Hager ሃገር

Hager  ሃገር Your Window to Ethiopia's Political, Social, and Economic Realities Shaping the Narrative of Ethiopian Affairs with Honest Journalism.
(1)

ቤንዚን 112.67 ብር ገብቷልከመጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሰረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስ...
23/03/2025

ቤንዚን 112.67 ብር ገብቷል

ከመጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሰረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት ተወስኗል።
ከመጋቢት 14/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ
ቤንዚን 112.67
ኬሮሲን 107.93
ነጭ ናፍጣ 107.93
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109.22
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106.75 ብር በሊትር የሚሸጥ ይሆናል።

በትግራይ ክልል የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ስጋት መኖሩን ነዋሪዎቹ ተናገሩ‼️የትግራይ ወታደራዊ አመራር ሰሞኑን መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ዕቅድ መኖሩን በመግለጫቸው ካሳወቁ በኋላ ...
26/01/2025

በትግራይ ክልል የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ስጋት መኖሩን ነዋሪዎቹ ተናገሩ‼️
የትግራይ ወታደራዊ አመራር ሰሞኑን መፈንቅለ መንግስት የማድረግ ዕቅድ መኖሩን በመግለጫቸው ካሳወቁ በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
ውጥረቱን ተከትሎ የሆነ ነገር ሊፈጠር ይችላል በሚል ከወትሮው በተለየ ገንዘብ ለማውጣት ባንኮች በሰልፍ ተጨናንቀዋል ሲሉ እማኞች ገልፀዋል። በገበያ ማእከላት በተለይ የፍጅታ ሸቀጦች ላይ የፍላጎት መጠን በጣም ጨምሯል።
ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆናል ብሎ የሰጋው ህዝብ ሰማይን ደግፎ ኑሮውን እየመራ ነው። በዚህ ብቻ ግን አልተገደበም። የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ጀምሯል። «መንግስት የሚያፈርስ የትኛውም አካል አንታገስም» የመኾኒ ህዝብ በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ይዞት የወጣው መፈክር ነው።

26/01/2025

አዲስ ሪኮርድ!!
በስፔን ግማሽ ማራቶን ሚኪያስ ባረጋ የቦታ ኮርስ ሪኮርድ በመስበር ኣሸነፈ እንኳን ደስ ኣለህ የጅግና ወንድም

በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች ፈርሰዋል!!በጅማ ከተማ “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከባለቤታቸው፣ ከሚኒስትሮች እና ከ...
25/01/2025

በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች ፈርሰዋል!!
በጅማ ከተማ “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከባለቤታቸው፣ ከሚኒስትሮች እና ከሌሎችም እንግዶች ጋር በመሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በትላንትናው ዕለት ተዘዋውረው ጉብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ጉብኝት በኋላ በሰጡት ገለጻ፤ በጅማ ከተማ ለተከናወኑ “የገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ተናግረዋል።

በከተማይቱ የነበረ መስጂድ እና ከአንድ ሺህ በላይ የመቃብር ቦታ ቀድሞ ከነበሩባቸው ቦታዎች መነሳታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የጅማ ከተማ ነዋሪዎች “ቤቶቻቸውን ሲያፈርሱም” ሆነ ቦታዎችን ለፕሮጀክቶቹ ሲያስረክብ “ካሳ አለመጠየቃቸውን” አብይ በአድናቆት አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተወለዱበት በሻሻ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የጅማ ከተማ ህዝብ፤ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ “ ‘እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው’ ያለው” ሲሉም በገለጻቸው ላይ ጠቅሰዋል።

“የጅማ አካባቢ ማህበረሰብ ለእነዚህ ህልሞች፣ ለእነዚህ ሃሳቦች መወለድ የነበረው ሚና፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርት መሆን ያለበት ነው” ሲሉም አብይ በገለጻቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ጅማ፤ ከሌሎች ቦታዎች በተለየ መንግስት ለሚያፈልቀው ሃሳብ “የተከታይነት” (followership) አመለካከት እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል

መነኸሪያ ሬዲዮ ይቅርታ ጠየቀ፣ ፕሮግራሙ ታግዷል።*******************************************ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግ...
25/01/2025

መነኸሪያ ሬዲዮ ይቅርታ ጠየቀ፣ ፕሮግራሙ ታግዷል።
*******************************************
ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ መቅረቧ ይታውቃል፡፡
የቀረበችው “ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ማዋል” በሚል ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈችውን የተዛቡ አመለካከቶችን በተመለከተ ይቅርታ ለመጠየቅ እና ከስህተቷ ሌሎች ትምህርት እንዲወስዱ ነው፡፡
በመሆኑም በርካታ አድማጮቻችን በግለሰቧ መቅረብ መከፋታቸውን ነግረውናል፡፡ ለተፈጠረው ጉዳይ ጣቢያችን ይቅርታ እየጠየቀ ላልተወሰነ ጊዜ በተባበሪ አዘጋጆች የሚቀረበው የብርሐን መንገድ የተሰኘ ፕሮግራም የታገደ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የፕሮግራሙ አዘጋጆች በቀጥታ ስልክ መስመር የገባ አድማጭን ያቋረጡበት መንገድ ከሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ በመሆኑ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ገበያን ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም አስጀመረችኢትዮጵያ በአጼ ሀይለስላሴ አስተዳድር ዘመን የስቶክ ግብይት የሚፈቅድ ስርዓት የነበራት ቢሆንም በደርግ ዘመን ተቋርጦ ነበር...
10/01/2025

ኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ገበያን ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም አስጀመረች
ኢትዮጵያ በአጼ ሀይለስላሴ አስተዳድር ዘመን የስቶክ ግብይት የሚፈቅድ ስርዓት የነበራት ቢሆንም በደርግ ዘመን ተቋርጦ ነበር፡፡
አሁን ደግሞ ከ50 ዓመት በኋላ የስቶክ ግብይትን ዳግም ያስጀመረች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አስጀምረዋል፡፡
በዚህ የግብይት ስርዓት መሰረት ኩባንያዎች አክስዮኖቻቸውን በይፋ ለገዢዎች መሸጥ የጀመሩ ሲሆን ሸማቾች ደግሞ ለሚገዙት አክስዮን ዋስትና የሚሰጥ ተቋምም ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ይህን የአክስዮን ግብይት የሚያሳልጡ ሁለት መንግስታዊ ተቋማት የተቋቋሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት እና የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ ናቸው፡፡

 #በፎቶ፡ በ   ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመበ  #አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/20...
10/01/2025

#በፎቶ፡ በ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡
የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡
የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን መግለጻቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡
ፎቶ፡ አሚኮ

09/01/2025

ዛሬ ከምሽቱ 1:30 ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች ይህ በቪድዮ ላይ የሚታየው ግዙፍ 'ነገር' ሰማይ ላይ መታየቱን በአካባቢ ያሉ ሰዎች መመልከታቸውን እያሳወቁኝ ይገኛሉ
ምዕራብ ጉጂ ዲምቱ አካባቢ ያለ አንድ ነዋሪ "በጣም አስፈሪ የሆነ ግዙፍ ነገር ከሰማይ ሲወርድ ነበር፣ ግቢ ውስጥ ያለነው ሰራተኞች በግርምት ተሰባስበን ነው ያየነው። እየተቀጣጠለ ሚወርድ ነው ሚመስለው፣ ክስተቱ የሕዋ ከሆነም ብታጣሩልን" በማለት ገልፆታል።
ቪድዮው ላይ የሚታየው ምን እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ብታሳውቁን በሚል አጋራሁት።
በቅርብ ቀናት የጠፈር ስብርባሪ ኬንያ ውስጥ ባለ አንድ ገጠራማ ቦታ መውደቁ ይታወሳል።

ዜና: ማንኛውም  #የነዳጅ ውጤቶች አጓጓዥ ተሸከርካሪ ጂ.ፒ.ኤስ (መከታተያ) እንዲገጥም የሚያስገድድ አዋጅ ጸደቀየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ...
09/01/2025

ዜና: ማንኛውም #የነዳጅ ውጤቶች አጓጓዥ ተሸከርካሪ ጂ.ፒ.ኤስ (መከታተያ) እንዲገጥም የሚያስገድድ አዋጅ ጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፤ በሁለት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተአቅቦ።
የጸደቀው አዋጅ የነዳጅ አጓጓዥ ተሸከርካሪዎችን በተመለከተ ባሰቀመጠው ግዴታ መሰረት ማንኛውም የነዳጅ ውጤቶች አጓጓዥ ተሸከርካሪ ጂ.ፒ.ኤስ (መከታተያ) እንዲገጥም ይገደዳል።
የነዳጅ ማደያዎች ያልተቆራረጠ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስገደድ፣ ነዳጅ በማደያ ውስጥ እያለ ያለ በቂ ምክንያት አገልግሎት ያለመቋረጥ የሚል ድንጋጌ በአዋጁ መካተቱም ተገልጿል።
ነዳጅ መንግሥት ከተመነው የመሸጫ ዋጋ በላይ ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር እንዲቀጡ በአዋጁ ተደንግጓል፤ የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ማከማቸትም ያስቀጣል።

31/12/2024

አርበኛ ዘመነ ካሴ ለአማራ ፋኖ በጎጃም ለክፍለ ጦር አመራሮች ያደረገው ንግግር Dec 2024

ትላንት ለሊት በአፋር ክልል በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ከ20 በላይ ቤቶች እና ሱቆች ፈረሱ  በአፋር ክልል በትላንትናው ዕለት በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በገቢ ረሱ ዞን፤ ዱለሳ ...
31/12/2024

ትላንት ለሊት በአፋር ክልል በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ከ20 በላይ ቤቶች እና ሱቆች ፈረሱ
በአፋር ክልል በትላንትናው ዕለት በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በገቢ ረሱ ዞን፤ ዱለሳ ወረዳ፣ ድሩፉሊ ቀበሌ የሚገኙ ከ20 በላይ ቤቶች እና ሱቆች መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳዳሪ ተናገሩ። የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬም አለመቆሙን የገለጹት ነዋሪዎች፤ “ከፍተኛ ስጋት” ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመላው ዓለም የደረሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚመዘግቡ ተቋማት፤ በአዋሽ አካባቢ ትላንት ሰኞ ታህሳስ 21፤ 2017 ስምንት የመሬት መንቀጥቀጦች መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው፤ ከለሊቱ 7 ሰዓት ገደማ የተከሰተው እና በሬክተር ስኬል 5.1 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሆነ ከጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል የተገኘው መረጃ ያሳያል።
በአፋር ክልል በዱለሳ ወረዳ፣ ድሩፉሊ ቀበሌ በተለምዶ ቀበና ተብሎ በሚጠራው አነስተኛ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዳውድ አደም፤ ትላንት ለሊት ሰባት ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለሰከንዶች የቆየ ቢሆንም፤ በቤታቸው ያለውን ቴሌቪዥን፣ ቁምሳጥን እና ብፌ መሰባበሩን ተናግረዋል።
በመሬት መንቀጥቀጡ ሳቢያ እርሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ ሰባት ያህል ቤቶች “ሙሉ ለሙሉ መውደቃቸውን” እና ፍየሎች ሞተው መመልከታቸውንም አስረድተዋል።
ቤታቸው ከፈረሰባቸው የቀበና ከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዱ አቶ ዳንኤል ደርሳ ናቸው። በትላንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ስምንት ክፍል ያለው ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተናግረዋል።
በትላንትናው ዕለት በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያደርሰውን ጉዳት በመፍራት፤ ከልጆቻቸው እና ከባለቤታቸው ጋር አስፓልት መንገድ ዳር ማደራቸውንም አክለዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋልየመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬክተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 መካከል ተመዘግበዋልየመሬት መንቀጥቀጦቹ ሌሊት ላይ ...
31/12/2024

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል
የመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬክተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 መካከል ተመዘግበዋል
የመሬት መንቀጥቀጦቹ ሌሊት ላይ በተደጋጋሚ የተከሰተ ሲሆን ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ተሰምቷል
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካ ሰርቬይ መረጃ ያመለክል።
የመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬትከተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 ማግኒትዩት መካከል መመዝገባቸውንም ነው ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።
በአዋሽ እና መትሃራ አካባዎች ከትናንት ቀን ጅምሮ እስከ ሌሊት ድረስ ከ4.5 እስከ 4.7 ማግኒትዩት መካከል የተመዘገቡ ከስምንት በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!

Adresse

Schulstasse
Lorsch
64653

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Hager ሃገር erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Hager ሃገር senden:

Teilen