A.B.C news

A.B.C news News Hub

01/06/2026

አዲስ መረጃ 🚫
እስከ ለሊቱ 6:00 ተራዝሟል::
የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

01/06/2026

አዲስ መረጃ 🚫
ወልቂጤ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወልቂጤ ምርጫ ጣቢያ ታዛቢዎቼ ተደብድበው ተባረዋል፣ ሞተር ተነጥቀናል፣ እንዲሁም የምርጫ ወረቀት በፌስታል ሲበተን አይተናል ሲል ጎጎት ፓርቲ ምርጫው እንዲቆም ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ማቅረቡን አስታወቀ፤ ይሁን እንጂ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ምርጫ አስተባባሪ አቶ ነጋሽ በበኩላቸው፣ የቀረበው ክስ ከእውነት የራቀ መሆኑንና በተባለው ጣቢያ የፓርቲው ሁለት ታዛቢዎች በሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ በሌላ ጣቢያ ግን አንድ ታዛቢ ባጅ በመጠየቁ አኩርፎ ከመውጣት ውጭ ምንም የደረሰበት ድብደባ እንደሌለ በምርመራ ማረጋገጣቸውን ለሪፖርተር ዘጋቢ አስረድተዋል።

01/06/2026

አዲስ መረጃ 🚫
143 የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም::
በጸጥታ ችግር ምክንያት 143 የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት አለመከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል “በተወሰኑ ቦታዎች” የድምጽ መስጠት ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉም ቦርዱ ገልጿል።
ቦርዱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው።

01/06/2026

አዲስ መረጃ 🚫
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ተማሪዎች ተሰብስበው የአርሰናል እና ፒኤስጂ የቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ እያዩ በነበረበት ወቅት በተከሰተው ፍንዳታ የተጎዱ ተማሪዎች ለህክምና ወደ ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል መምጣታቸውንና የሞቱ ተማሪዎች እንዳሉ የጤና ባለሞያዎች አረጋግጠዋል። የሞቱ ተማሪዎች ቁጥር 3 ደርሷል " አንዱ ተማሪ ድንገተኛ ክፍል ላይ እንደደረሰ ህይወቱ አልፏል። ሁለቱ ደግሞ ኦፕራሲዮን ክፍል ከገቡ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው "

31/05/2026

የሞቱ ተማሪዎች ቁጥር 3 ደርሷል
አዲስ መረጃ 🚫
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ተማሪዎች ተሰብስበው የአርሰናል እና ፒኤስጂ የቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ እያዩ በነበረበት ወቅት በተከሰተው ፍንዳታ የተጎዱ ተማሪዎች ለህክምና ወደ ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል መምጣታቸውንና የሞቱ ተማሪዎች እንዳሉ የጤና ባለሞያዎች አረጋግጠዋል። የሞቱ ተማሪዎች ቁጥር 3 ደርሷል " አንዱ ተማሪ ድንገተኛ ክፍል ላይ እንደደረሰ ህይወቱ አልፏል። ሁለቱ ደግሞ ኦፕራሲዮን ክፍል ከገቡ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው "

29/05/2026

አዲስ መረጃ 🚫
የመቀሌ ነዋሪዎች ስጋት
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ አፈሳ እና እስር ህዝቡን ሌላ ስጋት ውስጥ ከቶታል። ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ከ 30000 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ወደ ክልሉ ልዩ ሀይል መግባታቸው ታውቋል። የሰሞኑ አፈሳ እና እስር በርካታ ሰዎችን ያሳሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከወትሮው በተለየ መልኩ የትግራይ ተወላጆች በአውቶብስ ወደ አዲስ አበባ ለመሳፈር ከፍተኛ ሰልፍ እንደታየ የመቀሌ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

29/05/2026

አዲስ መረጃ 🚫
የአልጀዚራ የግጭት መቆጣጠሪያ እንደሚያሳየው ከ Janurary 2022 እስከ may 15/2026 ድረስ በኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ ከ7,400 በላይ ግጭቶች ተመዝግበዋል።
ከግጭቶቹ ከግማሽ በላይ (3,719)
በአማራ ክልል በፋኖ እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ጭምር የተመዘገቡ ናቸው።
በኦሮሚያ ክልል 2,735 ግጭቶች የተመዘገቡት በ OLA በሚመራው የትጥቅ አመጽ እና ከተለያዩ የጋራ ግጭቶች ጎን ለጎን ነው። ሌሎች ክልሎችም አለመረጋጋት አጋጥሟቸዋል፣ በትግራይ ክልል 262 ግጭቶች ሲመዘገቡ፣ በምዕራብ ጋምቤላ ክልል ደግሞ 144 ግጭቶች ተመዝግበዋል። ከላይ ያለው ካርታ ባለፉት አራት አመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የተፈፀሙ አጠቃላይ ግጭቶች መሆኑን አልጀዚራ ይፋ አድርጓል።

29/05/2026

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ጄነራል ታደሰ ወረደ መታገታቸውን ወይም የቁም እስረኛ መደረጋቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን «ኢትዮጵያ ቼክ» አረጋግጧል።
​ባለፉት ቀናት እንደ "አንዳፍታ" እና "አባይ ሚዲያ" ባሉ ታዋቂ ገጾች የተሰራጨው ይህ ወሬ «አፍሪካ ኢንተለጀንስ»ን ዋቢ ቢያደርግም፣ ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ ግን ስለ ጄነራሉ መታገት የተጠቀሰ ነገር የለም።
​ኢትዮጵያ ቼክ በቀጥታ ለጄነራል ታደሰ ወረደ በስልክ ደውሎ የጠየቀ ሲሆን፣ ጄነራሉም፦ "እኔ አልታገትኩም፣ የቁም እስረኛም አልተደረግኩም፤ የAfrica Intelligence ዘገባ ላይም ይህ አልተገለጸም" በማለት መረጃውን አስተባብለዋል።
​በመሆኑም ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቀቁ መሰል የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ከመጋራታቸው በፊት በትዕግስት ምንጫቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

29/05/2026

አዲስ መረጃ 🚫
በትግራይ ክልል ለረጅም ጊዜ የተጣለው የፌደራል መንግስቱ የነዳጅ እገዳ እና የአቅርቦት ቅነሳ በትራንስፖርት፣ በሕክምና እና በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሎ የክልሉን መንግስት ሲያሰማድር ቆይቷል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የዶክተር ደብረጽዮን አስተዳደር ባለፈው ሳምንት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ግን በትላንትናው ዕለት አዲስ ተስፋ የሚሰጥ እርምጃ ታይቷል። በትግራይ አመራሮች እና በኤርትራ መካከል ቀደም ሲል ከተደረገው የኤርትራን ወደብ የመጠቀም "ፅምዶ" ስምምነት ተጨባጭ ውጤት እንደሆነ በሚገመት ሁኔታ፣ ነዳጅ ከአሰብ ወደብ ተነስቶ በድንበር ከተማዋ ዓዲ ዳዕሮ በኩል ወደ ትግራይ ከተሞች መግባት ጀምሯል፤ ይህም ለክልሉ ትልቅ እፎይታን ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

29/05/2026

አዲስ መረጃ 🚫
በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ የተገነባውና "በረዋቅ" የተሰኘው ዘመናዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለምረቃ ተዘጋጅቷል። ይህንን ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ የትምህርት ተቋም የቀድሞው የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተለያዩ ተቋማትንና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን በማስተባበር በትውልድ አካባቢያቸው ያስገነቡት ታሪካዊ ስጦታ ነው።
ትምህርት ቤቱ ትምህርትን በዲጂታልና በርቀት ለመስጠት የሚያስችሉ (LED) ስክሪኖች፣ ስማርት ቤተ-መጻሕፍት፣ የተሟሉ ላቦራቶሪዎች፣ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም የእግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን ያካተተ ነው። የትምህርት ጥራትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅም በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከ40 እንዳይበልጥ ተደርጎ የተዋቀረ ሲሆን፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለትውልድ ባበረከቱት በዚህ የማይጠፋ የልማት አሻራ ትልቅ ምስጋና እና አድናቆት ተችሯቸዋል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A.B.C news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to A.B.C news:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share