Central Hotel Bensa Daye

Central Hotel Bensa Daye EBC ODOO Sidaamu Afoo Facebookete Qoola Hawalle Keerunni Daggini!!

ዓለማችን በእለቱአሜሪካ አሜሪካ በኒዮርክ እና አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች   ቲክቶክን በመንግስት  ኮምፒዩተሮች አገልግሎት ላይ እንዳይውል ገደብ ጣለች።ቲክቶክ በመንግሥት መገልገያ ኮምፒዩተሮች...
19/08/2023

ዓለማችን በእለቱ

አሜሪካ

አሜሪካ በኒዮርክ እና አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ቲክቶክን በመንግስት ኮምፒዩተሮች አገልግሎት ላይ እንዳይውል ገደብ ጣለች።

ቲክቶክ በመንግሥት መገልገያ ኮምፒዩተሮች ላይ አገልግሎት ላይ እንዳይውል ያገደችው ኒዮርክ ከደህንነት ሥጋት ጋር በተያየዛ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

ኢሲያ

ህንድ አንዳንድ የሩዝ ምርት ከሀገር ውጭ መላክን አገደች

ምክንያት ደግሞ የእህል ዋጋ ንረት፣የዋጋ ግሽበትና የሩዝ ምርት እጥረት እንዳይገጥማት በመሥጋት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።

በዓለማችን ሩዝ በመላክ ቀዳሚ የሆነችው ህንድ የሩዝ ምርት ወደ ወጭ መላክ መቆሟን ተከትሎ በዓለም የሩዝ ዋጋ ጣራ ነክቷል ተብሏል።

መካከለኛ ምስራቅ

በጋዘ ሰርጥ የሚኖሩ 9 ፍልስጤማዊያን ሴቶች ታሪካቸውን ፣ ባህላቸውንና ቅርሳቸውን ለመጠበቅና ለማቆየት ያለ ድካም ይሰራሉ።

በበጎ ፈቃደኝነት ሥራውን የሚከውኑት ሴቶቹ የቆዩ መጽሃፍትን ወደ ዲጂታል በመቀየር ለተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራልም ብለዋል

አዎሮፓ

ዴንማርክ እና ደች ለዩክሬን ኤፍ 16 የጦር ጀት ድጋፍ አደረጉ
ድጋፉ ለዩክሬን እንዲተላለፍ አሜርካ መፍቀዱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቭላድምር ዞለንስክ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመሥግነው ፣ከራሺያ የሚመጣባቸውን ጦር ለመመከት እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።

አፍርካ

የብሪክስ አባል ሀገራት በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ጉባኤ ያካሄዳሉ ተባለ ።

በጉባኤው አዳዲስ አባል ሀገራት እንደሚሳተፉ የተጠቆመ ሲሆን የተቋሙ መመሥረት ከምእራባዊያን ጫና ለመላቀቅ ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ ስነገርለት ቆይቷል።

በጉባኤው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድምር ፑቲን እንደማይሳተፉ እየተነገረ ይገኛል። ምክንያቱ ደግሞ በዩክሬን ጦርነት ፈጽመውታል በተባለው የሰብኣዊ ወንጀል የሥር ማዘዣ ስለወጣባቸው ነው ተብሏል።

ደቡብ አፍርካ ከአፓርታይድ ነጻ እንዲትወጣ የያኔዋ የሶቭየት ህብረት የአሁኗ ሩሲያ የማይተካ ሚና መጨዎቱዋን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ...
14/08/2023

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

14/08/2023

Spoortete Odoo

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ -ግብር ለውሃ ሃብት ጥበቃ ካለው ፋይዳ አኳያ ሀገራት ሊተገብሩት እንደሚገባ ተጠቆመኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለዘላቂ የውሃ ጥበቃ ካለው...
14/08/2023

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ -ግብር ለውሃ ሃብት ጥበቃ ካለው ፋይዳ አኳያ ሀገራት ሊተገብሩት እንደሚገባ ተጠቆመ

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለዘላቂ የውሃ ጥበቃ ካለው ፋይዳ አኳያ ሀገራት በአርዓያነት ወስደው ሊተገብሩት እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለፁ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደተናገሩት ፥ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለዘላቂ ውሃ ሀብት ጥበቃ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።

የሚተከሉ ችግኞች ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳቸው ባሻገር ምንጮች እንዲጎለብቱ እና ለወንዞች ፍሰት መጨመር ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ፥ ይህም ከኢትዮጵያ አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።

በአጠቃላይ መርሐ ግብሩ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋምና ለውሃ ሀብት ጥበቃ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው፤ ሌሎች ሀገራት በአርዓያት ሊወስዱት እና ሊተገብሩት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ ከተቋማት ጋር በመተባበር የውሃ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እየሰራ መሆኑንም ነው ያነሱት።

ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 25 ቢሊየን ችግኝ መትከሏ ይታወቃል።

በሁለተኛው ምዕራፍም 25 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል የታቀደ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ በዘንድሮው ክረምት ከ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የዘገበው ኢዜአ

ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ተጀመረበአዲስ አባባ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረ ተገለፀ።እርምጃውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ...
10/08/2023

ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ

በአዲስ አባባ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረ ተገለፀ።

እርምጃውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር እየወሰዱ ነው ተብሏል።

እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ በሚደርስ ጥቆማ መሰረት አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል።

ቢሮው ፤ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ መሆኑ ገልጾ " ይህንን አስጸያፊ በሰውም በአምላክም ዘንድ የተጠላ ደርጊት በሚፈጽሙና በሚያስፈጽሙ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቆማት ላይ ካለ አንዳች ርህራሄ ከህብረተሰቡ በሚደርሰን ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰዳችንን አጠናክረን እንቀጥላልን " ሲል አሳውቋል።

በዚህም ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ " አበባ ገስት ሐውስ " በሚባል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት እርምጃ እንደተወሰደበት አሳውቋል።

የተቋሙ ኃላፊም በከተማው ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

ከግብረሰዶም ፀያፍ ተግባር ጋር የተገናኘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይቻላል። (ኢ ፕ ድ)

የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙና የሕዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ሊሆኑ ይገባል - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙና...
10/08/2023

የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙና የሕዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ሊሆኑ ይገባል - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙና የሕዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ ሊሆኑ እንደሚገባ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አዘጋጅነት "መገናኛ ብዙኃን ለአገር ግንባታ" በሚል መሪ ሃሳብ ለፌደራልና ለክልል የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎችና አርታኢያን ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፤ መገናኛ ብዙኃን በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነት እንዲጸናና አንድነት እንዲጠናከር መሥራት አለባቸው ብለዋል፡፡

መንግሥት ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንደምሰሶ የያዛቸው አቅጣጫዎች ከግብ እንዲደርሱ መገናኛ ብዙኃን የራሳቸውን በጎ አስተዋጽዖ ማድረግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡

የብዝኃ-ኢኮኖሚው ምሰሶ በሆኑት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ዘርፎች ላይ ትላልቅ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ለአብነትም መንግሥት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ግብርናን በማስፋፋት በርካታ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

መገናኛ ብዙኃንም ይህ ዕቅድ ከግብ እንዲደርስ ከማገዝ ባሻገር እውነተኛ መረጃዎችን ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በተለይም መንግሥት ሜካናይዜሽንን በመጠቀም በስንዴ ልማት የሚያከናውነው ውጤታማ ሥራ ላይ መሥራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ በሌማት ትሩፋትና አረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የዘገባዎች ትኩረት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በሌላ መልኩም በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተሰሩ ባሉ ተግባራት ዙሪያ በስፋት መሥራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

አካታች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲረጋገጥ መንግሥት እየሰራ ያለውን በጎ ሥራ ሕዝቡ ተገንዝቦ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ መገናኛ ብዙኃን የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም እንዲረጋገጥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙ ዘገባዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የሚሰሩ ዘገባዎች አካታች ሊሆኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ለምርመራ ጋዜጠኝነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ ለስኬታማነቱ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፤ መገናኛ ብዙኃን በዘገባዎቻቸው ለአገር ግንባታ አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በዚህም ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችሉ ሚዛናዊ ዘገባዎችን መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

10/08/2023
አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየአርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡...
09/08/2023

አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ለረዥም ጊዜ በህመም ላይ የቆየው አርቲስት አብነት በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ነበር።

ከዚህ ውስጥ አሉላ አባነጋ፣ የቼዝ ዓለም፣ ዳኛው፣ እስረኛው ንጉስ እና ነቅዕ ቴአትሮች ላይ ተውኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አያስቅም፣ አንድ እድል፣ ላምባዲና፣ ሰበበኛ፣ ባንቺ የመጣ፣ ቁልፉን ስጭኝ፣ የነገርኩሽ እለት፣ ፍቅር እስከ መቃብር እና አትሸኟትም ወይ በተሰኙ ፊልሞች ላይ በመተወን አድናቆትን አግኝቷል።

ስንቅ ፣መለከት፣ ትርታ እና ለወደዱት ደግሞ የተሳተፈባቸው ቲቪ ድራማዎች ሲሆኑ፥ በግሉም የቅብብሎሽ ድራማን ደርሷል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአንጋፋው አርቲስት አብነት ዳግም ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡

 ተዋናይ አብነት ዳግም ባደረበት የስኳር ህመም ምክንያት ቀደም ሲል ከባድ ህመም ላይ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን።ትላንት ላይ ህመሙ በመበርታቱ እና በመዳከሙ ምክንያት ወደ ጤና ጣቢያ ቢሄድም ...
09/08/2023



ተዋናይ አብነት ዳግም ባደረበት የስኳር ህመም ምክንያት ቀደም ሲል ከባድ ህመም ላይ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን።

ትላንት ላይ ህመሙ በመበርታቱ እና በመዳከሙ ምክንያት ወደ ጤና ጣቢያ ቢሄድም እሱን ለማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል

ተዋናይ አብነት ዳግም በብዙ ቲያትሮች እና ፊልሞች እንዲሁም ማስታወቂያዎች ላይ በብቃት የሚተውን በጣም ትልቅ ባለሙያ ነበር ።

* ለቤተሰቦቹ
* ለአድናቂዎቹ
* ለስራ ባልደረቦቹ

መጽናናትን እንመኛለን

ነፍስ ይማር!!!

😭😭😭

via ጉርሻ pageጉርሻ page

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በሲዳማ ክልል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉየትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በሲዳማ ክልል ወንዶገነት ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የችግን ተከላ መርሃ ግ...
09/08/2023

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በሲዳማ ክልል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በሲዳማ ክልል ወንዶገነት ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የችግን ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

አመራሮቹ በወንዶ ገነት ከተማ ለሚገኘው ትምህርት ቤት 20 ኮሚፒውተሮች ፣ 3500 መፅሐፍትን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም አቅም ለአጠራቸው 1000 ለሚጠጉ ተማሪዎች የቦርሳ ድጋፍ እንዲሁም 700 ለሚሆኑ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።

በዕለቱም የሲዳማ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሣ ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚ ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና ሌሎች ስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከሲዳማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

EBC News Sidaamu Afoo

ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ********************ኢትዮጵያ በፈተና የምትፀና ሀገር!ኢትዮጵያ በየዘመኑ ከዉስጥና ከዉጭ በሚያጋጥሟት በርካታ ፈተናዎችን አልፋ ዛሬ...
07/08/2023

ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ
********************

ኢትዮጵያ በፈተና የምትፀና ሀገር!

ኢትዮጵያ በየዘመኑ ከዉስጥና ከዉጭ በሚያጋጥሟት በርካታ ፈተናዎችን አልፋ ዛሬ የደረሰች ስትሆን አንድነቷና ቀጣይነቷ በጠንካራ አለት ላይ እንዲመሠረት ካደረጉት ጉዳዮች መካከል የህዝቦቿ ህብረትና አንድነት በጉልህ የሚጠቀስ ነው፡፡ በመሆኑም የህዝቦቿ ህልዉናና እጣ ፋንታም በእጅጉ የተሳሰረ ነዉ።

ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ካቆሟት እና የህዝቦቿን አንድነት ካስተሳሰሩ ዘመን ተሻጋሪ ተቋማት መካከል እንዱና ዋነኛዉ የሀገር መከላከያ ነዉ። መከላከያችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተወከሉበት የኢትዮጵያን ህብረብሔራዊነትን አጉልተዉ ከሚያሳዩት ተቋማት መካከል አንዱና ዋነኛው ሆኖ የሀገራችን የግዛት አንድነትና ሉኣላዊነት በመጠበቅ ስያገለግል ቆይቷል፤ እያገለገለም ይገኛል፡፡

ሀገር ወዳዱ፤ ቆራጡ እና ህዝባዊው መከላከያ ሰራዊታችን በሀገር ዉስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በተሰጡት ግዳጆች ላይ በመሰማራት በታላቅ የሀገር ፍቅር ስሜትና በጀግንነት አኩሪ ታሪክ የገነባ ህዝባዊ ሰራዊት ነዉ፡፡ የሀገራችን ጋሻ እና የሰላማችን የሁል ጊዜ መከታ የሆነው መከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜ ከዉጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና ከውስጥ በጽንፈኛ ሃይሎች የሚቃጡባትን አደጋዎችን በማክሸፍ ኢትዮጵያን በሙሉ ክብሯ እና አንድነቷ እንድትፀና ደሙን፣ አጥንቱን እና ተኪ የሌላትን ነፍሱን ሲገብር የኖረ ሰራዊት ነው፡፡

ይህንን የሀገሪቱን ታላቅ ተቋም ጽንፈኞች ከዉስጥ እና ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ከዉጭ ተቀናጅተው የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ ማሽነሪዎቻቸዉን በመጠቀም ለማጠልሸትና ለማዳከም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ሰራዊታችን ህብረብሄራዊነቱን ጠብቆ ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል፡፡ በመሆኑም መከላከያን መንካት ማለት የሀገር ሉኣላዊነትን መንካት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች ህልውናና እጣ ፋንታ በእጅጉ ተሳስሮ እያለ ጃውሳው ጽንፈኛ ሀይል በኣማራ ብሄራዊ ክልል የህዝብን ጥያቄ ያነገበ በማስመሰል ነፍጥ አንግቦ መከላከያ ሰራዊታችንን በማጥቃት ክልሉን የጦር አዉድማ እያደረገ ይገኛል፡፡ የክልሉ ህዝብ እራሱን በራሱ የሚያስያስተዳድር ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ የሚመራ ሆኖ ሳለ የአማራ ህዝብ ከሀገሪቱ ህዝቦች በተለየ ሁኔታ ጥያቄ ያለው በማስመሰል ነፍጥ ያነሱ እነዚህ በአቋራጭ ስልጣን ለመቆጣጠር ነውጠኛው ሀይል ክልሉን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ወደ ኋላ እየመለሰው ይገኛል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ያላገገመውን የክልሉን ህዝብ ነጣቂው ጃውሳው ዳግመኛ ለከባድ መከራ እየዳረገ ይገኛል፡፡
ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በደም፣ በአጥንት እንዲሁም በአስተዳደራዊ መዋቅር የተሳሰረው የአማራ ህዝብ የእርሻ ወቅትን በጠበቀ መልኩ መሬቱን በአዝርት እንዳይሸፍን መጭው ጊዜ ፈተና እንዲሆንበት ጃውሳው ጽንፈኛው ሀይል ጋሬጣ በመሆኑ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ህዝብን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳስቧል፡፡

የአማራ ህዝብም ሆነ መላው የሀገራችን ህዝቦች በምርጫ የመሰረቱት መንግስት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የዜጎች የጋራ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
“እኔ ካልመራኋት” በስተቀር ሀገር አትቀናም በሚል አጉል የጽንፈኞች ነጠላ ትርክት የሚጃጃለው ነውጠኛው ጃውሳ በህዝብ ጥያቄ ስም የራሱን የስልጣን ጥማት ለማርካት የክልሉን መንግስት በማፍረስ እና ክልሉን በማተራመስ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ

Address

Addis Ababa
Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Hotel Bensa Daye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share