
06/09/2023
በጳጉሜን ቀናት የተሰየሙት መሠረታዊ ሃሳቦች የድሬዳዋ መገለጫ እና መትጊያ ሆነው ያገለግላሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ገለጹ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
በአስተዳደሩ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚደረጉ ጥረቶች በጳጉሜን ቀናት ለማጠናከር በተደራጀ አግባብ በትኩረት እንደሚሰራም ክቡር ከንቲባው አክለዋል።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ክቡር ከንቲባው ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፤ በኢትዮጵያ ደረጃ በጳጉሜን ቀናት የተሰየሙት መሠረታዊ ሃሳቦች የድሬዳዋ መገለጫ እና መትጊያ በመሆን ያገለግላሉ ብለዋል።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
በአገልግሎት፣ በመስዋዕትነት፣ በበጎነት፣ በአምራችነት፣ በትውልድ እና በአብሮነት የተሰየሙት የዘንድሮ የጳጉሜን ቀናት በድሬዳዋ የህዝብን መሠረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተቀናጀ መንገድ ለመመለስ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማጠናከር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
ዛሬ በሁሉም ተቋማት የተሻለና የተቀናጀ የአገልጋይነት ቀን ተደርጎ ለህዝብ ነፃ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ አመልክተው፤ በትራንስፖርት ዘርፍ ለዜጎች ነፃ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።
ለሀገር ሉአላዊነትና ለዜጎች ነፃነት ታላቅ መስዋዕትነት የከፈሉትን ጨምሮ በየመስኩ ታላቅ ስራ ያከናወኑ ሰዎችን በማስታወስ ይከበራል ሲሉ ገልጸዋል።
የበጎነት ቀን በጎነት በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲሰርፅ በሚያግዝ መንገድ ይከበራል ብለዋል።
እንደ ክቡር ከንቲባ ከድር ገለፃ፤ ድሬዳዋ የንግድና የኢንዱስትሪ መናኸሪያ፤ የነፃ የንግድ ቀጣና መሆኗን በትክክል በሚያንፀባርቁ ሁነቶች የአምራችነት ቀን እንደሚከበርም ገልጸዋል።
በተለይ የአብሮነት ቀን የድሬዳዋ ልዩ ሃብት የሆነው የአብሮነትና የአንድነት መገለጫን በትውልድ ውስጥ እንዲሰርጽ በሚያስችሉ ልዩ ልዩ ክዋኔዎች እንደሚከበር አብራርተዋል።
Dire Dawa Mayor Office & Management