/02/2025

https://youtu.be/KhJrQU3ZfMA

እንኳን ወደ ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ በደህና መጡ! የአማራ ፋኖ ትኩስ የድል ዜናዎ፡፡ የአማር ህዝብ ተጋድሎ ሰኮቃ ደምጽ የሆነ ሚዲያ የአማራ ህዝብን ሰቀቃ የድል ጉዞ ከምንጩ ይዘግባል፡፡ .....

በጎንደር ቀጠና ደራ ሀሙሲት አርብ ገብያ፣ገላዉዲወስ እና ሳና ከባድ አዉደዉጊያ መደረጉ ተሰማ!!!የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ከጧቱ ጀምሮ ከአገ...
06/01/2025

በጎንደር ቀጠና ደራ ሀሙሲት አርብ ገብያ፣ገላዉዲወስ እና ሳና ከባድ አዉደዉጊያ መደረጉ ተሰማ!!!

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል አፋብኃ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ከጧቱ ጀምሮ ከአገዛዙ ጥምር ጦር ጋር ከባድ አዉደዉጊያ ያደረገ ሲሆን ከፍተኛ ድል መቀዳጀት ችሏል።

ጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ ከባተ አንደኛ ኮር ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተዋርሪ ክፍለጦር፣ጉና ክፍለጦር፣እንዴሁም የኮሩ ተወርዋሪ ኃይል ከአገዛዙ ጦር ጋር አንገት ለአንገት በመተናነቅ በደርዘን የሚቆጠር ኃሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።

የኮሩ አንደኛዋ ክፍለጦር የጣና ገላዉዲወስ ክፍለጦር በደራ አርብ ገብያ ከተማ በመግባት ጠላትን አፈር ሲያስልሱት አርብ ገብያ እና ገላወዲወስ ከተማን መቆጣጠር ችለዋል።

በአርበኛ አመኑ አለም አንተ የሚመራዉ የአፋብኃ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር በጠላት ላይ በወሰደዉ እርምጃ ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሀይል ድል የተደረገ ሲሆን የአገዛዙ ቀሪ ኃይል ሙትና ቁስለኛ ለማዉጣት መቸገሩ ታዉቋል።

እንደ ንብ የሚናደፉት የጉና ክፍለጦር እና የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር ኩኮሩ ተወርራ ኃይል ጋር በመጣመር የመጠዉን ጠላት የአፈር ሲሳይ አድርገዉታል።

ዝርዝር መረጃዉን እንመለስበታለን!

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!

Facebook https://www.facebook.com/share/17EDDFWEwU/

telegram https://t.me/gfmn21

Tweeter https://x.com/GlobalFanomedia

Rumble https://rumble.com/user/Globalfanomedia

Whats App https://chat.whatsapp.com/G9rAvTRmNmd7WuPL2HeAeb

TikTok https://www.tiktok.com/

Share your videos with friends, family, and the world

https://youtu.be/MRnfpcHciPU
05/31/2025

https://youtu.be/MRnfpcHciPU

ሰበር ዜና - ቀጥታ ከግንባር | ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡ ፋኖን ተቀላቀለ | ታላቅ ጀብዱ በጎጃምና ጎንደር ትንቅ * ንቅ

ሰበር ዜና!አፋብኃ የአጭር ሞገድ ሬድዮ ስርጭት ሊጀምር ነዉ።እዛዉ ሀገር ቤት ዉስጥ ባሉት ጀግና ታጋዮች ይመራል ተብሏል።አላማዉም!የትግሉን አላማ ማስረፅ ።ወቅታዊ መረጃዎችን ለሁሉም ማዳረስ።...
05/31/2025

ሰበር ዜና!

አፋብኃ የአጭር ሞገድ ሬድዮ ስርጭት ሊጀምር ነዉ።

እዛዉ ሀገር ቤት ዉስጥ ባሉት ጀግና ታጋዮች ይመራል ተብሏል።

አላማዉም!

የትግሉን አላማ ማስረፅ ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ለሁሉም ማዳረስ።
ሀሰተኛ መረጃ ማክሸፍ።

ተደራሽነቱ፣

ለገጠሩ ማህበረሰብ፣

ኢንተርኔት እና የሞባይል ስርጭት በደንብ ለማይደርስበት ቦታ በአግባቡ እንዲደመጥ ይደረጋል (if the internet blocked)

ከቀጠናው ውጭ ላለው ማህበረሰብ ትክክለኛውን መረጃ መስጠት የመሳሰሉት ይገኙበታል።

ምን አሰባችሁ ጎበዝ!?

ወንድም እህቶቻችን መሬት ላይ ስራቸዉን እየሰሩ ነዉ።

አዎ . . አማራ ያሸንፋል!

https://youtu.be/QvpVWkXE94E
05/30/2025

https://youtu.be/QvpVWkXE94E

ሰበር መረጃ | በወሎ በ4 ግንባር የተደረገው የፋኖ ፍልሚያ | እስቴ መካነየሱስ - ጥናፋ | የአርበኞች ክ/ጦር ጥሪ | Fano News

https://youtu.be/Ap40EYX2Brs
05/30/2025

https://youtu.be/Ap40EYX2Brs

ከፋኖ ጋር ውሎ - ቀጥታ ስርጭት | "ድሉ የማይቀር ነው : አንድነታችንን እናጠንክር!" | ከአርበኛ ሰፈር መለሰ ጋር የተደረገ ቆይታ

ቋራ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!!============="የእናት ሆድ ዠንጉርጉር" የሚለው ብሂል ካለ ምክንያት አልተነገረም፤ አንዳንዱ ቅን፣ ትሁት፣ ደግና መልካም ይሆናል፤ ሌላው ደግሞ፦ ክፉ፣ ተንኮ...
05/30/2025

ቋራ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!!
=============

"የእናት ሆድ ዠንጉርጉር" የሚለው ብሂል ካለ ምክንያት አልተነገረም፤ አንዳንዱ ቅን፣ ትሁት፣ ደግና መልካም ይሆናል፤ ሌላው ደግሞ፦ ክፉ፣ ተንኮለኛ፣ ተንኳሽ፣ ሸረኛ፣ ምቀኛ፣ ሴረኛ ይሆናል። አንዳንዱ ደግሞ ለሆዱና ለሆዱ ብቻ የሚኖር አለ፤ እንደ ጋማ ከብት ቀን ከለሊት ያገኘውን ሁሉ በመጋጥ ይጠመዳል። እርሱን ይድላው እንጅ የሌላው ረሃብ፣ ስደት፣ መገደል፣ በግፈኞች ዱላ መቀጥቀጥ፣ መታሰርና መሰቃየት ለእርሱ ምንም አይደለም። ከመጣው የአገርና የህዝብ ጠላት እግር ስር ወድቆ የሚያሸረግድ፣ የሚያጎበድድ ባንዳ ይሆናል። ህሊና ቢስ ስለሆነ በትንሽ ትልቁ መዋረድ እድል ፈንታው ሆኖ ይቀራል።

በሌላኛው በኩል ደግሞ ለህሊናቸው ክብርና ሞራል የሚጨነቁ የአገራቸውና የህዝባቸው ጉዳይ የሚያብከነክናቸው፣ የሌላው መከራ እና እንግልት የሚያማቸው፣ በፍትህ ርትህ ላይ የማይደራደሩ፣ በእውነትና በሰብአዊነት አምድ ላይ የቆሙ እውነተኛ የህዝብ ልጆች ሆነው ይገኛሉ። የህዝባቸው ጥቃትና ውርደት እረፍት ይነሳቸዋል። እየተራቡና እየተጠሙም ቢሆን ግፈኞችን፣ ሴረኞችንና በዳዮችን እስከ ሂዎት መጨረሻቸው ድረስ በቆራጥነት በመታገል ተለይተው ይታወቃሉ። ይህ ሁኔታ በአማራ ግዛት ወቅታዊ ሁኔታ ውስጥ ጎልቶና ገዝፎ ይስተዋላል።

ርዕሰ ጉዳያችንን በጎንደር ቋራ ምድር ስለተካሄደው የአማራ ፋኖ አንድነት ዳግም ውልደትና የአንድነት ቃል ኪዳንን ያውጃል፣ ይዘከራል።

ከቋራ ምድር የተካሄደው የአማራ ፋኖ ቃል ኪዳንን ለመከወን ከአንድ ወር በላይ እልህ አስጨራሽ ጉዞና ውይይት ከተደረገ በሓላ ግንቦት 01/2017 ዓ.ም በቋራ ምድር የአማራ ፋኖ ቃል ኪዳንን እውን ለማድረግ የተከፈለው መስዋትነት ቋንቋ ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ነበር። አርበኛ ምሬ ወዳጆ ከእነ ሰራዊቱ ከወሎ፣ አርበኛ ሐብቴ ወልዴ ከእነ ስራዊቱ ከመሃል ጎንደር፣ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ከሽዋ ከእነ ስራዊቱ፣ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእነሰራዊቱ ከጎጃም ተነስተው ጎንደር ቋራ ምድር ለመድረስ የእግር ጉዞው በርካታ ቀናት ፈጅቷል፤ በሽ የሚቆጠር ኪሎ ሜትር ጫካ ጋራ ሸንተረሩን አንዳንዴም ዋናውን አውራ ጎዳና ተከትለው ቀን ከለሊት በመጓዝ ጎንደር ቋራ ለመድረስ ሊኖር የሚችለውን ድካምና እንግልት አዕምሮ ያለው ሁሉ ሊገምተው ይችላል።

በጉዞው መራብ፣ መጠማቱ፣ የሌሊት ቁር፣ የቀን ሀሩር፣ የዱር አውሬው እባብና ጊንጡ፣ የእቅልፍ እጦትና የአካል ዝለቱና የደህንነቱ ስጋት ..... እነዚህ ሁሉ የጉዞው ተግዳሮቶች ነበሩ። በዚያ ላይ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶችና በአማራ ውስጥ የበቀሉ አረሞች የተጓዡ ፋኖ የደህንነት ስጋቶች የመሆናቸውን ጉዳይ ደምረን መመልከት ይቻላል።

ወደ ርዕሰ- ጉዳያችን ዘልቀን ከመግባታችን በፊት ታዳሚዎቻችን ሁለት ጉዳዮችን አፅዕኖት ሰጥተው ሊመለከቱት ይገባል። አንደኛውና ዋናው ጉዳይ የጎንደር ፋኖ በቋራ ቃል ኪዳን ለመከተም በየአቅጣጫው የተመሙትን የፋኖ አርበኞች የማስተባበርና የመምራት ሀላፊነቱን ወስዶ በድል ማካሄዱ፣ መላ አካባቢውን ከደህንነት ስጋቶች አፅድቶ ቋራን የፋኖ ነፃና አስተማማኝ ቀጠና በማድረጉ የጎንደር የፋኖ አመራሮችና አባላቶች በአጠቃላይ ህዝቡ የእንግዳ ተቀባይነቱን ታሪክ ያሳዩበት ሂደት ሆኖ በመታየቱ ምስጋናና ክብር ሊቸራቸው ይገባል።

ሁለተኛው አፅእኖት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ደግሞ የአማራ ህዝብ ልብ ሙሉ በሙሉ ከአረሞቹና ከአብይ የኦህዴድ አገዛዝ ጋር እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። የኦህዴድ ብልፅግናው መንግስት ከአዲስ አበባ ውጭ አንዳችም ስፍራም ሆነ አቅም እንደሌለው መረዳት ይቻላል። ያ ሁሉ የፋኖ አርበኞች ከየ አቅጣጫው እየተመመ ከታሪካዊቷ የቋራ ምድር ሲደርስ አንዳችም መረጃ የለውም። ይህ በራሱ የሚያሳየው ከጥቂት አረሞች በስተቀር መላው የአማራ ህዝብ ከፋኖ ጎን መቆሙን ነው። በዚህ ረገድ በወገኖቼ ኮርቻለሁ። አሁንም ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ጠልቀን ከመግባታችን በፊት ስለ ታሪካዊቷ ጎንደር ቋራ ጥቂት ልበል።

ቋራ የአገር አድባር- የጎንደር ዋርካ ደብር፣ ቋራ የአማራ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ደጄን- የግፉዓን እምቢባዮች መጠጊያ፣ የፋኖ ጄግኖች መብቀያ ማበቢያና ማፍሪያ፣ የአፄ ቴዎድሮስ የገብርየ፣ የእነ አለሜና የእና አሞራው ውብነህ የደም አጥንት ክፋይ፣ የእነ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ እነ አርበኛ ሰፈር መለስ፣ የእነ አርበኛ ጎቤ መልኬ፣ የእነ አርበኛ ሰጠኝ ባብል፣ የእነ አርበኛ አበራ ጎባው፣ የእነ አርበኛ ባሻ ጥጋቡና ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው አርበኞች የጄግንነት ዝና የናኘባት፣ ቋራ የድል የቃል ኪዳን ምድር- ቃል ማሰሪያ፣ የአምባገነኖች እስትንፋስ ማብቂያ፣ ቋራ የፋኖ አንድነት ድል ምስራች መንገሪያ፣ የብርሃን ቀንዲል ማብሪያ፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሽዋና ጎንደር ወጣት ጎልማሳ የአማራ ፋኖ አንድነት ዳግም ተወልዶ የተማማለባት የካሳ ኃይሉ፣ የበላይ ዘለቀ፣ የንጉስ ሚካኤል፣ የሚኒሊክ የጀግንነት መንፈስ ዳግም ውልደት፣ እንደገና የማቆጥቆጥና የማበብ ተስፋን ተመልክተንበታል።

የአማራ አንድነትም ሆነ የኢትዮጵያ ህልውና የነፃነት ብርሃን ዳግም በቋራ ፈንጥቋል። የመይሳው ልጆች፣ የንጉስ ሚካኤል ልጆች፣ የአፄ ሚኒሊክ ልጆችና የበላይ ዘለቀ ልጆች የዋዛ አይደሉም፣ ለውሃ ጥም ጤዛ ልሰው በዱር አድረው ድንጋይ ተንተርሰው እግራቸው እስኪዝል ቀን ከሌሊት ተጉዘዋል። በዚህ በሰለጠነ ዘመን በአባቶቻቸው ወኔ ጉልበትና የማይነጥፍ ሞራል ታግዘው ዳግም በቋራ ተወለዱ። የቋራው ዳግም ውልደት ከቶውንም ያለ መስዋትነት አልተገኘም። አያሌ የአማራ ልጆች የሂዎት መስዋትነት ከፍለውበታል። ይህ ሁሉ ጀግንነት የህወሃት ኢህአዴግና የኦህዴድ የግፍ ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ ባደረሰው መጠነ ሰፊ ጥቃትና የዘር ማጥፋት መጠን በምጥ ተወልዷል። የግፍ ፅዋው በሞላው መጠን የህልውና ትግሉም በዚያው መጠን እንደ ቋያ እሳት ተቀጣጥሏል። እናም ከአራቱም አቅጣጫ የተመሙት የአማራ የቁርጥ ቀን አርበኞች የዘመኑ ክስተት ሆኑ። ለአማራ ህዝብ ልዩ ሽልማቶች ሆኑ።
እናም በቋራ ቃል ኪዳን የአማራን ማንነት ገነቡ፣ ቃል ኪዳን ለአማራ ህዝብ ህልውና፣ ቃል ኪዳን እስከ ሂዎት መስዋትነት፣ ቃል ኪዳን ለፍትህና ለእኩልነተ በቋራ ተመሰረተ።

"ቋራ!..... ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!" አሉልሽ ጀግኖችሽ ልጆችሽ። ኦ! ቋራ....

እንደሚታወቀው በየዘመናቱ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው ግፍና በደል ባየለ ቁጥር እምቢኝ ባዩ የህዝብ ልጅም የዚያኑ ያህል በየመስኩ በየጎጡ መጀገኑ አልቀረም። ዛሬም ያለው ፋኖ እንደ ቀደምት አባቶቹ በደል በቃኝ ብሎ ተነስቷል። የአያት የቅድመ- አያቶች የጀግንነትና የአንድነትን መንፈስ ወደዚህ ትውልድ ተሸጋግሯል፤ ስሜቱ ተጋብቷል። ለዚህም ነው ከወሎ፣ ከሸዋ፣ ከጎጃምና ከጎንደር ተሰባስበው የቋራ ምድሩን የአንድነት ቃል ኪዳን የፈፀሙት። እናም የተጋድሎ ድርሻቸውን ለመዘከር ከወሎ የአማራ ፋኖ ልጀምር።

የወሎ አማራ ፋኖ
"ቋራ!- ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!"
=================

ብዙዎች ስለወሎ የቆንጆ መናኸሪያነትና የፍቅር ሰገነትነቱ እያዜሙ የጀግንነቱን ነገር ቢደብቁትም ከያኔው የተህነግ/ህወኃት ወረራ ጀምሮ የገዘፈ ጀግንነቱ ገዝፎ በመውጣት እስከአሁኑ ተጋድሎ ለነፃነቱ ሲል እንደአለት ፀንቶ መቆሙን አስመስክሯል። ታዲያ የወሎ አማራ ፋኖ እንደ አምባሰል የተራራ ሰንሰለቶች እጅ ለእጅ ተያይዞ በንጉስ ሚካኤል የጀግንነትን መንፈስ ታጅበው የመሪያቸውን አርበኛ ምሬ ወዳጆን እግር እየተከተሉ ወደ ጎንደር ቋራ ምድር ተመሙ።

የአሁኑ የነፃነት ተጋድሎ የሁለት አመት የትግል ወጀብ ያላናወጠው የወሎው የፋኖ መሪ አርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ የፋኖ አባላትን ይዞ ከሽ ኪሎ ሜትር ያላነሰ የእግር ጉዞ በማድረግ ጎንደር ቋራ ምድር መድረስ ችሏል።

አርበኛ ምሬ ወዳጆ በህወሓት ወረራ ወቅት፦ አርበኛ መምህር ሞላ ደስዩ፣ አርበኛ አበበ ፋንታው፣ አርበኛ ተሾመ ፈንታየና ሌሎች አርበኞች ጋር ሆኖ የምስራቅ አማራ ፋኖን የመሰረተና በመሪነት የአሁኑን ግዙፍ የአማራ ፋኖ በወሎን ያህል ተቋም የገነባ ውድና ብርቅየ የህዝብ ልጅ ነው።

በህወሓት ወረራ ወቅት በመጀመሪያ በወሎ ግንባር በሁሉም ቀጠናዎች በተለይም በድሬሮቃ : ቦሩ ሜዳ ግንባር፣ በመካነ ሰላም፣ ቀይ መብራትና ገነቴ ግንባር፣ ኃላ ላይም በወልዲያ ዙሪያ፣ በላጎ፣ ቆቦ ዙሪያ፣ ከዋጃ በር ተክላይ እስከ ተኩላሽ፣ አርበት፣ ዲኖ፣ ወርቄ አካባቢዎች በተደረጉ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎች ተዋግቶ የማዋጋት የመሪነት ሚናውን በቆራጥነት ተወጥቷል። ታድያ ከአውደውጊያ የድል የበላይነት ፈንጠዝያ ባሻገርም
ምሬ ወዳጆ በመራቸው አውደ ውጊያዎች ቀኜ የሚላቸው የትግል አጋሮቹን፦ አርበኛ መምህር ሞላ ደስየ፣ አርበኛ መምህር መሀመድ ቢሆነኝ፣ አርበኛ መምህር አሸናፊ አለሙ፣ ኮማንዶ ዳንኤል አለሙ፣ አርበኛ ሲላምላክ ደጉ፣......... እና ሌሎች አርበኞችም የሂዎት መስዋትነት ሲከፍሉ የሀዘን ስሜቱን ዋጥ አድርጎ ለሌላ ከፍ ያለ ድል ይዘጋጅ ነበር።

ከህወሓት ጋር የተካሄደው ፍልሚያ ሲጠናቀቅም የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ በ2016 ዓ.ም መባቻ ሰሞን ፊቱን ወደ አማራ ፋኖ አዞረ፤ የሂዎት መስዋትነት ከፍሎ ኢትዮጵያን ከመበተን ያዳነውን የአማራ ፋኖ ትጥቁን እንዲፈታና እንዲበተን ተፈለገ። ይህን የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ አፍራሽ ውሳኔ በመቃወም ከአፍራሹ አገዛዝ ጋር ፍልሚያ ከገጠሙት የህዝብ ልጆች፤ አርበኛ ፋኖ ምሬ ወዳጆ አንዱ ነበር። እርሱ በመራቸው አውደ ውጊያዎችም ከተራ ወታደር እስከ ኮለኔል ማዕረግ ያላቸውን እግረኛ ወታደሮች ደምስሷል፤ ከክላሽንኮቭ እስከ ሞርተር ያሉ አያሌ መሳሪያዎችን በመማረክ ታላላቅ ጀብዶችን መፈፀም የቻለ ጀግና መሪ ነው። ይህ አይበገሬ ፋኖ ነው ዛሬም ሸህ ኪሎ ሜትሮችን የእግር ጉዞ አድርጎ ለቋራው የአንድነት ቃል ኪዳን የበቃው። ወደፊትም የተጋድሎ ወኔውን አድሶ አዳዲስ ታሪኮችን ያስመዘግባል ተብሎም ይጠበቃል።

የሽዋ አማራ ፋኖ
"ቋራ!- ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!"
==================

በሚኒሊክ ስክነትና ቸርነት_ በጣይቱ ብጡል ጥበብና ብልህነት የታነፀው የሽዋ አማራ ፋኖ፦ እባብና ጊንጡን እየረገጠ፣ ጫካ ሰንበሌጡን እየጣሰ፣ ሽ ኪሎ ሜትር አቋርጠው የታሪክ እምብርት የደም ቃል ኪዳን መሬት ከሆነችው አገር በውድ ልጃቸው በኢንጅነር ደሳለኝ ሲያሽብ ሽዋ እየተመራ ከጎንደር ቋራ ደረሰ።

መቼም የሽዋ ማህፀን አገር ወዳድ የህዝብ ልጆችን ለማፍራት አይታክታትም፤ የሚኒሊክ የአይበገሬነት፣ የጥበብና የብልህነት መንፈስ በዘመናት ሂደት ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል። በእርግጥ በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ጀግኖች በሰላም ጊዜ ተገቢውን አክብሮት ባያገኙም በቁርጥ ቀን ግን ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጠው የሚፋለሙ ጀግኖችን አጥታ አታውቅም። ይሄው የሽዋው የፋኖ መሪ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ ከብዙዎቹ አንዱ ተጠቃሽ ነው። ኢንጅነር ደሳለኝ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ፣ የካበተ እውቀት ያለውና አንደበተ ርዕቱ የሆነ ጀግና ነው።

የአማራ ፋኖ በሸዋ በአማራ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት ላይ ፊት ለፊት ተኩስ የገጠመበትን የማያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም የደብረ ብርሃን ጠባሴ፣ ዋስ ማደያ ትንቅንቅ በጥቂት የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመግጠም 169 ሙትና 48 ቁስለኛ የተደረገበት አውደውጊያ የመራው ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ነበር። ይህ የመጀመሪያው ስለነበር እንጅ ስፍር ቁጥር የሌለው በድል የታጀበ ውጊያዎችን መርቷል።

ታማኙ አርበኛ ለአማራ ፋኖ አንድነት ትልቅ ስራ የከወነ ሲሆን ለአንድነቱ ደግሞ ከሸዋ ምንጃር ተነስቶ ከቴዎድሮስ ቀዩ ከታሪካዊው ቋራ ድረስ በእግር በመግባት ከጓዶቹ ጋር የጋራ ቤቱን አቁሟል።

የጎጃም አማራ ፋኖ
"ቋራ!- ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!"
=================

ጎጃም ከትናንት እስከ ዛሬ ጀግኖችን ማብቀል ያውቅበታል፤ አዎ! የጎጃም ፋኖዎች በፍጥረት መጀመሪያ በሆነው በጊዮን ወንዝ ባህልና ትውፊት፣ በጣና ታሪካዊ ዜማ ከአድማስ አድማስ ተጠራርተው ተሰባሰቡ፤ በሸበል በረታ፣ የአባይ በርሃ የበላይ ዘለቀ የጀግንነት መንፈስ እየተነዱ በመሪያቸው በአርበኛ ዘመነ ካሴ አማካኝነት ወደ ቋራ ምድር ነጎዱ።

የእነ በላይ ዘለቀ የእምብኝ ባይነት የአርበኝነት መንፈስ የወረሰው የጎጃም ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ በማፍራት ማህፀነ ለምለም ነው ለማለት ይቻላል። የህወሓት አምባገነን አገዛዝን ተቃውሞ በኤርትራ በርሃ ከተንከራተቱ የጎጃም አንበሶች መካከል አርበኛ ዘመነ ካሴ ይጠቀሳል። አርበኛ ዘመነ በአካዳሚክ እውቀት የላቀ ነው። ፋኖ ዘመነ ካሴ፦ የአማራ ህዝባዊ ሀይልን መስርቶ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል። ህዝቡንም አንቅቷል፤ በዚህ ስራውም ተሻጋሪ ትግሎችን አድርጓል። በጎጃም ምድር እየተደረገ ባለው የነፃነት ተጋድሎ አዳዲስ የውጊያ ስልቶችን በመንደፍና ዘመቻዎችን በማዎጅ የአገዛዙ ኮለኔሎችን የደመሱበት፣ ከአገር አቋራጭ መገናኛ ሬድዮ እስከከባድ መሳሪያ የተማረከበት አውደውጊያን መርቷል።

ታዲያ ለአንድ የጋራ ቤት ግንባታው፤ አርበኛው የፋኖ አባላቱን እየመራ ቀን ከለሊት ተጉዞ ጎንደር ቋራ ምድር ደርሷል። ታሪካዊውን የአማራ ፋኖ የአንድነት ቃል ኪዳን በማድረግ የራሱን አሻራ አሳርፏል።

የጎንደር አማራ ፋኖ
"ቋራ!- ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!"
=================

የቋራ ምድር እና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እና ቋራ የማይረሳሱ እናት እና ልጅ ናቸዉ። የኢትዮጵያ መከራ ሲበዛ ቋራ ቀድማ እምባ ማበስ ታዉቅበታለች።የቆራ ምድር እና ልጆቿ ለእናታቸዉ ኢትዮጵያ ብዙ ታሪካዊ ስራዎችን አበርክተዋል።እናት ሀገር ኢትዮጵያ በታመመችበት ጊዜ ቋራ ሀኪምም መድሀኒትም በመሆን ከበሽታዋ ትፈዉሳታለች።በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ክፉኛ የታመመችዉ ኢትዮጵያ መድሀኒት የተገኘዉ ከበጌምድር ግዛት ቆራ ነበር።ቋራ ኢትዮጵያን ከክፉ በሽታ የታደገች የቃል ኪዳን ምድር ናት።በጎንድር መሬት ቃልኪዳን መፈፀም ቀላል ትርጉም የለዉም።ማተባቸዉ የጠበቀዉ ጎንደሬዎች የተሰጣቸዉን እምነት በማፅናት እና ቃላቸዉን በመጠበቅ የሚታወቁ ኩሩ አማራዎች ናቸዉ።ከደጋጎቹ ወሎዮች፣ ከሸዋዎች፣ ከጎጃሞች ጋር የተሳሰረ እና የጠበቀ ስነ ልቦና ያላቸዉ ጎንደሬዎችቃል ኪዳን ለመቀበል ወደር የማይገኝላቸዉ ስለመሆናቸዉ የአደባባይ እዉነት ነዉ።ቋራ በኢትዮጵያውያን የቃል ኪዳን ምድር በመባል ትጠራለች።ከቋራ ሰማይ ስር እና ከቋራ ምድር ላይ አንድ እዉነት አለ እሱም ቃልን ማክበር ነዉ።ለቃላቸዉ የሚታመኑት ጎንደሬዎች ከወንድሞቻቸዉ የሚመጡ አደራዎችን ለመቀበል እምነት ተጥሎባቸዋል።

ኩሩና ቀብራራው ጎንደር፦ የራስ ደጀን እና የጉና የተራራ ግርማ ሞገስ ተላብሰዉ ልክ እንደ ተራሮቹ የገዘፈ እምነት፣ ፅናት እና ጀግንነት አላቸዉ። በካሳ ሀይሉ አገር ቋራ እምነት መቀበል እና ቃል ኪዳን መፈፀም እንዲሁም ማተብ አጥብቆ ማሰር የተለመደ ቁምነገር ነዉ።በቋራ ምድር ልክ እንደ ቀደሙ በሚመስል መልኩ መይሳዉን እና ገብርየ የሚመስሉ ቃል ኪዳን ተቀባዮች ተፈጥረዋል።

ቋራ ለዳግም ቃልኪዳን የተመረጠች ሙሽራ በመደረጓ አማራን ለማዳን ለሚደረገዉ የቃልኪዳን ሰነድ ዝግጅቷን አጠናቃ በተጠንቀቅ ተሰለፈች።

አገራቸዉን ከበሽታ ለመታደግ ወደ ቋራ የሚተሙት አርበኞች በብዙ ፈተናዎች ታጅበዉ አሰልችዉን መከራ ጨርሰዉ ከሚናፍቋት የቃል ኪዳን ምድር ቋራ ደረሱ።

በቋራ ምድር ቃል ኪዳን ፈፃሚዎችን ለመቀበል ከህፃን እስከ አዋቂ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተስለፈዉ በጉጉት ሲጠባበቁ ከሰነበቱ በኋላ ጀግኖች ወንድሞቻቸዉን በደስታ ተቀበሏቸዉ።

ቋራ ወንድሞቻን ለመቀበል ብዙ ክስተቶችን አስተናግዳለች።በአርበኛ ሀብቴ ወልዴ የሚመራዉ የቀጠናዉ ፋኖ የቃል ኪዳኑ ሰነድ እስኪፈፀም ከደቡብ እስከ ሰሜን ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በስዉር ተልዕኮ ተሰቶት ግዳጁን በሚገባ ተወቷል።ከጎንደር የተነሰዉ የፋኖ መሪ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ብዙ ኪሎሜትሮችን አቆራርጡ ከአያቱ ሀገር ቋራ ከተመ።ለቃል ኪዳኑ ድግስ ሲባል ቋራ ቀድሞ የገበዉ ከወራቶች በፊት ነበር።ከመሃል ጎንደር ደጋማ ክፍል ተነስቶ ከምዕራቡ የበረሀ ምድር እስኪገባ ድረስ በርካታ መሰናክሎች አጋጥመዉታል።አርበኛ ሀብቴ ወልዴ በአያቱ አገር ቋራ እስኪ ገባ ድረስ በጦርነት፣ በርሀብ፣ በጥም፣ በብርድ፣ በሙቀት እና በመሰል አደገኛ ችግሮችን በማለፍ ነዉ። ብዙ ዉጣዉረዶችን አልፎ ቋራ የከተመዉ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ በቋራ በሚገኙት ወንድሞቹ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። የአርበኛ ሀብቴ ወልዴን መምጣት ሲጠባበቁ የነበሩ ቋረኞች መንገድ በመክፈት ከጣላት ጋር ለሁለት ሳምንታት ተናንቀዋል።አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ቋራ ከደረሰ በኋላ ከጓዱ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ አርበኛ ሸጋ ጌታቸዉ እና መሰል አርበኞች ጋር በመገናኘት ለቃልኪዳኑ ሰነድ ዝግጅት ጀመሩ።ሌላኛዉ አድካሚ ጉዞ ያደረገዉ ደግሞ በጎንደር ቀጠና ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆነዉ የበረሀዉ አናብስት አርበኛ አስቻለዉ በለጠ ነዉ።ከአባቱ ዋዋ ጎቤ አገር አርማጨሆ ተነስቶ ከአያቱ መይሰዉ ካሳ ቅየ ቋራ እስኪደርስ ድረስ በርካታ ችግሮችን አስተናግዷል።የበረሃውን ሀሩር፣ ሙቀት፣ ዉሀ ጥም፣ ዕርሀብ እና ድካም ተቋቁሞ ቋራ ከተፍ ያለዉ አርበኛ አስቻለው በለጠ ፅናቱ እንደ ገብረየ ጀግንነቱ እንደ መይሳዉ ሲሉ ጓዶቹ አሞካሽተዉታል።ከአርማጭሆ ጎንደር፣ ከጎንደር ቋራ አሰልችዉን ጉዞ አድርጎ ከወንድሞቹ ጋር በመሆን ለቃል ኪዳን ድግሱ ሽር ጉዱን ተቀላቅሏል።አርበኛ አስቻለው እግሮቹ ዝለዉ ቋራ ሲገባ በጓዶቹ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ጓዶቹን ለመቀበል መንገድ በመጥረግ እና ጠላትን ከመንገዱ በማስወጣት ከፍተኛዉን ድርሻ የተወጠዉ ደግሞ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ነዉ።ሰፊዉን የቋራን በረሀ ከጠላት ጋር በመተናነቅ ጓዶቹን በመዳፉ አስገብቷል። የቴዎድሮስ ልጅ ቀጠናዉን ከጠላት በማፅዳት ቋራን ለቃል ኪዳን መፈፀሚያ ሞሽሮ አስቀምጧታል።የህዝብ ግንኙነት ስራውን በማሳለጥ ደግሞ ከፍተኛ ሃላፊነት የተወጣው የቴዎድሮስን መንፈስ የተላበሰው አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ ነው። እነ ሀብቴ ወልዴ እና እነ አስቻለዉ በለጠ ደግሞ የተሞሸረችዉን ቋራ ለእንግዶች እንድትስብ አድርገዉ ኩለዋታል።

የቋራ ምድር እና ልጆቿ የጀግንነት ወኔ መንፈስ ተሞሽረዉ አካባቢውን ከሰው ጋኔል ከጂኒዎቹ- ከሰው ጊንጥ ከእባቦቹ በማፅዳት፣ በአማራ ህዝብ የእንግዳ ተቀባይነት እሴት ከየአቅጣጫው ወደ ቋራ የተመመውን የፋኖ ሀይል እንደ ወላጅ እናት አቅፎና ደግፎ በጋለ የወንድምነት ስሜት መቀበል የቻለው በጎንደሩ የፋኖ መሪ በአርበኛ ሀብቴ ወልዴ ወታደራዊ አመራር ሰጭነት ነው።

የጎንደሩ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ተዋጊና አዋጊ ነው፣ የቴዎድሮስ፣ የገብርየ፣ የእነ አሞራው ውብነህ፣የእነ ጎቤ መልኬ፣ የእነሰጠኝ ባብል፣የእነ አርበኛ መሳፍንት፣ የእነ አርበኛ ሰፈር መለስ የእምቢኝ ባይነት አርበኝነት መንፈስ ያነፀው፣ በጦር መሃዲስነቱ የተመሰከረለት ነው።

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የጎንደር አማራ ፋኖን ከመሰረቱት አርበኛ ሲሳይ ኣሸብር፣ አርበኛ ባዬ ቀናው፣ አርበኛ አንተነህ ድረስ፣ አርበኛ ውባንተ አባተ፣ አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱና ሌሎች አርበኞች መካከል የተገኘ ሲሆን የተሰጠውን የመሪነት ሚና የተወጣ እና ከእነ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር አብሮ የሰራ የቅርብ ወዳጁም ነበር።በኮማንዶ አሰልጣኝነቱም ብዙ ጀግኖችን አፍርቷል። አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ህውሃት ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ኢትዮጵያን ለመበታተን ወረራ ሲያካሄድ በቁርጠኝነትና በጀግንነት የጦር መሪ በመሆን የታገለ የህዝብ ልጅ ነው። በጭና፣ በዘሪማ፣ በጨው በር፣ በደብረዘቢጥ እና በተለያዩ ቦታዎች የህወሓትን ፅኑ ምሽጎችን የሰባበረ፣ በደንቢያ፣ በእብናት ከዚህ አለፍ ብሎም በ2011 ዓ/ም በጎጃም ደብረ ኤሊያስ የአብይን ሰራዊት ቁም ስቅሉን አሳይቶታል። በተወርዋሪ ተዋጊነቱ የሚታወቀው አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የኦህዴድ ሰራዊት ጋር ባደረጋቸው አውደ- ውጊያዎች ከነፍስ ወክፍ እስከ ቡድን መሳሪያ እና ወታደራዊ ሎጅስቲክ ወዘተ የማረከ የዘመናችን እንቁ አርበኛ ነው።

በዚህ መራር ተጋድሎም የቅርብ አጋሮቹ የሆኑትን አርበኛ ውባንተ አባተን፣ አርበኛ ናሁሰናይ፣ አርበኛ ኩሩቤል፣ አርበኛ እሸት እንደሻው፣ አርበኛ ከፍያለው ደሴ አርበኛ በሪሁን አርበኛ ማሩ ከቤ፣ አርበኛ አንጋው ተገኝ ...… የመሳሰሉ የህዝብ ልጆችን እና የቅርብ ቤተሰብ የሆኑትን እንቁ አርበኞች እነ ዳኒኤል ገብየሁንና ሌሎችንም አጥቷል።

አርበኛ ሀብቴ ወለልዴ ለቁጥር የሚታክቱ አያሌ የጀግንነት ገድሎችን የፈፀመ ሲሆን ፤የቋራን የአንድነት ቃል ኪዳን ለማስፈፀም በግንባር ቀደምትነት አስተባብሯል፣ መርቷል፣ ከየ አቅጣጫው የተመሙትን ፋኖዎችን ደህንነት ለማስጠበቅና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ከስጋት ነፃ ቀጠና በማድረግ ሃላፊነቱን ተወቶአል። በክብር የመጡት የፋኖ መሪዎቻችንም በልዩ የፋኖ ኮማንዶ ጥበቃ ተደርጎላቸው ያለምንም ስጋት ድርጅታቸውን እንዲመሠሩት እና ከድርጅታዊ ምስረታ መልስም መሪዎች ወደመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ የጥበቃ የሽኝት ግዳጃቸውን እንዲወጡ አድርጓል።

የጄኔራል ተፈራ ማሞ አርበኝነት
ቋራ"!- ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!!
==================

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር በመሆን የአማራን ህዝብ በሂዎት የመኖር መብት ለማስከበር ከህወሓትም ሆነ ከኦህዴድ አገዛዝ ጋር መራር ፍልሚያ ያካሄደ፣ በጡረታ ዘመኑ ከህመሙ ጋር እየታገለ በአማራ ግዛት የተካሄዱ ውጊያዎችን የመራ የቁርጥ ቀን የጦር ጄግና ነው። ከላስታ ምድር አይና ቡግና የበቀለው የሽምቅ ውጊያ ጠበብቱ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ህውሃት በኢትዮጵያ በተለይም በአማራው ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል በመቃወሙ ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋር በእስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል። ከዚያም በአማራ የፀጥታ ሀይል ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ አያሌ የትግል እንቅስቃሴዎችን አድርጓል። ጥንቅቅ ያለ ለህዝብ ቀድሞ ሟችና ታማኝ ሰራዊት ገንብተዋል።

በተለይ በህወሃት ወረራ ወቅት የመከላከያ ሰራዊቱ ሲዳከምና ትህነግ አንሰራርታ ግስጋሴዋ ሲበረታ ጀነራሉ ለእረፍት ከተቀመጠበት ጀግንነቱና የጦር ጠበብትነቱ ታምኖበት በአስቸኳይ ወደጦሩ እንዲቀላቀል ተደርጎ ደጋማውን የጋሸና እስታይሽና ድልብ ቀጠና ህመሙን ችሎ እያነከሰ ጦሩን ከፊት በመምራትና በማዋጋት አስደናቂ ውጤት ያስመዘገበ ነው። እየቆየም በሁሉም ግንባር ለተሰለፈው የልዩ ሃይል ልዩ መመሪያን በመስጠት አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል።

መጭው ጊዜ ቁልጭ ብሎ የታየው ጄነራሉ ለልዩ ሃይሉ ልዩ ያለውን ስልጠና እንዲወስድና የቡድን መሳሪያ እንዲታጠቅ ይወተውት ነበር። ይህ በአገዛዙ አልተወደደለትም ነበርና ራሱን ከጦሩ አግልሎ ህመሙን ለማስታመም ቢሞክርም ጥሩ ህክምና ተነፍጎት በቤት ውስጥ አርፎ ቢቀመጥም መሳደዱ አልቀረለትም ነበር። የልዩ ሃይሉ መበተን ትልቅ ውለታ የዋሉትና ማርከህ ታጠቅ የተባሉት የፋኖ አባላት ውጊያ ሲከፈትበት ሞሰቡን ገልብጦ ያበላና ሰንጋውን አርዶ ትኩስ ያጎረሰው የአማራ ህዝብ ሲከዳና ሲጨፈጨፍ አልሆንልህ ያለው ጄነራል ተፈራ ከህመሙ ሳይሽርና በቂ እረፍት ሳይወስድ ዳግም በሸዋ ግንባር ፋኖን ተቀላቅሎ ለአማራ ህዝብ ታማኝነቱን እያሳየ ቀጥሏል።

ይህ ጉምቱ የጦር ጠበብት በየበረሀው እየተንከራተተ የጦር ልምዱን ለተተኪው ወጣት የፋኖ አመራር እያካፈለ ከጨፍጫፊው ስርአት የሚቃጣን ጥቃት እየመከተ ዛሬም ከነክብሩና ሞገሱ አለ።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ በታመመ እግር የማያመው ተራማጅ ልበ ሙሉ የጦር አርበኛ ነው። ስሙ ብቻ የሚያታግል የአማራ እናት የወለደችው የጠላት እራስ ምታት የጦር ጠበብት ነው። አሁን ላይ ለአማራ የህልውና ትግል መስዋትነት ዋጋ እየከፈለ ያለ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን የአይን ብሌን ሆኖ ተገኝቷል።

የቋራ የአማራ ፋኖ የአንድነት ቃል ኪዳን፦የሂዎት መስዋትነት የተከፈለበት፣ አያሌ መራና እንግልት የታየበት እንደመሆኑ መጠን ከሆደ ባሻነት የፀዳ ሊሆን ይገባል። የኦህዴድ አገዛዝ ወታደሮች በጀግንነት ረገድ ከአማራ ፋኖ ጋር ለንፅፅር የሚቀርብ አይደለም። በህዝብና በአገር ፍቅር፣ በጀግንነት ወኔም ሆነ በአላማ ፅናት ከፋኖ ጋር አይወዳደርም። እናም አገዛዙ በፋኖ ውስጥ የተለያየ የተጣመመ አስተሳሰብ እየነዛ ፋኖውን መከፋፈልና ትግሉን ማዳከም ጥሩ ዘዴ አድርጎ እየተጠቀመበት ነው።

ውድ የአማራ ፋኖ አርበኞች! ስለ ቋራ ቃል ኪዳን በሰፊው የማብራራው ምክኒያቴ የተመሰረተው አንድነት ለአማራ ህዝብ እንደ ትልቅ ምዕራፍ በመመልከቴና ወደ መጨረሻው የተቆአም አደረጃጀት ቅርፅ ስለሚኣመጣ ነው ብዬ ስለማምን ነው።
በመሆኑም በአማራ ህዝብ ስም የገባችሁትን ቃል ኪዳን እውን እንስኪሆን ድረስ እስከ ሞት ድረስ የታመናቹሁ ናቹሁ ብየ አምናለሁ። ምክንያቱም ትግሉን እዚህ ከፍ ያለ ደረጃ ያደረሳቹሁ የህዝብ ልጆች ስለሆናቹሁ አሁንም ከዚህ የተሻለውን ውጤት በገባችሁት ቃል ኪዳን መሰረት እንደምትፈፅሙት በመተማመን ነው።

ከቡድን ስሜት፣ ከጎጥ አስተሳሰብ የፀዳቹሁ ሆናቹሁ ቃል ኪዳናቹሁን በትናንሽ የስልጣን ፍላጎት አሊያም በሌላ አንዳች ያልተገባ ምክንያት ብታፈርሱ የአፄ ቴዎድሮስ፣ የእምየ ሚኒሊክ፣ የንጉስ ሚካኤል እና የበላይ ዘለቀ አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋችኋል። በአማራ ህዝብ የደም እዳ ትያዛላቹሁ፣ የድል ጊዜውን ታራዝማላቹሁ፣ መከራችንን ታገዝፉታላቹሁ።

ስለዚህ የህዝብ አደራ አለባቹሁ። የምንለማውም ሆነ የምንጠፋው በአማራነታችን እንጅ እንደ ወሎ፣ ጎጃም፣ ሽዋ ጎንደር አይደለም። ፋኖን በመከፋፈል የትግሉን መንፈስ ለማጨለም የምትታትሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ወይም ከዚህ ከፍ ያለ ሚዲያ የምትጠቀሙ እሾሆች ከጥፋት ተልኳችሁ ታቀቡ፤ እንደ ፋኖ በጀግንነት ለመዋጋት ወኔ ካጣቹሁ በቃ ዝም በሉ። እስከ መቼ በወሬ አገርና ህዝብ እያፈረሳቹሁ ትኖራላቹሁ? ይብቃቹሁ።

በመጨረሻም
በዚህ በቋራው የአማራ አንድነት ቃል ኪዳን ጉባኤ ላይ የተለየ አመለካከት በመያዛቸው ምክንያት ያልተካፈሉ ሌሎች ጀግኖች መኖራቸውንም መዘንጋት አልችልም። ለምሳሌ ከወሎ ኮኔለር ፋንታሁን ሙሃባው ይጠቀሳል። በአያሌ የውጊያ አውደ-ግንባሮች ላይ በጀግንነት የተዋጋና ያዋጋ የአማራ ህዝብ ባለውለታ ነው።

ሌላኛው የንጉስ ሚኒልክ አድባር ያፈራችው የሽዋው ፋኖ አርበኛ መከታው ማሞ ነው። ይህን አርበኛ የማውቀው ከ2014 ዓም ጀሞሮ ነው። አርበኛው በባህሪው ዝምተኛና አዳማጭ ነው። ተዋግቶ በማዋጋትም የተዋጣለት ጀግና ነው። በአካባቢው ፋኖ እንዲደራጅም የበኩሉን አሻራ ያሳረፈ የአማራ ህዝብ ባለውለታ ነው።

በተጨማሪም የትግል ጓዶቹ አባ ናደው ብለው የሚጠሩትን የጎንደሩ አርበኛ ደረጄ በላይን ብንመለከት እራሱ ከሚያደርገው አርበኝነት ባለፈ ሁለት ልጆቹን ለአማራ ህልውና ትግል የገበረ እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦችንም በመስዋትነት ለአማራ ህዝብ ሲል የተነጠቀ ጀግና አርበኛችን ነው። አርበኝነቱን ለመመስከር አርበኛ ደረጄ በላይ የዋለበትን አውደ- ውጊያዎችን ማስታወስ በቂ ነው።

ይሁን እንጅ እነዚህ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ያለባችሁን የአማራ ህዝብ አደራ አስባቹሁና አሰላስላቹሁ ካላችሁበት መስመር ወደ አንድነቱ የምትቀላቀሉበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን አምናለሁ።

ስለዚህ በተቻለ መጠን በነገር ሁሉ ለአማራ ህዝብ ህልውና መቀጠል የቋራ የአንድነት ቃል ኪዳን ቃለ መሀላ መጠበቅ ይኖርባቹሃል። ወደ ፍትህና ነፃነት መድረስ ይኖርብናል፣ አማራው እንደ ሰው በነፃነት እንዲኖር በአንድነት ከመታገል ውጭ አማራጭ ስለሌለን ነው። አለበለዚያ እንደኩርድ ተበታትነን እንቀራለን። ማንነታችን ይጠፋል፣ ታሪካችን ይፋቃል፣ ማህበራዊ እሴቶቻችንን እናጣለን፣ በምድር ላይ ተሳዳጆችና ተቅበዝባዦች እንዲሁም ጎስቋሎች ከመሆናችን በፊት ተግዳሮት ባጋጠመን ቁጥር ቆም ብለን ደጋግመን ማሰብ ባህላችን እናድርግ። ቃል ኪዳናችንን በታማኝነት እንጠብቅ። እንበርታ!!! ድል እናደርጋለን።
ድል ለአማራ ፋኖ

ቀለብ ስዩም አበራ
21/09/2017 ዓ/ም

ሰበር የግንባር መረጃ | አገዛዙ ደፍሮ የማይውልበት ቀጠና - ውርጌሳ | "ነፍስ ውጭ - ነፍስ ግቢ" በጎጃም እና ጎንደር | Fano News
05/29/2025

ሰበር የግንባር መረጃ | አገዛዙ ደፍሮ የማይውልበት ቀጠና - ውርጌሳ | "ነፍስ ውጭ - ነፍስ ግቢ" በጎጃም እና ጎንደር | Fano News

የጎጃም ግንባር የውሎ ዘገባየአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የጎጃም ቀጠና በተለያዩ አውደ ገንባሮች ባደረገው ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ። በአገዛዙ ብልፅግና ስምሪት ተሰቷቸው ህዝብን በመዝረፍ ሲ...
05/29/2025

የጎጃም ግንባር የውሎ ዘገባ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የጎጃም ቀጠና በተለያዩ አውደ ገንባሮች ባደረገው ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ። በአገዛዙ ብልፅግና ስምሪት ተሰቷቸው ህዝብን በመዝረፍ ሲያማርሩ የነበሩም በበፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል

በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር በቲሊሊ ዘንገና ብርጌድና ቡያ ገረመዉ ሻለቃ ጥምረት ከግምጃ ቤት ወደ ቡያ ተንቀሳቅሶ የነበረውን አድማ ብተና እና ሚኒሻ ከባድ ቅጣት አድርሶበታል።

በዛሬው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ለተከታታይ 2:00 በዘለቀዉ አወደ ውጊያ ሆድ አደሩ ከመሸገበት ቦታ ከበባ በማድረግ ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድና ቡያ ገረመዉ ሻለቃ በፈፀሙት ጥቃት 3 ክላሽ ከነ መሉ ትጥቅ እንዲሁም 1 አብራራው ሲማረክ፤ 5ሚነሻና 4አድማ ብተና ሃይል እስገወዲያኛው ተወግደዋል።

ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ሀይል ቁስለኛ ሁኖ ወደ መጣበት ግምጃቤት ከተማ እየፈረጠጠ የገባ ሲሆን በዚህ አስደማሚ የሩጫ ትርኢት በሚመስለው ውጊያ ተጨማሪ ሀይል ከእንጅባራ ከተማ በመድረስ ከመደምሰስ አትርፏቸዋል ሲል
የጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ የህ/ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ አለበል አወቀ አስታውቋል።

በሌላ መረጃ
ዘራፊው የጠላት ኃይል በሺንዲ ወበርማ ማር ወለድ ቀበሌ በሀይላችን ላይ ከጥዋቱ12:00 ሰአት ከበባ ለመፈፀም ቢያስብም የሺንዲ ወበርማ ብርጊድ ንስር ሻለቃ እና የጓጉሳ ብርጌድ አባላት ጋር በጥምረት ባደረግነው ኦፕሬሽን ከበባውን ጥሶ መውጣት ተችሏል ሲል የ5ተኛ ክፍለ ጦር ጓጉሳ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ገልጿል።

በዚህ ትንቅንቅ ፋኖን በከበባ አጠቃለሁ ያለው የብልፅግናው ስርዓት አስጠባቂ ሃይል በጓጉሳ ብርጌድ ነበልባል የፋኖ አባላት በተፈፀመበት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ 17 ሙትና በርካታ ቁስለኛ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሰናል ሲል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ገልጿል።

በተጨማሪም በዚሁ ዕለት የብልፅግናው ወበር አስጠባቂው ሚኒሻ የአድማ ብተና እና ፖሊስ ሀይል ከአዘና ከተማ በመነሳት "አምበራ፣ ደገራ እና ድኩሻ ቀበሌዎች ላይ ወረራ በማካሄድ በህዝባችን ላይ ከባድ የሆነ ዘረፋና እገታ እንዲሁም ጭፍጨፋ ፈፅሟል ሲሉም አክለው ገልፀዋል።

እደ አብነትም ከሴቶች የእጅ ቀለበት እና የጆሮ የወርቅ ጌጣጌጦችን : የአንገት ጌጦጌጦችን እና ቤት ሰብሮ በመግባት ገንዘብ እና አልባሳት በተጨማሪም የሶላር መብራት ፖናሎችን ስለመዝረፉና የፋኖ ቤተሠብ በሚል ከአረጋውያን እስከ እመጫት ድረስ እገታ መፈጸማቸውን አብራርተዋል።

ይህንን በማስቀጠል ከዋለ ከአደረ በበሗላ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ የጓጉሳ ብርጌድ ሀይል ግንቦት18 ቀን 2017 ዓ.ም ጠላት ሬሽን እና ሀይሉን ጭኖ ወደ ድንኩሻ በመምጣት ላይ እያለ በጀግኖች ሀይላችን ስልት አማካኝነት የጫነውን ሬሽን ሙሉ በሙሉ የማረከ ሲሆን በወሰደው ኦፕሬሽን 10 ሙት እና በርካታ ቁስለኛ በማድረግ ጠላት ተቆጣጥሮት የነበረውን ቀጠና ለማስለቀቅ ተችሏል።

ከዚህ በመቀጠል በትናንትናው ዕለት ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም መነሻውን ሺንዲ ከተማ ያደረገው የብልፅግና ጨፍጫፌውና ዘራፊው ብድን ፋኖን አጠፋለሁ በሚል እሳቤ ወደ ድንኩሻ ቀበሌ በመምጣት ላይ እያለ በጀግኖት ክንደ ብርቱ የጓጉሳ ብርጌድ አባላት በሠሩት የደፈጣ ስልት 4 ሙት : 2 ቁስለኛ በማድረግ ጠላትን ወደ መጣበት ቀጠና አስገብተውታል ሲል የ5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ/መምሪያ ሀላፊ
፲/አ ኢ/ር ዘመኑ አማረ ገልጿል።

በሌላ በኩል
ተሽከርካሪ እያስቆሙ የተሳፋሪዎችን የእጅ ስልክ ሲነጥቁ፣ ቀለበት፣ የአንገት ሃብል እና የተለያዩ ንብረቶችን ሲዘርፉ የነበሩ አገዛዙ ያሰማራቸው ዘራፊዎች በአፋብኃ የጎጃም ቀጠና ጎጃም አገዉ ምድር 3ኛ ክ/ጦር ስር በሚገኘው በቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከተያዙ ጀምሮም አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገ በኋላ አስተማሪ ቅጣት ይጠብቃቸዋል የተባለ ሲሆን ሌሎችም ከዚህ ተምረው እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

በትናንትናውም ዕለት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጎጃም ቀጠና የበላይ ዘለቀ 8ኛ ክፍለጦር ዛም በረሃ ብርጌድ በትናንትናው እለት በርካታ የጠላትን ሃይልን መደምሰስ ሲቻል ቀሪውን ቁስለኛ አድርጓል።

በተመሳሳይ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ አቸፈር ወንድዬ አቤ ጉበኛ ብርጌድም ትናንት ግንቦት 20 ቀን ከሀሙሲት በመነሳት ወደ ልምታን የተንቀሳቀሰዉን የጠላት ሃይል በክ/ጦሩ ልዩ ኮማንዶ ጦር ድባቅ ተመቷል።

ልዩ ኮማንዶው ጦሩ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን 2 የጠላት ሃይል መደምሰስ ሲቻል ብዛት ያለዉ የጠላት ሃይል ቁስለኛ ሁኗል።

@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
የፋኖ ድምፅ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCoRwyRf4F1B_onG2D4y5o0g

Facebook https://www.facebook.com/share/17EDDFWEwU/

telegram https://t.me/gfmn21

Tweeter https://x.com/GlobalFanomedia

Share your videos with friends, family, and the world

Address

Calgary, AB

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዓለም አቀፍ ፋኖ ሚዲያ ኔትወርክ-Global Fano Media Network-GFMN:

Share