
31/10/2024
፣
የጤና ባለሙያዎች፣ እንደማንኛውም ተቀጣሪ 'የሥራ ማቆም አድማ' የማድረግ መብት ያላቸው ቢሆንም፣ ካለባቸው ሙያዊ እና ሕጋዊ ግዴታ አኳያ፣ የሥራ ማቆም አድማቸው የጤና ተቋሙን መደበኛ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የሚያቋርጥ መሆን የለበትም። አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ማቋረጥ ሕጋዊም ሆነ የሙያዊ ሥነ-ምግባር ተጠያቂነት ሊያስከትል ስለሚችል።
1. የትርፍ ሥራ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለኝም በሚል መደበኛ ሥራ ማቆም፣ ሕገ ወጥ አካሄድ ነው።
2. ችግሩ አስተዳደራዊ ሆኖ፣ መፍትሄ ለማግኘት ሌሎች ሰላማዊ አማራጮችን አሟጠው መጠቀም ነበረባቸው። የሥራ ማቆም አድማ፣ ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና የመጨረሻ አማራጭ በመሆኑ።
3. ሌሎች አካባቢዎች ያሉ አንዳንድ ጤና ተቋማት ባለሙያዎች ያልተከፈላቸው ስላሉ፣ ችግሩ local አይደለም። ስለዚህ የሥራ ማቆም ምክንያታቸው (just cause) አመክኖያዊ አይደለም።
4. የሥራ ማቆም ውሳኔያቸው ተመጣጣኝ አይደለም። በታካሚዎች ላይ ሊያደርስ ከሚችለው መንከራተት እና ጉዳት አኳያ።
5. የሥራ ማቆሙ ውሳኔ ያሰቡትን ውጤት ሳይሆን፣ ያልገመቱት አሉታዊና እነርሱን የሚጎዳ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በቅድሚያ አላጤኑም። ምክንያቱም በሕጋዊ ማሕበር ያልተደገፈ ውሳኔ፣ ብቻቸውን ያስቀራቸዋል፣ ለአስተዳደራዊ እርምጃም ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።
ሲጠቃለል፣ አድማውን በአስቸኳይ አቁማችሁ ወደ ሥራችሁ ተመለሱና ጥያቄያችሁን በአግባቡ ለሚመለከተው አቅርቡ። መልሱንም በትዕግስት ጠብቁ።