
16/06/2022
የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገራት ጋር ባለው የተለያዩ ግንኙነቶች ላይ ጫና የማሳደር የትዊተር ዘመቻዎች
June 16, 2022
ትዊተር በኢትዮጵያ በዋነኝነት በአንድ በኩል መንግስትን ኢላማ ላደረጉእናበሌላ በኩል መንግስትን ለወገኑ ፖለቲካዊ ዘመቻ ፉክክሮች መድረክ ሆኖ ይገኛል። ዘመቻዎቹ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ጫናዎች ለማሳደር የሚካሄዱ ናቸው። ይህንንም ጫና ለመፍጠር ከመንግስት እስከ የሚዲያ አካላት፣ ከበይነ መንግስታት እስከ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አመራሮች እና ተቋማት ላይ የተለያዩ ዘመቻዎቹ ሲካሄዱ ቆይተዋል። በዚህ ሪፖርት የሚዳሰሰው በተለያዩ ሀገራት በመንግስት አካላት ላይ ትኩረት አድረገው የተካሄዱ የትዊተር ዘመቻዎች ሲሆኑ አጠቃላይ ዘመቻዎቹ ኢላማ ካደረጓቸው አካላት መካከል የመንግስት አካላት የአንበሳውን ድርሻ ሸፍነው ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታዎች ላይ መንግስትን ኢላማ በማድረግ እና መንግስትን በመወገን ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄዱ ከ261 ሺህ በላይ የትዊተር ዘመቻ ትዊቶች ላይ በጥናቱ ዳሰሳ ተደርጓል። መንግስትን ኢላማ ያደረጉ ዘመቻዎቹ ከዘመቻ ትዊቶቹ መካከል 210 ሺህ (80%) የሚጠጋ የሚሸፍኑ ሲሆን መንግስትን የሚወግኑት 51 ሺህ (20%) ያህሉን የዘመቻ ትዊቶች አሰተራጭተዋል። መንግስትን ኢላማ ያደረጉ ዘመቻዎቹ 3,900 በሚሆኑ የትዊተር አካውንቶች ትዊት ሲደረጉ መንግስትን የወገኑት በ2,300 ያህል አካውንቶች ተሰራጭተዋል። መንግስትን ኢላማ ያደረጉ ዘመቻ ያካሄዱት የትዊተር ተጠቃሚዎች ካላቸው የአካውንት የቁጥር ብልጫ በተጨማሪ በዘመቻዎቹ የተሳትፎ ቁርጠኝነት አሳይተዋል። ከዚህም አንጻር መንግስትን ኢላማ ያደረጉ ዘመቻ ተሳታፊዎች በአማካይ በአንድ አካውንት 54 ትዊቶች ሲያሰራጩ መንግስትን የሚወግኑ ዘመቻ አካውንቶቹ በአንድ አካውንት በእጅጉ ያነሳ በአማካይ 22 ትዊቶች ብቻ ትዊት አድርግዋል።
ትዊተር በኢትዮጵያ በዋነኝነት በአንድ በኩል መንግስትን ኢላማ ላደረጉእናበሌላ በኩል መንግስትን ለወገኑ ፖለቲካዊ ዘመቻ ፉክክሮች መድረክ ሆኖ ይገኛል። ዘመቻዎቹ በኢትዮጵያ መንግስ.....