
12/09/2025
ሰበር መረጃ
👉ላመነው ሰጤም እየመጣ ነው!
የፀረ ሰላም ሃይሉ ጃውሳ በውስጡ በተፈጠረው ውጊያ እየታወከ ይገኛል። በዚህም ቡድኑ አንደኛ ክ/ጦር በሚል የሚጠራው የሌባ ስብስብ ብትንትኑ ወጥቷል። የእርስ በርስ መገዳደሉ በሌሎችም ላይ ተባብሷል። የቡድኑ አመራር የሆኑት ቻላቸው አስናቀ፣ መንግስቱ አማረ እና ላመነው ለጉድ እየተለባለቡ ነው። በዚህ የእርስ በርስ ጦርነት ሙጂብ እና ስላባት የተባሉት የላመነው ተከታዮች ቆስለው በነመንግስቱ ተማርከዋል። እነመንግስቱ ላመነውን ለመግደል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አሁንም ገፍተውበታል።
ላመነውም እነሱን አጥፍቶ ለመጥፋት ላይ ታች እያለ ነው። ላመነው መንግስቱን እና ቻላቸውን ከመታ በኋላ እጁን ለመንግስት የመስጠት ፍላጎት እንዳለውን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሌላው የላመነው ጠባቂ እጁን ለመንግስት ሰጥቷል። እጁን ከሰጠ በኋላ የጎጃሙ ጃውሳ የማይወጣበት የጎጠኝነት ትብታብ ውስጥ እንደገባ ተናግሯል። በቡድኑ ውስጥ የሚደረገው የእርስ በርስ ውጊያ እና ነቆራ አንድም የስልጣን ሽኩቻ እንደሆነ በመግለፅ የታጣቂው መሪዎች በጎጥ ተከፋፍለው በጎሪጥ እንደሚተያዩም የላመነው ሰጤ ጠባቂ እጅ ከሰጠ በኋላ አንስቷል።