የሀበሻ ጥበብ ሥራና በልትና ደቡብ አፍሪካ ጆርጅ

የሀበሻ ጥበብ ሥራና በልትና ደቡብ አፍሪካ ጆርጅ one kembata

አስደሳች ዜና ለዳምቦያና አከባቢው ማ/ሰብ በሙሉእንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዳምቦያ ከተማ አዲስ ማሜ መድኃኒት መደብር ስራ መጀመሩን ያበስራል።ምናልባትም የ...
17/09/2025

አስደሳች ዜና ለዳምቦያና አከባቢው ማ/ሰብ በሙሉ

እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዳምቦያ ከተማ አዲስ ማሜ መድኃኒት መደብር ስራ መጀመሩን ያበስራል።

ምናልባትም የጤና እክል ብያጋጥምዎ በሃኪሚዎ ትዕዛዝ ወደ ማሜ መድኃኒት መደብር ከመጡ በተመጣኝ ዋጋ የሚፈልጉትን ያገኛሉ።

በተጨማሪም ኮስሞቲክስ እና ሌሎችም የአዋቂና የህፃናት ንህፅና መጠበቂያዎች ይገኛሉ።

አድራሻ፡- ዳሽን ባንክ ዳምቦያ ቅርንጫፍ ትንሽ አለፍ ብለው ወደ ታሪካዊቷ ሰጦ ገበያ መሄጃ መንገድ ላይ ባስተቀኝ እንገኛለን።

ትክክለኛና በሃኪምዎ የታዘዘልዎትን መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ከፈለጉ ወደ ማሜ መድኃኒት መደብር ጎራ ይበሉ።

መልካም አዲስ ዓመት!!

thank you ምርጫቹ እኛ ስለሆንን  አዳዲስ የሀገር ባህል ልብስ እና ሽፎን ይፈልጋሉ ፣ለሠርግ ለመልስለልደት ለበዓል እና ለተለያዩ ዝግጅቶች ! በደቡብ አፊሪካ ባሉበት ቦታ ሆነው ይዘዙን ...
11/09/2025

thank you ምርጫቹ እኛ ስለሆንን
አዳዲስ የሀገር ባህል ልብስ እና ሽፎን ይፈልጋሉ ፣
ለሠርግ
ለመልስ
ለልደት
ለበዓል እና ለተለያዩ ዝግጅቶች !
በደቡብ አፊሪካ ባሉበት ቦታ ሆነው ይዘዙን በጥራት አዘጋጅተን እንልካለን
ለበለጠ መረጃ 👇👇
0626841742
የሀበሻ ጥበብ ሥራና በልትና George ደቡብ አፍሪካ

08/09/2025
Thank you ምርጫችሁ ስለደረጋችሁን
08/09/2025

Thank you ምርጫችሁ ስለደረጋችሁን

07/09/2025
03/08/2025
ጥቂት ስለ ወላጆቼ፦   በከምባታ ዞን ሚሽግዳ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የቤናራ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከሕፃንነቴ ጀምሮ ያደኩባት ቤተክርስቲያን ነች። ቤተክርስቲያኒቱ  ከ70 ...
02/08/2025

ጥቂት ስለ ወላጆቼ፦

በከምባታ ዞን ሚሽግዳ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የቤናራ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከሕፃንነቴ ጀምሮ ያደኩባት ቤተክርስቲያን ነች። ቤተክርስቲያኒቱ ከ70 ዓመታት በላይ የዘለለ የምሥረታ ታሪክ አላት። ወላጆቼም የዚህቹ ቤተክርስቲያን መስራች መሪዎች ነበሩ።

ታዲያ ቤተክርስቲያኒቱ ከ1930ዎቹ መገባደጃ እስከ 1970ዎቹ መግቢያ ድረስ ለአምልኮ አገልግሎት የምትጠቀምበትን ቦታ ከመሬታቸው በነፃ ቆርሰው የሰጡት ወላጆቼ ነበሩ። ከመረጠው የወንጌል እውነት የተነሳ፣ ቤተክርስቲያኒቱ የምትገነባበትን ቦታ በነፃ በመስጠቱና ሚሽነሪዎች ሲመጡ በእንግድነት በመቀበሉ አባቴ እስከ ደርግ ዋዜማ ድረስ አብዛኛውን ዕድሜውን የጨረሰው ከዱራሜ፣ ሆሳዕና እስከ አሰላ ድረስ በነበሩ ወህኒ ቤቶች ነበር፤ እስቲ በአንድ ወቅት አባቴ ስለእስር ቤት ውሎው ለእኛ ለልጆቹ ከነገረን ውስጥ ለዛሬው አንዱን ብቻ ላካፍላችሁ፦

ከላይ ጠቀስ እንዳደረኩት የመካነ ኢየሱስ ሚሽነሪዎች(ፈረንጆች) ለወንጌል አገልግሎት በመጡ ቁጥር የሚያርፉትና የሚስተናገዱት እኛ ቤት ነበር፤ በዘመኑ ቋንቋ ቤታችን በነፃ የገስት ሀውስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር፤ ታዲያ በአንድ ወቅት "እነዚህን አዲስ ትምህርት የሚያስተምሩ ፈረንጆችን በቤቱ እየተቀበለ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረላቸው ያለው ሄራሞ አናሞ ስለሆነ ወህኒ ቤት ቀርቦ ይጠየቅ" የሚል ክስ በአካባቢው ባለባቶች ቀርቦ አባቴ ወደ እስር ቤት ተወሰደ። ከእስር ቤት ተጠርቶ ወደ ችሎት በቀረበበት ዕለትም ዳኞቹ "ለምንድነው ለእንግዳ ትምህርት አስፋፊ ፈረንጆች ማረፊያ የሰጠኸው?" በማለት በጠየቁት ጊዜ የአባቴ ምላሽ፦ " የኢትዮጵያ መንግስት የእነዚህ ፈረንጆች እግር የሀገሪቱን አፈር እንዲረግጥ ጠረፍ ላይ ፈቃድ ሰጥቶአቸው ካስገባቸው በኋላ የእኔ በእንግድነት መቀበል ምን ይደንቃል?" የሚል ነበር። ዳኞቹ ለዚህ የአባቴ መስቀለኛ ጥያቄ ምላሽ አልነበራቸውምና አስፈራርተው ብቻ አባቴን በነፃ ለቀቁት። ደግሞም እውነት እኮ ነው፤ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ ቀጥሎም ወደ ደቡብ ሄደው ወንጌልን እንዲሰብኩ የፈቀደው በወቅቱ የነበረው ማዕከላዊ መንግስት ነው፤ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ "እንግዶቹ ለምን ቤትህ አደሩ?" የሚለው ጥያቄ ምንም ዓይነት አመክንዮአዊ መሠረት የለውም፤ አባቴና ሌሎች ጓደኞቹም፣ በታሰሩ ቁጥር ወደ ችሎት ቀርበው ለሚጠየቁት ጥያቄ የሚሰጡት ምላሽ የዘመኑን ትምህርት ካልቀሰሙ ገበሬዎች የሚጠበቅ አልነበረም፤ ለነገሩ በማቴዎስ ወንጌል ምዕረፍ 10-18 -20 ላይ ራሱ ጌታ ኢየሱስ “ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ፤ አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።” ብሎ የለ?

በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ምስረታ ትልቅ ቦታ ያላቸውና ባለምጡቅ አዕምሮው ባለቤት የሆኑት በኋላም በደርግ የግፍ አገዛዝ የተገደሉት ቄስ ጉዲና ቱምሳ በ1950ዎቹ ወደ ከምባታ፣ሚሽግዳ ባቀኑበት ወቅት ከአባቴ ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበራቸው። አባቴ ስለ ቄስ ጉዲና ምጡቅ አዕምሮና አስተዳደራዊ ብቃት ባነሳ ቁጥር መጨረሻ ላይ የሚያነሳው ስለ ቁመታቸው ነበር...ቄስ ጉዲና ቱምሳ ረጅም-ቁመተ ሎጋ ሰው ነበሩ!!

ወላጆቼንና እነ ቄስ ጉዲናን ጨምሮ፣ የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መስራች አባቶች በመከራው ዘመን በብዙ እንግልትና ስደት ወንጌልን ለቀጣዩ ትውልድ ቢያስረክቡም፣ ዛሬ ስደት በሌለበት በእነ ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ የአመራር ዘመን በአፍቅሮተ-ሥልጣንና ገንዘብ ሰበብ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ፈተና ላይ ወድቆ እንደማየት ምን የሚያሳዝን ነገር አለ? ለነገሩ በታሪክ ውስጥ ቤተክርስቲያንን ከውጭ የሚከፈትባት ውጊያና ጦርነት አንበርክኳት አያውቅም፤ የቤተክርስቲያን አንድነት ሁሌም ፈተና ላይ የሚወድቀው ከውስጥ ከሚነሳ ጦርነት ነው፤ የጭቃ ውስጥ እሾክ አደገኛ ነው።

ለማንኛውም ከሥር የምታዩት ምስል የአባቴ ሄራሞ አናሞና የእናቴ ዲንዳሜ አርፍጮ ነው፤ ሥዕሉን ከሳለልኝ በኋላ ትናንት ቢሮዬ ድረስ መጥቶ ያስረከበው ወዳጄና የማደንቀው ሰዓሊ ዳሳለኝ እናውጋው ነው፤ በጣም አመሠግነዋለሁ! ሁለቱም ወላጆች በዘመናቸው እግዚአብሔርን አገልግለው፣ 11 ልጆችን፣ 27 የልጅ ልጆችንና ለ6 ልጆች ቅድመ አያት ሆነውና ዕድሜ ጠግበው ተከታትለው ወደ አምላካቸው የሄዱት ከጥቂት ዓመታት በፊት ነበር። በነገራችን ላይ ሠዓሊው ከምስላቸው ፊት ለፊት 11 አዳይ አበባዎችን ያስቀመጠው እኛን ልጆቻችን እንዲወክሉለት ነው፤ በአሁኑ ወቅት የሁላችን ታላቅ የሆነውን ወንድማችንን አቶ ሳሙኤል ሄራሞን ጨምሮ ከቤተሰቦቻችን ገሚሱ የሚኖሩት በሰሜን አሜሪካ ፔንስሊቪኒያ ስቴት ውስጥ ነው። ለመረጃ ያህልም እኔ ለቤተሰባችን 10 ኛ ልጅ ነኝ። አመሠግናለሁ። መልካም ቀን!
Getahun Heramo

02/08/2025
🎬 ከዱራሜ እስከ ዋሽንግተን - የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራየኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ እግርኳስ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ ባለፈው ሳምንት የእግርኳስ ተጫዋች...
06/10/2024

🎬 ከዱራሜ እስከ ዋሽንግተን - የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ እግርኳስ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ ባለፈው ሳምንት የእግርኳስ ተጫዋችነት ፊርማዋን በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው ዲሲ ፓወር እግርኳስ ክለብ አኑራለች፡፡

ለሁለት አመት የሚቆየው ይህ ኮንትራትም ሎዛ አበራን በሰሜን አሜሪካ የመጀመርያዋ ኢትዮጵያዊ የፕሮፌሽናል ተጫዋች

04/10/2024

ማንደራሜ❤❤❤❤

Address

George South

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀበሻ ጥበብ ሥራና በልትና ደቡብ አፍሪካ ጆርጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የሀበሻ ጥበብ ሥራና በልትና ደቡብ አፍሪካ ጆርጅ:

Share