
22/07/2025
አስተማሪ ታሪክ!
ከማጣት በስተጀርባ ያለው በረከት!
አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በማዕበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩ ውስጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና አንድ ጎጆ ቤት ውስጥ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል።ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ... እየሮጠ ቢመለስም ጎጆውን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዶታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ጥለኃኝ ከቤተሰቦቼ ነጠልከኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኝለህ ብሎ አለቀሰ አማረረ ...
ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ... የመርከቡ ሶዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት ከዚያም ለመርከቡ ሰዎች ጠየቃቸው።
እንዴት አገኛቹኝ እዚህ አከባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣቹ አላቸው ...
መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዙረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭስ አየን እና እዚ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተን አገኘን አሉት ።
አቤት አምላኬ ለካ ከዚ መከራ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሽዋ ጎጆዬን ያፈረስከው ወደ ትልቁ ቤት ልትወስደኝ ነው አለ።
አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ግዜ መጠጋት ያለብንን አምላካችንን እንረሳልን ከዝያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን።
ያጣነውን የሰጠን ፈጣሪ አእምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን!