Gamo nation

Gamo nation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo nation, Digital creator, .

መሪን ማክበርና መቀበል ለእግዚአብሔር መታዘዝ ነዉ።ጋሞ የሀገሩን መሪ እጆቹን ዘርግቶ እጥብ ሳር ይዞ እንኳን በደህና መጣህ ብሎ ተቀብሎ እንግዳውን ቤት ያፈራዉ አብልቶና አጠጥቶ ተንከባክቦ በ...
16/08/2025

መሪን ማክበርና መቀበል ለእግዚአብሔር መታዘዝ ነዉ።

ጋሞ የሀገሩን መሪ እጆቹን ዘርግቶ እጥብ ሳር ይዞ እንኳን በደህና መጣህ ብሎ ተቀብሎ እንግዳውን ቤት ያፈራዉ አብልቶና አጠጥቶ ተንከባክቦ በቤቱ አሳደረዉ።

ደጉ ባለሀገሩ ሰዉ ወዳዱና አክባሪዉ ጨዋዉ የጋሞ ህዝብ በደማቅ የተቀበለው እንግዳ በአደባባይ ወቶ እጆቹን ዘርግቶ እርጥብ ሳር ይዞ መሪዉን መርቆ ወደመጣበት በክብር ሸኜዉ።

የኢትዮጵያ 87ቱ ብሄር ብሄረሰቦች ስም‼ 1. ትግራይ2. አማራ3. አፋር 4. ኦሮሞ5. ሶማሌ6. ሲዳማ7. አገው8. ዎላይታ9. ከምባታ10. ሀዲያ11.  #ጋሞ❤12. ጉራጌ13. ኢሮብ14. አር...
16/08/2025

የኢትዮጵያ 87ቱ ብሄር ብሄረሰቦች ስም‼

1. ትግራይ
2. አማራ
3. አፋር
4. ኦሮሞ
5. ሶማሌ
6. ሲዳማ
7. አገው
8. ዎላይታ
9. ከምባታ
10. ሀዲያ
11. #ጋሞ❤
12. ጉራጌ
13. ኢሮብ
14. አርጎባ
15. ቱለማ
16. ስልጤ
17. ሺናሻ
18. አኝዋክ
19. ኑዌር
20. ሀመር
21. ኩናማ
22. ጉምዝ
23. በርታ
24. በና
25. አሪ
26. ሙርሲ
27. ቡሜ
28. ካሮ
29. ፀማይ
30. ኮንሶ
31. ዳሰነች
32. ቦረና
33. ገርባ
34. ሀላባ
35. አርቦሬ
36. ባጫ
37. ቤንች
38. ባስኬቶ
39. ቡርጂ
40. ጫራ
41. ጋዋዳ
42. ጌዲኦ
43. ጊዶሌ
44. ጎፋ
45. አደሬ
46. ከፊቾ
47. ኮንታ
48. ኒያንጋቶም
49. ናኦ
50. ቀቤና
51. ሱርማ
52. ከንባታ
53. የም
54. ወርጂ
55. ዲዚ
56. ዶንጋ
57. ዳውሮ
58. ዲሜ
59. ምዓን
60. ኮሞ
61. ማረቆ
62. ሞስዬ
63. ኦይዳ
64. ቦዲ
65. ፈዳሼ
66. ኮሬ
67. ማሌ
68. ማኦ
69. መሰንጎ
70. መዠንገር
71. ቀዋማ
72. ቀጨም
73. ሸኮ
75. ዘየሴ
76. ዘልማም
77. ሽታ
78. ቤተ እስራኤል
79. ማሾላ
80. ኮጉ
81. ድራሼ
82. ገባቶ
83. ጌዲቾ
84. ብራይሌ
85. ሙርሌ
86. ኮንቶማ
87 ወለኔ ....

እናተ ከብሄራችሁ ውጪ ስንቶቹን ብሄሮች ታውቃላችሁ ??

 ❤❤✌9/11/2017 አ .ም 49ኛ አመት❤ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንኳን ተወለድክ❤❤❤
15/08/2025

❤❤✌

9/11/2017 አ .ም 49ኛ አመት❤

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንኳን ተወለድክ❤❤❤

የጠቅላዩ ZUGA SUNTHAበጋሞ ብሄረሰብ ባህል ግለሰቦች  በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ደረጃ  እንዲኖራቸው  የሚሰጣቸው  የመጀመሪያ ዕርከን የማዕረግ ስም ZUGA SUNTHA ይባላል፡፡ ይህ...
14/08/2025

የጠቅላዩ ZUGA SUNTHA

በጋሞ ብሄረሰብ ባህል ግለሰቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ደረጃ እንዲኖራቸው የሚሰጣቸው የመጀመሪያ ዕርከን የማዕረግ ስም ZUGA SUNTHA ይባላል፡፡

ይህን የማዕረግ ስም ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የማዕረግ ስም ተሰጥቷቸው እንደነበር ይታወሳል።

ለጠቅላይ ሚንስትሩ የተሰጠውን SUNTHA የሚያስታውስ በኮሜንት ወዲህ ይበለኝ።

በዚሁ አጋጣሚ ZUGA SUNTHA የመጀመሪያ የማዕረግ ስሞች እና የአማርኛ አቻ ትርጉማቸው
👉አባ፦ ባህሩ፣ቻዩ፣ ታጋሹ፣ ሩኁሩህ፣
👉አፋ፦ ሰማዩ፣ ትልቁ፣
👉አሻ፦ ጥላው፣ ከለላው፣ አዳኙ
👉አይሳ፡-አሳዳሪው፣ ለጋሹ፣ ረዳቱ፣
👉ቦላ፡- የበላዩ፣ የተሻልከው፣
👉ቦርቃ፡- ገንዳሹ፣ ረፍራፊው፣
👉ጮልቦ፡- ጨማሪው፣ ሞልቶ ሰጪው
👉ጮሻ፡- አጥጋቢው፣ ጋባዡ፣
👉ዳዳ፦ መብረቁ፣ ኃይለኛው፣ ጀግናው፣
👉ዲቻ፡- አሳዳጊው፣ ተንከባካቢው፣
👉ሀርቃ፦ አርበጅባጁ፣ አጣሪው፣
👉 ካራ፡- ውብ፣ ጥበበኛው፣
👉ካልሣ፡- መጋቢው፣ አጥጋቢው
👉 ካማ፦ ጥላው፣ ከለላው፣
👉 ካንሳ፡- ዘላቂው፣ ተቋቋሚው፣
👉ፔራ፡- አሟሟቂው፣ ቀስቃሹ
👉ፖሻ፡- ተርታራው፣ በታኙ፣
👉ቶልባ፦ እላፊ ሰጪው፣ ያለስስት ሰጪው፣
👉ሳሎ፡ ሰማዩ፣ ሩቅ አሳቢው፣
👉ሻራ፡ ደመናው፣ ንጹህ፣
👉ዎጋ፡- ታላቁ፣ የተከበርከው፣
👉ዎልቃ፡- መከታው፣ ጉልበቱ፣
👉ፄራ፦ ጠርዙ፣ ጫፉ፣ ከሁሉ የላቅከው፣
👉ፆና፦ አሸናፊው፣ ባለድሉ፣
👉የልኣ፡- አድባሩ፣ ሰብሳቢው፣
👉ዙማ፡- ተራራው፣ ከፍ ያልከው፣

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለሀገርና ለዞኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ "አባ" የሚል የክብር ማዕረግ ስም በጋሞ አባቶች እንደተሰጣቸው ይታወሳል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደግሞ ለአንዲት ለተከበረች ፣ ለሀገሯ አስተዋጽአ ላበረከተች ሴት የሚሰጠውን "እርጼ" የተሰኘ የማዕረግ ስም የጋሞ አባቶች ተሰጥተዋል ።


የአዲስ አበባን መለያ የተነቀሰችው ዝነኛ የሆሊውድ ተዋናይ እውቋ የሆሊውድ ተዋናይት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎቿ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ የሰውነት ንቅሳቷ ከማጌጫነት ያለፈ ነው። አንጀሊና ...
14/08/2025

የአዲስ አበባን መለያ የተነቀሰችው ዝነኛ የሆሊውድ ተዋናይ

እውቋ የሆሊውድ ተዋናይት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎቿ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ የሰውነት ንቅሳቷ ከማጌጫነት ያለፈ ነው።

አንጀሊና በሰውነቷ ላይ ንቅሳት ማድረግ የጀመረችው ከዓመታት በፊት ሲሆን፣ ወሳኝ የምትላቸውን ጉዳዮችን በንቅሳት መልክ በሰውነቷ ላይ ታሰፍራለች።

አንጀሊና ጆሊ ከተነቀሰቻቸው ምልክቶች መካከል በቀኝ ክንዷ ላይ የከተሞች መለያ ኮድ ይገኛል ። ይህ “N 9° 2' 0" E 38° 45' 0" የሚለው ንቅሳት የዚህ ንቅሳት ትርጉም የጂፒኤስ መለያ ነው።

ይህም በጉዲፈቻ የወሰደቻት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችውን አንደኛ ልጇን ዘሀራን ለማስታወስ ስትል የተነቀሰችው ነው።

ቁጥሩ የአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መለያ ኮድ ሲሆን፤ በሌላ አገላለጽ ይህንን ቁጥር ጉግል ላይ ብንፈልገው የአዲስ አበባን ካርታ ያሳያል።

አንጀሊና ጆሊ በተጨማሪም በትከሻዋ እና በክንዶቿ ላይ የተለያዩ ትርጉም ያላቸው ንቅሳቶችን አስፍራለች።

ስለ እምነት እና የመንፈስ ብርታትን በተመለከተ የተጻፉ ጥቅሶች፣ የልጆቿን የልደት ቀን እና ስም እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የወሰደቻቸው የጉዲፈቻ ልጆቿ የትውልድ ሀገር መለያ ኮድ ከንቅሳቶቿ መካከል ይገኙበታል።

በዚህም መሰረት ሜይ 13, 1940 የሚል የሮማውያን ቁጥር ያለበት ንቅሳትም ተነቅሳለች።

ይህ ቀን የሚያመለክተው በ1950 ዎቹ የኢንግላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል እስካሁንም ዝነኛ የሆነውን አባባል የተናገሩበት ቀን ነው።

ቸርችል በእለቱ ለሀገራቸው ሕዝብ ንግግር ባቀረቡበት ወቅት "ከደም፣ ከእንባ እና ከላብ ውጪ የምሰጣችሁ ነገር የለኝም" በማለት ተናገረው ነበር ።

ይህ አባባላቸው እስካሁንም ድረስ የሚጠቀስ ሲሆን፤ አንጀሊና ጆሊም ይህንን ንግግር ለማሰብ ነው ቀኑን በግራ ክንዷ ላይ የተነቀሰችው።

የአዲስ አበባን መለያ በሰውነቷ ላይ ተነቅሳ የምትዞረው ዝነኛ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ አዲስ አበባን ሰሞኑን የጎበኘች ሲሆን፤ ብሔራዊ ቤተመንግስት ተገኝታ ጉብኝት አድርጋለች ።

አንጀሊና ጆሊ በአዲስ አበባ በነበራት ቆይታ ከቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ጋር ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ወደ ዓለም አቀፍ የጥበብ ኢንዱስትሪ ለመሳብ በምንችልባቸው ዘዴዎች ላይ ተወያይተዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝታም የሆስፒታሉን የሥራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት በግሎባል ሄልዝ ኮሚቴ (ጂኤችሲ) በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደር ግ ተናግራለች ።

ወርቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቁርጥ ቀን ልጆች Tilahun KebedeBerhanu Zewdie Zeta
14/08/2025

ወርቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቁርጥ ቀን ልጆች

Tilahun Kebede
Berhanu Zewdie Zeta

 ❤
13/08/2025

  💁✌ክፍል አንድ (1) ጋሞ ሆይ ልብ ብለህ አድምጠኝ ..........ልክ ያጣው ስድብ ፣ ገደብ አልባዉ ንቀት ፣ የማይቋረጥ ጥላቻዉና አሉታዊ የቀን ከለት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻው በአንድ ...
12/08/2025

💁✌

ክፍል አንድ (1)

ጋሞ ሆይ ልብ ብለህ አድምጠኝ ..........

ልክ ያጣው ስድብ ፣ ገደብ አልባዉ ንቀት ፣ የማይቋረጥ ጥላቻዉና አሉታዊ የቀን ከለት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻው በአንድ ግለስብ ላይ ያነጣጠረ በክልሉ ፕረዚዳንት በክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ላይ ብቻ ግቡን ያነገ እንዳይመስልህ ። እንደዛ ካሰብክማ እንደሚባለው እዉነትም አንተ እጅግ የዋህ ህዝብ ነህ።

ይቀጥላል ............

በጥቅት ወራቶች ዉስጥ ላሳያችሁን አንፀባራቂ ለዉጥ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏👉ክቡር ዶክተር መስፍን መንዛ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ 👉ክብርት ወ /ሮ ልሳነወርቅ ካሳዬ የአርባምንጭ ከተማ ብል...
12/08/2025

በጥቅት ወራቶች ዉስጥ ላሳያችሁን አንፀባራቂ ለዉጥ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

👉ክቡር ዶክተር መስፍን መንዛ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ
👉ክብርት ወ /ሮ ልሳነወርቅ ካሳዬ የአርባምንጭ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ /ቤት ሀላፊ

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አመራርነት የፊት መስመር ቁልፍ ቦታውን ከትልቅ ሀደራ ጋር ተቀብላችሁ በአጭር ጊዜ በከተማዋ የማይታመንና እጅን በአፍ የሚያስጭን አስደናቂ ለዉጥ አምጥታችኋል። የአርባ ምንጭ ከተማን ነዋሪዎቿ በሚመኙት ልክ እየገነባችሁ ትገኛላችሁ ። በዚህ አያያዛችሁ ከቀጠላችሁ አርባምንጭ ከተማን በምስራቅ አፍርካ ተወዳዳሪ የሌላት እጅግ ዉብና ማራኪ ከተማ እንደምታደርጓት ቅንጣት ያክል ጥርጥር የለንም ።

አሁን ላይ በአርባምንጭ ከተማ እየታዩ ባሉት ግንባታዎችና ለዉጦች እኛ ነዋሪዎቿ እጅግ ደስተኞች ነን።

❤❤❤

በ 10 ቢሊየን ዶላር (1.4 ትሪሊየን ብር)  ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለሚገነባው  የአህጉሪቱ ግዙፍ ኤርፖርት ሲቲ  ግንባታ በዛሬው እለት የፋይናንስ አቅርቦት ስምምነት  ከአፍሪካ ልማት ባንክ  ተ...
11/08/2025

በ 10 ቢሊየን ዶላር (1.4 ትሪሊየን ብር) ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለሚገነባው የአህጉሪቱ ግዙፍ ኤርፖርት ሲቲ ግንባታ በዛሬው እለት የፋይናንስ አቅርቦት ስምምነት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ 3,975 ሄክታር ላይ ሚገነባ ሲሆን 100 ሚሊየን ተጓዦች በዓመት ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የአጉሪቱ ግዙፍ ፕሮጀክት አዲስ አበባንና የኤርፖርት ከተማውን በ12 ደቂቃ ውስጥ የሚያገናኝ ዘመናዊ ፈጣን ባቡሮች የሚገነቡ ይሆናል ።

ኤርፖርቱ ሲጠናቀቅ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ በ3 እጥፍ በማሳደግ ማለትም በዓመት እስከ 25 ቢሊየን ዶላር (3.5 ትሪሊየን ብር) ገቢ የሚያስገኝ ይሆናል ።

ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet

የጋሞ ህዝብ ሆይ የምትወደዉና የሚወድህ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ አርባምንጭ ከተማ ይመጣልና በአደባባይ ግልብጥ ብለህ ወተህ ተቀበለው ።ጋሞ ሆይ ጠቅላይ ሚንስትርህን ...
10/08/2025

የጋሞ ህዝብ ሆይ የምትወደዉና የሚወድህ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ አርባምንጭ ከተማ ይመጣልና በአደባባይ ግልብጥ ብለህ ወተህ ተቀበለው ።

ጋሞ ሆይ ጠቅላይ ሚንስትርህን በክብር ተቀበለው ።

የጋሞ ሙዚቀኞች፣ ጨንቻ 1965 ዓም / Gamo Musicians. Chencha 1972    #ታሪካችን
09/08/2025

የጋሞ ሙዚቀኞች፣ ጨንቻ 1965 ዓም / Gamo Musicians. Chencha 1972
#ታሪካችን

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo nation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share