Abdu Man Views

Abdu Man Views Yet to share

17/02/2026

ሰበር ዜና

ረመዳን ሙባረክ! ሼር ያድርጉ

የታላቁ የመረዳን ፆም ነገ እሮብ የካቲት 11 አንድ ብሎ እንሚጀመር ተገለፀ

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ነገ እሮብ የካቲት 11 እንደሚጀምር ታውቋል::

ረመዳን ሙባረክ!

አላህ ሃቁን ጠብቀው የሚፆሙት ያድርገን!
አሚን!

ፆም ስንፈታ (ስናፈጥር) መመገብ የሌለብን ምግቦች ????ረመዷን 2018/ 1448رمضان/Ramadan 20266 ቀን ቀረው/ 6 days to go1ኛ. የተቀነባበሩ እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦ...
11/02/2026

ፆም ስንፈታ (ስናፈጥር) መመገብ የሌለብን ምግቦች ????
ረመዷን 2018/ 1448رمضان/Ramadan 2026
6 ቀን ቀረው/ 6 days to go
1ኛ. የተቀነባበሩ እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች፟፟- ስኳር የበዛባቸው ምግቦች፤ መጠጦች እና ጣፋጮች (ለስላሳ፣ ከረሜላ፣ ጣፋጭ ዳቦና ኬኮች) → የደም ስኳር በፍጥነት መጨመር (blood glucose spike) ያስከትላሉ
2ኛ. የተጣራ ካርቦሃይድሬት (ነጭ ዳቦ ፣ ፓስታ) → የፋይበር እጥረት ስላለባቸው ሆድ መንፋት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
3ኛ. የተጠበሱ እና ቅባት ያላቸው ምግቦች፟- ፈጣን ምግቦች፣ በጣም የተጠባበሱ ምግቦች፤ ከባድ ዘይቶች → ለመዋሃድ አስቸጋሪ ናቸው አልፎ አልፎም ለሆድ ህመም ሊዳርጉ ይችላሉ።
4ኛ. ቅመም የበዛባቸው እና ስፓይሲ ምግቦች፟፟- እንደ ቃሪያ፤ ሚጥሚጣ፤ ትኩስ መረቅ → የጨጓራ ህመምን ሊያባብሱ ይችላሉ
5ኛ. ከፍተኛ ቅባት ያላቸው ወይም ቅባት የበዛባቸው ምግቦች፡-የኮሌስትሮል መጠንን ይጨምራሉ እንድሁም ለኢንሱሊን ሬዚስታንስ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ →እንደ በርገር እና ከባድ ሶስ ያለባቸው ምግቦች ከፆም በኋላ በቀላሉ ለመፈጨት አስቸጋሪ ናቸው
6ኛ. Carbonated Drink፟ ለስላሳ እና እንደ አምቦ/ኩል ውሃ ያሉ መጠጦች→ ድሃይዲሬሽን (ድርቀት) እና የጨጓራ መቆጣት ያመጣሉ
7ኛ. የወተት ተዋጽኦዎች (አንዳንድ ሰዎች ላይ) ፡- አንዳንድ ሰዎች በባዶ ሆዳቸው የወተት ተዋጽኦዎችን ሲወስዱ በቀላሉ ያለ መፈጨት/ያለመዋሀድ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል
8ኛ. ከመጠን በላይ ካፌይን፟- ቡና እና የኃይል መጠጦችን ማብዛት → ድሃይዲሬሽን እና የጨጓራ መቆጣት ያመጣሉ፡፡
9ኛ. ከፍተኛ-ፋይበር እና ጥሬ አትክልቶች (በባዶ ሆድ መውሰድ)፟ ጥሬ ብሮኮሊ፣ ጎመን፣ ባቄላ → ከጾም በኋላ ወዲያውኑ ለመዋሃድ አስቸጋሪ ስለሆኑ በባዶ ሆድ መውሰድ አይመከርም፡፡
10ኛ. የአልኮል መጠጦች፡- ሰውነትን ለድሃይዲሬሽን (ድርቀት) ያጋልጣሉ እንድሁም ጉበት ተግባር ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ...............ይቀጥላል................
አላህ ለረመዷን በሰላም ያድረሰን
አሚን
ለተመሳሳይ መረጃዎች ፔጁን ፎሎው ያድርጉ

ፆምና ኮሌስትሮል ረመዷን 2018/ 1447رمضان/Ramadan 2026ረመዷን 12 ቀን ቀረው/ 12 days to goየፆም ተፅዕኖ በኮሌስትሮል ላይ1. Fasting Reduces LDL ("መጥፎ...
05/02/2026

ፆምና ኮሌስትሮል
ረመዷን 2018/ 1447رمضان/Ramadan 2026
ረመዷን 12 ቀን ቀረው/ 12 days to go
የፆም ተፅዕኖ በኮሌስትሮል ላይ
1. Fasting Reduces LDL ("መጥፎ" ኮሌስትሮልን ይቀንሳል)
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጊዜያዊ ጾም (IF) እና የተራዘመ ጾም Low density lipoprotein (LDL) ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ይረዳል።
ይህ የሆነበት ምክንያት ጾም የስብ ሜታቦሊዝምን በማበረታታት የኤልዲኤል ቅንጣቶችን ማምረት በመቀነስ Low density lipoprotein LDL/መጥፎ ኮሌስትሮል እንድቀንስ ይረዳል።
2. Improves High density lipoprotein
ፆም ጥሩ ኮሌስትሮል እንድጨምር በማድረግ ከፍተኛ መጠን ያለው አላስፈላጊ ኮሌስትሮ ከደም ውስጥ ለማስወገድ ይረዳል።
3. Reduces Triglycerides
በፆም ወቅት የምናስገባው ካሎሪ ስለሚቀንስና የኢንሱሊን ሴንሲቲቪት ስለሚጨምር ትራይግሊሴራይድ እንድቀንስ ይረዳል፡፡
4. Improves cholesterol metabolism- ፆም የኮሌስትሮል ሜታቦሊዝምን በማሻሻ የተበላሹ ህዋሶችን ከደም በማስወጣት ራስን በራስ ለማከም (Autophagy) ይረዳል። ይህም የኮሌስትሮል በደም ቧንቧዎች መጠራቀምን ለመግታት ይጠቅማል
5. የሆርሞን ማስተካከያ፡- በፆም ወቅት የሚደረጉ የሆርሞን ለውጦች የኮሌስትሮል መጠን ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።
6. የክብደት መቀነስ እና ኮሌስትሮል፡- ፆም ለክብደት መቀነስ ይዳርጋል፣ይህም ብዙ ጊዜ ከኮሌስትሮል መጠን መሻሻል ጋር ይያያዛል። የክብደት መቀነስ በተለምዶ LDL ኮሌስትሮልን እና ትራይግሊሪየስን በመቀነስ HDL ኮሌስትሮልን ይጨምራል።

አላህ (ሱ ወ) ለረመዳንን ወር ፆም በሰለምና ጤና ያድርሰን!! አሚን
.......ይቀጥላል .......

ከዝና ወደ እምነት፤ የሉን ጉዞበአንድ ወቅት በአለም አቀፍ ታዋቂነት ስር ቆሞ ነበር፤ አሁን እሱ በመመሪያው ብርሃን ውስጥ ቆመ፡፡በብዙዎች ዘንድ ሉን በመባል የሚታወቀው በሙሉ ስሙ ቻውንሲ ሆው...
28/01/2026

ከዝና ወደ እምነት፤ የሉን ጉዞ

በአንድ ወቅት በአለም አቀፍ ታዋቂነት ስር ቆሞ ነበር፤ አሁን እሱ በመመሪያው ብርሃን ውስጥ ቆመ፡፡

በብዙዎች ዘንድ ሉን በመባል የሚታወቀው በሙሉ ስሙ ቻውንሲ ሆውኪንስ ከራፕ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ወጥቶ እስልምናን ተቀብሎ አሚር ጁነይድ ተባለ። የእሱ ጉዞ ወደ ፍጹምነት አልነበረም - ስለ ቅንነት ነበር፡፡ ሰላምን ያገኘው በጭብጨባ ሳይሆን በጸሎት ነው። አሁን ድምፁን የሚጠቀመው ለመዝናኛ ሳይሆን ለዳእዋ ነው።

አላህ እሱንም ሆነ ሀቅን የሚሹትን ሁሉ ይምራቸው። 🌙አሚን

አንጀሊና ጆሊ ከጋዛው የዘር ማጥፋት በተዓምር ከተረፈ ህፃን ጋርAngelina jolie with survivor of the genocide Thank you Angie 🙏
08/01/2026

አንጀሊና ጆሊ ከጋዛው የዘር ማጥፋት በተዓምር ከተረፈ ህፃን ጋር
Angelina jolie with survivor of the genocide
Thank you Angie 🙏

Address

Addis Ababa
Ababa

Telephone

+251984795443

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdu Man Views posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abdu Man Views:

Shortcuts

Share