Musilm Voice

Musilm Voice ኦላይን ሾፐ

17/10/2024

ኒቃብ አድርጋችሁ ኒቃቡን የማይመጥን ስራ የምትሰሩ እህቶች በእናተ መጥፍ ባህሪ የተንሳ ኢስላምን ባታሰደብ መልካም ነው ..... አሏህ ያሰተካከላችሁ እናተንም እኛንም .... መልካም አዳር 🥷

 #ሀረም &  #መዲና4 አዳዲስ የሐረመይን ኢማሞች ተጨምረዋል 🗣የሁለቱ ሐረሞች አስተዳደር ፕሬዝዳንት የሆኑት ሸይኽ ዶ/ር ዐብዱ-ር'ረሕማን ሱደይስ፤ መካህ ላይ ለመስጂደ-ል-ሐረም ሁለት አዲስ...
04/10/2024

#ሀረም & #መዲና

4 አዳዲስ የሐረመይን ኢማሞች ተጨምረዋል 🗣

የሁለቱ ሐረሞች አስተዳደር ፕሬዝዳንት የሆኑት ሸይኽ ዶ/ር ዐብዱ-ር'ረሕማን ሱደይስ፤ መካህ ላይ ለመስጂደ-ል-ሐረም ሁለት አዲስ ቋሚ ኢማሞችን፣ መዲናህ ላይ ለመስጂደ-ን'ነበዊይ 2 አዲስ ቋሚ ኢማሞችን መሾማቸው ዛሬ ተነግሯል።

መካህ ላይ ኢማም ተደርገው የተሾሙት ባለፈው ረመዿን ላይ ለተራዊሕና ለተሃጁድ ኢማምነት ተጋባዥ አሰጋጂ ተደርገው ሚሊዮን ሙስሊሞችን ያስደመሙት ሁለቱ ቃሪኦች ናቸው። የተከበሩ ሸይኽ በድር አ-ት'ቱርኪ እና ሸይኽ ዶ/ር ዋሊድ አል-ሸምሳን ናቸው።

መዲናህ ላይ አዲስ የተጨመሩት ኢማሞች ደግሞ ሸይኽ ዶ/ር ዐብዱ-ል'ሏህ አል-ቁራፊይ እና ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ በርሃጂይ ናቸው።

√ በዚህም የመስጂደ-ል-ሐረም ቋሚ ኢማሞች ስም ዝርዝር፦

1) Sheikh Abdul Rahman Al Sudais
2) Sheikh Saleh Bin Humaid
3) Sheikh Usamah Khayyat
4) Sheikh Faisal Ghazzawi
5) Sheikh Maher Al Muaiqly
6) Sheikh Abdullah Juhany
7) Sheikh Bandar Baleelah
8)Sheikh Yasir Al Dawsary
9) Sheikh Badr Al Turki
10) Sheikh Waleed Ash Shamsan

√ የመስጂደ-ን'ነበዊይ ቋሚ ኢማሞች ስም ዝርዝር፦
1) Sheikh Ali Hudaify
2) Sheikh Hussain Ale Sheikh
3) Sheikh Salah Al Budair
4) Sheikh Abdul Bari Thubaity
5) Sheikh Abdul Mohsin Al Qasim
6) Sheikh Abdullah Al Buayjan
7) Sheikh Ahmad Bin Talib Hameed
8)Sheikh Ahmad Hudaify
9) Sheikh Khalid Muhanna
10) Sheikh Abdullah Al Qurafi
11) Sheikh Muhammad Barhaji

አላህ ሁላቸውንም ይጠብቃቸው። እኛንም አላህ ወደቤቱ መመላለስን ያግራለን።

 #አባትነት ♥♥♥ገጠራማ  የቬትናም ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ ከተው ወንዙን አቋርጠው ወደ ትምህርት ቤት ያደርሳሉ።ወላጆች ይህን የሚያደርጉት ልጆቻቸውን ከውሃ በመጠበ...
29/09/2024

#አባትነት ♥♥♥
ገጠራማ የቬትናም ከተማ ወላጆች ልጆቻቸውን በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ ከተው ወንዙን አቋርጠው ወደ ትምህርት ቤት ያደርሳሉ።

ወላጆች ይህን የሚያደርጉት ልጆቻቸውን ከውሃ በመጠበቅ ትምህርት ቤት ልብሳቸው ደርቆ እንዲደርሱ እና እርጥብ እንዳይሆን ለማድረግ ና ብሩህ የሆነ የትምህርት ቀን እንዲኖራቸው ነው ። ይህን ድርጊት በየቀኑ ይፈፅማሉ #አባትነት

Hijra Tube ✍️

ይህ ከህግ ውጭ የተፈጸመ ወንጀል ብቻ አይደለም፤ ይህ ግልጽ የእስልምና ጥላቻም ጭምር ነው..! ሴትን ልጅ ደብድቦ መሬት ከጣለ በኃላ እንኳን የማይራራ አካል ዙሪያችንን ከቦናል። ያሳፍራል፣ ያ...
10/09/2024

ይህ ከህግ ውጭ የተፈጸመ ወንጀል ብቻ አይደለም፤ ይህ ግልጽ የእስልምና ጥላቻም ጭምር ነው..! ሴትን ልጅ ደብድቦ መሬት ከጣለ በኃላ እንኳን የማይራራ አካል ዙሪያችንን ከቦናል። ያሳፍራል፣ ያስቆጫል..!

የመጀመሪያው ትውልድ ለኃለኛው አንድም የተወው ነገር የለም🗣
10/09/2024

የመጀመሪያው ትውልድ ለኃለኛው አንድም የተወው ነገር የለም🗣

28/08/2024

ኮልፌ ቀብር ላይ ቁጭ ብላችሁ ጫት እና መስለ ንግሮችን የምታደርጉ ስዎች አሏህን አትፈሩም ውይ ከኢስላም የሚያስወጣ ተገባር ላይ ካልዘወተርን አላችሁ እሳ በተለይ ሴቶች 🗣️

አስቸኳይ ትብብር ስለመጠየቅ   ፖስፖርት መዲና ጠፋቶብኛል።መጥፈቱን ያወኩት ወደ መካ ከተመለስኩ በኃላ ስለነበር ወደ ተመልሼ ሆቴልና ሌሎች ቦታዎችም ሳፈላልግ ቆይቻለሁ አላገኘሁትም።ከጠፋ 3 ...
07/04/2024

አስቸኳይ ትብብር ስለመጠየቅ



ፖስፖርት መዲና ጠፋቶብኛል።መጥፈቱን ያወኩት ወደ መካ ከተመለስኩ በኃላ ስለነበር ወደ ተመልሼ ሆቴልና ሌሎች ቦታዎችም ሳፈላልግ ቆይቻለሁ አላገኘሁትም።
ከጠፋ 3 ቀን ሆኖታል ወድቆ ያገኘ ወይም ሌላ መረጃ የሰማችሁ ካላችሁ ብታሳውቁኝ።
ከፓስፖርቱ ጋር አብሮ ሌላ እቃ፣የኪስ ቦርሳና ሁለት ቪዛ ካርዶችም አብረው ስለጠፋ ምናልባት ፓስፖርቱ ሌላ ቦታ ወድቆ ሊገኝ ስለሚችል ድንገት ያያችሁ ወይም የሰማችሁ ሰዎች እንድትተባበሩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።አመሰግናለሁ።

ያገኛችሁ ወይም ማንኛውም መረጃ ያላችሁ:-
+966501886625 በመደወል ወይም
+251944752393 በዋትሳፕ ወይም ቴሌግራም ልታሳውቁኝ ትችላላችሁ።

 (ሼር ማድረግ ሶደቃ ነው ወገን። ወገኑን የሚረዳ የአላህ እርዳታ ከሱ ጋር ነው።)~ወ/ሮ ሐሊማ ሰይድ እባላለሁ ሰሜን ወሎ ወልድያ ከተማ ነው የምኖረው። ከባለቤቴ ሙሀመድ ሁሴን (አባናኖ) ጋ...
31/03/2024


(ሼር ማድረግ ሶደቃ ነው ወገን። ወገኑን የሚረዳ የአላህ እርዳታ ከሱ ጋር ነው።)
~
ወ/ሮ ሐሊማ ሰይድ እባላለሁ ሰሜን ወሎ ወልድያ ከተማ ነው የምኖረው። ከባለቤቴ ሙሀመድ ሁሴን (አባናኖ) ጋር ተጋብተን አ. አ. እንንኖር ነበር ከዛም አረብ ሀገር በመሄድ ወለድን። #ሶስተኛዋ አ. አ. ተወለደች።
ልጆቼ
1ኛ አብዱልመጅድ ሙሀመድ ሁሴን
2ኛ ፎዝያ ሙሀመድ ሁሴን
3ኛ መሬም ሙሀመድ ሁሴን

አ.አ. አየር ጤና አካባቢ እንኖር የነበረ ሲሆን ባለመግባባትችን እና በኑሮው መክበድ ምክንያት በ1994 ተመልሼ ወደ አረብ አገር ስሄድ ልጆቼን አክስታቸው ጋ ሰጥቼ ብሄድም አባታቸው ከአክስታቸው ቀምቶ ወሰዳቸው።

አረብ ሀገር እያለሁ ለልጆቼ የምችለውን እያደረኩ የነበረ ቢሆንም ለምን ጥለሽ ሄድሽ በሚል ልጆቼን ከ1997 ጀምሮ ሊያገናኘኝ አልቻለም።

ትልቁ ልጄ አብዱልመጅድ በ1997 አ.አ ዳንዲቦሩ ትምርት ቤት እየተማረ ትምርት ቤቱ እየሄድኩ አገኘው የነበረ ቢሆንም በሌላ ጊዜ ስሄድ ትምርት ቤቱን ለቋል ተብሎ ላገኘው አልቻልኩም።

ለማግኘት ብዙ ግዜ አ.አ ተመላለስኩ እንኖርበት የነበረው ሰፈር ጠየቅኩ ላገኛቸው አልቻልኩም። በእናትነት አንጀት ይህን ሁሉ አመት እነሱን እያሰብኩ አለሁ አባታቸው አልፎ አልፎ ቢደውልም ልጆቹን ግን እንዳገኛቸው አይፈቅድም።

ሲደውል ልጆቹ ትልቁ ልጄ አብዱልመጅድ ጂማ ዩንቨርሲቲ መካከለኛዋ ፎዝያ ጎንደር ዩንቨርሲቲ እንደተማሩ ነግሮኛል።
ልጆቼን ከ 20 አመት በላይ ሳላገኛቸው እዬኖርኩ ነው እባካችሁ ይህን የምታዩ ሁሉ ሳልሞት ልጆቼን እንዳገኛቸው አግዙኝ።

ስልክ
0921568570
0910633833

ኢማም ኢብኑል-ጀውዚይ ( አላህ ይዘንላቸውና፦"ፈረስ እንኳ የእሽቅድድም ሜዳ ላይ የመጨረሻው ዙር ላይ ሲደርስ ኀይሉን አሟጦ ተጠቅሞ ሌሎች ፈረሶችን በመቅደም ከግቡ ላይ ቀድሞ ለመድረስ ይጥራል...
29/03/2024

ኢማም ኢብኑል-ጀውዚይ ( አላህ ይዘንላቸውና፦

"ፈረስ እንኳ የእሽቅድድም ሜዳ ላይ የመጨረሻው ዙር ላይ ሲደርስ ኀይሉን አሟጦ ተጠቅሞ ሌሎች ፈረሶችን በመቅደም ከግቡ ላይ ቀድሞ ለመድረስ ይጥራል" ፣እነሆ ከፈረስ በላይ እንጂ በታች ልንሆን ፈፅሞ አይገባምና እኛም ወደ ጀነት በሮች በመልካም ስራ ልንሽቀዳደም ይገባናል፡፡” ይላሉ

አላህ ይወፍቀን!

🛑ወጣቶች ላይ የተጋረጡ አደጋዎችን እንዴት እንከላከል?✨ልዩ የወጣቶች ስልጠና!🎙 በኡስታዝ መንሱር ሑሴን እና በኡስታዝ ዩሱፍ ሑሴን🕌 ትሮፒካል በሚገኘው ውቡ ነጃሺ መስጂድ📆 ነገ ቅዳሜ መጋቢት...
22/03/2024

🛑ወጣቶች ላይ የተጋረጡ አደጋዎችን እንዴት እንከላከል?

✨ልዩ የወጣቶች ስልጠና!

🎙 በኡስታዝ መንሱር ሑሴን እና በኡስታዝ ዩሱፍ ሑሴን

🕌 ትሮፒካል በሚገኘው ውቡ ነጃሺ መስጂድ

📆 ነገ ቅዳሜ መጋቢት 14/2016

🕒 ከጠዋቱ 3፡00 - 6:00

22/03/2024

ጾምና ሙቀት
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

ሙቀት በበረታበት ጊዜ እየተቸገሩ መጾም ምንዳን ከፍ ያደርጋል። ደጋግ የአላህ ባሮች ዱኒያ ላይ መቆየትን እንዲመኙና እንዲወዱ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከልም አንዱ ጾም በሚከብድበት ጊዜና ቦታ ላይ ችግሩን ተቋቁሞ መጾም ነው።

📌 አቡ አድ'ደርዳእ رضي اللہ عنہ
"በሙቀት ጊዜ (በረሃ ውስጥ) ጥምን ተቋቁሜ መጾም፤ የሌሊት ሰላት ላይ የሚደረግ ሱጁድና እውቀትን አዋቂዎች ዘንድ ተንበርክኮ መማር ባይኖር ኖሮ ዱኒያ ላይ መቆየትን አልፈልግም ነበር" ሲሉ፤

ታላቁ ሰሓቢይ ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ደግሞ ምን ትመኛለህ ተብለው ሲጠየቁ "በጋ ላይ መጾም፤ በአላህ መንገድ እየታገልኩ ጠላትን በሰይፍ መምታትና እንግዳን በክብር ማስተናገድ " ብለዋል።

📌ስለዚህ የዘንድሮ ጾም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሙቀት በበረታበት ወቅት ላይ መሆኑ ይበልጥ ሊያስደስተን ይገባል።

📌ከመሆኑም ጋር የሙቀትን ድካም የሚያቀንሱ ነገሮችን ማድረግ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፥ በማንኛውም ሰዓት ገላን በቀዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ፊት እና ጸጉር ላይ ውኃ ማፍሰስ፣ አፍን በውኃ መጉመጥመጥና መልሶ መትፋት፣ ከጸሐይ መሸሽ፣ አናትና ደረት ላይ የረጠበ ፎጣ ማስቀመጥ ወዘተ።

📌 የዱኒያው ቀላል ሙቀት የጀሀነሙን ከባድ ግለት አስታውሷቸው ከርሱ የሚድኑበትን መልካም ስራ ለመስራት ደፋ ቀና ከሚሉ ባሮች አላህ ያድርገን!

📌ማታ ማታ ተራዊሕ ላይም ሙቀት አልችልም ብሎ ሰላት ትቶ ከመሄድ ይልቅ ታግሶና የጀሀነምን ግለት እያስታወሱ አላህን ከጀሀነም ጠብቀኝ ብሎ መማጸን በላጭና ብልሕነት ነው።

✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ረመዷን 10/1445 ዓ.ሂ
ዛዱል መዓድ

እንዲህ አይነት ነገሮችን የምታሰራጩ ሰዎች አላህን ፍሩ። ማስረጃ የሌለውን ነገር ወደ ዲን ማስጠጋት ከባድ ጥፋት ነው።IbnuMunewor✍️
19/03/2024

እንዲህ አይነት ነገሮችን የምታሰራጩ ሰዎች አላህን ፍሩ። ማስረጃ የሌለውን ነገር ወደ ዲን ማስጠጋት ከባድ ጥፋት ነው።

IbnuMunewor✍️

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Musilm Voice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Musilm Voice:

Share