05/16/2026
በቆርቆሮ አጥር ስር ህይወቱ አለፈ‼
የዕለት ጉርሱን ለመፈለግ የወጣው የቀን ሰራተኛ ሁሴን ወዕሌቦ፣ የድካሙን ዋጋ ሳይቀበልና የቀረበለትን ምሳ ሳይቀምስ በቆርቆሮ አጥር እንደተደገፈ ህይወቱ ማለፉ ተሰማ።
ሟች አቶ ሁሴን በሃላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ጋለቶ ቀጠና ልዩ ቦታው ሜጦማ በሚባል ስፍራ፣ ግንቦት 06/2018 ዓ.ም ረፋድ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቆሎ ለመኮትኮት በ700 ብር ተቀጥሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ገደማ ቀጣሪዎቹ ምሳ ይዘውለት በሄዱበት ወቅት በተቀመጠበት ህይወቱ አልፎ አግኝተውታል።
ከፍተኛ ድካም፣ የደም ስኳር መጠን ማነስ ወይም የአካባቢው የሙቀት ሁኔታ ለድንገተኛ ህልፈቱ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።የቁሊቶ ከተማ ፖሊስ አስክሬኑን ለቤተሰብ አስረክቧል።ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።