Amanuel .G .K

Amanuel .G .K Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amanuel .G .K, Digital creator, Addis Ababa.
(1)

ይህ ገፅ በኪነ -ጥበብ : #በታሪክ : #በሳኮሎጂ : #በፍልስፍና:የተመረጡ ፖስቶች : #ቪድዮዎች የምንጋራበት : የምንማማርበት ገፃችን ነው። , በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዛሬ 📖 ለ📖 💪ነገ
t.me/Ama1214dream

11/12/2025
10/12/2025

ወይ ጉድ 🤦‍♀️🤦‍♂️🤷‍♀️🤷‍♂️

‎ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። #1. በጎ ፍቃድ ወይም   ግንኙት ምክኒያት❗‎‎ #የትዳር አጋሮች በሳምንት ውሰጥ በአማካይ ከ 5 ጊዜ በላይ በስሜት ላይ የተመጣጠነ እርካታ...
09/12/2025


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
#1. በጎ ፍቃድ ወይም ግንኙት ምክኒያት❗

‎ #የትዳር አጋሮች በሳምንት ውሰጥ በአማካይ ከ 5 ጊዜ በላይ በስሜት ላይ የተመጣጠነ እርካታውን የሚያስገኝ በጎ ፍቃድን መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ይህም ያለ ምንም መሸማቀቅና እርስበራሳቸው ያለ መደባበቅ መከወን እንዳለበት ሳይንሰ ይመክራል።

‎ #የተለየ የስሜት ለውጥና የግንኙነት አለመጣጣም ከታየ ችግሩን በንግግርና በውይይት በባለሙያ ታግዘው እንዲመከሩና እልባት እንድያገኙ ይመከራል።❗

‎👉 #2. እልህ ፣ፉክክር፣ቅናትና የመጥፎ ሰው ምክር✋ ❗
‎ #ይሄም በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰ የፀረ ትዳር ከርሰ እንደሆነና ይህም ስሜት ከተስተዋለ ፈጠን ብለው በኋይማኖት ሰዎችና በባለሙያ እንድመካከሩ ሳይንስ ያሰተምራል❗

‎👉 #3. ሱስ፣ #ዝሙትና ንቀት ✋❗

‎ #በዘመናዊነት የሚጠረጠር ትዳር በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ነው። ትናንሸም ይሁን ትላልቅ አውሎንፋስ በተነሳ ወቅት በቤቱ ላይ የሚጣለው አመኔታ የልብ ትሪታን ፍራሃትን ያስተጋባል ፣ቤቱ በንቀት ዓይን ይታያል፣በጠንካራው መሠረት ለመስራት የግድ ይፈርሳልና፣ #ዝሙት ሌላኛው የትዳር ነቀርሳ ነው። ከድርጊቱ መታነጽ ያሰፈልጋል❗

‎ #ሱስ አደገኛ አምልኮ ነው፣የዚህ መዘዙ ተዘርዝሮ አያልቅምና፣መብተው የባለሙያና የኋይማኖት ሰዎች ምክርን ይፈልጋል።በዚህ የተጠቁ ሰዎች ከድርጊቱ እንኳን እንዳይታቀብ አስቀድሞ የሚጠቀሙበት አደገኛው ንጥረ ነገር ከልክ በላይ የሆነ በራስ መተማመን እንድሰማቸው ስለሚያደርግ የመጨረሻ አምባገነኖች አክራረዎችና ግትሮች ያደርጋቸዋል። ንጥረ ነገሩን ባልተጠቀሙበት ወቅት የማይጨበት የባህሪይ ለውጥ ይዘው ይመጡና የሚጨበጥ ፀባይ እንኳን እንዳይኖር ያደርጋል።

‎ #በዚህ የተጠቁ ሰዎች ለነገሮች ደንታ አይሰጡም፣ለትዳሮቻቸው፣ለማህበራዊ ኑሮአቸውና ለግል ሥራቸውም የተዛባ የጊዜ አጠቃቀምን ይከተላሉ።❗

‎ 👉 #4.ገቢ አለመኖር፣የኋይማኖት ልዩነት፣የዋህነት፣ቁንጂና ❗

‎ #በዚህም አለመግባባትና፣አለመመካከር ቀስበቀስ የትዳር ከርስ ነው።

‎👉 #5. የማህበረሰብ ተጽእኖ ፣የትምህርት ደረጃ አለመመጣጠን፣የመኖሪያ ቦታ መረጣ፣የአየር ንብረት ተጽእኖ፣ብሔረተኝነት፣የሥልጣን ደረጃ፣ፖለትካ፤ድጋሜ ጋብቻና ህመም ❗

‎ #ከላይ በተጠቀሱ ሚክኒያቶች በዓመት ውሰጥ ከ 100➡30% የትዳር አጋሮቻቸው እንደሚፈቱና፣ይህም የባለሙያ ምክርን ይበልጥ እንደሚፈልግ ሳይንሰ ይናገራል።❗

‎እባካችሁ ምክሩን ለሌሎች ያጋሩ ❗

‎👉 ገጹን ለተጨማሪ ትምህርት ነክ መረጃ ያድርጉ❗


Google pixel 4xlLMC 8.4+XML 🌈🌄🌴Édit : Lr🖌️🎨
09/12/2025

Google pixel 4xl
LMC 8.4+XML 🌈🌄🌴
Édit : Lr🖌️🎨

09/12/2025

እንዴት አደራችሁ 🙏🙏🙏🙏
09/12/2025

እንዴት አደራችሁ 🙏🙏🙏🙏

 ✅ከሰወች ጋር ስንኖር በዝምታ የምናክመው ህመም ካለ ዝምታን እንምረጥ‼️𝗗𝗿. 𝗔𝗯𝗶𝘆 - 𝗝𝗶𝗺𝗺𝗮 ☑️ዝምታችን  ጣዕም ሰጥቶ መልካም  ፍሬ የሚያፈራልን ከሆነ በጥልቁ ዝምታ ውስጥ ዝም እንበ...
09/12/2025


✅ከሰወች ጋር ስንኖር በዝምታ የምናክመው ህመም ካለ ዝምታን እንምረጥ‼️
𝗗𝗿. 𝗔𝗯𝗶𝘆 - 𝗝𝗶𝗺𝗺𝗮
☑️ዝምታችን ጣዕም ሰጥቶ መልካም ፍሬ የሚያፈራልን ከሆነ በጥልቁ ዝምታ ውስጥ ዝም እንበል።

☑️በመናገራችን ደግሞ የምናቀናው ጠማማነት ካለ በፍቅር እንናገር።

☑️በመናገራችንም ሆነ በዝምታችን ህመምን ካላከምን የቆምንበት ቦታ የእኛን መኖር አልፈለገምና በትህትና ዞር እንበል።

☑️ምንጊዜም ንግግራችን ከዝምታችን ተሺሎ ሲገኝ እንናገር ካልሆነ ግን ዝምታ ጥበብ ነው።

.

🛑  #ለምንድነው በቂ እንቅልፍ ተኝተንም ሁሌም ድካም የሚሰማን? (የአእምሮና  የአካላችን አለመግባባት ሚስጥር)🧠"ትክክለኛው እረፍት የሚገኘው ከእንቅልፍ ሰአት ብዛት ሳይሆን፣ አእምሯችን እና...
08/12/2025

🛑 #ለምንድነው በቂ እንቅልፍ ተኝተንም ሁሌም ድካም የሚሰማን? (የአእምሮና የአካላችን አለመግባባት ሚስጥር)🧠

"ትክክለኛው እረፍት የሚገኘው ከእንቅልፍ ሰአት ብዛት ሳይሆን፣ አእምሯችን እና አካላችን ሲጣመሩ ነው።"

1. 🤯 እኛ እዚህ ነን፤ አእምሯችን ሌላ ቦታ ነው (የችግሩ ምንጭ)

ስትተኛ መተኛት፣ ስትበላ መብላት፣ ስትሰራ መስራት ነበረብን። ነገር ግን በዚህ ዘመን የምናደርገው ነገር እና የምናስበው ነገር አይገናኝም።

✓ ሰዎች እየሰሩ ስለ መብላት ያስባሉ፤
✓ እየበሉ ስለ መተኛት ያስባሉ፤
✓ እየተኙ ደግሞ ስለ ስራ ይጨነቃሉ።

❌ አካላችን እዚህ ነው፤ አእምሯችን ግን ሌላ ቦታ ነው።
ይህ አለመናበብ ( ) ውስጣዊ ሰላማችንን ይነሳናል፣ ጉልበታችንንም ይጨርሳል። ለዚህም ነው ሙሉ እረፍት የማይሰማን።

2. ✅ የ"አሁን" ጊዜ ጥበብ: በአካልና በአእምሮ መገኘት

? በአካልም በአእምሮም "አሁን" ላይ መገኘት ነው።

✓ ስትነዳ መንዳት ብቻ።
✓ ስትሰማ በትኩረት መስማት ብቻ።
✓ስትሰራ ስራህን ብቻ።
✓ 🗣️ "የትም ሁን፤ ሙሉ በሙሉ እዚያው ሁን።"
✓ 🗣️ "ስትራመድ ተራመድ፤ ስትበላ ብላ።"
✓ 🗣️ "ስለ ቀድሞው አትዳክር፣ ስለ ነገ አትመኝ፣ አእምሮህን በዛሬው ጊዜ ላይ ብቻ አኑር።"

ትክክለኛው እረፍት የሚገኘው ከእንቅልፍ ሰአት ብዛት ሳይሆን፣ አእምሯችን እና አካላችን ሲጣመሩ ነው።

👇የዕለቱ ጥያቄ፡

እርስዎስ? ትኩረትዎን ሰብስበው በአሁን ጊዜ (Present) ለመኖር ይቸገራሉ? ይህንን አለመናበብ (misalignment) ለማሸነፍ ምን ያደርጋሉ? ሃሳብዎን ኮሜንት ላይ ያካፍሉን።
ከማህበራዊ ሚድያ የተተረጎመ

  ለማስቆም 12 ውጤታማ መንገዶች! | 12 Effective Ways To Stop Armpit Sweatinበራስ መተማመናችንን የሚጎዳውን የብብት ላብ እንዴት እናስቁም? ቀጣይነት ያለው ከልክ ያ...
08/12/2025


ለማስቆም 12 ውጤታማ መንገዶች! | 12 Effective Ways To Stop Armpit Sweatin
በራስ መተማመናችንን የሚጎዳውን የብብት ላብ እንዴት እናስቁም?

ቀጣይነት ያለው ከልክ ያለፈ የብብት ላብ ምቾትን ከመንሳት ባሻገር በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር ይችላል።

ነገር ግን አይጨነቁ! ይህንን ችግር ለመፍታት እና ቀኑን ሙሉ ጽድት ብለው ለመዋል የሚረዱ 12 ቀላል እና ውጤታማ ዘዴዎችን ከዚህ በታች አዘጋጅተን አቅርበናል!

1️⃣ ጠንከር ያሉ የላብ መከላከያዎችን (Antiperspirants) ምርቶችን ይጠቀሙ!

አንቲፐርስፐራንት (Antiperspirants) ምንድን ነው? አንቲፐርስፐራንት ማለት የላብ መውጫ ቀዳዳዎችን በመዝጋት ላብን የሚቀንሱ ምርቶች ናቸው።

እንዴት እንጠቀማቸው? ከፍተኛ ኃይል ያላቸው (Clinical/Prescription strength) ፀረ-ላብ ምርቶችን ቆዳዎ በአግባቡ እንዲመጥና የተሻለ ውጤት ለማግኘት በተለይ ማታ ወደ መኝታ ሲሄዱ ወይም ከመተኛትዎ በፊት መቀባትዎን አይርሱ።

2️⃣ አየር የሚያስገቡ ልብሶችን ይልበሱ

ከጥጥ፣ ከቀርከሃ (bamboo)፣ ወይም እርጥበትን ከሚስቡ ጨርቆች (moisture-wicking fabrics) የተሠሩ ለስላሳ እና በቀላሉ አየር የሚያስገቡ ልብሶችን ይልበሱ። እነዚህ ልብሶች አየር እንዲዘዋወር እና እርጥበት እንዳይከማች ይረዳሉ።

3️⃣ በመደበኛነት/በየጊዜው ሰውነትዎን ይታጠቡ
�አዘውትሮ ሰውነትን መታጠብ ለመጥፎ ሽታ የሚዳርጉ ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ እና ቆዳን ንጹህ ለማድረግ ይረዳል።

4️⃣ የብብት ፀጉርን ይላጩ ወይም ያስተካክሉ

የብብት ፀጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር ላብ እና ባክቴሪያ የሚጠራቀምበትን ቦታ ይቀንሳል። ይህም ብብትዎ ቶሎ እንዲደርቅ እና ሽታ እንዳያመጣ ይረዳል።

5️⃣ የሚያቃጥሉ ምግቦችን እና ካፌይን ይቀንሱ! ☕🌶️�••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በርበሬ/ሚጥሚጣ የበዛባቸው ምግቦች እና እንደ ቡና ያሉ መጠጦች የላብ እጢዎችን በማነቃቃት ሰውነታችን በይበልጥ እንዲያልበው ያደርጋሉ።

እነዚህን ምግቦች እና መጠጦች መቀነስ ለውጥ ያመጣል።

6️⃣ ላብን የሚመጡ ፓውደሮች ይጠቀሙ!

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••�

ላብን የሚመጡ የሰውነት ፓውደሮችን መጠቀም እርጥበትን በመቀነስ ልብስዎ በላብ እንዳይበላሽ ይከላከላሉ።

7️⃣ የውስጥ ልብሶችን ወይም ላብ ማድረቂያ ጨርቆችን (Pads) ይጠቀሙ!

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ላብን የሚከለክሉ የውስጥ ቲሸርቶች (undershirts) ወይም ሊጣሉ የሚችሉ ትንንሽ የላብ መከላከያ ፓድ (Sweat pads)፤ በላብ እና በውጪ ልብስዎ መካከል (ወደ ዋናው ልብስዎ እንዳይደርስና እርጥበት እንዳይታይ) እንደ ላብ መከላከያ ሆነው ያገለግላሉ።

8️⃣ ጭንቀትን ይቆጣጠሩ! 🧘🏽‍♀️

•••••••••••••••••••••••••••••

�ጭንቀት ወይም ጫና ሲበዛብን ሰውነታችን ብዙ ላብ ያመነጫል። እራስን ማረጋጋት፣ የጥልቅ አተነፋፈስ ልምምዶችን መስራት፣ ሜዲቴሽን፣ እና አጭር የመዝናኛ ጊዜዎችን መውሰድ የላብ መጠንን ለመቀነስ/ለመቆጣጠር ይረዳል።

9️⃣ በቂ ውሃ ይጠጡ! 💧

•••••••••••••••••••••••••

�በቂ ውሃ መጠጣት የሰውነትን የሙቀት መጠን ለማስተካከል/ለመቆጣጠር ይረዳል። ይህም ሰውነታችን በላብ አማካኝነት ራሱን የማቀዝቀዝ ፍላጎቱን ይቀንሳል።

🔟 ተፈጥሯዊ መፍትሄዎችን ይሞክሩ! 🍋

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

አንዳንድ ሰዎች እንደ አፕል ሳይደር ቪኒገር (Apple Cider Vinegar)፣ ዊች ሃዘል (Witch Hazel)፣ ወይም ቤኪንግ ሶዳ (Baking Soda) ያሉ ተፈጥሯዊ ነገሮችን ተጠቅመው ለጊዜያዊ የላብ መቆጣጠሪያነት መፍትሔ/እፎይታ ያገኛሉ።

1️⃣1️⃣ በሐኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶችን ያግኙ! 💊

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በገበያ ላይ የሚገኙ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚገኙ ምርቶችና ዲዮድራንቶች ካልሰሩ፤ የቆዳ ሐኪም በማማከር በሐኪም የሚታዘዙ ጠንከር ያሉ መድሃኒቶችን መጠቀም ይቻላል።

1️⃣2️⃣ ዘመናዊ የህክምና አማራጮችን ይመልከቱ! 👨‍⚕️

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••�

ከመጠን በላይ ላብ ላለባቸው ሰዎች (ይህም ሃይፐር ሃይድሮሲስ - Hyperhidrosis ይባላል)፤ እንደ ቦቶክስ (Botox) መርፌ፣ አይዮንቶፎሬሲስ (iontophoresis)፣ እና ሌሎች ዘመናዊ የሕክምና አማራጮችን ከሐኪም ጋር በመመካከር መጠቀም የብብት ላብን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል።

እነዚህን ዘዴዎች አጣምሮ በመጠቀም የላብ መጠንን መቀነስ እና የዕለት ተዕለት ምቾትዎን መጠበቅ/ማሻሻል ይችላሉ።

ነገር ግን ላቡ ከልክ በላይ ከሆነ እና የዕለት ተዕለት ህይወታችንን የሚያውክ ወይም የሚረብሽ የሕክምና ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው።
ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅዎ ያጋሩ!
እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏

የጠቢቡ ሰሎሞን ፍርድ ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠል...
07/12/2025

የጠቢቡ ሰሎሞን ፍርድ

ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡

‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡

ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡

ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡ የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡

ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ› ሲል አሰናበታቸው፡፡

በማግሥቱ ሦስቱ ጓደኛሞች መጡ፡፡ ችሎቱም ተጀመረ፡፡

ንጉሥ ሰሎሞን ‹የእናንተን ጉዳይ ከመመልከቴ በፊት ሦስታችሁም ጠቢባን መሆናችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም በሚከተለው ታሪክ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ እፈልጋለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው እየተማሩና እየተጫወቱ አደጉ፡፡ ወደፊት ትልቅ ሰው ሲሆኑ ተጋብተው አብረው ለመኖር ቃል ተግባቡ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የኑሮ መሥመር አለያያቸውና በተለያዩ ቦታዎች መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ በዚህ መካከልም ሴቷ ቃል ኪዳንዋን ረሳችውና ሌላ ባል አገባች፡፡ ጋብቻው በተፈጸመበት ቀን ማታ የገባቺው ቃል ኪዳን ትዝ አላት፡፡ ደነገጠች፡፡ ነገሩን ለባልዋ ነገረቺው፡፡ ባልዋም ለቃል ኪዳን ትልቅ ቦታ የነበረው ሰው ነበርና ‹በይ ተነሺ ቃል የገባሺለትን ሰው እንፈልገው፤ ስናገኘውም ቃል ኪዳኑን ማፍረሳችንን ነግረነው፣ የገንዘብ ካሣም ከፍለነው ይቅርታ ያድርግልን፡፡ ያለበለዚያ ትዳራችን ይበላሻል› አላት፡፡

ሁለቱ አዲስ ተጋቢዎች ልጁ ይገኝበታል ወደሚባለው ቦታ ሩቅ መንገድ ተጉዘው አገኙት፡፡ የሆኑትንም ነገር ሁሉ ገለጡለት፡፡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው፣ ገንዘቡን እንዲቀበላቸው ለመኑት፡፡ ልጁ ቀና ሰው ስለነበር ይቅርታ አደረገላቸው፡፡ ‹ያልሠራሁበትን ገንዘብ አልቀበልም› ብሎ ገንዘቡን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ እነርሱም አመስግነውት ተመለሱ፡፡ ሲመለሱ በመንገድ ላይ አንድ ዘራፊ አጋጠማቸውና የያዙትን ገንዘብ ነጠቃቸው፡፡ ልጂቱም ገንዘቡ በምን ምክንያት እንደተያዘ ታሪኩን እያለቀሰች ለዘራፊው ነገረቺውና እንዲመልስላቸው ለመነቺው፡፡ ዘራፊውም በታሪኩ ተደንቆ የወሰደውን ገንዘብ መለሰላቸው፡፡

ንጉሥ ሰሎሞን ይህን ታሪክ ከተረከ በኋላ ‹ከባልየው፣ ከሚስቱ፣ ከቀድሞ ወዳጇና ከዘራፊው የትኛው ሰው የበለጠ ምስጋና ይገባዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡

የመጀመሪያው ነጋዴም ‹ለእኔ የበለጠ ምስጋና የሚገባት ሴቲቱ ናት፡፡ ቃል ኪዳንዋን አስታውሳ ይቅርታ ለመጠየቅ መነሣቷ ያስመሰግናታል› ሲል ሐሳቡን ሰጠ፡፡

ሁለተኛው ነጋዴም ‹ለእኔ ግን የበለጠ ምስጋና የሚገባው ባልዋ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚስቱ ቃል ኪዳንዋን ማፍረሷን ስትነግረው ቃልዋን ተቀብሎ፣ ቤት ንብረቱን ትቶ፣ ገንዘቡን ይዞ ወደ እጮኛዋ ዘንድ መሄዱና ይቅርታ መጠየቁ ያስመሰግነዋል› ሲል አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ባልና ሚስቱ ያደረጉት ነገር የሚገርምና የሚያስመሰግን ነው፤ ነገር ግን የቀድሞ እጮኛዋ ሞኝ ሰው ነው፤ ገንዘቡን መቀበል ነበረበት› ሲል ሐሳቡን ለገሰ፡፡

ንጉሥ ሰሎሞንም ሐሳባቸውን ከሰማ በኋላ ሦስተኛውን ነጋዴ ‹ገንዘቡን የሰረቅከው አንተ ነህ› አለው፡፡ ሰውዬውም ደነገጠና ወደ ንጉሡ ተመለከተ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ‹ያልደከመበትን ገንዘብ የሚመኝ አእምሮ ባይኖርህ ኖሮ ያንን ልጅ ሞኝ አትለውም ነበር፡፡ አስተሳሰቡ ከሌለ ድርጊቱ አይመጣም፡፡ አንተ ውስጥ ተጣምሞ የበቀለ ነገር አለ፡፡ ሁለቱ ጓደኞችህ ታማኝነትን ዋጋ ሰጥተውታል፤ አንተ ግን ለታማኝነት ዋጋ አልሰጠኸውም፡፡ ስለዚህ ካንተ በቀር ይህን ሊያደርግ የሚችል ሰው የለም፡፡

የአንተን አእምሮ ሳየው የተሠራበትን ነገር አየሁት፡፡ አእምሮ ሲሰጠን ተሠርቶ አልተሰጠንም፡፡ እንዲሠራ ተሰጠን እንጂ፡፡ ሰው በርስቱ ላይ እንዴት ያለ ቤት እንደሚሠራ መወሰንና ቤቱን መገንባት የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ የሚጠቀመው ዕቃ የሚገነባበትም መንገድ የቤቱን ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ አእምሮም እንዲሁ ነው፡፡ በሕግ፣ በምግባር፣ በትምህርት፣ በጥበብ፣ የተገነባ አእምሮ ያንተን ዓይነት አስተሳሰብ አይኖረውም፡፡ አሁን የሰጠኽው ሐሳብ ያሳለፍከውን ሕይወት፣ የተዘራብህን ዘርና የተሠራህበትን ነገር አሳይቶኛል፡፡ ወላጆችህን አየኋቸው፤ ጓደኞችህን አየኋቸው፣ መምህሮችህን አየኋቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ወይም ከእነዚህ አንዱ የዘራብህ ዘር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ዘር ባንተ ላይ መዘራቱን አታውቀው ይሆናል፡፡ ግን ተዘርቶብሃል፡፡

‹አንድ ታሪክ ልንገራችሁ› አላቸው ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡ እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው፡፡ ሁሉም ሌባውን ያወቀበት መንገድ አስደንቋቸዋል፡፡ ምንጣፍ ላይ ቁጭ አሉ፡፡

አንድ ቀን አንድ ልጅ እኔ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ፡፡ የመጣው አባቱን ገድሎ ነው፡፡ ረበናቱ ሁሉ ‹አባቱን የገደለ ፈጽሞ ይሙት ይላልና ይገደል› ብለው ወሰኑበት፡፡ እኔ ግን ይህንን ነገር ያደረገበትን ምክንያት ለመረዳት ስለፈለግኩ ጠየቅኩት፡፡ ነገሩም እንዲህ ነበር፡፡ አንድ አባት ልጁን ሁል ጊዜ አንድ ነገር ያስተምረዋል፡፡ ጓደኞቼ መቱኝ ሲለው ‹በላቸው› ይለዋል፡፡ ፍየሉ ወጋኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ ዕንቅፋት መታኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ የአባቱ መፍትሔ ሁልጊዜ ‹በለው› ብቻ ነበር፡፡ ልጁ በዚህ ትምህርት ነበር ያደገው፡፡ አደገ፡፡ ጎለመሰ፡፡ ፈረጠመ፡፡ ያገኘውን ሁሉ እየደበደበ፡፡

አንድ ቀን የአባቱን በጎች ወስዶ አባቱ ሳይፈቅድለት ሸጠና መጣ፡፡ አባቱ ለምን እንደሸጠ ሲጠይቀው ‹ገንዘብ ያስፈልገኛል› አለው፡፡ አባቱ ተናደደና በበጎች መጠበቂያ ጅራፍ መታው፡፡ ያን ጊዜ ልጁ ድንጋይ አንሥቶ እንደ ቃየል አባቱን አናቱን መትቶ ገደለው፡፡ ልጁን ለምን አባቱን እንደገደለ ስጠይቀው ‹አባቴ ያስቸገረኝን ሰው ሁሉ እንድመታ አስተምሮኛል፡፡ አባቴም ስላስቸገረኝ መታሁት፡፡ ለመሆኑ ከመምታት በቀር ምን ማድረግ እችል ነበር?› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ይህ ልጅ ሌላ ነገር አልተማረምና ያደረገው የተማረውን ነው፡፡ ሰው የትምህርቱ ውጤት ነውና› አለው፡፡ ሰውዬውም በነገሩ ተገርሞ ገንዘቡን መለሰ ይለናል ሚድራሽ የተባለው የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ፡፡

ይህንን ታሪክ ሳነብ ዛሬ በልጆቻችን ኅሊና እየገነባን ያለነው የዘረኛነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል፡፡ እያንዳንዳችን ለሌላው ብለን የምናስታጥቃቸው ነገር አፈሙዙ ወደራሳችን ሊዞረን እንደሚችል ያሰብንበት አልመሰለኝም፡፡ የተጣመመ ሐሳብ እያሰጠን፣ የተጣመመ ትውልድ አፍርተን የተስተካከለች ሀገር አንደመመኘታችን ያለ ሞኝነት ከወዴት ይገኛል?

Address

Addis Ababa

Telephone

+251905264394

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel .G .K posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amanuel .G .K:

Share