Yohannes Mulu

Yohannes Mulu I am Global digital literacy Professional. "nothing happens until someone sells something"

ስራ ቅጥር ፍለጋ በየታፔላው፣ በየ ሰሌዳው መንከራተት ይብቃችሁ ዉድ ቤተሰቦቼ እኔ የትም ገብቼ እዚሁ እለጥፍላችኋለሁ ብቻ እናንተ ቤጁን ብቻ አርጉ

ቲክቶክ ላይ እንዴት ታዋቂ እንደምትሆኑ እና ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ (ከ ሀ እስከ ፖ) የሚያስረዳ መፅሐፍ ሲሆን አንብባችሁ ስትጨርሱ ተጨማሪ ርዳታ ከፈለጋችሁ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በ...
24/07/2025

ቲክቶክ ላይ እንዴት ታዋቂ እንደምትሆኑ እና ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ (ከ ሀ እስከ ፖ) የሚያስረዳ መፅሐፍ ሲሆን አንብባችሁ ስትጨርሱ ተጨማሪ ርዳታ ከፈለጋችሁ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ደራሲውን ማግኘት ትችላላችሁ!

መፅሐፉን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ👇
Yebuna.com
https://ye-buna.com/Yohannesmulu?ref=product_detail&product=6871c2d1f1da5_Yohannesmulu

ለለበለጠ መረጃ
ስልክ - 0989546363
telegram t.me/yohannesmulu

TikTok - www.tiktok.com/yohannes__mulu

21/07/2025

የመጽሐፉ ርዕስ: የታንጉት ምስጢር

ደራሲ: ብርሃኑ ዘሪሁን

የገጽ ብዛት: 297

የታተመበት ዓመት: 1979

Rating :- 9.3

የዚህ መጽሐፍ ፀሐፊ እውቁ ደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ዘርይሁን ነው።ደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱትና የአማርኛን ስነ-ጽሑፍ ካዘመኑት ታላላቅ የብዕር ሰዎች አንዱ ነው። ደራሲው በርከት ያሉ መጽሐፎችን ከመጻፉ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንትም ሆኖ ሰርቷል።ብርሃኑ በአማርኛ ስነ-ጽሑፍ በጣም የሚታወቅበት ልዩ ሪከርድ አለው። ይኸውም በታሪካችን የመጀመሪያውን የልብ ወለድ trilogy አሟልቶ የጻፈ መሆኑ ነው።ብርሃኑ ዘርይሁን በርከት ያሉ መጻሕፍትን ለተደራሲያን አቅርቧል።በስነ-ጽሑፍ ምሁራንና በአንባቢያን በጣም የተደነቀለት ስራው ግን ይህ "የታንጉት ምስጢር" የተሰኘ ታሪካዊ ልብ ወለድ ነው።የእሱ ስራዎች የኢትዮጵያን ታሪክ እና ማህበራዊ ገጽታዎች በአንባቢያን ልብ ውስጥ በሚቀር መልኩ የመሳል ችሎታውን ያሳያሉ።

ደራሲው ብርሃኑ ዘሪሁን "የታንጉት ምስጥር" የተሰኘውን መጽሐፍ ለመጻፍ እንደመረጃ ምንጭነት በዋናነት የኢትዮጵያን ታሪክ፣ በተለይም የቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት አካባቢ የነበሩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን፣ እንዲሁም የባህልና የአኗኗር ዘይቤዎችን በጥልቀት አጥንተዋል።መፅሐፉም የደራሲውን የታሪክ ጥልቅ ግንዛቤ ያሳያል።ይህ ደራሲው ዘመኑን በሚገባ ተረድተውት ለትረካቸው ዳራ መሆኑን ያመለክታል።በተጨማሪም በመጽሐፉ ውስጥ ያሉ የገጸ-ባህሪያት ውስጣዊ ግጭቶች እና ምስጢሮች፣ ደራሲው የሰው ልጅን ስነ-ልቦና ለመዳሰስ ያላቸውን ግንዛቤ ያንፀባርቃሉ። "የታንጉት ምስጢር" የኢትዮጵያን ታሪክ፣ በተለይም የጎንደር ዘመን እና ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ሥልጣን ላይ የወጡበትን ወቅት በልቦለድ መልክ በማቅረብ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።መጽሐፉ የዚያን ዘመን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ገጽታዎችን በሕያው ትረካ ያሳያል።ከታሪካዊ ዳራው ባሻገር፣ መጽሐፉ የሰው ልጅን ማንነት፣ የቤተሰብ ምስጢሮችን፣ ፍቅርን፣ ክህደትን፣ ምኞትንና ታማኝነትን በጥልቀት ይዳስሳል።መጽሐፉ ለታሪክ ተማሪዎችም ሆነ ለጠቅላላ አንባቢዎች ስለኢትዮጵያ ታሪክ እና ስለሰው ልጅ ተፈጥሮ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ይሰጣል።

የመጽሐፉ ዋና ፍሬ ሐሳብ በለውጥና በሽግግር ዘመን ውስጥ የሚያጋጥሙ ክስተቶች ከግለሰቦች ሕይወት፣ ቤተሰባዊ ምስጢሮች እና ውስጣዊ ግጭቶች ጋር እንዴት እንደሚቆራኙ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ማንነትና ዕጣ ፈንታ በእነዚህ ሁኔታዎች እንዴት እንደሚፈተን ነው።ይህ ሐሳብ በንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ዘመን በጎንደር ከተማ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ውጣ ውረዶች ዳራ ላይ የገጸ-ባህሪያትን ታሪክ በማሳየት ይገለጻል።ይህ ዋና ፍሬ ሐሳብ ከመጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጀምሮ በግልጽ ይንጸባረቃል።ጎንደር በቴዎድሮስ ሥርዓት ውስጥ በነበረች ጊዜ የነበረው ማኅበራዊ ትርምስ ሲገለጽ እና የዋና ገጸ-ባህሪያት (ለምሳሌ ቴዎድሮስ ራሳቸው እና የገብርዬ የመሳሰሉት) ታሪክ ሲዳሰስ ይህ የሐሳብ ክር ተጠናክሮ ይሄዳል።"የታንጉት ምስጢር" የሚለው ርዕስ በመጽሐፉ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስውር ሆኖ በቆየው፣ በመጨረሻ ግን በሚገርም ሁኔታ በሚገለጸው የቤተሰብ ታሪክ እና በንጉሥ ቴዎድሮስ እኅትና ልጇ ዙሪያ በፈጠረው ድብቅ ማንነት የተወሰደ ነው።ይህ ምስጢር የብዙዎችን ሕይወት የነካ እና የመጽሐፉን ክስተቶች የሚያንቀሳቅስ ማዕከላዊ ነጥብ ነው።

ደራሲው ከንድፈ ሃሳባዊ መነጽር ስለማኅበራዊ ፋይዳዎች እና ተኃድሶ ያለውን ምልከታ በመጽሐፉ መግቢያ እና በታሪኩ ሂደት ይገልጻሉ።ደራሲው ታሪክን እንደ ማሳ በመውሰድ ማኅበራዊ አስተሳሰብ የዘራውን ማኅበራዊ ሕይወት እንደሚያበቅል፣ እንደሚያሸት እና እንደሚያፈራ ያብራራሉ።ማሳው በወቅቱ ካልታረመ ዝባዝንኬው በርክቶ ጠቃሚ ፍሬ እንደማይሰጥ ሁሉ፣ ማኅበራዊ ሕይወትም ያለ ለውጥ እና እንክብካቤ ዕዳሪ እንደሚሆን ይገልጻሉ።ይህ ደግሞ ብርሃኑ ዘሪሁን የለውጥን እና የተሀድሶን አስፈላጊነት ከታሪክ አኳያ እንዴት እንደተመለከቱ ያሳያል። ደራሲው ብርሃኑ ዘሪሁን "የታንጉት ምስጥር" የተሰኘውን መጽሐፍ ለመጻፍ ያስገደደው ሁኔታ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የነበረው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ሽግግር፣ በተለይም የጎንደር ዘመን ማብቂያ እና የንጉሥ ቴዎድሮስ መነሳት ነው።ደራሲው ይህንን ታሪካዊ ወቅት፣ የፖለቲካ ትርምሱን፣ የማኅበራዊ መስተጋብር ለውጡን እና በውስጡ የሰዎችን የግል ሕይወት በልቦለድ መልክ ለመዳሰስ ተነሳስተዋል። መጽሐፉ ጎንደር የሥልጣን ማዕከል ከነበረችበት ዘመን ወደ አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት ስትሸጋገር የገጠማትን ማኅበራዊ ትርምስ በሕያው ቋንቋ ይገልጻል።"የሚተራመሰው ማኅበራዊ ግንኙነት ግን በወጉ ሊቀመጥ አልቻለም። ሊቀመጥም አይችልም ነበር።" በሚለው ሐሳብ የዚያን ጊዜውን ውስብስብነት ያሳያል።

አጼ ቴዎድሮስ በመጽሐፉ ውስጥ እንደ ጠንካራ መሪና የለውጥ አራማጅ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሰውም ጭምር በስሜትና በቤተሰብ ምስጢሮች የተጎዳ ገጸ-ባህሪ ሆነው ቀርበዋል።በተለይም የእኅታቸው ታሪክ እና የታንጉት ምስጢር በእሳቸው ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ ጥልቅ ትንታኔ ይሰጣል።እኅታቸውን በግዞት የላኳቸው በከባድ ቅጣት ቢሆንም፣ ውስጣዊ ህመማቸው እና የቤተሰብ ፍቅራቸው በተዘዋዋሪ ይገለጻል። በሌላ በኩል ገብርዬ: የቴዎድሮስ ታማኝ ሰው ሆኖ፣ የቴዎድሮስን የግል ሕይወት እና የታንጉትን ምስጢር ጠባቂ ነው።የእሱ ገጸ-ባህሪ የታማኝነትን፣ የጥንቃቄን እና የዝምታን ኃይል ያሳያል።ለቴዎድሮስ ያለው ወዳጅነት እና የቤተሰብ ምስጢርን የመጠበቅ ኃላፊነት ስሜቱ ታሪኩን የበለጠ አሳማኝ ያደርገዋል። የታሪኩ ማዕከላዊ ምስጢር የሆነችው ታንጉት፣ የኩራት፣ የንቀት እና የተደበቀ ማንነት ምልክት ነች።አባቷ ከቅማንት ሴት በመውለዳቸው አፍረው ደብቀዋት መኖራቸውን በመናገር፣ ደራሲው የዘመኑን ማኅበራዊ መድልዎ እና የቤተሰብ ውጥረቶችን ያሳያል።የእሷ ኩራት እና የእኅትነት ጥሪን አለመቀበል የዚያን ዘመን ማኅበራዊ እሴቶችና ገደቦች ውጤት ነው።ደራሲው በገጸ-ባህሪያቱ ውስጣዊ ግጭቶችና ምርጫዎች አማካኝነት የሰው ልጅን ፍላጎት፣ ፍርሃት፣ ፍቅር እና የመኖር ትርጉም ይዳስሳሉ።ምስጢሮች በሰዎች ሕይወት ላይ የሚፈጥሩትን ጫና እና ውጤት በጥልቀት ያሳያል። ደራሲው የታሪክን ጥልቀት ከልቦለዳዊ ትረካ ጋር በማዋሃድ ታሪኩን ሕያው ያደርጉታል።ቋንቋቸው ገላጭና ስሜት ቀስቃሽ ሲሆን አንባቢው ወደ ዘመኑ ድባብ ዘልቆ እንዲገባ ያስችለዋል።

በመጨረሻም መጽሐፉ የኢትዮጵያን ታሪክ በጥልቀት መመርመር እና ከዚያም መማር አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።ታሪካዊ ሽግግሮች እንዴት ማኅበራዊና ግለሰባዊ ሕይወትን እንደሚነኩ ለመረዳት ያስችላል ፤ ብሎም ካልታረመና ዕዳሪ እንደሚሆን በመጠቆም፣ ማኅበራዊ ችግሮችን በመንቃት መፍታትና ሀገራዊ ተሀድሶን መቀበል አስፈላጊ መሆኑን ያበረታታል።የቤተሰብ ምስጢሮች በግለሰቦች እና በቤተሰብ ግንኙነት ላይ የሚኖራቸውን ተጽዕኖ መረዳት እንዲሁም ግልፅነትና ይቅርታ የመንፈስ ሰላምን ለማግኘት ወሳኝ መሆናቸውን እናያለን። መጽሐፉ የቴዎድሮስን ዘመን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሽግግር ዳራ በማድረግ የታንጉትን ምስጢር እና የብዙ ገጸ-ባህሪያትን የሕይወት ውጣ ውረድ በስሜት ቀስቃሽ መንገድ ያሳያል።ደራሲው ታሪክን ሕያው በማድረግ የሰው ልጅን ማንነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት እና የለውጥን አስፈላጊነት በመጠቆም ለዘመናችንም ጭምር ጠቃሚ መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ።ይህ መጽሐፍ በታሪካዊ ልቦለዶች ለሚደሰቱ፣ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እና የሰው ልጅ ስነ-ልቦና በጥልቀት ለመረዳት ለሚፈልጉ አንባቢዎች ሁሉ ጠቃሚና ተነባቢ ሥራ ነው።

Reviwer :- Henok Fasil is an associate editor at Think Ethiopia

ይህን ዳሰሳ ያቀረብኩት ሄኖክ ፋሲል እባላለሁ።በትምህርት ዝግጅቴ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለኝ ስሆን በኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና ዘርፍ 6 ዓመት የስራ ልምድ አለኝ።

የምስራች በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አይስልክ መፅሐፍ (eBook) ገበያ ላይ ዋለ!Take your copy now! at www.ye-buna.com/yohannesmulu
09/07/2025

የምስራች በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው
አይስልክ መፅሐፍ (eBook) ገበያ ላይ ዋለ!
Take your copy now! at www.ye-buna.com/yohannesmulu

Are youvready to grab your copyiSelk is Coming!
09/06/2025

Are youvready to grab your copy
iSelk is Coming!

My book አይስልክ is Comingሰኔ 04/2017 ዓ/ም የኔ ቲክቶክ Live ላይ ይመረቃል።  ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
07/06/2025

My book አይስልክ is Coming
ሰኔ 04/2017 ዓ/ም የኔ ቲክቶክ Live ላይ ይመረቃል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

26/04/2025

በምድር መገፋፋት ለኔ ነው የሚገባው ማለት
በሰማይ ግን አብረን እንሁን ና ወደኔ ዕምነት እያሉ ደግሞ ሌላ ጦርነት መክፈት።
ምን ጉድ ነው?

የቢዝነስ ባለቤት ከሆናችሁ የ FACEBOOK Ad አሰራር በአጭር ጊዜ በመማር የራሳችሁን ቢዝነስ ማስተዋዎቅ ትችላላችሁ። ከነፃ የክፍያ ካርድ ጋር የፌስቡክ Ad አሰራር ከ ሀ እስከ ፖ ስልጠና...
02/12/2024

የቢዝነስ ባለቤት ከሆናችሁ የ FACEBOOK Ad አሰራር በአጭር ጊዜ በመማር የራሳችሁን ቢዝነስ ማስተዋዎቅ ትችላላችሁ። ከነፃ የክፍያ ካርድ ጋር የፌስቡክ Ad አሰራር ከ ሀ እስከ ፖ ስልጠና ተዘጋጅቷል።
የሚያስፈልጋችሁ ሞባይል ስልክ ብቻ ነው።
ስልጠናው Online ለ አንድ ሳምንት ነው። አስፈላጊ ሲሆን 1 to 1 Assistance እስከ 5 ወር ድረስ ይኖራችኋል።
ይህ ስልጠና
1ኛ, ለትላልቅ ቢዝነስ መሪዎች
2ኛ ለሪል ኢስቴት ባለቤቶች
3ኛ, ለሪል ኢስቴት ሴልሶች
4ኛ, ለትናንሽ ሱቆችና አገልግሎት ሰጪዎች
5ኛ, ለOnline ነጋዴዎች
6ኛ, ለሶሻል ሜዲያ ማርኬተሮች እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጄ ተግባራዊ ስልጠና ሲሆን። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በየራሳችሁ ፌስቡክ ፔጅ የማስታወቂያ አሰራርን የምትማሩበት ነው።

ስልጠናው የሚያካትታቸው;-
1, ግራፊክስ ዲዛይይን አሰራር በቀላል መንገድ
2ኛ, ኮንተንት ክሬሽን
3ኛ, ማስተር ካርድ አወጣጥ
4ኛ, ፌስቡክ Ad አሰራር እና
ለ እያንዳንዱ ሰልጣኝ ለ አምስት ወር የሚቆይ ነፃ ድጋፍ...

ለተጨማሪ መረጃ ለመመልከት ከ 80 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትን የቲክቶክ አካውንት እና ከ 5 ሺህ በላይ ተከታይ ያሉትን ቴሌግራም ቻናል መመልከት ትችላላችሁ

TikTok Account
https://www.tiktok.com/?_t=8rsGBLb3pTD&_r=1

Telegram channel
https://t.me/yohannesmulu1

ለመመዝገብ
በTelegram
t.me/yohannesmulu

በስልክ
0913171017
ይደውሉልን

Achieved Diploma in Global Digital Literacy

Address

Piazza
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohannes Mulu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yohannes Mulu:

Share