አደይ ሚዲያ Adey Media

  • Home
  • አደይ ሚዲያ Adey Media

አደይ ሚዲያ Adey Media News feed

ሰን የተናገረው "ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የመጣሁት በሜሲ ምክንያት ብቻ አይደለም፤ በእርግጥ የእሱ እዚህ መኖር ወደ ሊጉ እንድመጣ ተፅዕኖ ነበረው።""ሜሲ የሊጉን ገፅታ ከፍ አድርጎታል።...
11/10/2025

ሰን የተናገረው

"ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የመጣሁት በሜሲ ምክንያት ብቻ አይደለም፤ በእርግጥ የእሱ እዚህ መኖር ወደ ሊጉ እንድመጣ ተፅዕኖ ነበረው።"

"ሜሲ የሊጉን ገፅታ ከፍ አድርጎታል። በተመሳሳይ መልኩ እኔም ተጽዕኖ ማሳደር እፈልጋለሁ። ከእሱ ጋር ለመጋፈጥ እና እሱ ሲጫወት ለማየት እጓጓለሁ።

ምፓፔ ጉዳት አስናገደፈረንሳይ አዘርባጃንን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ  1 ጎል እንዲሁም 1 አሲስት በማድረግ ደምቆ ያመሸዉ ኪሊያን ምፓፔ የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንዳጋጠመዉ ዲዲየር ዴሾ ተናግ...
11/10/2025

ምፓፔ ጉዳት አስናገደ

ፈረንሳይ አዘርባጃንን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ 1 ጎል እንዲሁም 1 አሲስት በማድረግ ደምቆ ያመሸዉ ኪሊያን ምፓፔ የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንዳጋጠመዉ ዲዲየር ዴሾ ተናግረዋል።

"ባለፈዉ የተጎዳበት ቁርጭምጭሚት ላይ ሌላ ጉዳት አጋጥሞታል፤እረፍት በሚያደርግ ጊዜ ህመሙ ይበልጥ ይቀንስለታል። በጨዋታዎች ወቅት ንክኪዎች ያጋጥማሉ" ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

በዚህም የተነሳ ምፓፔ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን ካምፕ በመልቀቅ ወደ ማድሪድ እንደሚሄድ ሌኪፕ ዘግቧል።

የባርሴሎናው ተጫዋች ዳኒ ኦልሞ በጉዳት ምክንያት ከ 3 እስከ 4 ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ተዘግቧል።
11/10/2025

የባርሴሎናው ተጫዋች ዳኒ ኦልሞ በጉዳት ምክንያት ከ 3 እስከ 4 ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ተዘግቧል።

"ማንቸስተር ዩናይትድ ለዮኬሬሽ ዝዉዉር ከፍተኛ ገንዘብ አቅርበዉ ነበር"የቪክተር ዮኬሬሽ ኤጀንት ስለ ተጫዋቹ ወደ አርሰናል እንዴት እንደተዘዋወረ እና ስለ ዝዉዉሩ ሂደት ተናግሯል።ኤጀንቱ ሲና...
11/10/2025

"ማንቸስተር ዩናይትድ ለዮኬሬሽ ዝዉዉር ከፍተኛ ገንዘብ አቅርበዉ ነበር"

የቪክተር ዮኬሬሽ ኤጀንት ስለ ተጫዋቹ ወደ አርሰናል እንዴት እንደተዘዋወረ እና ስለ ዝዉዉሩ ሂደት ተናግሯል።

ኤጀንቱ ሲናገር "ስፖርቲንግ ሊዝበን ሰዎች እኛ ሳናዉቅ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት ደርሰዉ ነበር፤ማንቸስተር ዩናይትድም ለዝዉዉሩ ከፍተኛ ገንዘብ አቅርቦ ነበር እና ዝዉዉሩ ከባድ የነበረዉ በዚህ ምክንያት ነዉ ።ሲል ተናግሯል።

ኤጀንቱ አክሎም " ምናልባት ሁጎ ቪየና(የቀድሞዉ የስፖርቲንግ ሊዝበን የስፖርት ዳሬክተር) ቢሆን ኖሮ ዮኬሬሽ ወደ አርሰናል የሚያደርገዉ ዝዉዉር በሰዐታት ዉስጥ ያልቅ ነበር"

"የስፖርቲንግ ሊዝበን ሰዎች ማድሪድ ተጫዋቹን እንዲያስፈርመዉ ጠይቀዉ ነበር ነገር ግን ተጫዋቹ ከመጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ አርሰናል ብቻ ነበር የሚፈልገዉ" ሲል ተናግሯል።

አውስትራሊያዊቷ በአንድ ሰዓት ውስጥ 733 ፑል አፕ በመሥራት ሪከርድ ያዘች*******እርስዎ ምን ያህል ፑል አፕ ይሰራሉ? አውስትራሊያዊቷ ጄድ ሄንደርሰን ከሰሞኑ 733 ፑል አፕ በመስራት አ...
10/10/2025

አውስትራሊያዊቷ በአንድ ሰዓት ውስጥ 733 ፑል አፕ በመሥራት ሪከርድ ያዘች
*******

እርስዎ ምን ያህል ፑል አፕ ይሰራሉ? አውስትራሊያዊቷ ጄድ ሄንደርሰን ከሰሞኑ 733 ፑል አፕ በመስራት አዲስ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ አስመዝግባለች።

ጄድ ሄንደርሰን ከዚህ ቀደም እ.አ.አ. 2016 ላይ በኢቫ ክላርክ 725 ፑል አፕ በመሥራት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ የግሏ ማድረግ ችላለች።

በአማካይ በአንድ ደቂቃ 12 ፑል አፕ የሰራችው ጄድ ሄንደርሰን በአንድ ወቅት ረጅም ሰዓታትን ፑል አፕ በመሥራት ሪከርድ ለመያዝ አቅዳ ጉዳት ደርሶባት ነበር።

አሁን ላይ ሪከርዱን በመስበሯ ደስተኛ መሆኗን ገልፃ ጠንክራ በመስራቷ ውጤቱን እንዳስመዘገበች መናገሯን ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ አስታውቋል።

'Messi IS The Solution' :Pep Guardiola🎙🇪🇸 ፔፕ ጋርዲዮላ:🗣 "ለ4 ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ እንዲሰሩት የሰጠኋቸው ስራ አንድ ተጫዋች ሁሉንም ጠቅልሎ ሲሰራው አይቼ በጣም ተ...
10/10/2025

'Messi IS The Solution' :Pep Guardiola🎙
🇪🇸 ፔፕ ጋርዲዮላ:🗣 "ለ4 ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ እንዲሰሩት የሰጠኋቸው ስራ አንድ ተጫዋች ሁሉንም ጠቅልሎ ሲሰራው አይቼ በጣም ተገረምኩ ማመን እንኳ አልቻልኩም።

መሀል ሜዳ ላይ ለዣቪና ኢኔሽታ የሰጠኋቸው ሚና ሊዮኔል ሜሲ መሀል ገብቶ እየፈፀመው ነበር... ከፊት ለሄነሪና ለሳሙኤል ኤቶ የሰጠኋቸውም ሚና ከፊት ሆኖ ሊዮኔል ሜሲ እየፈፀመው ነበር።

በቃ ኳስ በሄደበት ሁሉ እየሄደ ሊዮኔል ሜሲ ስራዎችህን አቅልሎ ይሰራልሀል... ሊዮኔል ሜሲ 10 የሚል ማሊያ ከኳስጋ ሁሉም የሜዳ ክፍል ስመለከተው እነ ዣቪ ኢኔሽታ የሜሲ ስም ያለበት ማሊያ ለብሰው ገብተው አይደለም አ ብዬ ተጠራጥሬ አይቻቸው አውቃለሁ።

ሜዳ ውስጥ ሊዮኔል ሜሲ ከያዝክ በትርፍ 4 ተጫዋቾች ወደ ሜዳ እደገባህ ያህል ይሰማሀል... ሊዮኔል ሜሲ ለቁጥር አንድ ተጫዋች የሚመስል ሜዳ ውስጥ ግን ብቻውን ብዙ ቁጥር ያለው ተጫዋች ነው።

በኔ ስር ከተጫወቱ ብቻ ሳይሆን እግርኳስ ከተጫወቱት ሁሉ በብዙ ነገር የተሻለ ድንቅ ተጫዋች ነው።

አልጄሪያ ለዓለም ዋንጫ አለፈች**********በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ 7 ላይ የነበረችው አልጄሪያ በ2026ቱ መድረክ መሳተፏን አረጋግጣለች።በምድቡ ዘጠነኛ ጨዋታ ዛሬ ሶ...
10/10/2025

አልጄሪያ ለዓለም ዋንጫ አለፈች
**********

በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ 7 ላይ የነበረችው አልጄሪያ በ2026ቱ መድረክ መሳተፏን አረጋግጣለች።

በምድቡ ዘጠነኛ ጨዋታ ዛሬ ሶማሊያን 3 ለ 0 ያሸነፈችው አልጄሪያ በ2026 ዓለም ዋንጫ መሳተፏን ያረጋገጠች 4ኛዋ የአፍሪካ ሀገርም ሆናለች።

ሞሮኮ፣ ግብጽ እና ቱኒዚያ ቀደም ብለው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሀገራት ናቸው።

የሩበን አሞሪም ጫና እና የሰር ጂም ራትክሊፍ ምላሽባሕር ዳር: መስከረም 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ 2025/2026 የውድድር ዘመን ማንቸስተር ዩናይትድ ካደረጋቸው ...
10/10/2025

የሩበን አሞሪም ጫና እና የሰር ጂም ራትክሊፍ ምላሽ

ባሕር ዳር: መስከረም 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ 2025/2026 የውድድር ዘመን ማንቸስተር ዩናይትድ ካደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች ሦሥት ጨዋታዎችን አሸንፏል።

በሦሥት ጨዋታዎች ተሸንፎ እና በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል። 10 ነጥብ በመያዝ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የሒሳብ ስሌት መሠረትም የቡድኑ ደጋፊዎች እና አንዳንድ መሪዎች አጀማመሩ ደካማ መኾኑን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የቡድኑን አጀመማር ተከትሎም ፖርቹጋላዊው የ40 ዓመት አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም ጫና ውስጥ ገብተዋል። አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንቸስተር ዩናይትድን ማሠልጠን የጀመሩት እ.አ.አ 2024 ነበር።

አሠልጣኙ አሁን ማንቸስተር ዩናይትድን ወደ አሸናፊነት የማያመጡ ከኾነ ሥራቸውን ይልቀቁ የሚሉ ድምጾች መበራከታቸውን ዴይሊ ሜይል ስፖርት አስነብቧል፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን ባለድርሻ ሰር ጂም ራትክሊፍ ቡድኑ እስካሁን ባለው ጉዞው ጥሩ የሚባል አይደለም፤ ከሰባት ጨዋታዎች በሦሥቱ ተሸንፏልና ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም አሞሪም ይሰናበቱ የሚሉ እንዳሉ አንስተዋል።

እርሳቸው ግን አሠልጣኙን ለማሰናበት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ አሠልጣኝ አሞሪም በሥራ ላይ ይቆያሉ ነው ያሉት፡፡ በዘላቂነት ጠንካራ እና ጤናማ ቡድን ይመሠርት ዘንድም የሦሥት ዓመታት ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚችልም ባለሃብቱ ጠቁመዋል።

የስካይ ስፖርት ተንታኝ ጄሚ ካራገር ” መባረር አለበት መባሉን አልወድም እኔ ግን የሩበን አሞሪም የቆይታ ጊዜ የሚወሰነው ቡድኑ በቀጣይ በሚኖረው ጨዋታ ውጤታማ በመኾን እና ባለመኾን ላይ ብቻ ነው" ብሏል፡፡

ውጤቱ ከአውሮፓውያን አዲስ ዓመት በፊት እንደሚታወቅም ገልጿል።

🎙️|  ቴሪ ሄንሪ ስለ አንትዋን ሴሜንዮ፡- "በቅርቡ አነጋግሬዋለሁ። አሁን እያደረገ ያለው ነገር የማይታመን እና አስደናቂ እንደሆነ ነግሬዋለሁ። እሱ የብቃቱ ጫፍ  ላይ ነው። እናም የአርሰና...
10/10/2025

🎙️| ቴሪ ሄንሪ ስለ አንትዋን ሴሜንዮ፡-

"በቅርቡ አነጋግሬዋለሁ። አሁን እያደረገ ያለው ነገር የማይታመን እና አስደናቂ እንደሆነ ነግሬዋለሁ። እሱ የብቃቱ ጫፍ ላይ ነው። እናም የአርሰናል ደጋፊ ነው።"

የሊቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ቡድኑ ከኬፕ ቨርዴ ጋር በነበረው ጨዋታ በቀላል ስህተት ግብ በተቆጠረበት ግብጠባቂዉ ላይ ምርመራ ከፍቷል።ባለዉ የመልክ መመሳሰል “የሮናልዶ ...
10/10/2025

የሊቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ቡድኑ ከኬፕ ቨርዴ ጋር በነበረው ጨዋታ በቀላል ስህተት ግብ በተቆጠረበት ግብጠባቂዉ ላይ ምርመራ ከፍቷል።

ባለዉ የመልክ መመሳሰል “የሮናልዶ መንትያ” እየተባለ የሚጠራዉ ግብጠባቂ የፈፀመው ስህተት በቀላሉ ኳሱ በእጁ እና በእግሩ መካከል እንዲንሸራተት በማድረግ ግብ እንዲቆጠርበትበት በማድረጉ ነዉ ተብሏል።

"የሰዉነት ክፍሉን ፎቶ እያነሳ ይልክልኝ ነበር"የቪኒሺየስ ጁኒየር ፍቅረኛ የነበረቺዉ ብራዚላዊቷ ሞዴል አና ሲልቫ ከቪኒሺየስ ጁኒር ጋር በነበረችበት ጊዜ ተጫዋቹን ባህሪ ተናግራለች።ሞዴሏ"ቪኒ...
10/10/2025

"የሰዉነት ክፍሉን ፎቶ እያነሳ ይልክልኝ ነበር"

የቪኒሺየስ ጁኒየር ፍቅረኛ የነበረቺዉ ብራዚላዊቷ ሞዴል አና ሲልቫ ከቪኒሺየስ ጁኒር ጋር በነበረችበት ጊዜ ተጫዋቹን ባህሪ ተናግራለች።

ሞዴሏ"ቪኒሺየስ ጁኒየር ስለ ወ*ሲ%ብ* ብቻ ነዉ ሚያስበዉ፤እኔ ከሰዎች ጋር መነጋገር እወዳለሁ ነገር ግን ስለ ባለጌ ነገሮች ማዉራት አልፈልግም። ቪኒሺየስ ግን መነጋገር አይወድም እሱ ሁሌም ንግግሩ ስለ ወ§ ሲ*%ብ እና ስለ ወ%ሲ×ብ ብቻ ነዉ" ስትል ተናግራለች።

በተጨማሪም ሞዴሏ" የሰዉነት ክፍሉን(እርቃኑን) ፎቶ ይልክልኛ፤የኔንም እንድልክለት ይጠይቀኛል" ስትል ገልፃለች።

ተጫዋቹ በዚህ ጉዳይ በኢንስታግራም ገፁ ድሪጊቱን መፈፀሙን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል።

😥🇦🇷 አርጀንቲናዊዉ ኮከብ ለጆርዲ አልባ:🗣"አመሰግናለሁ ጆርዲ🙏💞 በጣም ትናፍቀኛለህ። ብዙ ጊዜ አብረን ከሆንን በኋላ ግራ መስመር ላይ አንተን ማየት ነበር አሁን ግን እዚያ ስፍራ ሳትኖር ሳ...
09/10/2025

😥🇦🇷 አርጀንቲናዊዉ ኮከብ ለጆርዲ አልባ:🗣"አመሰግናለሁ ጆርዲ🙏💞 በጣም ትናፍቀኛለህ። ብዙ ጊዜ አብረን ከሆንን በኋላ ግራ መስመር ላይ አንተን ማየት ነበር አሁን ግን እዚያ ስፍራ ሳትኖር ሳይ በጣም ይገርመኛል ...እብዱ ስንት አመት አመቻችተህ አቀበልከኝ ..አሁንስ ማን ይመልስልኝ ይሆን...???።"

Address


Telephone

+251920721818

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አደይ ሚዲያ Adey Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share