H_Ethiopia

H_Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from H_Ethiopia, Media/News Company, Addis Ababa.

18/02/2025

በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ #ቤንዚል 2 ሌትር 1500 ብር እየተሸጠ ነዉ ይገኛል ።

የ50 ትራንስፖርት 250 ገብቷል

በዉስጥ የደረሰኝ መረጃ

ህግ ከባለሀብታ በጣች እየሆነ እየመጣ መሠለኝ

ወቷል
05/02/2025

ወቷል

የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 31 ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል
#ቴሌግራም👉 https://t.me/Admas_Media

እንዲዚህ ፅፌላቹ ነበርተመልከቱ
19/12/2024

እንዲዚህ ፅፌላቹ ነበር

ተመልከቱ

08/12/2024

ከቤተ መግስት ወደብሔራዊ ወርቅ ባንክ ገባ የተባለዉን 400 ኬሎ ግራም ወርቃችንን አስቀምጠዉ መኮብለል ይችላሉ።😂😂

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምድረ ቻይና የመጀመሪያውን ደብር በመሰየም፣ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች! ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)ባሳለፍነው ሳምንት...
08/12/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምድረ ቻይና የመጀመሪያውን ደብር በመሰየም፣ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች!

ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ለሁለተኛ ምዕራፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በዕለቱ ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በማስከተል የአስተዳደር ሥራዎችን ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ፤ በዕለተ እሑድ በቻይና ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያ የሆነውን ቤተ ክርስቲያን "ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም" ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈፀም ምዕምናንን አቁርበዋል።

በዕለቱም አንድ ኢ-አማኒ የነበረች ግለሰብ እና ሕፃን በማጥመቅ የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ያደረጉ ሲሆን የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆንም ሹመት አከናውነዋል።

በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው የተሳተፉ ሲሆን መጋቤ ሐዲስ ለይኩን ብርሃኑ "ሔዶም ታጠበና እያየም ተመለሰ" በሚል ርዕስ አስተምረዋል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ ብፁዕነታቸው ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ቤይጂንግ ከተማ አቅንተዋል።

መረጃውን ያደረሰን የብፁዕነታቸው ጽ/ቤት ነው

08/12/2024

በአዲስ አበባ የሚሰማው ተኩስ ምንድን ነው?

- በተኩሱ አንድ ሴት መገናኛ አካባቢ ተመትታ ህይወቷ አልፏል

- በአምቦ ከተማም በተመሳሳይ በተባራሪ ጥይት ተመትተው ሁለት ሰዎች ሞተዋል

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንደ ገርጂ፣ ጃክሮድ፣ ሾላ፣ 6 ኪሎ፣ መነን፣ ጎሮ ወዘተ ያሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ድምፅ ያለው ተኩስ ሲሰማ ነበር።

በርካታ ነዋሪዎች በድምፁ ተደናግጠዋል፣ መረጃ የሰጠ የመንግስት አካልም የለም።

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት ተኩሱ ከሰሞኑ ከመንግስት ጋር እርቅ ፈፀሙ በተባሉት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት የተተኮሰ ነው።

መገናኛ አካባቢ አንዲት ሴት በተኩሱ ምክንያት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉም ታውቋል። በተመሳሳይ ባለፉት ጥቂት ቀናት በአምቦ ከተማ በታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት ሁለት ሰዎች በተባራሪ ተመትተው እንደሞቱ ታውቋል።

ታጣቂዎቹ የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከሸገር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ወደ ሰማይ እየተኮሱ እንደገቡ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

"ታጣቂዎቹ በቅጥቅጥ አና በሃይሉክስ መኪና ተጭነው ሾላ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ተኩስ አየተኮሱ እየተጓዙ ነበር" ያለን አንድ የአይን ምስክር በሁኔታው በርካቶች እንደተደናገጡ ገልጿል።

ህዝብ በሚንቀሳቀስበት ጎዳና ላይ ድርጊቱ መፈፀሙ እንዳሳዘናቸው የገለፁት ነዋሪዎች ህዝብን በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ ቀድሞ ባልተገለፀበት ሁኔታ ማሸበር አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ሾላ ፖሊሲ ጣቢያ ከሚገኙ አንድ የፖሊስ አባል ድርጊቱን ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶች ከተኮሱ ቦታ በድንጋጤ ሲሸሹ ይታይ እንደነበር ገልፀዋል።

ተጠባቂው የአርሰናል እና ማንቺስተር ዩናይትድ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ አርሰናል ከማንቺስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደር...
04/12/2024

ተጠባቂው የአርሰናል እና ማንቺስተር ዩናይትድ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ አርሰናል ከማንቺስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

በሩበን አሞሪም አሰልጣኝነት የውጤት መሻሻል ያሳየው ማንቺስተር ዩናይትድ ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ላለመራቅ ጨዋታውን የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቶ የሚጫወተውን አርሰናልን በኤሜሬትስ ስታዲየም ይገጥማል።

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት ባደረጓቸው 241 የእርስ በእርስ ግጥሚያዎች ማንቺስተር ዩናይትድ 99 ጨዋታዎችን በድል ተወጥቷል፡፡

አርሰናል በበኩሉ 89 ጊዜ በድል ሲያጠናቅቅ፤ በቀሪዎቹ 53 ግጥሚያዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ በሚደረጉ ሌሎች ተጠባቂ ጨዋታዎች ማንቺስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከሊቨርፑል እንዲሁም ሳውዝሃምፕተን ከቼልሲ ምሽት 4፡30 የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

04/12/2024

አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 29ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል

03/12/2024

ከተላኩልኝ መልዕክቶች አንዱ እንዲህ ይላል:- ይላል ፋሲል የኔ አለም
👇👇👇👇👇
“ ሰላም ፋሲሌ እንዴት ነህ?
ያው ቲቪያችን እየሰራ አደለም ። እናንተ ለመሥማት እድሉ ሰሞኑ የለኝም ።

አንድ ነገር ገርሞኝ ላካፍልህ ወደድኩኝ ። አሰሪዬ ቅርብ ጊዜ ሕንፃ ሰርቶ ጨርሶ 1ኛ ፎቅ ላይ አከራየና ለባንክ ካገኘው ግብር ሊከፍል ወደ ገቢዎች ይሄዳል። ያከራየህበትን ብር ምን አደረከው? ብለው ይጠይቁታል ። አጠፋሁት በላሁበት ይላቸዋል ። እነሱም አትችልም ይሉታል ። እንዴት ብሎ ይጠይቃል። መብት የለህም፣ አሸባሪ ረድተህበትስ ቢሆን ይሉታል ። ኧረ በፍፁም እንደሱ አይነት ሰው አደለሁም ይላቸዋል ። አይ አንቀበልም አሉትና ሌላ አተካራ ውስጥ ገብተው ፣ ለማንኛውም እኔ ለመጠይቅህ ብር ዝግጁ ከሆንክ ደህና ፣ አሊያ ደግሞ ዘብጥያም ልትወርድ ትችላለህ ብሎት እርፍ ።

ግራ ሲገባው እሱ ከሚያገኘው በላይ ለመኖር ሲል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ለተቀመጠው ሰው አስረክቦ ወጣ ። የአብይ ብልፅግና ተብዬዎች እየገረሙኝ ነው። ግንባታ ፍቃድ ልትጠይቅ ብትሔድ ችግር ፣ ሰለ
ስንቱ ችግር ላውራልህ ። አሁን መርካቶ ውስጥ ያለውን ጣጣ ብታይ ፣ በቃ በዚህ ሀገር ተስፋ ትቆርጣለህ። ያሳዝናል በጣም።”

መረጃዉ የፋሲል የኔአለም ነዉ

የአቶ ታዬ ደንደዓ የዋስትና መብት መፈቀድ አስደሳች ቢሆንም ሁለት ጉዳዮችን ላንሳ:- አንደኛው አቶ ታዬ የተፈታው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተከሳሽ ምስክርነት ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ለማድረግ ነው።...
02/12/2024

የአቶ ታዬ ደንደዓ የዋስትና መብት መፈቀድ አስደሳች ቢሆንም ሁለት ጉዳዮችን ላንሳ:- አንደኛው አቶ ታዬ የተፈታው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተከሳሽ ምስክርነት ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ለማድረግ ነው። ከህግ በላይ መሆናቸውን ያስመሰከሩበት አጋጣሚ ነው። ታዬ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምስክርነት መቁጠሩ፣ ጥሩ ፖለቲካዊ ጨዋታ መጫወቱን ያሳያል።

ሁለተኛው አቶ ታዬ ከእስር ሲፈታ የአቶ በቲ ኡርጌሳ እጣ ፋንታ እንደማያጋጥመው ዋስትና የለውም። ከመፈታቱ ጋር ተያይዞ ብዙ አደጋዎች ከፊቱ እንዳሉ አይዘንጋ።

የፌደራል መንግሥት ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ይፋዊ ጥያቄ መቅረብ አለበት ተባለሕዳር 23/2017 ኤርትራ በኢትዮጵያ ይዛቸዉ ካለችዉ አካባቢዎች መዉጣት ይኖርባታል ሲሉ ዲፕሎ...
02/12/2024

የፌደራል መንግሥት ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ይፋዊ ጥያቄ መቅረብ አለበት ተባለ

ሕዳር 23/2017 ኤርትራ በኢትዮጵያ ይዛቸዉ ካለችዉ አካባቢዎች መዉጣት ይኖርባታል ሲሉ ዲፕሎማቶች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናግረዋል።

"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚቻለዉ ሕዝቡም ከስቃይ መዳን የሚችለዉ ኤርትራ ጧሯን ከኢትዮጵያ ማስወጣት ስትችል ነው" ሲሉ የተናገሩት፤ የኢሮብ አኒና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ አዉዓላ ናቸዉ።

"ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የፌደራል መንግሥት ኤርትራ ጧሯን ከኢትዮጵያ ግዛት ለቃ እንድትወጣ ይፋዊ የሆነ ጥሪ ማድረግ ሲችል ነው" ብለዋል፡፡

የድንበር ኮሚሽን ውሳኔንም በተመለከተ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት እንዲሁም በድንበር አካባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በውይይት መፍታት እንዳለባቸውም አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።

"ነገር ግን ማንኛዉም ዉይይት ከመደረጉ ቀድሞ የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት መዉጣት አለበት" ሲሉ አክለዋል።

"ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ የኤርትራ ሰራዊት ግማሽ ወረዳ ያህሉን የኢሮብ አካባቢን ጨምሮ ይዞ ይገኛል። በአልጀርሱ ስምምነት መሠረት የድንበር አካላይ ኮሚሽን በአየር ላይ ማስመሩ አሳውቆ ነበር" የሚሉት ደግሞ የቀድሞው ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ ናቸዉ።

"ይህንን ለብዙ ጊዜ ሲንከባለል የመጣዉን ችግር መፍታት ወሳኝ ነው" ያሉት የቀድሞ ዲፕሎማቱ፤ "መሬት ላይ ድንበር ማካለል ባልተደረገበት የራስ አድርጎ መዉሰድ ተገቢ አይደለም" ብለዋል፡፡

የኤርትራ ሠራዊት 6ዐ በመቶ የሚሆነዉን የኢሮብ ማህበረሰብ መቆጣጠሩን የኢሮብ አኒና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ገልጿል።

01/12/2024



1 የመከላከያ አባል #እናትኔና #ልጅ ሲደፍር በህዝቡ ብርቱ ክትትል ተይዞ #ተረሽኗል የተረሸነዉ እዛዉ በአባሎቹ ነዉ #ይገባዋል አሰዳቢ

መንግስ በአማራ ክልል ህግ ከማስከበር ጎንለጎን #የአንዳድ ጋጠወጥ የመከላከያ አባል ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when H_Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share