የኛ Tube

የኛ Tube የኢትዮጵያ ድምጽ፣ የኛ እይታ

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷልሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የምክክር ሂደት የሚያጠናቅቅበት ምዕራፍ ላይ ደርሷል።ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አራት የሥራ ቡ...
13/08/2026

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የምክክር ሂደት የሚያጠናቅቅበት ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አራት የሥራ ቡድኖች ተጠናቅረው በቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በተዘጋጁ የቃለ ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል ቢልም፤ በአራቱ የሥራ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙ “በርካታ” ተመካካሪዎች በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ አለመፈረማቸውን ከምንጮቿ ሰምታናል።

13/08/2026

የIMF ነገር🤔

50ሺህ ብር የሚያስቀጣው ደንብ ወደ ትግበራ ገባ‼በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ባሮች፣ ሬስቶራንቶች እና ሆቴሎች ውስጥ በሚሰሩ ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስና ጌጣጌጥ አጠቃቀም ላይ የተደ...
13/08/2026

50ሺህ ብር የሚያስቀጣው ደንብ ወደ ትግበራ ገባ‼

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ባሮች፣ ሬስቶራንቶች እና ሆቴሎች ውስጥ በሚሰሩ ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስና ጌጣጌጥ አጠቃቀም ላይ የተደነገገው አዲሱ ደንብ ቁጥር 178/2017 በሙሉ አቅሙ ወደ ትግበራ መግባቱ ተገልጿል።

የኛ Tube

13/08/2026

ሻደዩሳ ባሎ አብራ ኬቤርፅንስ🔥
ነሀሲ 17ስ አዲስ አበባዳ ውላጊ ታምትጝኔስ🔥

#የኛ

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arb...
13/08/2026

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arbitration) የምስለ-ችሎት ውድድር (FDI Moot) የዞኑ አሸናፊ በመሆን አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን ገለጹ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት በዚህ ፈታኝ ውድድር ከናይጄሪያ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 14 ቡድኖችን በመበለጥ ከሰብ-ሳሃራን አፍሪካ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።

ይህ የፀጉር አሰራር ምን ይበላል?የየት አካባቢስ ባህልስ ነው?
13/08/2026

ይህ የፀጉር አሰራር ምን ይበላል?
የየት አካባቢስ ባህልስ ነው?

13/08/2026

የአማራ የውርደት ዘመን ነው ይለናል
እውነትም የአማራ የውርደት ዘመን ነው ወይ? እስኪ ሀሳባችሁን አካፍሉን‼

#አማራ #የኛ

13/08/2026

Smile💙

#የኛ

በመተከል ዞን ታጣቂዎች በተፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩበቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸ...
13/08/2026

በመተከል ዞን ታጣቂዎች በተፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 6/ 2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እና መናኸሪያ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪ "ሕይወቱ ያለፈም፣ ከባድም ቀላልም ጉዳት የደረሰበትም ሰው አለ" ያሉ አንድ ነዋሪ "11 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን" እንደሰሙ ጠቅሰዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር "በትክክል አለመታወቁንም" ተናግረዋል።
"በገብርኤል እና በማሪያም እበያተ ክርስቲያን፣ በመስቀል አደባባይ ላይም ሞርታር መሣሪያ ተጥሎ" በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪው ተናግረዋል።
ወደ ከተማው በእግር የገቡ "አሸባሪዎች" ያሏቸው ታጣቂዎች በአድማ በታኝ እና በመከላከያ ኃይል "መመለስ መቻሉን" ተናግረዋል።
የመተከል ዞን አስተዳደር በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ አጥቂዎቹ "የጉሙዝ ታጣቂዎች እና የፋኖ ኃይሎች" መሆናቸውን ጠቁሞ ጥቃቱ ግን "መክሸፉን" ገልጿል።
ዞኑ፤ ታጣቂዎቹ ወደ ግልገል በለስ ከተማ ለመግባት እና በንጹኃን ዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ "ሙከራ" ማድጋቸውን ባወጣው አጭር መግለጫ ጠቅሷል።

ዞኑ ይህን ቢልም እንኳን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በከባድ መሣሪያ በታገዘው ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
ጥቃቱን ከፈጸሙት ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የገለጹት ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌላ የአካባቢው ነዋሪ "ቀይ ሰው ከዚህ አካባቢ ይውጣልን ነው የሚሉት" በማለት የጥቃቱ ዓላማ "ብሔር ተኮር" እንደሆነ ተናግረዋል።
በመናኸሪያ እና በእብያተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው "ሕዝብ የሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች" ስለሆኑ ነው ብለውም ያምናሉ።
በታጣቂዎች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል "ሰዓታት የወሰደ" የተኩስ ልውውጥ እንደተደረገም ነዋሪው ተናግረዋል።
መናኸሪያ አካባቢ የተጎዱት ሰዎች ወደተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎች መሆናቸውን አክለዋል።
በቤተ ክርስቲያን የተጎዱት "የሃይማኖት አባቶች" መሆናቸውን ተናግረዋል።
እስከ ንጋት አንድ ሰዓት ድረስ የተኩስ ልውውጥ እንደቀጠለ እና ከዚያ በኋላ "አካባቢው ሰላም እንደሆነ" ገልጸዋል።
ሆኖም ግን "ነገ ለሚያጋጥመው ምንም ዋስትና የለንም" ሲሉ ስጋታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሌላ ነዋሪ ደግሞ መናኸሪያ ሄደው አስከሬን ማንሳታቸውን ተናግረው፤ የቆሰሉ ሰዎች ወደ ፓዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪው የተኩስ ልውውጡ እስከ "ሦስት ሰዓት ድረስ" እንደቀጠለ እና መናኸሪያ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት "ከስምንት በላይ ሰዎች እንደሞቱ" ተናግረዋል።
"ከባድ ጉዳት ነው የደረሰው። እኔም መናኸሪያ የነበረውን በዐይኔ አይቻለሁ። ከስምንት በላይ ሰዎች እዚያው ሞተው ወድቀዋል። ቁስለኞቹ በሀይሩፍም፤ በአባዱላም እየተጫኑ ወደ ፓዊ ሆስፒታል ተወስደዋል። ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እኛም ሁለት ቁስለኞችን ወደ ሐኪም ቤት አስገብተናል" ብለዋል።
ወደ ማንኩሽ እና አሶሳ የሚጓዙ ሰዎች በመናኸሪያው ውስጥ እንደነበሩ እና "ሁለት ሞርተር ተተኩሶ አንደኛው እንደፈነዳ" ተናግረዋል።
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ንጹኃን ሰዎች እንደሆኑ የተናገሩት ነዋሪው "ቀድሞ እርምጃ መወሰድ" እንደነበረበት ሳይጠቅሱ አላለፉም።
አብዛኞቹ ሟቾች ወጣቶች እና መንገደኞች መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ነዋሪዎች አካባቢው አሁን መረጋጋቱን የተናገሩ ሲሆን፤ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከተማውን መቆጣጠራቸውንም ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ ነዋሪዎቹ አሁንም ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
"እንዲህ ዓይነት ነገር ግልገል በለስ ውስጥ ብዙ ጊዜ የተለመደ ነው። እንደዚህ ተኩሶች ይደረጋሉ። የሆነ ያህል ሕዝብ ይሞታል። ከዚያ በኋላ በነጋታው ሕዝቡ እንደ አዲስ ሥራውን ይጀምራል።
"የፀጥታ አካላት አሁን ላይ ምንም የሉም ማለት ይቻላል። ሰው የለመደው ነገር ስለሆነ ወጥቶ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" ሲሉ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ ገልጸዋል።
ቢቢሲ ከዞኑ አስተዳዳር እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለሥልጣናት ስለጥቃቱ እና ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ምላሽ አላገኘም።
በመተከል ዞን እንዲህ ዓይነት ተደጋጋሚ ጥቃቶች የሚፈጸሙ ሲሆን፤ ባለፈው ግንቦት እና ሚያዚያ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ እና በማረሚያ ቤት ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።
ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት ሲሆን፣ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጽማሉ።

Via:-BBC

የኛ Tube

ቀጣዩ የመንግስት አስተዳደር ሥርዓት ምን ይሁን የሚለዉ ውይይትበሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 27ኛ ቀን በሥራ ቡድኖች ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ምክክር ቀጥሎ ውሏል። በሰባቱ የሥራ ቡድኖች ቅዳሜ ...
12/08/2026

ቀጣዩ የመንግስት አስተዳደር ሥርዓት ምን ይሁን የሚለዉ ውይይት

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 27ኛ ቀን በሥራ ቡድኖች ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ምክክር ቀጥሎ ውሏል። በሰባቱ የሥራ ቡድኖች ቅዳሜ ነሐሴ 02 ቀን የጀመረው የተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ላይ አስተያየት የመስጠት ሂደት የቀጠለ ሲሆን፤ የፌደራል ከተሞች ጉዳይን እየተመካከረበት በሚገኘው የሥራ ቡድን 7 ደግሞ የተጠናቀረው የአጀንዳ ምክረ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ተነቧል።

Address

Gofa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኛ Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የኛ Tube:

Shortcuts

Share

Category