Ethio Press

Ethio Press Official FaceBook page of Ethio Press

15/08/2026
13/08/2026
"ሰራዊቱ በሰራው ህግ የማስከበር ሥራ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ዕቅድ ማክሸፍ ተችሏል" - ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማየምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ከምዕራብ ጎጃም ዞን...
30/07/2026

"ሰራዊቱ በሰራው ህግ የማስከበር ሥራ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ዕቅድ ማክሸፍ ተችሏል" - ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ

የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ከምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የስራ ኀላፊዎች ጋር ዞኑ ባከናወናቸው የህግ ማስከበር ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት በቀጣይ በጋራ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የሚያግዙ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል።

በመድረኩ የ302ኛ ኮር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል መላኩ ገላነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የፖለቲካ አመራሮችም ተገኝተዋል።

የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ክልሉ በ2015 ዓ.ም ገጥሞት ከነበረው የሰላም እጦት ችግር ተላቆ ሰላምን በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እያጸና መሆኑን ገልጸዋል።

የፌዴራል ተቋማትና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በቅንጅት በሰሩት የህግ ማስከበር ሥራ የታሪካዊ ጠላቶቻችን፣ የባዕዳንና የባንዳ ዕቅድ መክሸፉን ገልጸዋል።

እንደ ዋና አዛዡ ገለጻ፣ የጸጥታ መዋቅሩ የጽንፈኛውን ኃይል አከርካሪ በመስበርና እግር በእግር ተከትሎ በመምታት የክልሉን ህዝብ ሰላም ለማረጋገጥ እየሰራ ነው። ጥምር የጸጥታ ኃይሉ በከፈለው ዋጋም ክልሉ በሁለት እግሩ ቆሞ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ መዋቅር መዘርጋቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ ህዝብና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የጀመረው የህግ ማስከበር ተልዕኮ አስተማማኝ ሰላም እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዕድሜዓለም አንተነህ በበኩላቸው፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሉ የዞኑን ሰላም በአስተማማኝ ደረጃ ለማጽናት ሰፊ ሥራ መሥራቱን ገልጸዋል።

የዞኑ ህዝብ ለሰላምና ለልማት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ዕድሜዓለም፣ አስተዳደሩ አስተማማኝ ሰላም በማጽናት፤ ልማትንና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

21/07/2026
ምን ይላል? ተርጉምልኝማ!
20/07/2026

ምን ይላል? ተርጉምልኝማ!

13/07/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share