Dominant News

Dominant News Dominant Records

Dominant News is a digital news channel delivering global headlines, war updates, politics, trending stories, and youth-focused reports — on YouTube, TikTok, and Facebook.

ባለፈው አንድ ዓመት "ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን ጨምሮ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፈዋል" የተባሉ 39 ሺህ ሰነድ አልባ የውጭ ዜጎች መያዛቸው ተገለፀባለፈው አንድ ዓመት 39 ሺህ የውጭ ዜጎች ...
03/10/2025

ባለፈው አንድ ዓመት "ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን ጨምሮ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፈዋል" የተባሉ 39 ሺህ ሰነድ አልባ የውጭ ዜጎች መያዛቸው ተገለፀ

ባለፈው አንድ ዓመት 39 ሺህ የውጭ ዜጎች በሕገ-ወጥ ሰነድ ሲገለገሉ መያዛቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ። እነዚህ ግለሰቦች "ኢኮኖሚያዊ አሻጥርን ጨምሮ በህገወጥ ክንውኖች ውስጥ ሲሳተፉ የተገኙ ናቸው" ብሏል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጎሳ ደምሴ ማንኛውም ዜጋ ሕጋዊ ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲኖረው ይገደዳል ሲሉ ገልፀዋል።

ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው የሚንቀሳቀሱ የውጭ ዜጎች በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ፣ ጸጥታ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ የገለፁት አቶ ጎሳ ይህንን ለመከላከልም ባለፈው 2017 በጀት ዓመት ብቻ 39 ሺህ ሰነድ አልባ የውጭ ዜጎችን መያዝ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የተያዙት ሰነድ አልባ ሰዎችም "በኢኮኖሚ ላይ አሻጥርን የሚያከናውኑ፣ ሕገ ወጥ ማኅበራዊ ክንውን ላይ የተሰማሩ እና የኢትዮጵያን ደኅንነት በሚጎዱ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ናቸው" ብለዋል።

አግባብነት የሌላቸው ሰነዶችን የሚጠቀሙበት ምክንያትም "ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን ለማሳካት፣ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ከግብ ለማድረስ፣ የሚሠሩት ሥራ እና እንቅስቃሴያቸው እንዳይታወቅ ከመፈለግ የመጣ እንደኾነም" ጠቁመዋል።

አያይዘውም እነዚህ ጉዳቶች ያለሰነድ እና ፍቃድ ሲከናወኑ ደግሞ በሀገሪቱ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ በመኾኑ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን መናገራቸውን የዘገበው አሚኮ ነው።

03/10/2025

Baga Ayyaana Irreechaa Nagaan Geessan!
Ayyaana Gaarii!
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!

03/10/2025

እስኪ ኣንዳንዴም ኣብረን እንሳቅ!
"እየሱስ ክርስቶስ ዘግይተሃል ምጣ"

03/10/2025
03/10/2025

ነገረ ሞጣ!

" #ስለአህያ ስጋ ምን ያክል ታቃላችሁ??? #የአህያ ሥጋን ከበሬ ሥጋ እንዴት መለየት እንደሚቻል አንድ ወዳጄን ጠይቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቶኛል፡፡  “የአህያ ሥጋ ከበሬ ሥጋ ምንም ልዩነት...
03/10/2025

" #ስለአህያ ስጋ ምን ያክል ታቃላችሁ???

#የአህያ ሥጋን ከበሬ ሥጋ እንዴት መለየት እንደሚቻል አንድ ወዳጄን ጠይቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቶኛል፡፡ “የአህያ ሥጋ ከበሬ ሥጋ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ እንዲያውም እንደ በሬ ሥጋ ጮማ
ስለማይበዛውና ቀይ ስለሆነ ለክትፎ ተመራጭ ነው፡፡ ሉካንዳ ቤት ተቀላቅሎ ተሰቅሎ ብታየው እንኳን ከሱ ጋር አድርግልኝ እያልክ በምርጫ ተሻምተህ የምትገዛው ነው፡፡ ……… ችግሩ ከበላህና ከጠገብክ በኋላ እንደ አህያ አናፋ ፣ አናፋ ይልሃል ብሎኛል፡፡” 🤣😆😂😃😅😁
ያለ ሀኪም ምርመራ በየቦታው ታርደዉ በፌስታል የሚከፋፍሉና የሚጓጓዙ ስጋዎችን በየመኪናዎችና ሞተሮች ለየስጋ ቤቱ ይከፋፈላል ስለዝህ ምን ይላሉ????"

"ለኩላሊት ህመም አጋላጭ ከሆኑ ሁኔታዎች መራቅ ይገባል - የሕክምና ባለሙያ ለኩላሊት ህመም አጋላጭ መንስዔዎችን ዐውቆ በጥንቃቄ መኖር ለጤናማ ሕይወት ወሳኝ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች በአጽ...
03/10/2025

"ለኩላሊት ህመም አጋላጭ ከሆኑ ሁኔታዎች መራቅ ይገባል - የሕክምና ባለሙያ

ለኩላሊት ህመም አጋላጭ መንስዔዎችን ዐውቆ በጥንቃቄ መኖር ለጤናማ ሕይወት ወሳኝ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች በአጽንኦት ይገልጻሉ።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ሕክምና ትምህርት ከፍል ተባባሪ ፕሮፌሰርና የኩላሊት ስፔሻሊስት ሐኪም ዶክተር ለጃ ሐምዛ ከኩላሊት ጤና ጋር በተያያዘ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም፤ ስለ ኩላሊት ተግባራት፣ የኩላሊት መድከምና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ሙያዊ ገለጻ ሰጥተዋል።

👉 የኩላሊት ዋና ዋና ተግባራት

በርካቶች በተፈጥሮ ሁለት ኩላሊቶች ይዘው እንደሚወለዱና አልፎ አልፎ አንድ ኩላሊት ኖሯቸው የሚወለዱ እንዳሉ ዶክተር ለጃ ይገልጻሉ። በአጠቃላይ ጤናማ ሕይወት ለመኖር ኩላሊቶች አስደናቂ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ ያስረዳሉ። ከእነዚህ ተግባራት መካከልም ዋና ዋናዎቹ፡-

1ኛ. የደም ግፊት የተስተካከለ እንዲሆንና በሰውነት ውስጥ ያለው የፈሳሽ መጠን ሚዛኑን እንዲጠብቅ ማድረግ፤

2ኛ. ለሠርካዊ የኅዋሶች ጤናማ ተግባራት ወሳኝ ንጥረ ነገሮች እንዳይዛቡ ሚዛን መጠበቅ፤

3ኛ. ለደም ኅዋሶች መመረት የሚያስፈልጉ ብሎም ለዘወትራዊ የኅዋሶች ጤናማ ተግባራት አስፈላጊ ሆርሞኖችን ማምረት፤

4ኛ. ለአጥንት ጥንካሬና ለጥርስ ጤና አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን(ቫይታሚን ዲ፣ ካልሺየም እና ፎስፈረስ) ማምረትና ሚዛናቸውን መጠበቅ፤

5ኛ. በሰውነት ውስጥ የሚመረቱም ሆኑ ከምግብ፣ ከመጠጥ እና ከመድኃኒት ጋር ወደ ሰውነት የገቡ ለጤና ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ከሽንት ጋር ማስወገድ፤......"

03/10/2025

ምን ኣጣላቸው!?

03/10/2025

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 2ሺህ የሚጠጉ አውቶብሶች አሁን የሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ ይቀየራል ።
ጠ/ ር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

03/10/2025

👉 In America 🇺🇸, widespread access to lethal fi****ms has resulted in senseless killings.

Address

Peter Street
Addis Ababa
M5V2H1

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dominant News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dominant News:

Share