04/28/2025
#ሰበር ዜና
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደለ፡፡ ግድያው የተፈፀመው በሊችተንበርግ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሱቅ ውስጥ መሆኑን የኖርዝ ዌስት ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ሟቹ እድሜው 35 አመት የሆነ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ገልፆ ተጠርጣሪዎቹ ጭምብል አጥልቀው ወደትራክ ሱቁ ውስጥ መግባታቸውን አስረድቷል፡፡
ከዚያም ሟቹን ደረቱ ላይ በጥይት መተው ከአካባቢው መሰወራቸውን አስታውቋል፡፡ ገዳዮቹ ከሱቁ ውስጥ ምንም አይነት ንብረት አለመውሰዳቸው ደግሞ ድርጊቱን ከዝርፊያ ውጭ የሆነ አላማ እንዳለው የሚያሳይ እንደሚያደርገው አስረድቷል፡፡ ግድያው የተፈፀመው ሀሙስ እለት እንደሆነ ያስታወቀው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በማደን ላይ መሆኑን ማስታወቁን አይኦኤል ጋዜጣ ዛሬ ዘግቧል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያዊያን ላይ ተደጋጋሚ ግድያ እየተፈፀመ መሆኑን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡