Iftu Anwar

Iftu Anwar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Iftu Anwar, Addis Ababa.
(3)

የልብ ብርሃን ማለት የሀገርን ከፍታ አስቀድሞ የማየት፣ በፈተናዎች ውስጥ እንኳ የተስፋን ጎህ አሙቆ የመጠበቅ፣ እንዲሁም የትናንትናውን ክብር ከነገው ታላቅነት ጋር የሚያገናኝ የመንፈስ ጥንካሬ...
31/07/2026

የልብ ብርሃን ማለት የሀገርን ከፍታ አስቀድሞ የማየት፣ በፈተናዎች ውስጥ እንኳ የተስፋን ጎህ አሙቆ የመጠበቅ፣ እንዲሁም የትናንትናውን ክብር ከነገው ታላቅነት ጋር የሚያገናኝ የመንፈስ ጥንካሬ ነው።

የብርሃናማ ልብ ባለቤቶች ሀገራቸውን ሲመለከቱ ድክመቷንና ቁስሏን ብቻ ሳይሆን፣ ጥበቧን፣ ጽናቷንና እምቅ አቅሟን ያያሉ።

ልበ ብርሃኖች የታሪክ ባለዕዳ ሳይሆኑ የታሪክ ባለቤቶች ናቸው። ምክንያቱም፣ የትናንትናውን የተከበረ ታሪክ እያሰቡ፣ የዛሬውን ፈተና በጽናት እየተጋፈጡ፣ ነገን በብሩህ ተስፋ የሚገነቡ አርቆ አሳቢዎች ናቸውና!

እኛም ልባችንን አጥርተንና በፍቅር ሞልተን፣ የሀገራችንን ሉዓላዊነትና ጥቅሟን አስቀድመን የኢትዮጵያን ከፍታ በጋራ እናረጋግጣለን!

የአገር ህልውና፣ ልማት እና ዘላቂ ሰላም የሚፀናው በህዝብ እና በመንግስት መካከል ባለው ፅኑ እምነት ላይ ነው። ይህንን እምነት ከስሩ የሚሸረሽረው እና የመንግስትን የበጎ ጥረቶችና የፖሊሲ ስ...
29/07/2026

የአገር ህልውና፣ ልማት እና ዘላቂ ሰላም የሚፀናው በህዝብ እና በመንግስት መካከል ባለው ፅኑ እምነት ላይ ነው።
ይህንን እምነት ከስሩ የሚሸረሽረው እና የመንግስትን የበጎ ጥረቶችና የፖሊሲ ስኬቶችን የሚያጠለሽ ዋናው አደጋ ስር የሰደደ ሌብነት፣ የሙስና ሰንሰለት እና የሀብት ብክነት ናቸው።

ሙስና የወንጀሎች ሁሉ መነሻ፣ የህግ የበላይነት ጠላት እና የዜጎችን ተስፋ የሚያጨልም አገራዊ ስጋት በመሆኑ፣ ይህንን ስር የሰደደ ችግር በመሰረቱ ለመቅረፍ እና የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ገለልተኛና ጠንካራ የፍትህ ስርአት በመገንባት በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለን ጥፋተኛ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለህግ ማቅረብ እና Zero Tolerance በተግባር ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

በተጨማሪም አዳዲስ የታክስ፣ የፋይናንስ እና የፖሊሲ ለውጦች ከመተግበራቸው በፊት ለሌብነት በር እንዳይከፍቱ ጥብቅ ጥናት ማድረግ፣ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አሰራር በመተካት የሰውና የሰው ንክኪን መቀነስ እንዲሁም የአገር ሀብትና በጀት በቁጠባ ስርአት በመጠቀም ቅድሚያ ለዜጎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ለኑሮ ውድነት ማቃለያ፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለጤና እና ለትምህርት ጥራት ብቻ እንዲያውል ማድረግ ይገባል።

ኃላፊነትን በችሎታ፣ በስነ ምግባር እና በህዝብ አገልጋይነት ብቻ በመለካት ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት የተሸረሸረውን የህዝብ አመኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሶ ለመገንባት ያስችላል።

በአጠቃላይ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመቆጣጠር በፅኑ አገራዊ ቁርጠኝነት፣ በጠንካራ መዋቅራዊ ስርዓትና እና ለህግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ በመገዛት ብቻ ሲሆን፣ አገራዊ አንድነት፣ ወንድማማችነት እና የብልፅግና ጉዞ ፍሬ የሚያፈራው ተቋማት ከሌብነትና ብልሹ የአሰራር ስርዓት ፅዱ እና ሰው ተኮር ስራዎች በተጨባጭ ወደ መሬት ማውረድ ሲቻል ነው።

ወደ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ለምናደርገው ጉዞ የመፍትሔው መነሻ በጋራ ሀገራዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ውይይት ነው። ይህም የምህረትና የአንድነት መንፈስን በማጠናከር፣ የህዝብን ባለቤትነትና ባ...
28/07/2026

ወደ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና ለምናደርገው ጉዞ የመፍትሔው መነሻ በጋራ ሀገራዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ውይይት ነው።

ይህም የምህረትና የአንድነት መንፈስን በማጠናከር፣ የህዝብን ባለቤትነትና ባለአደራነት በተግባር ያረጋግጣል።
ይህ የአንድነት መንፈስ ከመንግስት የልማት እቅዶችና ጥረቶች ጋር ሲቀናጅ የሀገራችንን የእድገት ጉዞ ያፋጥነዋል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ የጽናትና የስራ ወዳድነት ባህልን በማጎልበት፣ የፈጠራ አቅምን በማበልፀግ፣ የውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ፣ እንዲሁም በመከባበርና ፍትህን በማስፈን በኩል በቅንጅት የበኩላችንን ድርሻ ስንወጣ፤ ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለነገውም ትውልድ የምትሻገር ጽኑና የበለፀገች ሀገርን ለመገንባት የሚያስችል ወርቃማ መሰረት ነው።

ዛሬ የገጠሙን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ስር የሰደዱ የመዋቅራዊ ስብራቶች ውጤት ናቸው። አሁን እየተወሰዱ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ ሀገራችንን ከጥገኝነት በማውጣት በራሷ አቅም እንድትቆም እና ዘላቂ...
27/07/2026

ዛሬ የገጠሙን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ስር የሰደዱ የመዋቅራዊ ስብራቶች ውጤት ናቸው።
አሁን እየተወሰዱ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ ሀገራችንን ከጥገኝነት በማውጣት በራሷ አቅም እንድትቆም እና ዘላቂ እድገት እንድታስመዘግብ የሚያደርግ ዘላቂ መፍትሄ ነው።
ማንኛውም መዋቅራዊ ሽግግር ጊዜያዊ ጫና ያለው በመሆኑ፣ የዛሬው ፈተናችን ጊዜያዊና ለነገዋ ጠንካራ ኢትዮጵያ የሚከፈል ዋጋ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በህዝብና የመንግስት ጠንካራ ትስስር፣ በፅናትና በጋራ ጥረት ይህንን ሽግግር አልፈን የጋራ ብልጽግናችንን እውን እናደርጋለን።

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

Rakkooleen har’a nu mudatan bu'aa rakkoolee caasaa kaleessaa hidda fageeffataniiti.

Tarkaanfiiwwan amma fudhatamaa jiran, Biyya keenya hirkattummaa irraa bilisa gochuun, dandeettii mataa sheetiin akka dhaabbattuu fi guddina waaraa akka galmeessitu kan taasisudha.

Riifoormiin kamiyyuu dhiibbaa yeroo kan qabu waan ta'eef, qormaanni har'aa yeroo gabaabaaf kan turuu fi Itoophiyaa cimaa boruutiif gatii kaffalamu ta'uu isaa hubachuun barbaachisaadha.

Tumsa cimaa Ummataa fi Mootummaan, cichoominaa fi tattaaffii waliiniitiin qormaata yeroo kana ceenee Badhaadhina waloo keenya ni dhugoomsina.

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ዘመነ ብዙ የፈተና ማዕበሎችን ተሻግራ ለዛሬዋ ታላቅነቷ የበቃች የጽናት ምድር ናት። ዛሬም ቢሆን የሚያጋጥሙን ጊዜያዊ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፈተናዎች፣ የህ...
26/07/2026

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ዘመነ ብዙ የፈተና ማዕበሎችን ተሻግራ ለዛሬዋ ታላቅነቷ የበቃች የጽናት ምድር ናት።

ዛሬም ቢሆን የሚያጋጥሙን ጊዜያዊ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፈተናዎች፣ የህዝባችንን የተፈጥሮ ጥንካሬ እና የነገ ተስፋ ከቶውንም ሊያደክሙት አይችሉም።

ይልቁንም ህዝባችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተሰለፈበት የምርጫ መስመር ካርዱን ሰጥቶ የራሱን መንግስት በመምረጥ ያሳየው ጽኑ እምነት እና የባለቤትነት ስሜት፣ ዛሬም በመንግስት እና በህዝብ መካከል ላለው ጠንካራ ትስስር እና የጋራ ቁርኝት ህያው ምስክር ነው።

በፈተናዎች ውስጥ አልፎ በተስፋ የተኮተኮተው ይህ ጽኑ አንድነታችን፣ አሁንም ሀገራችንን ወደፊት የሚያስፈነጥር እና ተስፋዋን የሚያለምልም ታላቅ ሀይል ነው። በአካባቢያችን ሰላም ሲፀና አምራቹ ወደ ማሳው፣ ሸማቹ ወደ ገበያው፣ ሰራተኛው ደግሞ ወደ ስራው በሙሉ ተስፋ እና ፍላጎት የመንቀሳቀስ አቅሙ ይጎለብታል።

ምክንያቱም፣
መንግስት ለዘላቂ ብልጽግና የጣለው ጠንካራ መሰረት እና በምርጫ ካርዱ ባለቤትነቱን ያረጋገጠው የህዝባችን ጽናት ሲቀናጁ አሁን ያሉብንን ጊዜያዊ ፈተናዎች በሙሉ በድል ማሸነፋችን አይቀሬ ነውና!

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

ላለፉት አምስት አሥርተ ዓመታት በለመለመ ተስፋ ስም የሕዝቡን እንባና ደም ለገዛ የፖለቲካ ሕልውናቸው መጠበቂያ ሲጠቀሙበት የኖሩ አካላት የተሸከሙት ጭንብል ዛሬ ላይ ተገፎ ወድቋል። ትውልድን ...
25/07/2026

ላለፉት አምስት አሥርተ ዓመታት በለመለመ ተስፋ ስም የሕዝቡን እንባና ደም ለገዛ የፖለቲካ ሕልውናቸው መጠበቂያ ሲጠቀሙበት የኖሩ አካላት የተሸከሙት ጭንብል ዛሬ ላይ ተገፎ ወድቋል።
ትውልድን ለይስሙላ ጦርነት ማገዶ በማድረግ፣ እናቶችን የሐዘን ማቅ አልብሰው፣ ሕፃናትን ከትምህርት ገበታቸው ነጥለው፣ ሕዝቡን ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ለመነጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ባይኖርም፣ የትግራይ ሕዝብ ደኅንነቱ፣ ልማቱ እና ብሩህ ተስፋው በጽኑ የተሳሰረው ከቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ወንድምና እህቶቹ ጋር በሰላም፣ በፍትሕ እና በወንድማማችነት በመኖር ላይ ብቻ መሆኑን በውል ተረድቷል።በመሆኑም የወደፊቷ ትግራይ የጦርነትና የሴራ መደበቂያ መሆኗ አብቅቶ፤ የምክክር፣ የሰላምና የልማት ምድር መሆኗ ያለምንም መጠራጠር እውን የሚሆንበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።

ምክክር እና የሰለጠነ ንግግር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተሰጡ ታላላቅ ጸጋዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ሀሳብ ከሀሳብ ሲገናኝ፣ የልብ በሮች ተከፍተው መግባባት ሲነግሥ፣ ሁከትና ግጭት ቦታቸውን ...
23/07/2026

ምክክር እና የሰለጠነ ንግግር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተሰጡ ታላላቅ ጸጋዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ሀሳብ ከሀሳብ ሲገናኝ፣ የልብ በሮች ተከፍተው መግባባት ሲነግሥ፣ ሁከትና ግጭት ቦታቸውን ለዕርቅና ለዕድገት ይለቃሉ።
ምክክር ቀለል ያለ የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የመንፈስ ትስስር፣ የጥበብ ምንጭ እና ጨለማን የሚገፍ የብርሃን ጭላንጭል ነው። ከበሰሉ ልቦች ጋር የሚደረግ የሰከነ ምክክር ደግሞ፣ አቅጣጫን ያሳያል፣ ጭንቀትን ያቃልላል፣ የተበላሹ ውሳኔዎችን ያስተካክላል።
በሀገር ደረጃ ደግሞ የምክክርና የንግግር ጠቀሜታ ከማንኛውም ነገር በላይ የጎላና የህልውና ጉዳይ ነው።
ሀገር የተለያየ ባህል፣ እይታና ፍላጎት ያላቸው ህዝቦች ስብስብ እንደመሆኗ፣ እነዚህን ልዩነቶች በፍቅርና በስልጣኔ ማስተናገድ የሚቻለው በውይይትና በምክክር ነው። ንግግር በጠፋበት ቦታ ሁሉ የሀሳብ ድህነት ይነግሳል፤ ሀሳብን በሃይል ለመጫን መሞከር ደግሞ የሀገርን መሰረት ያናጋል።
በአንፃሩ፣ ቁጭ ብሎ መነጋገር፣ የሌላውን እይታ በሰከነ መንፈስ ማደመጥ፣ እንዲሁም በጋራ እውነት ላይ መስማማት አገርን ከጥፋት የሚያድን ቁልፍ መፍትሔ ነው።
በአጠቃላይ፣ ምክክር የጥበበኞች መንገድ፣ የጠንካሮች ምልክት እና የሰላም መሰረት ነው። በሰዎች መካከል መከባበርን ይፈጥራል፤ ጥላቻን በፍቅር ይተካል፤ እንዲሁም የማይፈቱ የሚመስሉ የታሪክና የህይወት ውጣ ውረዶችን ያቃናል።
በመሆኑም በቤታችን፣ በስራ ቦታችንና በሀገራዊ ጉዳያችን ሁሉ ንግግርንና ምክክርን እንደ ቀዳሚ የህይወት መመሪያችን ብናደርገው፣ የጸና ህይወትንና የበለፀገች ሀገርን መገንባት እንችላለን።

ከ2010 ዓ.ም መጨረሻ አከባቢ ጀምሮ በኦሮሚያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) በነበረኝ የመጀመሪያ የሥራ ቅጥር፣ በይዘት አዘጋጅና የሚዲያ ሞኒተሪንግ እንዲሁም የፓርቲውን እሳቤዎች፣ መርሆዎችና እ...
22/07/2026

ከ2010 ዓ.ም መጨረሻ አከባቢ ጀምሮ በኦሮሚያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) በነበረኝ የመጀመሪያ የሥራ ቅጥር፣ በይዘት አዘጋጅና የሚዲያ ሞኒተሪንግ እንዲሁም የፓርቲውን እሳቤዎች፣ መርሆዎችና እሴቶች የሚያጎሉ ስትራቴጂካዊ መልእክቶችን በመቅረጽ ለሀገር ግንባታ አስተዋፅኦ ያበረከትኩበት፣ ከዚያም በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት በፕሮቶኮል ኦፊሰርነት፣በትሎሚ የወርልድ ባንክ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሮጀክት እንዲሁም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እያገለገልኩ እስካለሁበት ጊዜ ድረስ እና ባሳለፍኳቸው የስራ አጋጣሚዎች የተረዳሁት ትልቅ እውነት ቢኖር፣ በጽኑ እምነት ከተጓዙ የማያልፍ ፈተና፣ የማይሻገሩትም የተራራ ግድግዳ የለም! እነዚህ በፈተናዎችና በድል የተሞሉ ጊዜያቶች በየቀኑ አዲስ እውቀት የምቀስምባቸው፣ ውስጣዊ ጥንካሬዬንና የሙያ ብቃቴን የገነቡልኝ የታላቅ የሕይወት ትምህርት ቤት በሮቼ ነበሩ።

ምክንያቱም በየትኛውም ስራና የኃላፊነት ቦታ ላይ አጽንቶ ሊያቆመን የሚችለው የጠነከረ የስራ ሥነ ምግባራችን፣ የሙያ ብቃታችንና በላባችን የምናስመዘግበው ተጨባጭ ውጤት እንጂ በዘፈቀደ የሚሰጥ ዕድል አይደለም፤ ዕድል በበራችን ቢመጣ እንኳ፣ ያንን ዕድል አጽንተን ማቆየት የምንችለው በትጋታችንና ባልተቆጠበ ጥረታችን ውጤት ብቻ ነውና!

ህይወታችንን ከጊዜያዊ የጥቅም ትስስሮች ጋር ሳናያይዝ፣ እውቀታችንንና ወርቃማ ጊዜያችንን ሳናባክን፣ አርቀን በማሰብና ለህይወታችን ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በጸና አላማና ቁርጠኝነት ወደፊት መጓዝ ይጠበቅብናል የዛሬው መልዕክቴ ነው።

በመጨረሻም፤ ሕይወት በፈተና እሳት ውስጥ አልፋ እንደሚወጣ ወርቅ እንደመሆኗ መጠን፣ ያንን እሳት ታግሣችሁ፣ ምሬቱን በጽናት አሸንፋችሁ፣ የጨለማውን መጋረጃ ጥሳችሁ የራሳችሁን አዲስ ታሪክ የጻፋችሁ የብርሃን ባለቤቶች፤ እንዲሁም ተስፋ ሳትቆርጡ፣በየዕለቱ ከእሾሃማው የሕይወት ጎዳና ጋር እየታገላችሁ፣ ታሪካችሁን በላባችሁና በደማችሁ ለመቀየር በጽናት እየተጋችሁ ላላችሁ ብርቱ ሕልመኞች ሁሉ! ምሳሌዎቻችን ናችሁና!

ላቅ ያለ ምስጋና እና ክብር አለኝ!

ማንነታችን የተገነባበትና ታሪካችን የጸናበት ዋናው መሰረት እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ በጋራ በመቆምና በችግር ጊዜ እጅ ለእጅ በመያያዝ ነው። ዛሬ ላይ ሊያንበረክከን የሚችለው ብቸኛው እውነተኛ...
21/07/2026

ማንነታችን የተገነባበትና ታሪካችን የጸናበት ዋናው መሰረት እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ በጋራ በመቆምና በችግር ጊዜ እጅ ለእጅ በመያያዝ ነው።
ዛሬ ላይ ሊያንበረክከን የሚችለው ብቸኛው እውነተኛ ተፎካካሪያችንም ሆነ ልንጥለው የሚገባው ድህነት፣ ኋላቀርነትና የተዛባ አስተሰብ ናቸው።
በህዝቦች መካከል አለመተማመንን፣ ጥላቻንና መገፋፋትን ማንገስ የትኛውንም ማህበረሰብ ከጥፋትና ከውድቀት በስተቀር ወደ ስኬት ማድረስ አይችልም። ጦርነት፣ ግጭትና ጥፋት አሸናፊ የሌላቸው፤ በመጨረሻም የጋራ ቤታችንንና የነገውን ተስፋችንን የሚያጨልሙ ከንቱ መንገዶች ናቸው። ይልቁንም፣መንግስት የሚያሳየው ጥልቅ ትዕግስትና ሰፊ ልብ፣ ከህዝቡ ጥበብ፣ አስተዋይነትና የሰላም ናፍቆት ጋር ሲጋባ፣ ማንኛውንም ውስብስብ ችግር በውይይትና በበሰለ መንገድ የመፍታት ታላቅ ሀይል ይፈጠራል።ሆኖም ግን፣ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ሁለንተናዊነት የሚደረጉ የሰላም ጥሪዎችና የበጎ ፈቃድ እርምጃዎች የስልጣኔና የጥበብ እንጂ የድክመት ምልክቶች አይደሉም። በእነዚህ መልካም አጋጣሚዎች ላይ በቅንነት ከመሰለፍ ይልቅ፣ በውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ልዩ ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላትን አጀንዳ በመያዝ የጥፋት መንገድን መከተል በመጨረሻም የሚጎዳው የጠቅላላውን ማህበረሰብ ታሪክ፣ የኢኮኖሚ መሰረትና የነገ ተስፋ ነው። የገቡትን ስምምነቶችና የሰላም ቃሎችን በተግባር አለመተርጎም፣ ለውጭ ጣልቃ ገብነት በር ከፍቶ የሁላችንንም የጋራ መኖሪያ የጥቅም መጋደያ አውድማ ከማድረግ ውጭ ምንም የሚያስገኘው በጎ ውጤት የለምና የእነዚህን ተፈጥሯዊና ማህበራዊ መሰናክሎች ግድግዳ አፍርሰን፣ አቅማችንንና አእምሮአችንን ወደ እውነተኛው የእድገትና የብልጽግና ትግል ማዞር የህልውናችን መሰረትና የዘላቂ ስኬታችን ማረጋገጫ ነው!

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

ውቅያኖሶች በኃያላን ማዕበል ሲናወጡ፣ በርካታ አህጉራዊ ግዙፍ ተቋማት አውሎ ነፋሱን መቋቋም አቅቷቸው ሲረግፉ፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ግን ውጣ ውረዶችን ሁሉ ወደ እድልና...
20/07/2026

ውቅያኖሶች በኃያላን ማዕበል ሲናወጡ፣ በርካታ አህጉራዊ ግዙፍ ተቋማት አውሎ ነፋሱን መቋቋም አቅቷቸው ሲረግፉ፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ግን ውጣ ውረዶችን ሁሉ ወደ እድልና ብርታት በመቀየር፣ ማዕበሎችን ተሻግሮ ይኸው እንደ ግዙፍ ተራራ ቆሟል።
ይህ ተቋም የንግድ ጉዞ ብቻ አይደለም፤ የፅናት፣ የላቀ ብቃት እና የሀገር ፍቅር መገለጫ እንጂ! ላለፉት ስድስት አስርት ዓመታት፣ የሀገራችን የገቢና ወጪ ንግድ የደም ስር በመሆን፣ የኢኮኖሚውን ትንሳኤ በንቃት ደግፏል። ዛሬም የኢትዮጵያን የልብ ትርታ በዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች ላይ ሲያስተጋባ፣ የኩራታችን መገለጫ የሆነችው ባለሦስት ቀለሟ ሰንደቅ ዓላማችን በውቅያኖሶች ላይ በነፃነት ትውለበለባለች። ይህ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ ለአፍሪካም ኩራት የሆነ ህያው አርአያነት ነው።
ESL የዓለምን ወደቦች ከኢትዮጵያ ማዕዘናት ጋር እያገናኘ፣ ከባህር ባሻገር ያሉ ዕድሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማምጣቱን በሙሉ አቅም ቀጥሏል!

ይህ ሳምንት በፈተናዎች ውስጥ ስኬትን የምንቀዳጅበት፣ በጠንካራ ስራ ውጤትን የምናይበት እና የደስታ ማዕድ የሚሰናዳበት ይሁንልን።

መልካም ሳምንት!

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

Beyond the SEA!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Iftu Anwar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share