Koore Woga Tourism

  • Home
  • Koore Woga Tourism

Koore Woga Tourism Amaro kelle

05/08/2025
05/08/2025

"ዓባይ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲተባበር ተዓምር መሥራት እንደሚችል አሳይቷል"

- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
++++++++++++++++

l ዓባይ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲተባበር ተዓምር መሥራት እንደሚችል አሳይቷል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ዓባይ ግድብ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ፕሮጀክት እና ኩራት ነው።

ዓባይ ግድብን እያንዳንዱ ኢትዮጵያውያን በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው፣ በላባቸውና በጸሎታቸው ደግፈው አሁን ያለበት ደረጃ እንዳደረሱት ገልጸው፤ ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተባበረ ተዓምር መስራት እንደሚችል አሳይቷል ብለዋል።

በዓባይ ግድብ ዙሪያ እውነታን ያላገናዘቡ አስታያቶች እንደሚሰጡ ገልጸው፤ ለዓለም ህዝብ ደጋግመን የምንነግረው ዓባይ በኢትዮጵያ ጥረት የተሰራ መሆኑን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ ግድቡ ህልውናውን አግኝቶ ወደ ፍጻሜ እየደረሰ ሲሆን፤ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአሁኑ ስዓት መዘጋጀት ያለብን ግድቡን በማስመረቅ ለውጤት ማብቃት እና ሌላ የበለጠ ፕሮጀክት ለመስራት ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ዓባይ ግድብ ለኢትዮጵያ እና ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

ዓባይ ግድብ የግጭት ምንጭ ሳይሆን የትብብር መነሻ እንዲሆን የማድረጉ ነገር በኢትዮጵያ በኩል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሄለን ወንድምነው
++++++++++++++++++++++


#ኢትዮጵያ
#ዓባይ #ኤሌክትሪክ

የጋራ ታሪክ፣ የጋራ እሴት እና የጋራ ሕልም የሚቀዱበት ምንጩ የወል ትርክት ነው፡- ዳያሞ ዳሌ****************ነጠላ ትርክት ተንሰራፍቶ የቆየው የጋራ ማንነታችን የሆነውን የወል ትርክ...
04/08/2025

የጋራ ታሪክ፣ የጋራ እሴት እና የጋራ ሕልም የሚቀዱበት ምንጩ የወል ትርክት ነው፡- ዳያሞ ዳሌ
****************

ነጠላ ትርክት ተንሰራፍቶ የቆየው የጋራ ማንነታችን የሆነውን የወል ትርክት በመዘንጋታችን ነው ሲሉ የፖለቲካ ምሁርና ተንታኙ አቶ ዳያሞ ዳሌ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ከጋራና ከወል ትርክት ይልቅ በነጠላ ትርክት ላይ ለዘመናት ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ መቆየቱን የሚናገሩት የፖለቲካ ምሁሩ፤ በዚህ ሂደት የጋራ ማንነትን የመዘንጋት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

ትናንትን ከዛሬ ያስታረቀ፣ ነገን የተለመ የጋራ ፖለቲካዊ ስትራቴጂ፣ ካስማና ማገር የሆነው ኢትዮጵያዊ የወል ትርክት መዘንጋቱን ይገልጻሉ።

የወል ትርክት ተዋንያኑ ብዙ ናቸው፤ የጋራ ታሪክ፣ የጋራ እሴት እና የጋራ ሕልም የሚቀዱበት ምንጩ የወል ትርክት መሆኑንም ይናገራሉ ከኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 አቢይ ጉዳይ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ዳያሞ ዳሌ።

የፓለቲካ ምሁሩ አቶ አበራ ኢብሳ በበኩላቸው፥ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ኅብረ-ብሔራዊ ሀገር፣ ኅብረ-ብሔራዊ አነድነትን በማንበር ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የወል ትርክት በእጅጉ ያሻል ይላሉ።

የሀገረ መንግሥት ግንባታን ያሳኩ ሀገራት ይህን ማድረግ የቻሉት አዎንታዊ ትርክት ላይ በመሥራታቸው ነው የሚሉት አቶ አበራ፤ የወል ትርክታችን የጋራ እሴቶችን ከፍ የሚያደርጉ ትላልቅ ጉዳዮች ላይ መመስረት እንዳለበት ይመክራሉ።

ለዚህ የሚያስፈልገን ልዩነትን አለማስተናገድ ሳይሆን አለማጋነን ነው የሚሉት የፓለቲካ ምሁሩ፤ ትርክታችን የወል ማንነትን በመደፍጠጥ ነጠላ ማንነትን የሚያጎላ መሆን እንደሌለበት አክለዋል።

አንድ ገዢ ትርክት ህዝባዊ ህዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖረው ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ሚዲያዎች እና ሲቪክ ማህበራት የወል አጀንዳ በማድረግ በተከታታይነት ሊሠሩበት እንደሚገባም ነው ምሁራኑ ያመላከቱት።

ገዢ ትርክት ላይ ነጣይነት የሌለው አካታችነት መኖር አለበት የሚሉት ምሁራኑ፤ ይህም ሰፊ ማህበራዊ መሰረት ይኖረው ዘንድ ተቋማዊ አሠራር ተበጅቶለት በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኩል እየተከናወነ ያለበትን አግባብ በአብነት ጠቅሰዋል።

በመሀመድ ፊጣሞ

#ሀገረመንግሥት #የወልትርክት

ስለ   አስፈላጊነት የምናወራው ሉዓላዊነቱ ባልተከፋፈለ   (A State with undivided territorial sovereignty ) ሥር የብዝሃነት መብታችንን አስተናግደን በሰላም ለመኖ...
04/08/2025

ስለ አስፈላጊነት
የምናወራው ሉዓላዊነቱ ባልተከፋፈለ (A State with undivided territorial sovereignty ) ሥር የብዝሃነት መብታችንን አስተናግደን በሰላም ለመኖር ነው።

የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ ከተባሉ ሰላም ሊኖረን ይችላል ?

በክልል፣ በዞን፣ በልዩ ወረዳ ምክንያት ውስጣዊ ጦርነት የሚካሄድበት
አገረ መንግሥት የምር አገረ መንግሥት ሊሆን ይችላል?

---_እንወያይበት!
(ስድብ፣ ዛቻ፣ ፍረጃ እና ማንጓጠጥ አናስተናግድም!)

---ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም (KWT Political Conversation)

04/08/2025

የፕሬስ መግለጫ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል። መንግሥት ዜጎች በተለያዩ አገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ አጋጣሚ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ አገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማሳሰብ ይወዳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

04/08/2025

ከፍተኛ የግብር ጫና ዜጎችን ከመደበኛ ሥራ እያራቃቸው ነው ሲል አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ

በኢትዮጵያ ያለው የግብር ስርዓት፣ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ ላይ ባሉ ግብር ከፋዮች ላይ የሚጣለው ከፍተኛ የግብር ተመን፣ ዜጎች ወደ መደበኛ የስራ ዘርፍ እንዳይገቡ ተስፋ እያስቆረጣቸው መሆኑን የአይኤምኤፍ ሪፖርት አመለከተ።

የአለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ ) ባወጣው የቅርብ ጊዜ የግብር ግምገማ ላይ እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ የግብር ስርዓት አወቃቀር በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ባሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የግብር ተመን የሚጥል ሲሆን፣ ይህም ድርጅቶችና ሰራተኞች መደበኛ ባልሆነው የንግድ መስክ ውስጥ እንዲቆዩ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ደግሞ ለልማት የሚውለውን የግብር ገቢ እንዲቀንስ ያደርጋል።

ሪፖርቱ አክሎም፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያሳየች ብትሆንም፣ የግብር አሰባሰቧ ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ጠቅሷል። ከገቢና ትርፍ የሚገኘው የግብር ገቢም ቢሆን ደካማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ካፒታል የተመለከተዉ የአይኤምኤፍ ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ በብቃት የግብር ስርዓቷን ብታስተካክል ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርቷ (GDP) እስከ 17% የሚደርስ ገቢ ማግኘት ትችል ነበር፤ አሁን የምታገኘው ግን 8% ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በገንዘብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን ያሳያል።

ሪፖርቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የግብር አሰባሰብ መሰረትን በማስፋፋት፣ ከአላስፈላጊ የግብር ነጻነቶች በመውጣትና የግብር አክባሪነትን በማሻሻል ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ማስቀጠል እንደሚቻል አሳስቧል።

"በዚህ የሪፖርት ዘመን በአጠቃላይ በሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የቀጠለው የትጥቅ ግጭቶች እንዲሁም የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ...
04/08/2025

"በዚህ የሪፖርት ዘመን በአጠቃላይ በሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የቀጠለው የትጥቅ ግጭቶች እንዲሁም የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ ነው። በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የትጥቅ ግጭት በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ የነጻነት እና ሌሎች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ጥሰቶች ማስከተሉን ሪፖርቱ አመላክቷል። በተራዘመ የግጭት ዐውድ ውስጥ በተፋላሚ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ በሰዎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፤ የእገታ ተግባራት ተስፋፍተው መቀጠላቸውን፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍም ጥሰቶች መመዝገባቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ገልጿል። እንዲሁም አልፎ አልፎ በሚያገረሹ ግጭቶችና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በሰዎች ላይ የሞት፣ አካል ጉዳት እና እገታ መድረሱን፤ በተወሰኑ አካባቢዎችም የእንቅስቃሴ ገደቦች መደረጋቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። "

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ ተጠያቂነትን ማስፈን እና ተጎጂዎችን መካስ ያስፈልጋል..

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ባለ 152 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት በሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። ለ4ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ሪፖርት በበጀት ዓመቱ በየዘርፉ ባሉ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የተስተዋሉ ቁልፍ እመርታዎችን፣ አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ምክረ ሐሳቦችን እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያካተተ ነው።

ይህ ዓመታዊ ሪፖርት ኢሰመኮ በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች በተቋቋሙ የሥራ ክፍሎቹ በሰበሰባቸው ማስረጃዎች፣ ባከናወናቸው የክትትል እና ምርመራ ላይ መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው። በዚህም መሠረት ሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕን ጨምሮ የሲቪል እና የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ፣ የሴቶች እና የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች መብቶች፣ በኢሰመኮ የተስተናገዱ በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎችን ከመወጣት አኳያ ያለችበት ሁኔታን የሚያሳዩ ጉዳዮች በዝርዝር ተካተዋል።

በዚህ ሪፖርት ዘመን በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ አዎንታዊ አንድምታ ያላቸው ቁልፍ እርምጃዎች የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የተመላከቱትን ዋና ዋና ተቋማት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆች መቅረጽ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም ተጎጂዎችንና ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ረቂቅ ስትራቴጂ ማዘጋጀት፤ የሀገራዊ ምክክር ሂደት እና አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይገኙበታል።

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ለኢሰመኮ የውትወታ ሥራዎች አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ እርምጃዎች የተከናወኑ ሲሆን ለአብነት በአማራ ክልል ለዳኞች ያለመከሰስ መብት የሕግ ከለላ የሚሰጥ የአማራ ብሔራዊ ክልል ፍርድ ቤቶች የማጠናከሪያ አዋጅ መጽደቁ፤ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በ4 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ኢሰመኮ ከባለሥልጣኑ እንዲሁም እገዳ ከተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱ፤ በኦሮሚያ ክልል መንግሥትና “ጃል ሰኚ ነጋሳ” በተባለ ግለሰብ በሚመሩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ”) አባላት መካከል ስምምነት መደረጉ እና ይህንን ተከትሎ በክልሉ የተወሰኑ ዞኖች ያለው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ፤ “ወቅታዊ ጉዳይ” በሚል በተራዘመ እስር ላይ የነበሩ ሰዎች ከእስር መለቀቅ መጀመራቸው እና አዳዲስ ሕገ ወጥ እስራቶችም መቀነሳቸው መልካም እምርታ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክተዋል።

ሪፖርቱ በ2017 በጀት ዓመት የተስተዋሉ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችንም በዝርዝር አካቷል። በዚህ የሪፖርት ዘመን በአጠቃላይ በሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ የቀጠለው የትጥቅ ግጭቶች እንዲሁም የጸጥታ ችግሮች ጉዳይ ነው። በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የትጥቅ ግጭት በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ የነጻነት እና ሌሎች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ጥሰቶች ማስከተሉን ሪፖርቱ አመላክቷል። በተራዘመ የግጭት ዐውድ ውስጥ በተፋላሚ ቡድኖች በተፈጸሙ ጥቃቶች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ በሰዎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፤ የእገታ ተግባራት ተስፋፍተው መቀጠላቸውን፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍም ጥሰቶች መመዝገባቸውን ኢሰመኮ በሪፖርቱ ገልጿል። እንዲሁም አልፎ አልፎ በሚያገረሹ ግጭቶችና የጸጥታ መደፍረስ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በሰዎች ላይ የሞት፣ አካል ጉዳት እና እገታ መድረሱን፤ በተወሰኑ አካባቢዎችም የእንቅስቃሴ ገደቦች መደረጋቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ከጸጥታ ችግሮች በተጨማሪ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ለሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል፣ የንብረት ውድመት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት መሆናቸው፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው እና በርካታ ትምህርት ቤቶችም አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው በሪፖርቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ሆነው ተካተዋል። በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በስፋት የተከሰቱ የወባ፣ ኮሌራ እና ኩፍኝ በሽታዎች በጤና መብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው፣ ከጤና ባለሙያዎች የደመወዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ የሙያ ዕድገት ዕድሎች እንዲሁም ምቹ የሥራ ቦታ እና ነጻነት ጥያቄዎች በወቅቱ አለመመለስ ጋር ተያይዞ በበጀት ዓመቱ የተከሰተው የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ በጤና መብት ዘርፍ ላይ ጉዳት ማስከተሉ በሪፖርቱ ተገልጿል።

ሪፖርቱ የነጻነት መብትን በተመለከተ ካካተታቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል በግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች በ“ኮማንድ ፖስት” እና በ“ወቅታዊ ጉዳዮች” በሚል የሚፈጸሙ እስሮች እና ተያያዥ የነጻነት መብት ጥሰቶች መቀጠላቸው፣ የአስገድዶ መሰወር ድርጊትን ወይም ያሉበት ሳይታወቅ ሰዎችን አስሮ የማቆየት ጥሰቶችን ሊያቋቁሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጨምሮ የሕገ-ወጥ እስር ተግባራት አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎችም መፈጸማቸው ይገኙበታል። እንዲሁም በአብዛኛው የግጭት ዐውድ ውስጥ በሚገኙ/በቆዩ አካባቢዎች በታጣቂ ቡድኖች ወይም ሰዎች የሚፈጸሙ እገታዎች መከሰታቸውንና ይህም በነጻነት፣ የአካል ደኅንነት እና ሌሎች መሠረታዊ መብቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ሪፖርቱ አካቷል።

ኢሰመኮ በጥበቃ ሥር ያሉ(የታሰሩ) ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ በ66 ማረሚያ ቤቶች እና 473 ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም 9 መደበኛ ያልሆኑ ማቆያ ስፍራዎች ክትትል ያከናወነ ሲሆን በክትትሉ የለያቸው መልካም እመርታዎች እና አሳሳቢ ጉዳዮች በሪፖርቱ በዝርዝር ተመላክቷል። ሪፖርቱ ለኢሰመኮ የቀረቡ አቤቱታዎችን በተመለከተ በዝርዝር ያካተተ ሲሆን ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1524 ሰዎች በቡድንና በተናጠል ያቀረቧቸውን 1258 አቤቱታዎች ተቀብሎ ያስተናገደ መሆኑ ተገልጿል።

በ2017 በጀት ዓመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የጸደቀው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ማሻሻያ አዋጅ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ በሚዲያና የሲቪክ ምኅዳር ላይ እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትና የመደራጀት መብት ላይ ያላቸውን አንድምታ በዝርዝር ተመላክቷል።

ሪፖርቱ የሴቶችና ሕፃናት መብቶችን በተመለከተ ካካተታቸው አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል በአፋር እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚፈጸመው የሴት ልጅ ግርዛት ምክንያት የሴቶችና የሴት ሕፃናት በሕይወት የመኖር፣ የጤና፣ የአካል እና የአእምሮ ደኅንነት መብት እንዲሁም ከማንኛውም ኢሰብአዊ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ እና የሥቃይ እና የጭካኔ ተግባር የመጠበቅ መብቶቻቸውን ጨምሮ በርካታ መብቶቻቸው መጣሳቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ፋብሪካዎች የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዝርዝር የያዘ ነው።

በአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ዘርፍ በሪፖርቱ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል በልዩ አዳሪ እና አካቶ ቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአካል ጉዳተኞች የከባቢያዊ፣ ተቋማዊና የመረጃ ተደራሽነት ችግር መኖር፤ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መቀጠላቸው እና ይህንኑ ለማስቆምም የሚደረጉ ጥረቶች አነስተኛ መሆናቸው ተጠቃሽ ሲሆኑ በበጀት ዓመቱ የተስተዋሉ አበረታች እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው።

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰተኞች መብቶችን በተመለከተ ሪፖርቱ ዝርዝር ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች በመጠለያ ጣቢያዎችና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው የሚገኙ ተፈናቃዮች እንዲሁም ተመላሾች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ፣ ተደራሽ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተፈናቃዮች ያማከለ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲሁም ትምህርትና ጤናን ጨምሮ የተሟላ ማኅበራዊ አገልግሎት የማይቀርብላቸው መሆኑ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ለዳግም መፈናቀል የተዳረጉ ሰዎች መኖራቸው በበጀት ዓመቱ አሳሳቢ ሆነው ከቀጠሉ ጉዳዮች መካከል ናቸው።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ መሻሻሎች የተመዘገቡባቸውን ዘርፎች በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ በሪፖርቱ በተሸፈነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ በርካታ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ለመከሰታቸው እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋና ምክንያት የሆነውን በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የትጥቅ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረሶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ብቸኛው አማራጭ በመሆኑ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም በመጪው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚኖረውን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ መከበር እና መስፋፋት የተሻለ ለማድረግ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገና ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ትግበራን እና ሀገራዊ ምክክርን ማጠናከር፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በፈጸሙ አካላት ላይ ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ተጎጂዎች የሚካሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሙሉ ሪፖርት: https://ehrc.org/download/?p=34091

ጋዜጣዊ መግለጫ: https://ehrc.org/?p=34088

🇪🇹

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

03/08/2025
" አርባምንጭ ከተማ በአማሮ [የዛሬው ኮሬ ዞን ስም "አማሮ ወረዳ" ተብሎ በሚጠራበት ወቅት የተጻፈ መጽሐፍ ነው] ደጋማው ክፍል በሩቁ ትታያለች። ምን አለ መንገድ ኖሮ ደርሼ በተመለስኩ ያሰኛ...
02/08/2025

" አርባምንጭ ከተማ በአማሮ [የዛሬው ኮሬ ዞን ስም "አማሮ ወረዳ" ተብሎ በሚጠራበት ወቅት የተጻፈ መጽሐፍ ነው] ደጋማው ክፍል በሩቁ ትታያለች። ምን አለ መንገድ ኖሮ ደርሼ በተመለስኩ ያሰኛል። የዳርባ ማናና የዬሮ አካባቢ ኮሬዎች በእግር አርባምንጭ ደርሰው እንደሚመለሱ ያወሳሉ። ነገር ግን አድካሚና ፈታኝ እንደሆነም ይገልፃሉ። ከአርባምንጭ ደርባ ማናና፣ በዛም አማሮ ኬሌ የመኪና መንገድ ቢሰራ ጥቅሙ ምን ያህል ሰፊና ግዙፍ እንደሆነ ማወቅ የሚችለው ቦታውን የተመለከተ ሰው ብቻ ነው። ይህ መንገድ ቢከፈት ከአርባምንጭና ከሁለቱ ሐይቆች በስተምዕራብ ያለውን ክፍል በሙሉ በቀጥታ ከዲላና ከሀዋሳ፣ ሀገረማሪያምና ሞያሌ ---የሚያገናኝ ቁልፍ መስመር እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ሲያዩት ነው። በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የመንገድ ሥራ ልማት ይህንን ቁልፍ መስመር እስካሁን መክፈት አለመቻሉ ለምን ይሆን? ማሰኘቱም የሚቀር አይደለም።"

- የኦሔ ሥርዓት
የኮሬ ብሔረሰብ የባህል ሕግ ሥርዓት ፤ ገጽ 32-33 ፤2006 ዓ.ም የታተመ

(አዘጋጅ -አብዱልፈታህ አብደላ (ዶ/ር)

"በመግለጫው በሥም የተጠቀሱት አራት ድርጅቶች ሸጊ፣ አዱሊስ፣ ራማዳ ፔይ (ካህ) እና ታጅ የተባሉ የሐዋላ አስተላላፊዎች ናቸው። የሐዋላ አስተላላፊዎቹ በሜሪላንድ፣ ቨርጂኒያና ሚኒሶታ በሚገኙ ...
02/08/2025

"በመግለጫው በሥም የተጠቀሱት አራት ድርጅቶች ሸጊ፣ አዱሊስ፣ ራማዳ ፔይ (ካህ) እና ታጅ የተባሉ የሐዋላ አስተላላፊዎች ናቸው። የሐዋላ አስተላላፊዎቹ በሜሪላንድ፣ ቨርጂኒያና ሚኒሶታ በሚገኙ አካባቢዎች እንደሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። "

Address

MB

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Koore Woga Tourism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Koore Woga Tourism:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share