EthioPulse

EthioPulse Breaking and Current Ethiopian news, jobs vacancy, current affairs

https://t.me/EthioPulse1/414
28/09/2025

https://t.me/EthioPulse1/414

ሩስያና ኢትዮጵያ የተፈራረሙት👇‼️ ⚫️በኢትዮጵያ የኒውክሌር መሠረተ ልማት ግንባታ። ⚫️ለኒውክሌር ዘርፍ ባለሙያዎች ማሰልጠን። ⚫️የኒውክሌር ሃይልን የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጠና....

ቡታጅራ ምን ተፈጠረ❓❓ከትናንት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቡታጀራ ከተማ ግጭት ተቀስቅሷል።የግጭቱ ምክንያት ደሞ ለዘመናት በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ይተዳደርበት የነበረው የስናኖ...
28/09/2025

ቡታጅራ ምን ተፈጠረ❓❓
ከትናንት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቡታጀራ ከተማ ግጭት ተቀስቅሷል።
የግጭቱ ምክንያት ደሞ ለዘመናት በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ይተዳደርበት የነበረው የስናኖ ሴራ የዞኑ አስፈፃሚዎች ስናኖ ሴራ የእንቦር ቀበሌ አደለም የዶቢ ቀበሌ ነው ብለው በመወሰናቸው እና ዛሬ በመስቃን ወረዳ ዋና ከተማ ቡታጀራ ሴራና አዳራሽ ላይ ዝግጅት በማዘጋጀታቸው የተነሳ ሲሆን ይህም በተደጋጋሚ የመስቃን ወጣቶች ሽማግሌዎች ይሄ ልክ አደለም "ባህል የማጥፋት ተልዕኮ ነው " ብለው የመስቃን ወጣቶች ትናንት ምሽት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምረው በቡታጅራ ከተማ ወደ አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ አመፅ ማንሳታቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
በከተማዋ ሆቴሎች፣መኪኖች እና መገልገያ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
ዛሬም ድረስ አመፁ የቀጠለ ሲሆን በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል ብለዋል።
ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይልመድብን።

( #ኢትዮፐልስ)
===================
💎⬇️⬇️⬇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
Telegram
Telegram

🚨 ‎የሰሜን ኮርያ ሁለንተናዊ መሪ ኪም ወታደሮቻቸው ከሀገር አልፈው በሩሲያና ዩክሬንና ምዕራባውያን ጦርነት ላይ ታላቅ ጀብድ እየፈፀሙ መሆናቸውን የምዕራባውያን የበላይነት ለማስቆምና ሁለቱ ሀ...
26/08/2025

🚨 ‎የሰሜን ኮርያ ሁለንተናዊ መሪ ኪም ወታደሮቻቸው ከሀገር አልፈው በሩሲያና ዩክሬንና ምዕራባውያን ጦርነት ላይ ታላቅ ጀብድ እየፈፀሙ መሆናቸውን የምዕራባውያን የበላይነት ለማስቆምና ሁለቱ ሀገራት ፍትሃዊ አለም ለመፍጠር እየሰሩ እንደሆነ መናገራቸው ተሰማ ።

‎የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሰራዊቱ የባህር ማዶ ኦፕሬሽን መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት የሰሜን ኮርያ ወታደሮች ከራሳቸው አልፈው ሩሲያ ከዩክሬንና አጋሮቿ ጋር በምታደርገው ጦርነት የሀገራቸውን ጦር ታላላቅ ድሎችን እያስመዘገቡ በተሰማራበት አዉደ ዉጊያ በድል ላይ ድል እየተቀዳጀ መሆኑን አሞካሽተው ማመስገናቸዉን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግቧል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

‎ኪም በሩሲያ ኩርስክ ክልል ውስጥ ለሚያገለግሉት መኮንኖች እና ወታደሮች "ሞቅ ያለ ማበረታቻ ሰጥቷል" ፒዮንግያንግም የምዕራባውያን ተስፋፊነት የኔቶን ወወራ ለማስቆም ለሩሲያ እንዲዋጉ ከ10,000 በላይ ተዋጊዎችን እንደላከችም መሪዋ ተናግረዋል
‎ሲል የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት (KCNA) ሐሙስ ዕለት ዘግቧል።

‎ኪም በመዲናይቱ ላሉ ወታደራዊ አባላት ባደረጉት ንግግር በሩሲያ ታላቅ ድሎችን እያስመዘገበ የሚገኘዉ "የእኛ ጀግና ሰራዊት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

‎በኤፕሪል ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደሮቿን ከሩሲያ ወታደሮች ጋር ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር ማሰማራቷን የገለፁት ኩም ሰራዊታችን አሁን ማድረግ የሚገባውንና መደረግ ያለበትን እየሰራ ነው።ወደ ፊትም ያደርጋል። ብለዋል ።

‎ይህ በኪም እና በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ የተፈራረሙትን የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተከትሎ የጋራ መከላከያ ስምምነትንም አካል ሲሆን ከዚህ በኋላ ሰሜን ኮርያን የሚነካ ማንኛዉ ሀገር ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ወደጦርነት እንደሚገባ ማሳያ ነዉ ተብሏል ።

‎የኪም አስተያየት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩስያ እና የዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ ግፊት ባደረጉበት ወቅት መሆኑንና ፑቲን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለኪም ማሳወቃቸዉ ደግሞ ከሁለቱም ሀገራት መሪዎች ምን ያህል በተቀናጀ መልኩ አብረው እንደሚሰሩ ማረጋገጫ ተደርጓል ለዚህም ማሳያ ባለፈው ሳምንት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን ኮሪያን ወታደሮች “ጀግና” ሲሉ ማሞገሳቸዉና የሩሲያና ሰሜን ኮርያ ግኑኝነት መቼም የማይናወጥ መሆኑን መግለፃቸው ማረጋገጫ ተደርጓል ።

‎የደቡብ ኮሪያ እና የምዕራቡ ዓለም የስለላ ኤጀንሲዎች ፒዮንግያንግ በ2026 ተጨማሪ ከ10,000 በላይ ወታደሮችን ከመድፈኛ ዛጎሎች፣ ሚሳኤሎች እና የረዥም ርቀት ሮኬቶች ጋር ወደ ሩሲያ ኩርስክ ክልል እንደምትልክ አስታውቀዋል። እስካሁንም ለሩሲያ ሲዋጉ ወደ 600 የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ሲል ሴኡል ተናግሯል ሲል [አልጀዚራ] ዘግቧል።

🚨🇺🇸🇻🇪 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት የጦር መርከቦች ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ቬንዝዌላ እንዲጓዙ ማዘዛቸው ተመላከተ። ፕሬዝዳንቱ በቬንዝዌላ ያለውን ከፍተኛ የአደንዛዥ ዕፅ ...
26/08/2025

🚨🇺🇸🇻🇪 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት የጦር መርከቦች ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ቬንዝዌላ እንዲጓዙ ማዘዛቸው ተመላከተ።

ፕሬዝዳንቱ በቬንዝዌላ ያለውን ከፍተኛ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት በማለም ይህንን ውሳኔ መወሰናቸውም ተገልጿል።

አሜሪካ የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር የምትከሳቸው ሲሆን መሪውን ለመያዝ ለሚያግዛት እሰጣለሁ ያለችውን በዕጥፍ አሳድጋ 50 ሚሊዮን ዶላር ማድረጓ ይታወሳል።

ሶስቱ የአሜሪካ የጦር መርከቦች 4 ሺህ 500 የአሜሪካ ወታደሮችን ይዘው ወደ ቬንዝዌላ ዳርቻ እየተጓዙ መሆኑንና በሚመጣው እሁድ እንደሚደርሱ ስማቸው ያልተጠቀሰ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለስልጣናት መግለፃቸውን ሮይተርስ ዘግበዋል።

የጦር መርከቦቹ ጉዞ በቬንዝዌላ ያሉ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኖች በአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ስጋትነት ላይ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮ ለአሜሪካ ስጋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሚሊሻዎችን በበሀገሪቱ እንደሚያሰማሩ አስታውቀዋል።
ምንጭ [ሮይተርስ] ነው

ዜና: በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች አፈና፣ የዘፈቀደ እስራት እና ስወራ እንዳሳሰበው  #ሲፒጄ አስታወቀየዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ ዮናስ አማረ መ...
26/08/2025

ዜና: በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች አፈና፣ የዘፈቀደ እስራት እና ስወራ እንዳሳሰበው #ሲፒጄ አስታወቀ

የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ ዮናስ አማረ መታፈኑን፣ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከድር መሐመድ ኢስማኤል በዘፈቀደ መታሰሩን እንዲሁም የአሐዱ ሬዲዮ 94.3 “ቅዳሜ ገበያ” ፕሮግራም አዘጋጁ አብዱልሰመድ መሐመድ የት እንዳለ ሳይታወቅ መቆየቱ ስጋት እንደፈጠረበት አስታወቀ።

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የጋዜጠኞቹን ሁኔታ በዝርዝር አስቀምጧል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ለሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያቀረባቸው ጥያቄዎች መልስ አለማግኘታቸውን ጠቁሟል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ “ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ላይ አሳሳቢ ሪከርድ” እንዳላት እንዲሁም “ለጋዜጠኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ እየሆነች መምጣቷን” ጠቁመው ባለሥልጣናት ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ያለበትን እንዲያጣሩ፣ ጋዜጠኛ ከድር እና ጋዜጠኛ አብዱልሰመድን በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስበዋል።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/ 2017 ዓ/ም፦ የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ ዮናስ አማረ መታፈኑን፣ የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከድር መሐመድ .....

በየዓመቱ 250,000 ኢትዮጵያውያን እንደሚሰደዱ ሲገለጽ፤ ህገወጥ ስደትም አሳሳቢ ሆኗል።በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስደት የተለመደውን ትምህርት ላይ መሰረት ያደረገ የህይወት መንገድ በመተ...
25/08/2025

በየዓመቱ 250,000 ኢትዮጵያውያን እንደሚሰደዱ ሲገለጽ፤ ህገወጥ ስደትም አሳሳቢ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስደት የተለመደውን ትምህርት ላይ መሰረት ያደረገ የህይወት መንገድ በመተካት ላይ ይገኛል።

ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በሁሉም የትምህርት ደረጃ የትምህርት ተደራሽነት ቢስፋፋም አብዛኞቹ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ስራ ለማግኘት ይፈተናሉ።

70 በመቶ ህዝቧ ከ30 አመት በታች በሆነችው ኢትዮጵያ የከተማ የወጣቶች የስራ አጥነት ምጣኔ በ2022 25.3 በመቶ ነበር።

ከኢትዮጵያ በየአመቱ ታዲያ ከ250,000 በላይ ሰወች ከሃገር ይሰደዳሉ ሲባል መደበኛ ያልሆነ ስደትም የብዙሃንን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

ሰዎች እንዲሰደዱ የሚያደርጉ ምክንያቶች

ከ2000ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ ወደ ባህረ ሰላጤው ሃገራት መጓዝ ሲችሉ የአብዛኞቹ መዳረሻም ሳዑዲ አረቢያ ነበረች።

ከ2013-2018 ኢትዮጵያ በነዚህ ሃገራት የሚሰሩ ዜጎች እየሞቱ መሆኑን ተከትሎ በጊዜያዊነት ሰዎች ለስራ ወደነዚህ ሃገራት እንዳያመሩ እገዳ አስቀምጣ ነበር። በነዚህ ጊዜያትም በርካታ ሰዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሃገር ይወጡ ነበር።

በቂ የስራ ዕድል አለማግኘት፣ ግጭቶች እና አለመረጋጋት፣ በውጪ ሄዶ የተሻለ ኑሮን ለመኖር መመኘት፣ ቢዝነስ የመጀመር መንገዶች ውስንነት ሰዎች ስደትን የሚመርጡባቸው ምክንያቶች ናቸው።

በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች ደግሞ ስደት እንደ አጭርና ምርጡ የገቢ ማግኛ መንገድ ተደርጎ ሲወሰድ ውጪ ሃገር ዘመድ ያለው ሰውም ይከበራል የሚል ባህል አለ።

ሌላኛው ምክንያት በአማራ፣ ኦሮሚያ እንደዚሁም ትግራይ ክልል ያሉና የነበሩ ግጭቶች ወጣቶች መረጋጋትን ለማግኘት ስደትን እንዲመርጡ ሲገፋፋ ወጣቶቹ በጦርነት ወቅት ያላቸው ምርጫ ማቆሚያ አልባውን ጦርነት መቀላቀል አሊያም መሰደድ ነው።

በተጨማሪነት የሚነሳው ሌላኛው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት በህጋዊ መንገድ ለመውጣት የሚያስፈልጉ ህጎችን ጠንካራ ማድረጉ ነው።

ለምሳሌ እንደ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ የትምህርት ደረጃ ወዘተ ያሉ ነገሮች ከሃገር መውጣት የሚፈልጉ ሰዎች በቀላሉ ሊያሟላቸው የሚችሏቸው ነገሮቸ አይደሉም።

ከፓስፖርት ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች በራሱ አብዛኛው በቀላሉ ሊያሳካው የሚችለው ጉዳይ ስላልሆነ በህገወጥ መንገድ መሰደድን እንዲመርጡ ያደርጋል።

ሌላኛው ጉዳይ በህጋዊ መንገድ መሄድ ቢፈልጉ ጥቂት ዕድሎችን ብቻ ማግኘታቸው ነው። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የተፈራረመቻቸው ስምምነቶች የስራ ዕድልን የሚያቀርቡት በብዛት ሴቶች የሚሳተፉባቸው ለቤት ውስጥ ስራ መሆኑ የወንዶቹን እና የቤት ውስጥ ስራዎችን መስራት ለማይፈልጉት ምርጫቸውን ይገድባል።

የስደት መንገዶች

የመጀመሪያው በምስራቅ ያለው ሲሆን ይህም የቀይ ባህርን በመሻገር በየመን አድርጎ ሳዑዲ አረቢያ መግባት ነው።

ከ2014 ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ76 ሺህ በላይ ስደተኞች ሲሞቱ 1098 ያህሉ የሞቱት በዚህ መንገድ ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ በባህር ውስጥ ሰጥመው ነው።

በ2021 የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት እንዳስታወቀው ከተጠቀሰው አመት በፊት በነበሩ 5 አመታት ከሃገር የወጡ 51 ሺህ ኢትዮጵያውያን የገቡበት አልታወቀም።

ሁለተኛው ደግሞ የደቡብ መንገድ ሲሆን ይህም ከደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱ ናቸው

ይህ መንገድ ሁለተኛው ትልቁ የህገወጥ የስደት መንገድ ሲሆን ሶስተኛው መንገድ በሱዳን፣ ሊቢያ እና ሜድትራንያን ባህር አድርገው አውሮፓ የሚገቡ ናቸው።

ምን አይነት የመፍትሄ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ?

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከየትኛውም ጊዜ በላይ የኢኮኖሚ ዕድሎችን መፍጠር ሲጠበቅባት መንግሰትም የሙያ እና የስራ ፈጠራወችን በገጠራማው አካባቢ መደገፍ ይኖርበታል።

ሁለተኛው ህጋዊ የመሄጃ መንገዶች ማስፋፋት ነው። ይህም ከተለያዩ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በማድረግ ሊጠናከር ይገባል። እነዚህ ስምምቶቸ ሲደረጉ ወጣቶች ሊሰሩባቸው የሚችሉ የስራ ዘርፎችን ማካተትም ይገባል።

ህጋዊ ከሃገር የመውጫ መንገዶችንም ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ እና መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ እንዲወስኑ ትምህርቶችን መስጠትም ያስፈልጋል።

በተጨማሪ ሙያን መሰረት ያደረጉ ትምህርቶች እና የስራ ዕድሎች መመቻቸት ይኖርባቸዋል።

[ የዚህ ጹሑፍ ዋናው ቅጂ በThe Conversation ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን ጹሑፉ የዶ/ር ግርማቸው አዱኛ ነው። ]

ቡርኪናፋሶ በጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የሚደረግለት የወባ ፕሮጀክት እንዲቆም አዘዘች።በቢሊየነሩ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሜሊንዳ ጌትስ የተመሰረተው ጌትስ ፋውንዴሽን በቡርኪናፋሶ ወባ ላይ ትኩረት...
25/08/2025

ቡርኪናፋሶ በጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የሚደረግለት የወባ ፕሮጀክት እንዲቆም አዘዘች።

በቢሊየነሩ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሜሊንዳ ጌትስ የተመሰረተው ጌትስ ፋውንዴሽን በቡርኪናፋሶ ወባ ላይ ትኩረት ያደረገ ስራን ይደግፍ የነበረ ቢሆንም ከመንግስት ስራውን እንዲያቆም ተነግሮታል።

ፕሮጀክቱ'Target Malaria' የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የወባ በሽታን ለማጥፋት የዘረ መል ለውጥ የተደረገባቸውን የወባ ትንኞች መልቀት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲባል ሁሉንም ተግባራቱን እንዲያቆም ታዟል።

በተጨማሪ ወባን ለማጥፋት የሚለቃቸውን የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞችን እንዲያጠፋም ታዟል።

የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች በቡርኪናፋሶ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2019 ሲለቀቁ በዚህ ወርም ዳግም ተለቀው ነበር።

እነዚህ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች ጋር በተያያዘ ግን ሌሎች ጉዳቶችን ያስከትላሉ በሚል ውዝግቦች ነበሩ።

ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ በወባ በሽታ በብዛት የሚጠቁባት ዜጎች ካሉባቸው ሃገራት አንዷ ስትሆን 24 ሚሊየን ዜጎች ያሏት ሃገር በ2023 በበሽታው 8 ሚሊየን ሰዎች ተይዘው ከ16 ሺህ በላይ ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተው ነበር ተብሏል።

ከ2022 ጀምሮ በኢብራሂም ትራኦሬ ወታደራዊ መንግስት የምትተዳደረው ቡርኪናፋሶ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት እየሻከረ ሲሆን በዚህ አመት በሰኔ እና ሐምሌ ወር ብቻ 21 የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ተቋማትን ፈቃድም ነጥቃለች ተብሏል።

የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች እንዴት የወባ በሽታን ለማጥፋት እንደሚረዱ እና ስለሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ ከእዚህ እና ከእዚህ ማንበብ ትችላላችሁ።

Source: AFP

በኬንያ የቴክኖሎጂ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆኗል ተብሏል።ከዚህ ቀደም የኬንያ ዋነኛው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መዳረሻ የነበሩት የባንክ እና የማኑፋክቸሪን...
25/08/2025

በኬንያ የቴክኖሎጂ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆኗል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የኬንያ ዋነኛው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መዳረሻ የነበሩት የባንክ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ነበር ሲባል ለመጀመሪያ ጊዜ የቴክኖሎጂ ዘርፉ ከሁለቱ ዘርፎች በልጧል ተብሏል።

በወጣው ሪፖርት መሰረት የኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፉ በ2023 ከኬንያ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ውስጥ 38.6% ይዟል።

በተጨማሪ የባንክ ዘርፉ 27.6% ሲይዝ ማኑፋክቸሪንግ 16.7% የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስበዋል ተብሏል።

በአለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች እየጨመሩ ይገኛሉ።

ኬንያ በዘርፉ ለኢንቨስተሮች ምቹ የሆኑ የስታርትአፕ ከባቢ (Ecosystem) መፍጠሯ ለውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንቱ መጨመር ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

Source: Tech Africa

'ዶ/ር ደቦል' በሚል ስም ማህበራዊ ሚድያ ላይ የጤና ባለሙያዎችን ድምፅ በማሰማት የሚታወቀው ዶክተር ታሰረከሰሞኑ የጤና ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ ሲያሰሙት የነበረውን ድምፅ እና ሲያቀርቡት...
26/06/2025

'ዶ/ር ደቦል' በሚል ስም ማህበራዊ ሚድያ ላይ የጤና ባለሙያዎችን ድምፅ በማሰማት የሚታወቀው ዶክተር ታሰረ

ከሰሞኑ የጤና ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ ሲያሰሙት የነበረውን ድምፅ እና ሲያቀርቡት የነበረውን የመብት እና የጥቅም ጥያቄ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በማስተጋባት የሚታወቀው 'ዶ/ር ደቦል' ለእስር መዳረጉ ታውቋል።

'ዶ/ር ደቦል' በሚል ስሙ የሚታወቀው ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ ትናንት በባህር ዳር ከተማ ውስጥ እንደታሰረ የመረጃ ምንጮች ለመሠረት ሚድያ አረጋግጠዋል።

ከእስሩ በተጨማሪ 'ዶ/ር ደቦል' የሚለው የፌስቡክ ገፅ በመንግስት አካላት እንደተጠለፈ (ሀክ እንደተደረገ) የታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊትም የቴሌግራም አካውንቱን ለመጥለፍ ብዙ ሙከራ ሲደረግ እንደነበር የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ዶ/ር ዳንኤል ባህር ዳር በሚገኘው ጥበበ ግዮን ሆስፒታል የፅንስና የማህፀን ህክምና (Obstetrics and Gynecology) የመጨረሻ አመት ረዚደንት ሀኪም ሲሆን ከስድስት ወር በሗላ ምርቃት እንዳለው ታውቋል።

የጤና ባለሙያው 'Debol Surgery Bedside' የተባለ መፅሀፍ የፃፈ እንዲሁም 'MAC Ethiopia' የተባለ የህክምና ባለሙያዎች ከሙያቸው ውጪ ሌሎች ተሰጥዎቻቸውን ፈልገው እንዲያገኙ የሚያግዝ ድርጅትን ከመሰረቱ አንዱ ነው።

ዶ/ር ዳንኤል ምሳሌ የሚሆን፣ ላመነበት ወደሗላ የማይል እና በስራው የተመሰገነ እንደሆነ ባልደረቦቹ ለሚድያችን ተናግረዋል። ከእስሩ በሗላ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይሁን እንዲሁም የት ቦታ ታስሮ እንደሚገኝ እስካሁን ግልፅ መረጃ አልተገኘው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው መግለጫ የጤና ባለሙያዎች እስር እና እንግልት መኖሩን አረጋግጧል።

"የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጤና ባለሙያዎች ማህበር ላይ የጣሉትን እገዳ በፍጥነት በማንሳት ከባለሙያዎቹ ጋር ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ውይይት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል" በማለት ተቋሙ አሳስቧል።

"ወደስራ ተመለሱ ብለውን ስንመለስ እስር እያካሄዱ ነው። በተለይ ነቃ ያለ እንቅስቃሴ ሲያረጉ የነበሩትን እያሳደዱ እያሰሩ ነው" በማለት አንድ የጤና ባለሙያ ተናግሯል።

Address

Adama
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioPulse posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share