Ahun Times Media

Ahun Times Media Ahun Times is a digital media platform. Based in Ethiopia & covering news across the world.

10/06/2023

WORLD RECORD

🇪🇹's Lamecha Girma clocks 7:52.11 and breaks the 3000m steeplechase world record* 🔥

Ridiculous, absolutely ridiculous night at the



*Subject to the usual ratification procedures

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች Health Benefits of Beetroot (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)*ለጉበት ጤናማነትቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት...
02/11/2022

ቀይስርን የመመገብ የጤና ጥቅሞች
Health Benefits of Beetroot

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

*ለጉበት ጤናማነት

ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው።

*ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል

ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል።

*ካታራክትን ይከላከላል

ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል።

*የሃይል መጠንን ይጨምራል

ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል።

*ካንሰርን ይከላከላል

አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።

እባክዎን ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀ...
28/09/2022

የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣

✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ

• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል

• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት

✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

2. በቂ እረፍት ማድረግ

✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ

✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል

✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ

✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ

✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ

✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ

(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።

✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ

✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ

✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ

✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ

✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ

6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር ( PREECLAMPSIA)(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)በእርግዝና ጊዜ ሲለሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር እና ከፍተኛ መጠን ያለው የፕ...
14/09/2022

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር ( PREECLAMPSIA)
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

በእርግዝና ጊዜ ሲለሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት መጨመር እና ከፍተኛ መጠን ያለው የፕሮቲን መጠን በሽንት ውስጥ እንዲኖር ስለሚያደርገው በሕክምናው Preeclampsia (ፕሪኢክላምፕሲያ) ብለን ስለምንጠራው የሕመም ዓይንት በጥቂቱ ልንገራችሁ፡

በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊትን መጨመር የሚያስከትለው ትክክለኛ ምክንያት በእርግጠኝነት የማይታውቅ ቢሆንም በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ግን የሰውነት ስብ መከማቸት፤
የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ፤ ለማሕፀን የሚደርሰው የደም ፍሰት መቀነስ እና ተፈጥሮአዊ ሁኔታን እንደ ምክንያት ያስቀምጣሉ፡፡

በእርግዝና ጊዜ ለደም ግፊት መጨመር ሊያጋለጡ የሚችሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

•በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት መጨመር በአብዛኛው የሚከሰተው በመጀመሪያው እርግዝና ላይ እና ዕድሜያቸው ከ20ዓመት በታች ወይንም ከ40 ዓመት በላይ ያሉ ሴቶች ላይ ነው፡፡

በተጨማሪ፡- ከእርግዝናው በፊት የደም ግፊት ችግር ያለባት ሴት

- ከዚህ ቀደም በነበረ እርግዝና ጊዜ የደም ግፊት የነበረባት ሴት

- በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት ያጋጠማት እናት ወይም እህት ያላት ሴት

- የሰውንት ክብደት መጨመር

- በቁጥር ከአንድ ልጅ በላይ እርግዝና

- የስኳር ወይም የኩላሊት ሕመም ያለባት ሴት

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት መጨመር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• ከደም ግፊት መጨመርና በሽንት ውስጥ ከሚገኝ ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን በተጨማሪ

- ፈጣን የሆነ ሰውንት ክብደት መጨመር (በሰውነት ውስጥ የሚከማች ፈሳሽ)
- የሆድ ሕመም
- ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት
- ከሌላው ጊዜ የቀነሰ የሽንት መጠን ወይንም ምንም ሽንት አለመኖር
- ማዞር
- ከፍተኛ የሆነ ማስመለስና ማቅለሽለሽ ናቸው፡፡
ከመደበኛ የእርግዝና ክትትል በተጨማሪ አንዲት እርጉዝ ሴት የሚከተሉትን ሁኔታዎች ካስተዋለች ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ መታየት ያስፈልጋል፡፡

እነዚህም፡-
o የደም ግፊት መጠን ከ140/90 በላይ ከሆነ
o ድንገተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር
o የሆድ ሕመም
o ከፍተኛ የራስ ምታት
o የሽንት መጠን መቀነስ
o የዓይን በዥታ፤ተንሳፋፊ መስል ነገሮችን ማየት ካለ ናቸው፡፡
o ድንገተኛ ወይንም አዲስ የሆነ የእጅ የዓይን አካባቢ እና የፊት ማበጥ መጠነኛ የሆነ የእግር ማበጥ ግን በእርግዝና ጊዜ በአብዛኛው የሚከሰት ነው፡፡

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት መጨመር አንዳንድ ጊዜ ምንም ዓይነት ምልክትን ላያሳይ ስለሚችል አደጋ ላይ ላለመውደቅ መደበኛ የእርግዝና ክትትል ማድረግን አለማቋረጥና የደም ግፊት መጠንን በየጊዜው መለካት ተገቢ ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

የጆሮ ማሳከክ ምክንያቶች በጥቂቱ (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም )ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት...
23/08/2022

የጆሮ ማሳከክ ምክንያቶች በጥቂቱ

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም )

ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት ሲጎዳ ከሚከሰቱ ምልክቶች አንዱ የማሳአክ ስሜት ነው።

የጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችን ማወቅ በቶሎ መፍትሄዎቻቸውን እንድንፈልግ ይረዳናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችም ናቸው።

* የጆሮ ኩክ መከማቸት

የጆሮ ኩክ (Earwax) የምንለው ሰውነታችን የሞቱ ሴሎችንና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳበት መንገድ ሲሆን በብዛት በሚገኝበት ወቅት ግን የማሳከክ ስሜትን ይፈጥራል።

ጆሮን ለማጽዳት መሞከር ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ። ወደ ሀኪም በመሄድ ከታዪና ትክክለኛ ምክንያቱ የኩክ መጠራቀም ሆኖ ከተገኘ በጠብታ መድሀኒት ወይንም በህክምና ባለሞያ እርዳታ እንዲወጣ ይደረጋል።

*ኢንፌክሽን

የጆሮ ማሳከክ አንዳንዴ ደግሞ የኢንፌክሽን መኖር ምልክት ይሆናል። ጉንፋንን ወይንም ቶንሲልን የሚያስከትሉ ባክቴርያና ቫይረስ በደም ተዘዋውረው ወደ ጆሮ በመሄድ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

ውሀ ዋና የሚዋኙ ሰዎችም ውሃው በጆሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እና ተፈጥሮአዊ የሆነውን ጀርሞችን የመከላከል አቅም በእርጥበት ምክንያት እንዲያጣ ስለሚያድርግ ሌላው የኢንፌክሽን መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል።

የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ ወደ ሀኪም በመሄድ ጸረ ባክቴርያ የሆኑ የጆሮ መድሀኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው።

*የቆዳ አለርጂ

በጆሮዎ ውጨኛው ክፍል የሚገኘው ቆዳዎ በአለርጂ ምክንያት የማሳከክ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል።

የመዋቢያ ቅባቶች ወይንም ቁሳቁሶች አለርጂን ሊይስከትሉ ይችላሉ። የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ አለርጂው የተከሰተበትን ምክንያት ተከታትሎ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛም መጠቀም ማቆም ተገቢ ነው።

*ጆሮን በሹል እና ጎጂ ሊሆኑ በሚችሉ እንደ ጸጉር ሻጤ፣ አግራፍ፣ የክብሪት እንጨት በመሳሰሉት ማጽዳት የጆሮ ቆዳን ለመሰንጠቅ ስለሚችል ለኢንፌክሽን ይዳርጋል። ከዚህም ባለፈ የጆሮን ውስጣዊ ክፍል በመጉዳት የመስማት ችሎታችንን ሊያሳጣን ይችላል።

ጤና ይስጥልኝ

ለምፅ | Vitiligo👉ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው👉ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም👉ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ ...
22/08/2022

ለምፅ | Vitiligo

👉ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት (acquired) የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው

👉ለምፅ በንክኪ አይተላለፍም

👉ለምፅ ከህጻናት ጀምሮ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ሊታይ ይችላል

✔️ለምፅ በምን ምክንያት ይከሰታል?

👉ምክንያቱ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ከነዚህም መካከል "የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርአት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራች ህዋሳትን(melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው" የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።

በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከየስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata)....

👉ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና፣ ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል

✔️የለምፅ ምልክቶች

👉ለምጽ ያለበት ቦታ ወደ ነጭነት የሚያደላ ቀለም ሲኖረው ከዚህ ውጪ ማሳከክ ወይም ቦታው ላይ ቅርፍቶች መኖር የለምጽ ባህሪ አደለም

👉በማንኛውም የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

👉ለምፅ አንድ ቦታ ላይ ብቻ (focal)፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ብቻ (segmental) ወይም አብዛኛው የቆዳችን ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል

✔️የለምፅ ህክምና

👉የህክምናውን አይነት የሚወስኑ ሁኔታዎች ፦
🔹የህመሙ ጥንካሬ (severity)
🔹እየተስፋፋ መሆኑ ወይም ባለበት መቆሙ
🔹የህክምናው በቀላሉ መገኘት እና የህመምተኛው የመክፈል አቅም...

👉የህክምና አይነቶች
🔹የሚዋጥ
🔹 የሚቀባ
🔹 Phototherapy (ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ ብርሀንን በመጠቀም የሚሰጥ ህክምና)
🔹Excimer laser
🔹የቀዶ-ጥገና (surgery) ህክምና

🔹የማንጣት ህክምና (depigmentation)
አብዛኛው የሰውነት ክፍል በለምፅ ከተጠቃ እና ለማከም አስቸጋሪ ከሆነ ጤነኛውን የቆዳ ክፍል በማንጣት የማመሳሰል ሂደት ነው (Michael Jackson ይህ ህክምና ተደርጎለታል)

👉ስለህክምናው ሂደት ማወቅ ያለብን

🔹ህክምናውን ከጀመርን በኋላ የህክምናውን ውጤት ለማየት ከ 2-3 ወር ሊፈጅ ይችላል

🔹ጠቅላላ ህክምናው ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ያለማቋረጥ መከታተል ያስፈልጋል

🔹ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ ለምፁ እንደገና ሊመለስ ይችላል

🔹ከንፈር ላይ፣ጣት ላይ እንዲሁም ከቆዳው በተጨማሪ ፀጉርም አብሮ ነጭ ከሆነ የመዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው

✔️ለምፅን ባንታከምስ?

🔹ለምፅ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ጫና ያሳድራል
🔹እየሰፋ ሊሄድ ይችላል
🔹ቆዳችን በፀሐይ ጨረር እንዲጠቃ ሊያረግ ይችላል (ፀሐይ መከላከያ/sunscreen መጠቀም ያስፈልጋል)

✔️ በመጨረሻም

ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
በሆሳዕና ከተማና አካባቢው የቆዳ ህክምናና ምክር ሲፈልጉ: 0929296463

የእግር ጉዞ የማድረግ የጤና ጥቅሞች(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)በርካቶቻችን የእግር ጉዞን እንደመደበኛ የስፖርት ዓይነት አንቆጥረው ይሆናል፡፡ ነገር ግን በየእለቱ ለተወሰነ ደቂቃ የእግር ጉዞን...
16/08/2022

የእግር ጉዞ የማድረግ የጤና ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

በርካቶቻችን የእግር ጉዞን እንደመደበኛ የስፖርት ዓይነት አንቆጥረው ይሆናል፡፡ ነገር ግን በየእለቱ ለተወሰነ ደቂቃ የእግር ጉዞን ማድረግ እጅግ ጠቃሚ እና ለጤናም አስፈላጊ የሆነ ነገር መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

ከዚህ በታች ስለእግር ጉዞ ጠቃሚነት ጥቂት እላችኋለሁ፡፡

✔ የልብ ጤነንትን ይጠብቃል

መደበኛ የሆነ የእግር ጉዞን ማድረግ ለልብ ሕመም እና ለስተሮክ የመጋለጥን ዕድል ይቀንሳል፡፡ በደም ውስጥ የሚገኘውን መጥፎ የኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ ጥሩውን ያስቀራል፡፡ የደም ግፊት መጠንዎንም ይቆጣጠራል፡፡

✔ ለተለያዩ ሕመሞች የተጋላጭነት ዕድልን ይቀንሳል
ከልብ ሕመም በተጨማሪ ለስኳር፣ አስም እና ለሌሎች ሕመሞች መጋለጥን ይቀንሳል፡፡

✔ የተስተካከለ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ይረዳል
የእግር ጉዞን ማድረግ ቀላል የማይባል የሰውነት ስብን ለማቅለጥ ይረዳል፡፡

✔ የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል
አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን በተለይም ለሴቶች ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የአጥንት መሳሳት ችግር እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡

✔ኃይልን ይሰጣል
የእግር ጉዞን በየቀኑ የምናደርግ ከሆነ የሰውነታችንን የደም ዝውውር በሚገባ የሚረዳ ስለሆነ ጤናማ እና ንቁ እንድንሆን ያደርጋል፡፡

✔ ደስተኛ እንድንሆን ያደርጋል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የእግር ጉዞን የሚያደርጉ ሰዎች ደስተኛ እና ንቁ ናቸው፡፡

ጤና ይስጥልኝ

የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች፡፡(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)* የጨጓራ ህመም ሊከሰትባቸው ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል 1. ባክቴርያ2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መው...
05/08/2022

የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች፡፡
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

* የጨጓራ ህመም ሊከሰትባቸው ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል

1. ባክቴርያ
2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መውሰድ
3. ለረዥም ግዜ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች
4. የምንመገባቸው የምግብ አይነቶች

ወደ ጤና ማእከል በመሄድ ከምናገኛቸው የጨጓራ ህመም መድሀኒቶች በተጨማሪ የአመጋገብ ሁኔታችንን ማስተካከል ከህመሙ ፋታ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡

* የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ የምግብ አይነቶች በጥቂቱ:-

1. ፍራፍሬ ፡- ፍራፍሬዎች ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖች ፣ ፋይበር እና አንቲ ኦክሲደንቶችን ስለሚይዙ በእለት ተእለት የምግብ ፕሮግራማችን ላይ ማካተት ጠቃሚ ነው፡፡
እንደ ፖም እና ሃብሃብ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ የምግብ አይነቶች ሲሆኑ እንደ ብርቱካን ያሉት ደግሞ እንዲወሰዱ አይመከርም

2. አትክልት ፡- የተለያዩ የአትክልት አይነቶችን መመገብ ለጨጓራ ህመምተኞች ተስማሚ ሲሆን በምግብ አዘገጃጀት ላይ የሚጨመሩ እንደ ነጭ ሽንኩርት እና የተለያዩ ማጣፈጫ ቅመሞች ግን እንዲወሰዱ አይመከርም፡፡

3. ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ፡- የጨጓራ ህመም ላለባቸው ሰዎች ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ተስማሚ የሆኑ ሲሆን ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ላይ ግን ህመሙን ሊያባብሱ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህም የሚስማማቸው ሰዎች ብቻ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡

4. ስጋ ዶሮ እና አሳ ፡ - እነዚህ ምግቦች የጨጓራ ህመምተኞች ሊመገቧቸው የሚችሉ ሲሆን የማጣፈጫ ቅመሞች እና ቅባት ሳይኖርባቸው መመገብ ይቻላል ፡፡

5. በቀን ውስጥ የሚመገቡትን የምግብ ዓይነቶች ወደ ዳቦ፣ አጃ፣ ሩዝ፣ ድንች፣ ገብስ፣ ፓስታ፣ ማኮሮኒ ማዞር ለጤና ተመራጭ ነው፡፡

6. ፈሳሽ በሚገባ መውሰድ የጨጓራ ህመምን በከፍተኛ ሁኔታ ያስታግሳል፡፡ ንጹህ ውሀ መጠጣም ለሰውነታችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

እንደ ቡና ሻይ እና ለስላሳ እንዲሁም የአልኮል መጠጦች የጨጓራ ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲወስዷቸው አይመከርም፡፡

ጤና ይስጥልኝ!

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ...
02/08/2022

ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የስኳር ሕመም ምልክቶች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡
የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሆን፣ በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን መጨመር የኩላሊት ሥራ ያዛባል፡፡

2) የድካም ስሜት መሰማት
የስኳር ሕመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውንት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ሕመም ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡

3) የዓይን ችግር
ማናኛውም ዓይነት የዓይን ችግር የስኳር ሕመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የስኳር ሕመምተኞች ለግላኮማ የመጋለጥ ዕድላቸው ስለሚጨምርና በካታራክት (በዓይን ሞራ) ሊጠቁ ስለሚችሉ የዓይን ሕመም ከተሰማ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይመከራል፡፡

4) የእግር መደንዘዝ
የስኳር ሕመም የነርቭ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ጉዳት በአብዛኛው የሚከሰተው በእጃችንና በእግራችን ላይ ባሉ ነርቮች ላይ ነው፡፡ በነርቭ ወይንም በደም ሥር ላይ የሚደርስ ጉዳት የእግር መደንዘዝ ቀጥሎም የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡ ሕመሙ በጊዜ ብዛት እየባሰ የሚሄድ ሲሆን መጠጥ እና ሲጋራ ማጨስ ሕመሙን ያባብሰዋል፡፡

5) የቆዳ ላይ ኢንፌክሽንና በቶሎ የማይድን ቁስለት
የስኳር ሕመም ቆዳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የሰውነት ክፍላችንን ሊጎዳ ይችላል እንዲያውም የስኳር ሕመም ያለበት ሰው በቀላሉ በባክቴሪያ እና በፈንገስ የሚመጣ ለቆዳ ላይ ኢንፌክሽን ያጋልጣል እነዚህም ኢንፌክሽኖች ቁስለትን ያስከትላሉ በቶሎ ሊድኑም አይችሉም፡፡
ጤና ይስጥልኝ

የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝ...
26/07/2022

የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ

2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ

3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር

4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ፣ ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን

5) የጠዋት ፀሐይን መሞቅ ይህም ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም በሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል

6) የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ ምክንያቱም ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ ነው

7) ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ ይህም ሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል

ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!!
ጤና ይስጥልኝ!

ጡጦ አብዝቶ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የህፃናት የጥርስ መቦርቦር | Baby Bottle Cariesቤቢ ቦትል ኬሪስ (Baby Bottle Caries) በተለይ ማታ ማታ ለረጅም ሰዓታት ከውኃ...
12/07/2022

ጡጦ አብዝቶ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የህፃናት የጥርስ መቦርቦር | Baby Bottle Caries

ቤቢ ቦትል ኬሪስ (Baby Bottle Caries) በተለይ ማታ ማታ ለረጅም ሰዓታት ከውኃ ውጪ ወተትን ጨምሮ የተለያዩ ጣፋጭነት ያላቸው ፈሳሾችን በጡጦ መልክ ይዘው በሚተኙ ህፃናት የሚፈጠር የጥርስ መቦርቦር ዓይነት ነው።

ይህ የጥርስ መቦርቦር እንዲከሰት አፍ ውስጥ የሚኖሩ ባክቴሪያዎች (Normal Oral Floras) ጣፋጥነት ያላቸውን ምግቦችን በመመገብ ከመራባትም ባለፈ አሲድን እንደ ተረፈ ምርት ስለሚለቁ ይህ አሲድ እምብዛም ያልጠነከረውን የህፃናት ጥርስን በፍጥነት የመቦርቦት አቅም ኣለው።

ይህ የጥርስ መቦርቦር ዓይነት ብዙውን ጊዜ ከወላጆች ልምድ አንፃር የመጀመሪያ ልጆች ላይ ዘውትሮ የሚታይ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የላይኛው መንጋጋ የፊትለፊት ጥርሶች ያጠቃል።

የቤቢ ቦትል ኬሪስ (Baby Bottle Caries) ምልክቶች:

ይህ የጥርስ መቦርቦር ዓይነት አፍ ውስጥ የሚገኝ የትኛውንም ጥርስ መጉዳት የሚችል ሲሆን፣በተለይም የላይኛው መንጋጋ የፊት ጥርሶችን በተለየ መልኩ ይቦረቡራል። የተጎዱ ጥርሶች ጠቆር የማለት ወይም ቡናማ መልክ ሊኖራቸው ይችላል።

የመቦርቦር ሒደቱ እየጨመረ ሲመጣና ወደ ጥርሶች የደም ስርና ነርቮች ሲጠጋ ለቀዝቃዛ መጠጥ፣ ለብርድ (ለንፋስ)ና ለጣፋጭ ነገሮች የህመም ስሜት ይጀምራል። ሒደቱ ከዚሁ አንድ ደረጃ ጨምሮ የደም ስርና ነርቮችን ከነካ ልክ ትኩስ ነገር ሲበሉም ሆነ ሲጠጡ፣ በሚያጎነብሱበት ወቅት፣ በሚተኙበት ወቅትና እንዲሁ በራሱ ጊዜ ህመም መሰማት ይጀምራል።

የመጨረሻው የህመም ዓይነት ደግሞ የደም ስሮቹና ነርቮቹ በባክቴሪያ አልቀው ሲበሉና ወደ ጥርሱ አናት ሲወጡ የማበጥ ነገር ሊያስከትሉ ይችላሉ።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

✅ በወራቶች ልዩነት በጥርስ ሐኪም ክትትል ማስደረግ

✅ በተለይ ማታ ማታ ወተትን ጨምሮ ጣፋጭነት ያላቸውን ነገሮች ለህፃናት በጡጦ አስይዞ እንዲተኙ አለማድረግ

✅ ለልጆች ከተቻል ከ 6 ወር ጀምሮ በኩባያ ነገር እንዲጠጡ ማለማመድ

✅ ማታ ማታ ጡጦ አስይዞ ማስተኛት ግድ ከሆነም ጡጦውን በውኃ ሞልተው መስጠት

✅ ልክ እንደተመገቡ የአፋቸውን ንፅህና መጠበቅ

✅ ራሳቸውን ለቻሉ ህፃናት ፍሎራይድ የያዘ የጥርስ ሳሙናን ተጠቅመው በወላጅ ክትትል እንዲቦርሹ ማድረግ ምክንያቱም ድንገት ከዋጡት የጥርስ መበለዝ ከጊዜ በኋላ ስለሚያስከትል

✅ የተጎዳ ጥርስ ካለ ተገቢውን ህክምና ማድረግ

በ ዶ/ር አብዲልኑር ሺፋ(Dental Surgeon)

ኢትዮ-ጠቢብ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአዋቂዎች በተጨማሪ ለህፃናትም የተሟላ የጥርስ ህክምና አገልግሎት እጅግ ዘመናዊ በሆነው የጥርስ ህክምና ክፍሉና በዘርፉ በቂ የትምህርት ዝግጅት ከበቂ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።

ብጉር | Acne vulgaris◈ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የ...
09/07/2022

ብጉር | Acne vulgaris

◈ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።

◈ ብጉር ከጨቅላ ህጻናት ጀምሮ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።

◈ ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።

➡ ለብጉር መከሰት አራት መሰረታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ናቸው

1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል

2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production)

3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት

4-ብግነት (Inflammation)

➡ ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች

👉ጭንቀት (stress)
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉በወር አበባ አካባቢ
👉የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin...)
👉በስራ ሁኔታ የሚያጋጥሙ ኬሚካሎች

👉በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ (friction) ወይም ጫና (pressure) ፤ ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል
👉 ለረዥም ሰአት የፊት ማስክ ማድረግ
👉በውስጣቸው comedogenic ingredients የያዙ የፊትና የጸጉር ቅባቶች

➡ ብጉር እንዴት ይታከማል?

✔️ ብጉር በአብዛኛው ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቆዳ ህመም በመሆኑ በራሱ የሚጠፋውም ከእድሜ ጋር ተያይዞ ነው ፤ ስለዚህም ምልክቶቹን መቆጣጠር እንጅ በህክምና ማዳን (በአንድ ህክምና እስከ መጨረሻው እንዳይመጣ ማድረግ) አይቻልም።

በዚህም ምክንያት የብጉር ህክምና ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ታካሚዎች ከቆዳ ሐኪማቸው ጋር እየተመካከሩ ህክምናውን መከታተል ይኖርባቸዋል።

✔️ እዚህ ጋር ብጉር በራሱ ጊዜውን ጠብቆ የሚጠፋ ከሆን መታከም ለምን ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፤ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።

✔️ የብጉር ህክምና እንደ ጥንካሬው መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል

✔️ ከዋናው ህክምና በተጨማሪ በውስጣቸው Salicylic acid, Benzyle peroxide የያዙ መታጠቢያ ሳሙናዎች መጠቀም ያስፈልጋል

➡ ከህክምናው በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን

👉እንቅስቃሴ ማድረግ (ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል)
👉ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር (ጠባሳ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ)
👉ለቆዳ ጤና መጠበቂያም ሆነ ለውበት የምንጠቀማቸው ምርቶች Oil-free & non-comedogenic መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም (መጠቀም ያለብን የፀሐይ መከላከያ እንደ ቆዳችን አይነት ስለሚለያይ የቆዳ ሐኪም ያማክሩ)
👉ቆዳችን ላይ ጫና (pressure) የሚፈጥሩ ነገሮችን (helmets, ስልክ, የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ, የፊት ማስክ) መቀነስ
👉ሰውነታችንን ካላበን መታጠብ

✔️ በመጨረሻም ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት
በሆሳዕና ከተማና አካባቢው የቆዳ ህክምናና ምክር ሲፈልጉ 0929296463

Address

Ethiopia, Belay Zeleke At
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahun Times Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ahun Times Media:

Share