Meb Free thinker

Meb Free thinker esrael

 #በረከት በተስፋዬ ሲንድረም በኩል!(በማዕረግ ጌታቸው)የተስፋዬ ገብረአብ ትልቁ ጥፋቱ በታሪክም ሆነ በሳይንስ የማይረጋገጡ ጉዳዮችን ፖለቲካዊ ማዕቀፍ እየሰጠ ሕዝባዊ ለማድረግ መጣሩ ነው። ይ...
01/03/2026

#በረከት በተስፋዬ ሲንድረም በኩል!
(በማዕረግ ጌታቸው)

የተስፋዬ ገብረአብ ትልቁ ጥፋቱ በታሪክም ሆነ በሳይንስ የማይረጋገጡ ጉዳዮችን ፖለቲካዊ ማዕቀፍ እየሰጠ ሕዝባዊ ለማድረግ መጣሩ ነው። ይህን ችግር ተስፋዬ ሲንድረም ብዬ እጠራዋለሁ። ሲንድረሙ ዝንቅ ነው። መነሻው እውነት መድረሻው ግነት/ ውሸት። በረከት በላይነህ ባለፉት ጥቂት ወራት በሚሰጣቸው ቃለ-መጠይቆች በዚህ ጎዳና እያመራ ይመስለኛል። ልዩነት አብዛኛው ሕዝብ መሰማት የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች በማውራቱ የረባ ጥያቄ ሲቀርብበት አለመሰማቱ ነው።

የቆየውን ትተን ትናንት በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ ብቻ እናተኩር። በረከት በቆይታው ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበት ዲፕሎማሲያዊ ቁመና የአሰብ ወደብን ለማስመለስ የሚችል ነው ብሎ እንደሚያምን ጠቀሷል። የሚያስገርመው ግን ቆየት ብሎ የተናገረው ነገር ነው። ዳዊት ተስፋዬ "እንዴት?" የሚል ጥያቄ ሲያቀርብለት "በጉልበት" ሲል መለሰ። ተቃርኖው የዋዛ አይመስለኝም። የበረከት ሕሊናዊ መዝገበ ቃል ብዙ ጊዜ ከታሪክና ሳይንስ ጋር የሚጋጭ ነው። ለዚህ ማስረጃው በዓለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ጦርነትን ዲፕሎማሲ አድርጎ መግለጹ ብቻ አይደለም። ይልቁኑስ የሕግና የታሪክ አረዳዱም ከተስፋዬ ሲንድርም አላስመለጠውም።

በረከት በላይነህ በደጃፍ ቲቪ ደጋግሞ የኢትዮጵያን የአሰብ ወደብ ይገባኛል ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕግ (Accese to the sea) ሊዳኘው ይሞክራል። ይሁን እንጂ እዚህም ላይ ያለው ግንዛቤ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው። አንድ ጥያቄ ነገሩን ግልጽ ያደርገዋል። በረከት "አሰብ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግዛት ነው ብሎ ያምናል?" ምላሹ አጭርና ግልፅ ነው::

አዎ!

ታዲያ ተቃርኖው የሚወለደውም እዚህ ሥፍራ ላይ ነው። እርሱ ደጋግሞ የሚጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባሕር በር ለሌላቸው አገራት የሰጠው የመጠቀም መብት (Accese to the sea) ከወደብ ግዛት ይገባኛል ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም። ማንም አንባቢ በቀላሉ በበየነ መረብ ሊያረጋግጥ እንደሚችለው UN የባሕር በርን አስመልክቶ ያቀረባቸው አምስት የሕግ አንቀጾች አንዳቸውም ከበረከት መከራከሪያ ጋር ቅርበት የላቸውም፡፡ እውነታው እንዲህ ከሆነ ድንጋጌውን አላነበበውም አልያም አጣሞ ተረድቶታል ብሎ መናገሩ ድፍረት አይሆንም፡፡

እንዲህም ሆኖ አጭር ምሳሌ መስጠት ፍርደ ገምድል ከመባል ስለሚያድነኝ ወደዛው ልለፍ። ቦሊቪያ የባሕር በሯን ተነጥቃ የቀረችው በጦርነት ነው። የሚያስገርመው ግን መሪዎቹ ለዙፋናቸው ሲሉ ባደረጉት ስምምነት የሔደውን ወደባቸውን ለቺሊ ማጽናታቸው ይመስልል። ይህ የታሪክ አውድ ሂደቱ ቢለያይም በመጡንም ቢሆን ለበረከት ክርክር ቅርበት ያለው ነው::

በመሆኑም የሁለቱን አገራት ተሞክሮ ማጤን የባህር በር የመጠቀም ዓለም አቀፍ ሕግና የይገባኛል ጥያቄን ልዩነት ለመረዳት ያግዛል:: ቦልቪያዊያን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኇላ ዛሬ በአገራችን እንደሚታየው ሁሉ የወደብ ጉዳይን የፖለቲካ አጀንዳ ለማድረገው ችለው ነበር:: ይሁንና ጥያቂያቸው ግልፅኔና ቀጥተኛ ነው:: ጉዳያችን የወደብ ባለቤትነት እንጂ የመጠቀም (Accese to the sea) አይደለም አሉ::

ከፍ ብዬ እንደገለፅኩት ሁለቱ የሚታዩበት ዓለም አቀፍ ሕግ ፍፁም የተለያየ ነው::ስለሆነም ቦሊቪያ የተወሰደብኝን የባሕር በርን ልጠቅም ሳይሆን ይገባኛል ብላ ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ICJ ከሰሰች። ክርክሩ ለዓመታት ዘልቆም በ2018 ውሳኔ አገኘች። በረከት የተምታታበት እንዲህ ያለው መንገድ ነው:: ታሪካዊ ባለቤተነትን የባህር በር ከመጠቅም መብት ጋር ተሳክሮበታል::

እንዲህ ያለው የታሪክ ተሳክሮ አንድ ቦታ ላይ ብቻ የሚታይ አይደለም:: በየቃለ መጠይቁ የሚደጋግመውን የሰሜን ኢትዮጵያ ፖለቲካ አረዳዱን ላክል። ውስብስቡን የዘመነ መሳፍንት ዘመን አጣቅሶ ለመግለጽ የሞከረው ለራሱም ግልጽ ስላልሆነ ሁለቱን ፓርቲዎች ብቻ እንመልከት። በረከትም ሆነ በርካታ የአደባባይ ተንታኞች የሰሜን ኢትዮጵያ ብሔርነተኝነት የተወለደውና የተዳረው በኤርትራዊያን እንደሆነ አድርገው ጽፈዋል፤ተናግረዋል።

እነዚህ ሰዎች የሚዘነጉት አንድ ትልቅ ሀቅ አለ። እርሱም የኤርትራን ነፃነት ጥንስስ የጣለው፤ ብሎም ግብጽ በመሔድ በካይሮ ራዲዮ የዓየር ሰዓት አግኝቶ በፕሮፖጋንዳ ስራው በርካቶችን ወደ ትግል ያስኮበለለው፤ ቀደሚውንም የአስገንጣይ ድርጅት የመሰረተው የትግራዩ ወልደአብ ወለደማርያም መሆኑን መርሳታቸው ነው።

በረከት እና አንዳንድ የአደባባይ የታሪክ ተንታኞች የትግራይ ብሔርተኝነት የሻዕብያ ዲቃላ መሆኑን ቢገልጹም እውነታው ግን ሻዕቢያ ራሱ የትግራዩ ወልደአብ ወልደማርያም የልጅ ልጅ መሆኑ ነው። የወልደአብን የማንነት ቀውስና የታሪክ ተቃርኖ ለሌላ ጊዜ አቆይተነው በረከት ትናንት በስፋት ሊተነትነው የሞከረውን የሕወሓትና ሻዕቢያ ባንድ ሳምባ ነው የሚተነፍሱ ሙግት እንመልከት። በርግጥ እንዲህ ያለው ሀሳብ አገሩን ከሞላው ከራርሟል። ሁለቱ አማጽያን ሲሰርቁ ተስማምተው ሲካፈሉ ተጣሉም ተብሎ በብዙ ተለፏል።

ከፍ ብለን እንዳደረግነው ሁሉ ይህንንም በጥቂቱ ለመፈተሸ እንሞክር። ሕወሓትን አብዝቶ በመተቸት የሚታወቀው አረጋዊ በርኼ በሦስተኛ ድግሪ መመረቂያው ጽሑፉ ሁለቱ ድርጅቶቹ ፀብ የጀመሩት ፍቅራቸውን ሳያጣጥሙ መሆኑን ያነሳል።እርሱም ከርዕዮተ ዓለም ምርጫ ጋር የተያያዘ ነበር። በጊዜው ሻዕቢያ የሶቪየትን ሶሻላዚም ሲከተል ሕወሓት በአንፃሩ ጨቋኙን ደርግ የምትረዳን አገር ርዕዮተ ዓለም እየተከተሉ ጭቆናን መታገል ዘበት ነው ሲል ሞግቷል።

አለመግባባቱ እዚህ ላይ አልቆመም። ሻዕቢያ በነገው የኤርትራ አገርነት ውስጥ ድንበራችን የት ድረስ ነው ብሎ ጥያቄ ያቀረበው ገና በረሃ እያሉ ነበር። እዚህም ላይ ከሕወሓት ያገኘው ምላሽ የሚጥም አልነበረም። ስለዚህም ሁለቱ አማጽያን ወዳጅነታቸው ተፈቶ ስትራቴጅካዊ ጥምረታቸው ወደ ታክቲካል ወዳጅነት በይፋ መውረዱን የተለያዩ ሰነዶች ያስረዳሉ። በ1977 ዓ.ም ሻዕቢያ ለትግራይ ተረጅዎች እርዳታ የሚታላለፍበትን ኮሪደር ዘግቶ አዕላፍትን በርሃብ እስከመቅጣት የደረሰውም በሕወሓት ጸረ ዴሞክራት ተብያለሁ ግልፍተኝነት ጭምር ነበር::

በእኔ አረዳድ ሁለቱ ድርጅቶች አገር ይዘው ወደ ውጊያ ሜዳ የወረዱት አንድም በሻዕቢያ ስግብግብነት አንድም በታሪካዊ ቁርሿቸው ምክንያት ነው። በረከት ግን በትንታቴው እነዛን የከረሙ ባላንጣዎች ጠላታችን ባሉት ደርግ ላይ ያሳዩትን የአውደ ውጊያ ትብብር ብቻ ተውሶ በአንድ ሳንባ እንደሚተነፍሱ አድርጎ አቅርቧቸዋል። ፈረንጆቹ ቁጥር አይዋሽም የሚል ብሒል ስላላቸው ታሪኩን በቁጥር እንየው።

ሕወሓት ዛሬ የ51 ዓመት አረጋዊ ሲሆን ከሻዕቢያ ጋር በሰላም ያሳለፈበት ጊዜ በድምሩ 20 ዓመት ብቻ ይገመታል። በተቃራኒው ሁለቱ ፓርቲዎች የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ ከነበረው የ20 ዓመታት ግጭት ባለፈ ወደ ስልጣን ሳይመጡና ከመጡ በኋላ በድምሩ ከ27 ዓመት በላይ በጥርጣሬና በደመኝነት ሲተያዩ ቆይተዋል::

የበረከት በላይነህ ፖለቲካ ኢትዮጵያን የአካባቢው ራሽያ አድርጎ አሰብን በጉልበት መውሰድ እንደሚቻል ቢገልጽም እመኑኝ ከማለት በቀር እዚህ ግባ የሚባል መከራከሪያ እንኳን ማቅረብ የተሳነው ነው። በመውጫዬ ከቃለ-መጠይቁ ጋር አያያዤ ሁለት ነገሮችን መጠቆም ሳይኖርበኝ አይቀረም። የኤርትራ ፖለቲካ በጅምሩ በሶሪያ ሕገ-መንግሥት የታወጀ፣ በኢራቁ ባሕስ ባርቲ ማኒፌስቶ ላይ የሰፈረ፤ በሱዳንና ሱማሊያ መንግሥት ድጋፍ ዳዴ ማለት የጀመረ መሆኑ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ከማድረግ የዘለለ አጅንዳ እንደሆነ ያረጋግጣል።

ሌላም ላክል፤ በረከት ሥነ-ጽሑፍን ትቶ ባለፈው 10 ዓመት በንባብ ወደ ፖለቲካ ራሱን እንዳሳደገ በገደምዳሜ ነግሮናል:: ይሁንና ከሥነ- ጽሑፍ የተለየ የፖለቲካ መንገድ መኖሩን ለማወቅ የግድ በረከትን መሆን ይጠይቃል:: እኔ ግን እላለሁ:: ከታጎር እስከ ሴንጎር ከሌኒን እስከ ሒተለር የአገራት ሚትና ነፍስ የተሰራው በሥነ-ጽሁፍ ነው::

Maereg Getachew

አዶናይን ከእስር ስለመፈታቱ!….ይህ ሻንቅላ ሰምቶ ይሁን እንዴ? Please ሼር አድርጉለት!
12/19/2025

አዶናይን ከእስር ስለመፈታቱ!….ይህ ሻንቅላ ሰምቶ ይሁን እንዴ? Please ሼር አድርጉለት!

ይሄም ደግሞ ነገ ይመጣና ጸልዩልይኝ አሞኛል ይላል!!😁😁
12/19/2025

ይሄም ደግሞ ነገ ይመጣና ጸልዩልይኝ አሞኛል ይላል!!😁😁

ሰበር ዜና‼️‼️‼️ጀነራል ታደሰ ወረደ አዲስአበባ ገቡ። ጀነራሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በ4ኪሎ ይወያያሉ። ጀነራሉ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ ፌዴራል ...
12/17/2025

ሰበር ዜና
‼️‼️‼️
ጀነራል ታደሰ ወረደ አዲስአበባ ገቡ። ጀነራሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በ4ኪሎ ይወያያሉ።

ጀነራሉ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ ፌዴራል መንግሥቱ በወልቃይት እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቁን አንዳፍታ ሚዲያ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ከወጣው መግለጫ ለመረዳት ችሏል።

የትግራይ ህዝብ እንደ ቢያፍራ መጥፋት ኣለበት።ትግራይ' ብሎ መጥራትንም በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆን ኣለበት።
12/14/2025

የትግራይ ህዝብ እንደ ቢያፍራ መጥፋት ኣለበት።
ትግራይ' ብሎ መጥራትንም በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆን ኣለበት።

12/13/2025

ድካማችሁ ፍሬ አፍርቷል!!'' ግላዊ ምስጋና ለባህልና ማንነት ታጋዮች🙏🙏🙏 ''ታዴ የማመይ ልጅ''

ከጆርዲ የተባለችው እስከ የቲክቶክ አዋርድ ከአስነዋሪ አለባበስ እስከ የብልግና ንግግር ትግላቸዉ መሰረት ያደረገ።

መልካምነት መገለጫው ብዙ ነዉ ።
የመልካም ተግባር እሳቤ በራስ ተነሳሽነት በምድር ላይ እያለ በሃሳብ በገንዝብ በባህል እና መሰል ጉዳዮች ሽልማትን ሳያስብ የሚከዉኗቸዉ መልካም ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በጎ ተግባራት ናቸዉ ብዬ አምናለሁ ፡፡

በዚህ ሂደት ላይ ብዙ ጊዜ በጎነትን መልካምነት ከገንዘብና ቁሳዊ ጉዳዮች ጋር አገናኝተን በዚህ ዙርያ ላይ የሚሳተፉትን እዉቅና ምስጋና የምንሰጠውን ያህል በአእምሮ ልማት በባህል ታሪክ ማንነት እሴት አኗኗርና ማህበረሰባዊ ኖርም በማስጠበቅ የሚሰሩትን መልካም ስራቸውን ዘንግተን ወይም ሳንረዳቸዉ መልካምነታቸውን ሳንገላልጥላቸው ማለፍ ተለምዷል ፡፡

ይህን ያልኩት በተለይም ብዙ ደጋፊዎች ያሏቸዉንና ከጊዜ ወደጊዜ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ የመጣዉን ሃላፊነት የጎደለዉ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እና የምናስተላልፈውን መልዕክቶች ከማንነት ያፈነገጡ ሃሳቦችን (በተለይም ቲክቶክ ላይ ) የሚያስተላልፉ አካላትን በመታገል ተጠያቂነት እንዳለም ያሳዩትን ትግሉን ከፊት ሁነዉ የመሩትን ለማመስገን ነዉ ።

በእኔ እይታ እነዚህ ግለሰቦች ሀገሪቱ የ 10 ሚሊዮን የማይበልጡት የቲክቶክ ተጠቂዎች ብቻ ሳትሆን የመቶ ምናምን በባህላዊ አኗኗር የሚኖር ህዝብ መኖርያ ናት በሚል ከሰሞኑ የታዩትን ከባህል ማፈንገጦች በሚያቀርቧቸው በሳል እይታዎች እንዲታረሙ በማድረግ ከመንገድ እንዳንወጣና ሌላውም ባለማወቅም ሆነ በድፍረት እንዲህ አይነት ሃሳብ እንዳያስተላልፍ ኢትዮጵያዊነት ባህል ማንነት ስነምግባር እሴቶችን እንዲጠበቁ ያልታዩ ማህበረሰባዊ ችግሮች ትኩረት እንዲሰጡ ሲታገሉ ተመልክቻለሁ ።

በስልጣኔ ሰበብ እየወረሱን ያሉ መጤ ባህሎች እንዳይንሰራፉ እንደ አንድ ሃላፊነት የሚሰማዉ ዜጋ ልክ እንደታላቅ ወንድምና እህት እየገሰፁም ይገኛል ።

በዚህች ስህተትን መነገር በማንወድበት ሃገር
ተተቸን የሚሉ ሰዉችም በጥላቻ እየታዩ በግለሰብ ደረጃ ይህን ያህል መታገልና እንዲጠየቁ ማድረግ ትልቅነት ነዉና ምስጋናዬን ለመግለፅ ወደድኩ ።

እናመሰግናለን

በመጨረሻም እኔ ያነሳሁት ሀሳብ በጥቅሉ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንጂ የአንድ ግለሰብ አይደለም ።

https://youtu.be/JC3K39Tddr8?si=H3UHFd08fHjT89Zd
12/12/2025

https://youtu.be/JC3K39Tddr8?si=H3UHFd08fHjT89Zd

ኦዶናይ ጉዳይ ሰመረ ባሪያው ንግግር 4 ስህተቶች | Semere Bariaw | ashruka channel | amleset muchie | ስግጥ ፍምስ | Ethiopian tiktokers | Adonay Ethiopian tiktok | Ethiopian news

1960s  ሰዎች ለምንድነዉ የ አሁኑ ትዉልድ የሚሰራዉ አንድም ነገር የማይጥማቸዉ?ለምንድ ነዉ  የአሁኑ ትዉልድ ከባህሉ ከቋንቋዉ እና ከ ሃይማኖቱ የራቀ   እንዲሁም በአስተሳሰብ የዘቀጠ ዉዳ...
12/12/2025

1960s ሰዎች
ለምንድነዉ የ አሁኑ ትዉልድ የሚሰራዉ አንድም ነገር የማይጥማቸዉ?

ለምንድ ነዉ የአሁኑ ትዉልድ ከባህሉ ከቋንቋዉ እና ከ ሃይማኖቱ የራቀ እንዲሁም በአስተሳሰብ የዘቀጠ ዉዳቂ አድርገዉ የምያስቡት?

ለምንድ ነዉ የ አሁኑ ትዉልድ ፍላጎት የ ህይወት መንገድ እና ዓለም ያለችበት ሁኔታ መረዳት የማይፈልጉት?

ለምንድነዉ ሁሌ የድሮ ነገር ብቻ ትክክል ነበር ፣የ አሁኑ ዘመን አመጣሽ የማይረባ ነዉ ብለው የምያስቡት?
እነዚህ ሰዎች ለአሁኑ ትዉልድ አሻራ የሚሆን ጠቃሚ ስራ ምን ሰሩ??

በ1960ዎቹ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ገፅታ ነበራት?

ኢትዮጵያ ድሀ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ ነበረች፤ ጦርነት የበዛባት ሀገር ነበረች፣የብሄር እኩልነት ያልሰፈነባት ሀገር ነበረች፤ ብዙ የፖለቲካ ጥያቄ የሚነሳባት ነበረች፤ ሰዎች በአደባባይ የሚሰቀሉባት ተማሪዎች የሚገደሉባት ሀገር ነበረች... እጅግ የተማሩ ኢትዮጵያን ሊቀይሩ የሚችሉ ሰዎች የተጨፈጨፉበት ዘመን ነበር። መንገድ መብራት ዉሃ ስልክ ያልነበረበት ገጠር እና ከተማ የሚኖር ህዝብ በባዶ እግሩ የሚሄድበት ዘመን ላይ ነበረች....

የ1960s ዘመናዊ ሰዎች ግዜያቹ በምን ወይ እንዴት ነበር የምያሳልፍት ...?

ሬድዮ አንድ ለ አስር በማዳመጥ: የነ ማራዶና ፔሌ ካስ በማየት፤ በነ ኤልቪስ ፕርስሊ ጃኒ ካሽ ሙዚቃ አረቄ ቤት እና ጠጅ ቤት ማሪንጌቻ በመጨፈር፤ ቬል ባጊ ሱሪ ለብሶ ፀጉሮን አፍሮ አበጥሮ የዘመኑ ጥቁር አፍሮ አሜሪካዊ በመምስል፣ የ ጃንትራ ቮልታ የፀጉር ኣሰራር በመከተል ማዘር ኢንድያን ፊልም እና የሸክስፒር ትያትር ሰኔማ ቤት ገብቶ በማየት፤ መሀሙድ አደባባይ ቆሞ ሴት በመጠበቅ ወዘተ ...ቲክታክ ብቻ ነበር የቀራቸዉ.... በቻሉት አቅም የዘመኑ ዘመናይ ለመምሰል ሞክራል.. የዘመኑ ወጣቶች ባህል አክባሪ አልነበሩም። የዉጭ መፅሓፍ የዉጭ ፖለቲካ የዉጭ ሙዚቃ ማዳመጥ ዘመናዊነት ነበር..እንደ አሉላ ኣባነጋ ሳይሆን እንደ ቼጉቬራ መሆንን ነበር የማፈልጉት።

አሁን ደሞ ዘመኑ ተቀይራል ሮናልዶን እንጂ ፔሌን የሚያዉቅ የለም፣ ጃኒን እንጂ ጃኒ ካሽን የሚያውቅ ትዉልድ የለም፤ራፕ ሂፕ ሃፕ ዳንስሀል ወዘተ እንጂ ማሪንጌቻ ለማዳመጥ ፍላጎት ያለው የለም... መሀሙድ አደባባይ ቆሞ ፍቅረኛ ለመጠበቅ ግዜ የለም።
ከ አንድ ፖለቲከኛ ይልቅ አንድ አነቃቂ ተሰሚነት የሚያገኝበት ዘመን፤ ከ አንድ ዶክተር ይልቅ አንድ ዩቱዩበር ብዙ ገንዘብ የሚሰራበት ዘመን ላይ ነን።
እናንተ ብዙ ለፍቲችሁ 20እና 30 ዓመት ትምህርትተምራችሁ ገንዘብ የምትሰሩበት የነበረዉ ዘመን ተቀይራል ፣የ አሁኑ ትዉልድ በቀላሉ ገንዘብ መስራት የሚችልበት ኣጋጣሚዎች አሉት ፤እናንተ በ ሃያ ዓመት ያላገኛችሁትን ሀብት በ ሁለት ዓመት መስራት የሚችልበት አጋጣሚዎች አሉት ። በናንተ ዘመን ሀብታም ለመሆን የግድ ዕድሜህ 60 እና 70 መሆን አለበት በዚህ ዘመን ገና በ20 እና 30 ዓመት ዕድሜያቸዉ ሀብታም ወጣቶች አሉ። ይህ ለምን ያናድዳችኅል? ዓለም ያለችበት ዘመን ይህ ነዉ የቴክኖሎጂ ዘመን ይባላል፤ እናንተ ከቴክኖሎጂ ዘመን አይደላችሁም የህዘመን የዚህ ትዉልድ ዘመን ነዉ እናንተ የራሳችሁን ህይወት ምንም ሳትሰሩበት አልፋል፤

ኢትዮጵያ በናንት ዘመን በድህነት በርሀብ እንጂ በታላቅነታ አትታወቅም ነበር። . የናንተን ሀጥያት እና በደል ተሸክሞ እንተን አክብሮ ቤት ኪራያችሁን እየከፈለ ይቺ ሀገር ወደ ተሻለ ከፍታ ለማሻገር እየጣረ ያለው ትዉልድ ይህ ትዉልድ ነዉ።

ሁሉም ነገር የድሮ እንዲመስል ለምን ትፈልጋላችሁ... የናንተ ትዝታ የዚህ ትዉልድ ትዝታ ሊሆን አይችልም..ይህ ትዉልድ በዚች ሀገር የራሱ አሻራ ጥሎ ከንንተ የወረስነዉ ዘረኝነት፣ምቀኝነት፣ እና ጦርነት ገድሎ ማለፍ ይፈልጋል...ለምን ወደናንተዉ የሞት የደም እና የመጠፋፋት ዘመን ወደሃላ እንዲመለስ ትፈልጋላችሁ? ሀገር የወጣቱ ትዉልድ ነች እናንተ የወጣትነት ዘመናችሁ አልፋል..፤ በናንተ ዓይን ሁሉም ነገር ሃጥያት እና ነዉር ነዉ። የሚሰራ ሰዉ ደግፎ መክሮ እና አስተካክሎ ሀገርን እና ትወልድን እንዲጠቅም ከማድርግ ይልቅ ጠልፋችሁ ለመጣል ለምን ትፈልጋላችሁ?

እናንተ በዘመናችሁ መስራት የነበረባችሁን ስራ በስርዓቱ ብትሰሩ ኑሮ የ አሁኑ ትዉልድ ከዘረኝነት የፀዳ እና የለማ ይሆን ነበር...

እናንተ ዘረኝነት፣ጦርነት ፣እና ድህነት እንጂ ልማት አላወረሳችሁንም ። ሰግጠንም ይሁን ፈምሰን ሀገር እናልማበት፣ ሰላም እንስበክበት፣ ፈታ ብለን እንኑርበት ተዉን።

ኢትዮጵያ በናንተ ዘመን ትልቅ አልነበረችም በዚች ሀገር ለትዉልድ የሚጠቅም ጥሩ መሰረት እንዳስቀመጣችሁ የአሁኑ ትዉልድ እያላችሁ አታሸማቅቁን። ድሮ ቀረ እያላችሁ አዲስ ነገር እንዳንፈጥር፣ እንዳንሰራ እንድንፈራ ከዓለም እኩል እንዳንሄድ ቴክኖሎጂን የሰይጣን እያልን እንድንሸሽ እያረጋችሁ ወደኅላ አትጎትቱን። ይህ ትዉልድ ባህሉን እና እምነቱን አክብሮ ወደፊት እንዲራመድ አስተሳሰቡ እንዲያሳድግ እናንተ የሰራችሁትን ስህተት እንዳይ ደግም ከስድብ እና ከ እርግማን ዉጭ የሰራችሁት ነገር ምን አለ? የናንተ ትዉልድ በምን ይታወቃል በልማት ወይስ በጦርነት? የ አሁኑ ትዉልድ ተመችቶት እንዲኖር መሰረት ጥለናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ይህ ትዉልድ ወሮበላ እና ድሩዬ ብቻ ነዉ ብላችሁ ማሰብን አቁሙ...

በ አሁኑ ትዉልድም ስንት የተማረ ፤ስንት ሀገሩን እና ህዝቡን የሚወድ ብዙ ሃይማኖቱ እና ባህሉ አክባሪ ስርዓት ያለው ሰዉ አለ። ግዜዉ የኛ ነዉ። Bedilu Wakjira Tewodros Teklearegay

"ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን" ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን ሲሉ የትግራዩ ጀነራል ተናገሩ። ለአመታት...
12/11/2025

"ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን" ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው

ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን ሲሉ የትግራዩ ጀነራል ተናገሩ። ለአመታት በአዲስአበባ ታስረው የነበሩት የቀድሞው የሜቴክ ሀላፊ ጀኔራል ክንፈ ዳኘው አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተው ተከስተዋል። “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ እንደ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጀነራል ክንፈ ዳኘው የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ይልቅ ከኤርትራ ነፃነት እንደሚያገኝ አዲስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡ ጀነራሉ ብራኸ ከተሰኘ የዩቱዩብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከእስር ከተፈቱ በኋላ አልፎ አልፎ አነጋገሪ ሀሳቦችን በመሰንዘር የሚታወቁት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ትግራይ ነፃ ሀገር መሆን አለባት የሚለውን አቋማቸውን ደግመውታል፡፡ እንደ ጀነራሉ እምነት ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና መቀጠል የሚበጃት ስላልፎነ፣ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ወደ ቅድመ ጦርነት ሁኔታ እየተመለሰች ያለችው ትግራይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ስር መግባት እንደሌለባትም ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ በትግራይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ብቸኛ የግንኙነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው ያሉት ሲሆን፣ ከዚያ ውጭ ምንም አይነት ማሰሪያ የለም ብለዋል፡፡

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ይልቅ፣ ከኤርትራ ጋር መወዳጀት እንደሚሻለቸውም ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራም ይሁን ከፋኖ ኃይሎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት፣ ስልታዊ ወይስ ቋሚ የሚለውን ጉዳይ በግልጽ መበየን እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡

ትግራይ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለው የሚያምኑት ጀነራሉ፣ የሚፈጸመውን በፖለቲካዊ ቁርጠንነትና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የትግራይን ሀገርነት ለማደናቀፍ የሚንቃቀስ አካል ካለ ለመመከት ወይም ለኃይል አማራጭ ለመጨረስ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡

ስለ አሁናዊ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይና ኤርትራ ውጥረት የተጠየቀት ጀነራሉ፣ ግጭት ከተቀሰቀሰ የውክልና ጦርነት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥት መካከል በባህር በር ጉዳይ ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ፣ ሌሎች ኃይሎችን በውክልና የሚያሳትፍ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጠናው የሚቀሰቀስ ጦርነት በባህሪው የውክልና ጦርነት ያሉት ጀነራሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያነሳው የቀይ ባህር ጥያቄ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፍላጎት ነው ሲሊም ያጣጥላሉ፡፡ ምንም እንኳን ጀነራሉ ጥያቄ የውክልና ጉዳይ ነው ቢሉም፣ ኢትዮጵያ መፍትሔ ያላገኘ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ እንደላት ይታወቃል፡፡
|
ጀነራሉ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊቀሰቀስ ይችላል ያሉት ጦርነት፣ ትግራይን የወጊያ ማዕከል ሊያደርግ እንደሚችለም ጠቁመዋል፡፡ ትግራይ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የውክልና ጦር ሜዳ እንዳትሆን ከወዲሁ ስልታዊ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጀነራሉ መክረዋል፡፡

ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች ትግራይን ወደ ሀገርነት ለማሸጋገር በጋራ መቆም እንዳለባቸው ጀነራሉ መክረዋል፡፡ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ያሉትን የመገንጠል አጀንዳ እንደሚያቀነቅኑ ይታወቃል፡፡

ድሃ ስትሆን ማንም ኣይወድህም! ስቶድቅ ረጋጩ ብዙ ነው! ያለህበተን የኑሮ ሁኔታ ኣንተ ነህ የምታውቀው! ሰወች መፍረድ እና ስም መለጠፍ ልማዳቸው ነው።      ከሌለህ የለህም! የቀረችወንም ...
12/10/2025

ድሃ ስትሆን ማንም ኣይወድህም! ስቶድቅ ረጋጩ ብዙ ነው! ያለህበተን የኑሮ ሁኔታ ኣንተ ነህ የምታውቀው! ሰወች መፍረድ እና ስም መለጠፍ ልማዳቸው ነው።

ከሌለህ የለህም! የቀረችወንም ለመንጠቅ የሚዳዱ ጥቂቶች ኣይደሉም! እንደ ጋዜጠኛ ከሰራሀወ ስራ የተፈፀመብህ ድብደባ ኣይገባህም ነበር! ያጠፉሀው ካለ በህግ ኣግባብ ብትጠየቅ መልካም ነበር! እኛ ማነን በሰው የምንፈርድ!

በየቤቱ ጉዱን ተሸክሞ ሌላኛውን ሀጥያተኛ ኣድርጎ እራስን እንደ ፃድቅ መቁጠር የዛ ሰዉ ሀጥያት ገዝፎ ያሳብቅበታል! ይሄን በማለቴ የሚቃዎሙኝ ሰወች እንደሚኖሩ ኣምናለሁ! እኔን ማንም ፍረደ ገምድል ጥራዝ ነጠቅ ጫፍ የዞ የሚያወራ በነፈሰበት የሚነፍስ ኣቋም የሌለው እኔን ኣይነዳኝም!

ይልቁኑ ወንድሜ ከገጠመህ የጤና እክል፣ የሂወት ትግል እግዚኣብሔር ይፈውስህ፣ ምሀረት ያውርድልህ ወደ ቀልብህ ይመልስልህ!
ፀልዩለተ!

Melat Melania

Address

Toronto, ON

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meb Free thinker posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Meb Free thinker:

Share