
29/03/2022
የኢትዮጵያ ስደተኞች በሳውዲ አረቢያ
በግልጽ ላልታወቁ ወራት በሳውዲ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በረሃብ፣ በወረርሽኝ እና በፍትህ እጦት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ በዜጎች ጥያቄዎች ቢቀርቡም ምላሽ ሲሰጥ አልተስተዋለም፡፡
በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ በሳውዲ ወህይኒ ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በነገው ዕለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ከ7 እስከ 11 ወራት ከ100 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሐገራቸው እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡
7 killo | ፯ ኪሎ ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የዩቱዩብ ፕሮግራም ነው።