Addis Ababa Daily News

Addis Ababa Daily News Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa Daily News, Media/News Company, Addis Ababa.

በአማራ ክልል የሚገኘውን ጽንፈኛውን የማጽዳት ዘመቻው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አዴት ላይ ጽንፈኛው ከግለሰቦች በመስረቅ ደብቋቸው የነበሩት የግለሰቦችና የንግድ መኪኖች በዚህ መልኩ ተደብቀው ተ...
16/12/2024

በአማራ ክልል የሚገኘውን ጽንፈኛውን የማጽዳት ዘመቻው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አዴት ላይ ጽንፈኛው ከግለሰቦች በመስረቅ ደብቋቸው የነበሩት የግለሰቦችና የንግድ መኪኖች በዚህ መልኩ ተደብቀው ተገኝተዋል:: ጽንፈማው በያለበት እግሬ አውጪም በማለት በመሮጥ ላይ ነው::

 የራሱን የሰርግ መልስ ፕሮግራም አቋርጦ የአንዲትን ወላድ እናት ህይወት ያተረፈው ዶክተርትናንት እሁድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በሆሣዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሠቢያ...
16/12/2024


የራሱን የሰርግ መልስ ፕሮግራም አቋርጦ የአንዲትን ወላድ እናት ህይወት ያተረፈው ዶክተር

ትናንት እሁድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በሆሣዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሠቢያ ሆስፒታል የታዘብኩትን አንድ ሠናይ ተግባር ላካፍላችሁ።

ይህ ጀግና ወጣት ትናንት እሁድ በራሣቸው የመልስ ፕሮግራም ላይ ባሉበት የአንዲትን ወላድ እናት ህይወት እንድያድኑ መልዕክት ስደርሳቸው

ሙሽሪቷንና አጃቢ እንግዶቻቸውን አስፈቅደው የመልስ ፕሮግራሙን አቋርጠው ሆስፒታል በመምጣት የተሣካ ኦፕሬሽን በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር የወላዲቷን ህይወት ከነህፃኗ ማትረፍ ችለዋል።

እንደ ዶ/ር በየነ ዓይነት ለሙያቸው ክብር የሚሰጡ፣ የሰው ህይወት ለማዳን የገቡትን ቃለ-መሃላ የሚጠብቁ፣ በጎ ህልናና መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው ቅኖችን ፈጣሪ ያብዛልን።

Being an engineer is proud!  We will see in Jimma town soon! For Jimma town!
16/12/2024

Being an engineer is proud!
We will see in Jimma town soon!
For Jimma town!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጸደቀአዲስ አበባ ፤ ህዳር 15/2016 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤ...
25/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 15/2016 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ አዋጁን ያጸደቀው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው።

በዚሁ መሰረት መልሰው የተቋቋሙት ተቋማት፡-

1- የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

2- የስራ እና ክህሎት ቢሮ

3- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ

4- የፕላን እና ልማት ቢሮ

5- የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን

6- የህብረት ስራ ኮሚሽን

7- የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን

8- የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

9- የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

10- የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

11- የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ናቸው፡፡

ተቋማቱን መልሶ ማቋቋም ያስፈለገው የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ይጠቁማል፡፡

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው ታላቁ ሩጫ ምንድነው የሆነው? በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ታላቁ ሩጫ ላይ የተሳተፉ የስፖርት ቤተሰቦች ከ45,000 እስከ 50, ...
20/11/2023

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው ታላቁ ሩጫ ምንድነው የሆነው?

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ታላቁ ሩጫ ላይ የተሳተፉ የስፖርት ቤተሰቦች ከ45,000 እስከ 50, 000 የሚገመት ነው።

99.9℅ ተሳታፊ ስፖርት ለጤና፣ ለህዝቦች አንድነትና አብሮነት በሚል መርህ ሩጫውን አጠቅቆ ነው ወደቤቱ የተመለሰው።

ከጠቅላላው ተሳታፊዎች 1℅ አንኳ የማይሞሉ አንዳንድ በጥላቻ ልክፍት የተመቱ ግለሰቦች ለቲክቶክ መንደር ማሞቂያ ይጠቅመናል ብለው ያሰቡትን ከፋፋይ ሀሳብ አቀርሽተዋል።

እነዚያ ይመጣሉ እያሉ የዘመሩላቸው ያረጀውንና ያፈጀውን ስርዓት ለማስመለስ የሚኳትኑ ምስኪን የስልጣን ጥመኞች በ24 ውስጥ 4ኪሎ እንገባለን ካሉ ሰነባብተዋል።

ምኞት አይከለከልም ያለው ማን ነበር?

21/11/2022

ብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካው ዋነኛው ዓላማ ለሁሉም የምትስማማ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የምትመስል፣ የበለፀገች፣ የብሔሮችን መብት ከግለሰብ መብቶች ጋር አጣጥማ የምታስጠብቅ፣ ጠንካራ ፌደራላዊት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው።

ይህን ዓላማ ለማሳካት የምንከተለው መንገድ፦
👉 እስካዛሬ እንደ ሀገር ባስመዘብናቸው ድሎች ላይ መገንባት

👉 የቀድሞውን ትሩፋትና ስኬት ማስጠበቅና ማጠናከር

👉 ከቀድሞ ስህተቶች መማርና መታረም

👉 በጎውን በማስቀጠልና በማሳደግ፣ ክፉውን ማረምና አለመድገም ናቸው።

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!!
Addis Ababa Prosperity Party

 ;-
14/07/2022

;-

 Siidawwaan tibba kana eebbiffaman~~Siidaa Luba Guddinaa Tumsaa~Siidaa Sheek Mohammeed Rashaad Abdulle~Siidaa Dr.Hayilee...
08/07/2022


Siidawwaan tibba kana eebbiffaman~

~Siidaa Luba Guddinaa Tumsaa

~Siidaa Sheek Mohammeed Rashaad Abdulle

~Siidaa Dr.Hayilee Fidaa

~Siidaa Onesimoos Nasiib

~Siidaa Sheek Bakrii Saphaloo

26/06/2022

የህግ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ለሁሉም የሚበጀው የህግ በላይነት የሰፈነባት ሃገር ስትኖረን ነው፡፡ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን የሁላችንም ሃላፊነትና ተግበር መሆን አለበት!!
ህዝቡ በሁሉም አግባብ መንግስትን የጠየቀው ጠንካራ የህግ ማስከበር እንዲደረግና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ነው፡፡ ለዚህም ምላሽ መንግስት በየደረጃው ከህግ በላይ ነን የሚሉ ሃይሎችን ህግ ማስከበር በመጀመሩ ምክንያት በየቦታው ሰላም እየሆነ መጥቷል፡፡
አሁንም በዚህ የህግ ማስከበር ዘመቻ ህልውናቸው እያበቃ እንደሆነ የተረዱ ሃይሎች በጭካኔ በህዝብ ላይ ለፈፀሙት ድርጊት የእጃቸውን ያገኛሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ወደ ኋላ የሚመለስ የህግ ማስከበር ስራ አይኖርም፤ ይልቁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ሰዎችን በስሜት በማነሳሳት የህግ ማስከበሩን ዘመቻ ማደናቀፍ በጭራሽ አይቻልም!!

እኔ ወይም የእኔ ቡድን ብቻ ብሎ ማሰብ ለኢትዮጵያ አይሆንም !!ህብረብሄራዊነት ባለበት ጽንፈኝነት የበለጠ አደጋ ነው !! # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #በኢ...
19/06/2022

እኔ ወይም የእኔ ቡድን ብቻ ብሎ ማሰብ ለኢትዮጵያ አይሆንም !!
ህብረብሄራዊነት ባለበት ጽንፈኝነት የበለጠ አደጋ ነው !!
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

በኢትዮጵያ በመሰረታዊነት መቀየር (Transformed) መሆን ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ለዘመናት የተገነባው የፖለቲካ ልምምዳችን ነው። ፖለቲካችን በጽንፍ ወይም በዋልታ-ረገጥ ዕይታዎች የተወጠረ ነው።
በፖለቲካ ልሂቃን መካከል ጫፍ ና ጫፍ ቆሞ ገመድ መጓተት ፣ እልህ መጋባትና ማኩረፍ ፣ ብጥብጥ መፍጠርና የህዝብን ሠላም ማደፍረስ ፣ያለመደማመጥ ፣ እኔ /የእኛ ቡድን ብቻ ልክ ነን ፣ ፍፁም እውነተኛ ነን ብሎ ማሰብ፣የተለየ ሀሳብ የያዘን አካል እንደ ጠላት ማየት ፣ ስለሆነም የሀሳብ ልዩነት በሀይልና አውዳሚ በሆነ መንገድ የመፍታት አባዜ ውስጥ ቆይተናል። ይህ እጅግ ኋላቀር የፖለቲካ ልምምድ ጽንፈኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እያቆጠቆጠ እንዲመጣ መነሻ ሆኗል። በፅንፈኝነት ምክንያት ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ሰላም ፣አንድነትና ልማት ፈተና ውስጥ ነው።
ስለ ጽንፈኝነት (Extremism)
በርካታ መዝገበ ቃላት ሲተረጎሙ ኢ- ምክንያታዊና በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ርይኦተዓለም፣ ባህርይ፣ እምነትና ድርጊት እንደሆነ ያስቀምጣሉ ፡፡ አንዳንድ ምንጮች እንደሚገልጹት የጽንፈኝነት ተመሳሳይ ቃላት (ሃሳቦች) ዋልታ-ረገጥነት ፣ ዘረኝነትን፣ ሌላን ጥላቻ ፣ ያለመቻቻል፣ ኢ- ፍትሐዊነት፣ የሞራል ዝቅጠትና ልክ የለሽ ግለኝነት ናቸው፡፡
ጽንፈኝነት ዴሞክራሲያዊ አሰራርንና መንግስትን፣ የሕግ የበላይነትን፣ የግለሰቦች ነጻነትን፣ ልዩነቶችን ማክበርና ማስተናገድን፣ ችግሮችን በሕግና በውይይት መፍታትን፣ በመሬት ላይ ያለውን ማህበራዊ ስርዓት አይቀበልም፡፡
ጽንፈኝነት በሕብረተሰቡ ውስጥ ያለመረጋጋትን፣ ያለመተማመንንና ያለመተባበርን ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም ሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ይስተጋጎላሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት (2015) plan of action to prevent violent extremism በሚለው ዕቅድ/ ሰነድ እንደገለጸው ጽንፈኝነት የአንድን ቡድን ፍላጎት ለማሟላት፣ ሌለውን ወገን ለመጨቆንና ለማፈን፣ በወቅቱ ያለውን ማህበራዊና ፓለቲካዊ ስርዓት ለማናጋት፣ በአብዛኛው በሰዎችና በጾታዎች እኩልነት የማያምን አካሄድና ክስተት እንደሆነ ያመለክታል፡፡
ሰዎች ጽንፈኛ ሆነው አይወለዱም፣ በአንድ ቀንም ጽንፈኛ አይሆኑም ዘራቸው/ጎሳቸው ወይም ሃይማኖታቸውም ጽንፈኛ አያደርጋቸውም። ዕድገት፣ ኑሮ፣ ጓደኛ፣ ትምህርት፣ ሚዲያ፣ ውሎ፣ ወዘተ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡፡
የሳልታር (2004) ጥናት እንደሚያሳየው ጽንፈኞች የሰዎችን የእኩልነት መብት አይቀበሉም፣ የተለያዩ ብሔሮች ፣ ዘሮችንና ሃይማኖቶችን ይሳደባሉ አክብሮት የላቸውም፣ ጥላቻም ያንጸባርቃሉ ፣ዛቻና ማስፈራራትን ይጠቀማሉ፡፡
ጽንፈኝነት ሰላምን ያናጋል፣ ሰዎች ደህንነት እንዳይሰማቸው ያደርጋል፣ ለአገር ልማትም እንቅፋት ነው፡፡
ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በብዛቱም ሆነ በዓይነቱ በአውደሚነቱና የዜጎችን ሰላም በማወክ ረገድ ከፍተኛና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ከዕለት ተእለት እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል ፡፡ ጽንፈኞች የፓለቲካ ፕሮጀክታቸው መጠቀሚያ የሚያደርጉት ብሔር እና ሀይማኖትን ነው። ለዚህም ነው ዛሬ በሀገራችን በብሔር እና በሃይማኖት ስም ዘግናኝ ድርጊቶች እየተፈፀሙ ያሉት።
ለኢትዮጵያ ጽንፈኝነት በፍፁም ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያ በብዛሀነት ያገጠች ስትሆን ፤ጽንፍኝነት ደግሞ ከብዛሃነት ጋር እሳትና ጭድ ነው። ይህ ሁኔታ መቀየር አለበት።
የአገራችን የፖለቲካ ዕይታና ተግባር አካታች እና አሳታፊ ፣ በሀሳብ በላይነት የሚያምን ወደ መሆን መሸጋገር የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ነን። ፖለቲካችን ከመጠላለፍ ፣መጠፋፋትና ሴራ ወጥቶ ወደ አድስ አቅጣጫ የአስተሳሰብ ሽግግር ማድረግ አለበት። በውይይት እና ድርድር ፣ በፉክክር እና ትብብር መካከል ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል። በመብትና ግዴታ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታና የሃገር ሰላም ፀጥታ መካከል ሚዛን መጠበቅ አለብን። ህብረተሰቡ በአጠቃላይ፣ መንግስት፣ ት/ቤቶች ሚዲያ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ለሰላምና ለአገር አንድነትና ዕድገት የቆሙ ኃይሎች በሙሉ ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥተው ጽንፈኝነትን በጋራ መከላከል ተገቢ ነው።
ጽንፈኝነት ሄዶ ሄዶ አገር ያፈርሳል፣ ሰላም ያጠፋል ፣አዉዳሚ ነው።
የዛሬው ትውልድ ስለ ኢትዮጵያችን አንድነት ፣ ህዝቡ ሰላም ፣ ዕድገትና ብልፅግና ሲባል ጽንፈኝነትን በተባበረ ኃይል የመከላከል አገራዊ ኃላፊነት ወድቆበታል።
ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት !!!

በG7 ስብሰባ ላይ  ኢትዮጵያ ተወድሳለች ተሞካሽታለች‼️➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ይህም ተብሏል " ኢትዮጵያን ተመልከቱ.... ! አፍሪካ በምግብ ምርት ራሷን ትችላለች። ኢትዮጵያን ተመልከቱ የስንዴ...
02/06/2022

በG7 ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ተወድሳለች ተሞካሽታለች‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ይህም ተብሏል " ኢትዮጵያን ተመልከቱ.... ! አፍሪካ በምግብ ምርት ራሷን ትችላለች። ኢትዮጵያን ተመልከቱ የስንዴ ምርቷን በታላቅ እመርታ በተጨማሪ 2.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አስመንጭቃዋለች። ኢትዮጵያ ከዚህ በውሃላ ስንዴ ከውጭ አታስገባም። በሚቀጥለው ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ስንዴ ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር እንደምትሆን እርግጠኞች ነን። የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ግብርና እመርታ ደጋፊ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል።"
Akinwumi Adesina - የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት

ህንዳዊው ባለሀብት ስሙን "ለሚ ኦዳ" ብሎ  ቀየረትላንት ናሁ ቴሌቪዥን  ላይ ከፒተር ሾው ጋር ቆይታ የነበረው ህንዳዊው ባለሃብት በሞጋሳ ስርዓት "ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ" ያለ ሲሆን  ከዚህም የ...
30/05/2022

ህንዳዊው ባለሀብት ስሙን "ለሚ ኦዳ" ብሎ ቀየረ

ትላንት ናሁ ቴሌቪዥን ላይ ከፒተር ሾው ጋር ቆይታ የነበረው ህንዳዊው ባለሃብት በሞጋሳ ስርዓት "ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ" ያለ ሲሆን ከዚህም የተነሳ "ስሜ ለሚ ኦዳ ሆኗል" ብሏል።

የሐበሻ ስቲል ብረታ ብረት ድርጅት ማኔጅንግ ዳይሬክተር ኪቨን ራቫን ወይም "ለሚ ኦዳ" በድርጅታቸው በኩል ብዙ ህፃናትን እያስተማሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

የአማራ ጨቅላ ብሄርተኝነት ደቀመዛሙርቶቹን እያወዛገበ ነዉ።===የክርስቲያን  ታደለ  የፖለቲካ አላዋቂነት  ሲገለጥ!የአብን አመራሮች እና የብልጽግና  አመራሮች በፖለቲካ ርዕዮተአለም ሆነ   ...
16/05/2022

የአማራ ጨቅላ ብሄርተኝነት ደቀመዛሙርቶቹን እያወዛገበ ነዉ።
===

የክርስቲያን ታደለ የፖለቲካ አላዋቂነት ሲገለጥ!

የአብን አመራሮች እና የብልጽግና አመራሮች በፖለቲካ ርዕዮተአለም ሆነ የሚታገሉለት አለማ እንዲሁም የፓርቲ መርሃቸው የሰማይና የምደር ያህል ልዩነት እንዳለው ይታወቃል። አብን ብሄር ተኮር ሆኖ ለአማራ ብቻ እወክላለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በሌላ ጎኑ ደግሞ ብልጽግና ደግሞ ህብረ ብሄራዊና አካታች የሆነ ፓርቲ ነው ታዲያ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ሆድ እና ጀርባ መሆናቸው እየታወቀ አቶ ክርስቲያን ታደለ የአብንን አመራሮች ከአማራ ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር አላኮ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል ። ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ እንዲሉ የየትኛውን ከየትኛው ጋር ያገናኛል ሌላው የአብን አመራሮች እንዴት እንደ አንድ ትልቅ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የውስጣቸውን ችግር እንደሰለጠነ ሰው በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር መፍታት እየቻሉ ወደማይመለከተው ፓርቲ ማላከኩ የሁለተናዊ ውስንነት እንደሚስተዋልባቸው ያረጋግጣል።። ክርስቲያን ታደለ የተባለ ደነዝ በአብን ውስጥ በተደጋጋሚ በሚፈጥረው የዲስፕሊን ችግር ፓርቲው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተባለውን የቢጫ ካርድ አሳይቶታል። ታዲያ ይህ ሰው ችግሬ ምን ይሆን ብሎ ማስተካከል ያለብኝ ነገር ምንድነው በማለት ውስጡን ማየት ሳይችል ሌላኛውን ችግር ለመውቀስ እንዴት ይጣደፋል። እውነታው ግን ክርስቲያን/ደምለው በዋናነት በፓርቲው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው የፓርቲውን ሚስጥር በማባከን እንዲሁም በመዋለ ንዋይ በመታለል ከአማራው ጠላት ከሆነው ወያኔ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥ ፣ሰንዶችን በመፈራረም ላይ መሆኑን ስለተደረስበት ነው።
ሌላው ክርስቲያን እና አምሳያዎቹ ያልተረዱት ነገር ቢኖር አብን ሰማይ ዝቅ ቢል ምድር ከፍ ቢል የኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄር በሄረሰቦች መሪ ሆኖ መንግስት መሆን አይችልም ምክንያቱም አብን ክልላዊና አማራ ብሄር ብቻ ተኮር ነው ለምን ካልን አብን አማራን ብቻ ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ እንጂ ኢትዮጵያ ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አይደለም አለቀ!!ስለሆነም አብን በምርጫ 100% ቢያሸንፍ እንኳ ኢትዮጵያን ሳይሆን የሚመራው አማራ ክልልን ብቻ ነው ታዲያ የአብን የፖለቲካ ድርጂት ሃላፊ ነኝ የሚለው ደምለው ይህን ሳያውቅ ነው እንዴ የአብን ከፍተኛ አመራር እንደሆነ የሚነገረው! ይገርማል ብቻ !!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ ሕንፃ ጎበኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሸጎሌ የሚገኘው እና በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ ሕንፃ ጎብኝተዋል...
17/04/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ ሕንፃ ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሸጎሌ የሚገኘው እና በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ ሕንፃ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአሠራር ምቹ ያልሆነው የኢቢሲ የአሁኑ ሕንፃ በአዲስ እንደሚቀየር ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር ውይይት ባደረጉት ወቅት ቃል ገብተው ነበር።

በዛሬው ዕለትም በሸጎሌ የሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ሕንፃ ያለበትን ሂደት ተመልክተዋል።

አዲሱ የኢቢሲ ሕንፃ ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ሥራ የሚጀምር ሲሆን ሕንፃው ዘመናዊ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ስቱዲዮች ይኖሩታል።

ይህም ተቋሙ በይዘት እና አቀራረብ የተሻለ ሆኖ ለመውጣት እያደረገ ያለውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያሳድግለት ታምኖበታል።

ሕብረ-ብሄራዊነትና ወንድማማችነት ጽኑ የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ነው፡፡ መከባበር፤ ለጋራ ሀገራዊ ጥቅም አብሮ መቆም፤ ከልዩነት ይልቅ የጋራ እሴቶቻችንን ማጽናት ዘላቂ መፍትሄ ነው፡፡ ጽንፈ...
04/04/2022

ሕብረ-ብሄራዊነትና ወንድማማችነት ጽኑ የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ነው፡፡ መከባበር፤ ለጋራ ሀገራዊ ጥቅም አብሮ መቆም፤ ከልዩነት ይልቅ የጋራ እሴቶቻችንን ማጽናት ዘላቂ መፍትሄ ነው፡፡ ጽንፈኝነት የሚወክለው ብሄርም ሆነ ሃይማኖት የለውም፡፡ ለማንም ለምንም አይጠቅምም፡፡ ጸረ ህዝብ እሰከ ሆነ ድረስ ተመሳሳይ አቋም በመያዝ በጋራ ልንታገለው ይገባል፡፡

የአሜሪካ ቅዠት የሆነው የቻይና ኢኮኖሚ !! ከዛሬ 10 አመት በፊት ነበር ቻይና የጃፓንን የኢኮኖሚ ደረጃ በመንጠቅ ከአለም ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤትነቷን የተቆናጠጠችው። የቻይና ተአ...
31/03/2022

የአሜሪካ ቅዠት የሆነው የቻይና ኢኮኖሚ !!

ከዛሬ 10 አመት በፊት ነበር ቻይና የጃፓንን የኢኮኖሚ ደረጃ በመንጠቅ ከአለም ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤትነቷን የተቆናጠጠችው። የቻይና ተአምራዊ የኢኮኖሚ እመርታ በዚያው ግስጋሴ ይቀጥላል ብሎ የገመተ አልነበረም። አሜሪካን የሚያስጨንቅ የኢኮኖሚ ሀያልነትም በዚህ ቅርብ አመት ታሳካለች ብሎም የጠበቀ አልነበረም።

እርሷ ግን ተአምራዊ ህዝቦች ያሏት ተአምራዊ ሀገር ነበረችና ሁሉንም አልፋቸው ሄደች። አሜሪካ የቻይናን የኢኮኖሚ ግስጋሴ ለማስቆም ያላደረገችው ጥረትና ሴራ አልነበረም የቻይና ጡንቻ ግን የአሜሪካን የሴራ ምት ከምንም የማይቆጥር አለት ነበር።

ከሁለት አመት በፊት አሜሪካ የቻይናን ኢኮኖሚ ለማድቀቅ በርካታ ታሪፍና የማእቀብ አለንጋዎቿን ብታሳርፍባትም የቻይና ገላ ግን ጥይት የማይበሳው ደንዳና ነበር። አሜሪካ በቻይና ላይ በወሰደቻቸው እያንዳንዷ እርምጃዎች ተጎጂዋ ራሷ አሜሪካ ነበረች !

የኮሮና ወረርሽኝ አሜሪካን ድቅቅ አድርጎ ሲመታት ቻይና ግን ከአለም ዝቅተኛዋ የወረርሽኙ ተጠቂ ነበረች ! አሁን አሜሪካ ቻይናን ብቻዋን እንደማታስቆማት አምናለች። እናም ለጀሌዎቿ የአውሮፓ መንግስታት "ቻይናን አብረን እንመክት" ስትል ጥሪ ለማቅረብ ተገደደች። የቡድን 7 ሀገራት ቻይናን የሚገዳደር ጥምረት ለመፍጠር ቢስማሙም አሜሪካ ቻይናን ማስቆም መፎካከር ስላልቻለች ነው።

ቻይና "አንድ ቀበቶ አንድ መንገድ" ለተሰኘው ፕሮጀክቷ የመደበችው በጀት ብቻ 1.6 ትሪሊዮን ዶላር ነው። ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ አለምን በንግድና ቴክኖሎጂ የሚያስተሳስር ሲሆን ይህም ምእራባዊያንን ከአለም መሪነት መንበራቸው ገልብጦ የሚጥል ነው።

በአሁኑ ሰአት የቻይናን ያክል አስፈሪ ሀይል የለም ! በኢኮኖሚ አሜሪካን አልፋ ሂዳለች። በወታደራዊው ዘርፍ ያላትን ትክክለኛ አቅም የሚያውቅ የለም ምክንያቱም ቻይና እጅግ ሚስጥራዊ ሀገር ናትና! ቻይና በአመት ለጦር በጀቷ ከ 200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ትበጅታለች ቢባልም ጉዳዩን በቅርብ የሚያጠኑ ጠበብቶች ግን የቻይና የጦር በጀት ከ600 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ይናገራሉ። ይህም ከአሜሪካ ጋር ተቀራራቢ ማለት ነው።

ቻይና ከምእራባውያን አፍሪካን ቀምታቸዋለች ! ላቲን አሜሪካን ቀምታቸዋለች! አብዛኛው ኤዥያን ቀምታቸዋለች ! እንኳን ሌላው ቀርቶ አውሮፓ እንኳ ያለ ቻይና አይሆንላቸውም!

በ2021 በወጣው ሪፖርት ቻይና የዓለም ቁጥር አንድ ባለ-ፀጋነት ደረጃን ጨብጣለች። ቻይና አጠቃላይ ሀገራዊ ሀብቷ 120 ትሪሊየን ዶላር በማስመዝገብ አሜሪካን በልጣ የምድራችን ሀብታምነት ደረጃን መጨበጧ ይፋ ተደርጓል። የቻይና ሀብት በፈረንጆቹ 2000 7 ትሪሊየን ዶላር ነበር፡፡ በሁለት አስርት አመታት ውስጥ የ113 ትሪሊየን ዶላር እድገት ማስመዝገብ ችላለች። የአሜሪካ ሀገራዊ ጠቅላላ ሃብት 90 ትሪሊየን ዶላር በመሆን 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን " IMF " በጥናታዊ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።

   ቻይና ለአሜሪካ ባለስልጣት የቪዛ አገልግሎት ላለመስጠት ወሰነች።ይህ ውሳኔ አሜሪካ ለቻይና ባለሰልጣናት ቪዛ እንደማትሰጥ ከገለፀች በኃላ በቻይና የተሰጠ ተመሳሳይ የአፀፋ ምላሽ ነው።አሜሪ...
31/03/2022



ቻይና ለአሜሪካ ባለስልጣት የቪዛ አገልግሎት ላለመስጠት ወሰነች።

ይህ ውሳኔ አሜሪካ ለቻይና ባለሰልጣናት ቪዛ እንደማትሰጥ ከገለፀች በኃላ በቻይና የተሰጠ ተመሳሳይ የአፀፋ ምላሽ ነው።

አሜሪካ ሰኞ ዕለት በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ላይ እጃቸው አለበት ባለቻቸው የቻይና ባለስልጣናት ላይ ነው የቪዛ እገዳ ጥላ ነበር።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share