MH 𝕖𝕟𝕥𝕖𝕣𝕥𝕒𝕚𝕟𝕞𝕖𝕟𝕥

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • MH 𝕖𝕟𝕥𝕖𝕣𝕥𝕒𝕚𝕟𝕞𝕖𝕟𝕥

MH 𝕖𝕟𝕥𝕖𝕣𝕥𝕒𝕚𝕟𝕞𝕖𝕟𝕥 𝖒𝖍 𝖊𝖓𝖙𝖊𝖗𝖙𝖆𝖎𝖓𝖒𝖊𝖓𝖙

በስንቱ/ Besintu EP 13 "የሩዝ ውሃ"  ይህ ሲትኮም የተለያየ እድሜ ያላቸውን ቤተሰቦች እርስ በርስ ግንኙነት በሃገር ውክልና የሚቀርብ ነው
08/10/2022

በስንቱ/ Besintu EP 13 "የሩዝ ውሃ" ይህ ሲትኮም የተለያየ እድሜ ያላቸውን ቤተሰቦች እርስ በርስ ግንኙነት በሃገር ውክልና የሚቀርብ ነው

ይህ ሲትኮም የአንድን ቤተሰብ የተለያየ የእድሜ ውክልና ያላቸውን ቤተሰቦች እርስ በርስ ግንኙነት በሃገር ውክልና ምሳሌ በማድረግ የሚቀርብ ሲትኮም ነው፡፡ በመሆኑም የሶስት ትውልድ ው.....

የ12ኛ ክፍል ተፈታኟ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወንድ ልጅ ተገላገለችአዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ድሬ...
07/10/2022

የ12ኛ ክፍል ተፈታኟ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወንድ ልጅ ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበች ተማሪ ወንድ ልጅ በሠላም መገላገሏ ተገለፀ።

ከቡርቃ ዲምቱ መሰናዶ ትምህርት ቤት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደበችው ተማሪ ጽጌረዳ አበራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ዩኒቨርሲቲ ከደረሰች በኋላ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

ተማሪ ጽጌረዳ አበራ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ወንድ ልጅ በሰላም መገላገሏን ነው የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ኮማንድ ፖስት ዘርፍ የህክምና ግብረ ሀይል አስተባባሪ ዶክተር ሁሴን መሀመድ የገለጹት፡፡

በአሁኑ ሰዓት እናትና የተወለደው ህፃን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡

በተሾመ ኃይሉ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች    | የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፊታችን መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ይሰ...
07/10/2022

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

| የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፊታችን መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በፈተና ማዕከላት (ዩኒቨርሲቲዎች) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ ለፈታኞች የተከለከሉ ነገሮችን ይፋ አድርጓል፡፡

ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮችም የሚከተሉት ናቸው ፡-

• ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ፣

• ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስቲኮች ይዞ መገኘት፣

• ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ ፣ ፎቶ የሚያነሳ ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይፓድ፣ ታብሌት ኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውንም ፎቶ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም፣

• በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም ፣

• ማንኛውም አደንዛዥ እጸች (ጫት፣ ሲጋራ፣ የሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም ፣

• ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም ፣

• ማንኛውም አይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፣ ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)፣

• ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት፣

• ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት፣

• በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም ፣

• በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተከሰተ የመሬት መደርመስ አደጋ የእናት እና ልጅ ህይወታቸው አለፈመስከረም 25/2015 (ዋልታ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ ጀር...
05/10/2022

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተከሰተ የመሬት መደርመስ አደጋ የእናት እና ልጅ ህይወታቸው አለፈ

መስከረም 25/2015 (ዋልታ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ጎተራ ወንጌላዊት ህንጻ ጀርባ ሌሊት 10:12 ሰዓት ላይ የመንገድ መደገፍያ ግንብ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ተደርምሶ በቤታቸው ተኝተው የነበሩ የ35 ዓመት እናት እና የ7 ዓመት ልጇ ወዲያው ህይወታቸው አልፏል።

የድጋፍ ግንቡ መፍረሱን ተከትሎ የኮብልስቶን መንገዱም መሰረቱ ጭምር ተደርምሶ በቤቱ ላይ በማረፉ አደጋውን አባብሶታል ተብሏል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የጸጥታ አባላት የሟቾችን አስከሬን ከፍርስራሽ ውስጥ ማውጣታቸው ተገልጿል።

በቤቶቹ ውስጥ የነበሩ አራት ሌሎች ሰዎች ከአደጋው አምልጠው ራሳቸውን ማትረፍ መቻላቸው ተጠቅሷል።

በአደጋው ሶስት መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ንጋቱ

🇳🇬 ናይጄሪያኩላሊት ሽጦ ለፍቅረኛው አዲስ iPhone የገዛው ግለሰብበናይጄሪያ ይህ ተማሪ የሆነ ግለሰብ ለፍቅረኛው አንዱን ኩላሊቱን በመሸጥ አዲስ iphone 14 Pro Max በመግዛት መነጋ...
05/10/2022

🇳🇬 ናይጄሪያ
ኩላሊት ሽጦ ለፍቅረኛው አዲስ iPhone የገዛው ግለሰብ

በናይጄሪያ ይህ ተማሪ የሆነ ግለሰብ

ለፍቅረኛው አንዱን ኩላሊቱን በመሸጥ አዲስ
iphone 14 Pro Max በመግዛት መነጋገሪ ሆኗል

😭😭😭የገዛ ባለቤቷ ቆራርጦ ገደሎ ሽንት ቤት ውስጥ የተገኘችው ሚስት አቤቱ ይቅር በለን😭🙏እህታችን አልማዝ እሸቱ ባለቤቷ ከዚህ በፊት ሰው ገድሎ ታስሮ ነበር እሷ ግን ብዙ ዓመት ሙሉ ባሌን ብ...
04/10/2022

😭😭😭

የገዛ ባለቤቷ ቆራርጦ ገደሎ ሽንት ቤት ውስጥ የተገኘችው ሚስት

አቤቱ ይቅር በለን😭🙏

እህታችን አልማዝ እሸቱ ባለቤቷ ከዚህ በፊት ሰው ገድሎ ታስሮ ነበር

እሷ ግን ብዙ ዓመት ሙሉ ባሌን ብላ ጠብቃው እስር ቤት እየሄደችም ትጠይቀውም ነበር

ከተፈትም በኃላ በፍቅር አብረው እየኖሩ

አንዳንዴ

ሲመታት ከቤት ስትወጣ
ሲደበድባት ከቤት ስትወጣ

በመጨረሻ በትልቅ ሽማግሌ ይቅርታ የመጨረሻ እድል ስጪን ብሎ ለምኖ ታርቆ

በታረቀ በ21ኛ ቀን በእለተ እሁድ ቤት ውስጥ ቆራርጦ ገድሏት ሽንት ቤት ደብቋት በስልኳ ለቤተሰቦቿ

ገዳም ሄዳለች ፀሎት ላይ ነች
እያለ መልእክት ይልክም ነበር

ነገር ግን ቤተሰቦቿ ወደ ቤት ሲሄዱ አልማዝን ሽንት ቤት ተቆራርጣ ሞቷ አግኝተው

እያለቀሱ በመራራ ህዘን ቀብረዋታል::

Via ቤተሰቦቿ

ነብስ ይማር

😭😭😭

1. የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ሲመጡ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው።  ምክንያቱም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ...
04/10/2022

1. የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ሲመጡ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው። ምክንያቱም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ያለው ትልቁ የህይወት ለውጥ ነው።

2. ፍርሃት የፈሪም የጀግናም መነሻ ነው። ፍርሃት ለፈሪ ጭንቀቱ ሲሆን፤ ለጀግና ደግሞ ጀብዱው ነው።

3. መማር ባለሙያ ያደርጋል፤ መኖር ደግሞ አዋቂ ያደርጋል።

4. ሰው የሆነውን የሚሆነው በአጋጣሚ አይደለም።አዋቂው ሰው ህፃኑ ልጅ በልጅ አዕምሮው የፃፈውን ተውኔት የሚተውን ተዋናይ ነው። የልጅ ጭንቅላት የተባለውን ይይዛል፤ አዋቂ ደግሞ የያዘውን ይተገብራል። አዋቂው ሲያለቅስ ወይም ሲያዝን እንደህፃን አባብይው።

5. ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው።ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋው ነው። ቢሆንም ግን ህይወት ተከታታይ መሆኗን መገንዘብ ይጠቅማል። ዛሬ የምንኖረው በትላንት ምክንያት ነው።

6. ሰው መሆን ማለት ራቁታችንን ከተወለድን በኋላ፤ ከልብስ ጀምሮ አካላችንን ከሚሸፍኑት ሽፋኖች መላቀቅ ነው። ሰው ሰውነቱን የሚያጣው ራቁቱን ከእናቱ ማህፀን ሰው ሆኖ ተወልዶ በማህበረሰብ፣ በልብስ፣ በትምህርት፣ ሃይማኖት፣ በብሔር የመሰሉ ግዑዛን አልባሳትን በመደረብ ነው።

7. እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣረና ስላልሞከረ ሳይሆን ለውጥ ሂደት እንጂ መድረሻ ስላልሆነ ነው።

8. ጎዳና ላይ የሚያድር ሰው ብርዱን ይለምዳል፣ ፀሃዩን ይታገሳል፣ አውሬ ያስለምዳል፤ ሰውን ግን ይፈራል። ቀኑን ሙሉ ብርድ ሳንፈራ ደረታችንን ገልጠን ራቁታችንን የምንውል ሰዎች፤ ልክ ሲመሽ የውጪ በር ቆልፈን፣ከዛ የሳሎን በር ቆልፈን፣ የጓዳ በር ቆልፈን፣ አልጋችን ውስጥ ገብተን ብርድልብስ ለብሰን፣ ብርድ ልብሱ እንዳይኮሰኩሰን አንሶላ ደርበን፣ አንሶላው እንዳይቀዘቅዘን የለሊት ልብስ ለብሰን ...በነዚህ ነገሮች ሁሉ ተከልለን እንተኛለን። ይህን እንዲሆን ደግሞ ያደረገው ፍርሃታችን ነው።

9. በታሪክ ውስጥ ትልቁ አምባገነን ታሪክ ራሱ ነው።ሁላችንም የታሪክ ተገዢዎች ነን።

10. የማታሸንፈውን ሰው ተጠያቂ ማድረግ የፈሪነት መፍትሔ ነው።

11. እውነት እኮ የጊዜና የቦታ ድምር ውጤት ነው። የራስን ሃሳብ ሌላው እንዲገባው ማድረግ ማለት ፤ የራሱን ሃሳብ ድንበር አልፈን የሃሳብና አስተሳሰብ ወረራ አካሄድን ማለት ነው።

12. የሚጠፋ ነገር ዐይንህ ስር ተቀምጦ ያለማየትን የመሰለ ዕውርነት የለም። አንዳንዴ ከሞት በኋላ ስለሚኖር መኖር እየጓጓን የውሸት ማመን የለብንም። ስለፀሎታችንን ምንነት በአንክሮ መፈተሽ ያስፈልጋል

13. ሰው የምታውቀው ፍጡር አይደለም። ሁልጊዜ ሰውን የምናውቀው ይመስለናል። እኔ ሐኪም ስከሆንኩና የአንድ ሰው አካል ቀድጄ ልቡን ስላየሁት ሰውን ያወኩት ይመስለኛል። ነገር ግን ሰው በየትኛውም ደረጃ የሚታወቅ ፍጡር አይደለም።

በደረቁ ሳይንስ አጥንተህ ሰው ውስጥ ያለውን ፕሮቲን እንዴት እንደሚሰራ ስላወቅህ ሰውን አውቃለሁ ማለት አይቻልም።

የመማር አንደኛው ችግር (በተለይ እኛ ሐገር) ቶሎ መታበይና የምናውቀው እውቀት እኛ ያመጣነው ሳይሆን ቀድሞ በሌሎች የተፈጠረ መሆኑን የመርሳት ችግር አለብን። እኛ ያወቅነው ከእኛ በፊት የመጡት የፈጠሩትን ነው። ይህንን እንረሳና እኔ ተምሬ ሳውቅ ራሴን አዋቂና ሐሳቡን እኔ የፈጠርኩት የመምሰል ችግር አለብን።

14. እያወቅክ ስትሔድ ትልቅልነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው የምትረዳው "

ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህን ያሰፋል። የእይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው የምትሄደው። ሰፊ ከሆነው ዓለም ውስጥ አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳለህ። እያወቅክ ስትሄድ ትልቅነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው የምትረዳው።

ደራሲ
ዶ/ር ወንድምአገኝ ዳዊት

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በመምሰል ተሽከርካሪ ተከራይተው በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን የወንጀል ድርጊት የፈፀሙ ግለሰቦች በፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በ...
03/10/2022

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በመምሰል ተሽከርካሪ ተከራይተው በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን የወንጀል ድርጊት የፈፀሙ ግለሰቦች በፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ 3 ግለሰቦች ወንጀሉን ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ መሞታቸው ይታወቃል፡፡
***
ወንጀሉ የተፈፀመው መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዩኒሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው ብዛታቸው 13 የሚሆኑ ግለሰቦች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 75549 ኦ/ሮ ሚኒባስ ታክሲ በመከራየት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መስለው ወ/ሮ እሌኒ ነጋሽ የተባሉ የግል ተበዳይን በማሳፈር ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ትርፍ ሰው ስለጫንን ትራፊክ እንዳይቀጣን አጎንብሺ በማለት ከቦርሳዋ ውስጥ 15 ሺ ብር የዋጋ ግምት ያለው ዘመናዊ ሞባይል ስልክ ሰርቀው ገፍትረው በማስወረድ ለማምለጥ ሞክረዋል፡፡
ተከሳሾቹ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ሲጓዙ ቆሞ ከነበረ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭተው አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለቱ ወንጀል ፈፃሚዎች በአደጋው ህይወታቸው ሲያልፍ የተቀሩት ተከሳሾች ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወቃል፡፡ በወቅቱ የተሰረቁ ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮች ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ተገኝተዋል፡፡ በወንጀል ፈፃሚዎቹ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት እና የምርመራ መዝገብ በማደራጀት መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል ልኮ ክስ እንዲመሰረት ማድረጉንም የአ/አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የተከሳሾቹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ተከሳሽ ገነት ጥላሁን ፣ ቃልኪዳን ስመኝ እና ሃይማኖት ቴዎድሮስ እያንዳንዳቸው በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም እንዳልካቸው ገሰሰ እና እዮብ ሰለሞን በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ዘገባ፡- ኢንስፔክተር እመቤት ሀብታሙ AA POLICE

አዲስ አበባ 👉 የሚዘጉ መንገዶች የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድን እንዲጠቀሙ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአ...
30/09/2022

አዲስ አበባ 👉 የሚዘጉ መንገዶች

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድን እንዲጠቀሙ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፦

👉 ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

👉 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

👉 ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ

👉 ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

👉 ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

👉 ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

👉 ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ

👉 በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ

👉 ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ

👉 ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ

👉 ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

👉 ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ

👉 ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ

ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ #ከዛሬ መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

**የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ**የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ። በዚሁ መሠረት...
28/09/2022

**የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ**

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል።

1. ቤንዚን በሊትር - 57 ብር ከ05 ሣንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም
3. ኬሮሲን በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም ሲሆን

4. በሥራ ላይ የነበረው ዋጋቸው ባለበት የሚቀጥል የነዳጅ ውጤቶች

4.1. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር - 76 ብር ከ87 ሣንቲም

4.2. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ89 ሣንቲም

4.3. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ06 ሣንቲም እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

እነዚህ ተሽከሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

Via:- EBC

በምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈአዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወ...
28/09/2022

በምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የትራፊክ አደጋው ከኢንጪኒ ከተማ ወደ ሽኖ ከተማ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝባ ማመላለሻ አውቶብስ ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ ነው የተከሰተው፡፡

በተፈጠረው አደጋም የ15 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ መሆኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም በ30 ሰዎች ላይ ከባድ እና በሀሉት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ-ስርዓት በነገው ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል - ኮሚቴውመስከረም 18 ቀን 2015 (ኢዜአ) የተወዳጁና ድምጸ መረዋው አርቲስት ማዲንጎ አፈ...
28/09/2022

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ-ስርዓት በነገው ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል - ኮሚቴው

መስከረም 18 ቀን 2015 (ኢዜአ) የተወዳጁና ድምጸ መረዋው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ሐሙስ መስከረም 19 ቀን 2015 በአዲስ አበባ አራት ኪሎ መንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈጸም የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው አስታወቀ።

የተወዳጁን የኪነጥበብ ሰው ሥርዓተ ቀብር ለማስፈጸም የተቋቋመው ኮሚቴ ጉዳዩን አስመልክቶ በአርቲስቱ በመኖሪያ ቤት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

አርቲስት አረጋኸኝ ወራሽ፥ የወንድማችን ህልፈት ድንገተኛ በመሆኑ ሀዘናችን መሪር ነው፥ በዚህ ሁኔታ መግለጫ መስጠትም ከባድ ነው ብሏል።

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅን በአጭር መግለጽ ከባድ ነው፤ በህይወት ዘመኑ የሰራቸው ተግባራት ግን ትውልድ የሚማርባቸው ይሆናሉ ሲል ገልጿል።

በነገው ዕለት የአስከሬን ስንብት በመኖሪያ ቤቱ በማድረግ በወዳጅነት ፓርክም ከ6፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በመንግስት ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት እንደሚካሄድ ገልጿል።

በመቀጠልም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ተናግሯል።

ጎልማሳው የጥበብ ሰው ማዲንጎ አፈወርቅ ስለ ፍቅር፣ ትዝታ፣ ባህል፣ ሀገር፣ ታሪክና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ መልዕክቶችን በተስረቅራቂ ድምጹ በማዜም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ስራ ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል።

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት መሆኑም ይታወቃል።

በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሀገር አዘዞ ተወልዶ በደብረታቦር ያደገው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አ...
25/09/2022

አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።

የአለም ትልቁ ፊት አቶ አባይነህ አበራ። አቶ አባይነህ አበራ 25 ሴ.ሜ የሚረዝም ፊታቸው የአለም ትልቁ ወይም ረዥሙ ፊት ነው። በዚህም ምክንያት የአፍሪካን ትልቁና ረዥሙ ፊት በሚል የአፍሪካ...
25/09/2022

የአለም ትልቁ ፊት አቶ አባይነህ አበራ። አቶ አባይነህ አበራ 25 ሴ.ሜ የሚረዝም ፊታቸው የአለም ትልቁ ወይም ረዥሙ ፊት ነው። በዚህም ምክንያት የአፍሪካን ትልቁና ረዥሙ ፊት በሚል የአፍሪካ የድንቃድንቆችን ክብረወሰን በመስበር የክብር የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡ አቶ አባይነህ አበራ የዳውሮ ዞን የማረቃ ወረዳ ነዋሪ ናቸው።

ተወዳጅ አልበም ነገ ይለቀቃልበቀድሞ ጃኖ ባንድ የምናዉቃት ተወዳጇ ድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ የሰራችዉን "ተወዳጅ" የተሰኘ ሙሉ አልበም በነገው ዕለት ይለቀቃል። የአልበሙን መለቀቅ በ...
23/09/2022

ተወዳጅ አልበም ነገ ይለቀቃል

በቀድሞ ጃኖ ባንድ የምናዉቃት ተወዳጇ ድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ የሰራችዉን "ተወዳጅ" የተሰኘ ሙሉ አልበም በነገው ዕለት ይለቀቃል።

የአልበሙን መለቀቅ በማስመልከት ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ቦስተን ዴይ ስፖ ሚድታወን ክለብ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ድምፃዊት ሃሌሉያ እንዲሁም በአልበሙ ላይ የተሳተፉት ዳዊት ተስፋዬ እና ኤንዲ ቤተ -ዜማ በጋራ በሰጡት ማብራርያ አልበሙ 13 ሙዚቃዎች የያዘ ሲሆን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት ያህል ፈጅቷል።

ነገ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተርኔት የሚለቀቀዉ ይኸው አልበም በቅርብ ደግሞ በሲዲ እንደሚለቀቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም በቅርቡ በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ ሀገራት ኮንሰርት ለማዘጋጀት ዕቅድ እንዳላት ድምፃዊት ሃሌሉያና ባልደረቦቿ ተናግረዋል ።

አሉር ኮሚኒኬሽን እና ሌክሶ ኢንተርቴይመንት በተለያዩ የመዝናኛ ዘርፎች ተሰማርቶ የሙዚቃ ኮንሠርቶችን ኤቨንቶች የማስታወቂያ ሥራዎች የሚሰራ ድርጅት ነው።

ድጋሚ እሺ ብላለች ዳጊ 🧐💍❤️የእውነተኛ ፍቅር ተምሳሌቶችቤቢ ና ዳጊ ❤️💍"ዘመናችሁ በፍቅር ይለቅ"አርቲስት ዳግማዊት ፀሐዬ            እናአርቲስት ሳምሶን ታደሰ10ኛ አመት የጋብቻ በ...
23/09/2022

ድጋሚ እሺ ብላለች ዳጊ 🧐💍❤️

የእውነተኛ ፍቅር ተምሳሌቶች

ቤቢ ና ዳጊ ❤️💍

"ዘመናችሁ በፍቅር ይለቅ"

አርቲስት ዳግማዊት ፀሐዬ

እና

አርቲስት ሳምሶን ታደሰ

10ኛ አመት የጋብቻ በዓል እሁድ መስከረም 15 ከቀኑ 6:00 ጀምሮ

ከብርሃን ልጆች ህጻናት እና አረጋውያን ጋር በድምቀት ያከብራሉ፡፡

እንዲህ

* ሰርጋችሁን
* የጋብቻ በዓላችሁን

* ከህፅናት
እና
* ከአረጋውያን

ጋር የምትካብሩ ፈጣሪ እናንተም ያክብራችሁ::

ዘመናችሁ ይባረክ

የእውነተኛ ፍቅር ተምሳሌቶች

❤️❤️❤️🙏🙏🙏

ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በሙሉ፦(መስከረም  13/2015 ዓ.ም) የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 17/2015 የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት ...
23/09/2022

ለሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በሙሉ፦

(መስከረም 13/2015 ዓ.ም) የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 17/2015 የሚከበረው የመስቀል በዓል በሰላም ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ተወስኗል።
በዚሁ መሰረት ከእሁድ መስከረም 15/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ኤጀንሲው ያሳውቃል። ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጭምር ኤጀንሲው ያሳስባል።

MH entertainment

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MH 𝕖𝕟𝕥𝕖𝕣𝕥𝕒𝕚𝕟𝕞𝕖𝕟𝕥 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share