Asaye Derbie

17/07/2025

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ አንድ እስረኛ ሕይወቱ አለፈ።

እስረኛው ሕይወቱ ያለፈው በህክምና እጦት ምክንያት መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሐ ሚዲያ ገልፀዋል።

አቶ አባይነህ አለማየሁ የተባሉ የ63 ዓመት አዛውንት ከባህርዳር ወንድማቸውን ለመጠየቅ አዲስ አበባ እንደገቡ 'ከፋኖ ታጣቂዎች ተልዕኮ ተቀበለህ መጥተሀል' በሚል በፌደራል ፖሊስ ተጠርጥረው ለአራት ወራት ያህል በእስር ላይ መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ጨምረው ተናግረዋል።

አቶ አባይነህ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ፥ በምርመራ በቆዩበት ወቅት በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ችሎት ቀርበው የተናገሩ ቢሆንም በቂ ሕክምና ሳያገኙ ቆይተዋል ሲሉ የገለፁት ቤተሰቦቻቸው ጉዳቱ በጊዜ ሂደት አመርቅዞ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ብለዋል።

በማረሚያ ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈው አቶ አባይነህ 'ህመም እየተሰማኝ ነው ወደ ሕክምና ውሰዱኝ' ቢሉም አጃቢ የለም በሚል ሕክምና ሳያገኙ መዋላቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ባልደረባ ለሚዲያችን ተናግረዋል።

አቶ አባይነህ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የሽብር ወንጀል ችሎት በአራባ ሽህ ብር ዋስ እንዲፈቱ የበየነ ቢሆንም ፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ሽብር ለመፍጠር ሲያሴሩ አግኝቻቸዋለሁ በሚል ሌላ ክስ ከፍቶ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አድርጓቸዋል ብለዋል ቤተሰቦቻቸው።

ይሄው ፍርድ ቤት በሁለተኛውም ክስ በሠላሳ ሺህ ብር ዋስ ውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ቢበይንም ሳይለቀቁ መቆየታቸውን እና በዚህ መኃል በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ደብደባ ምክንያት እና በህክምና እጦት በማረሚያ ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ገለፀዋል።
በአቶ አባይነህ አማሟት ምክንያት የተቆጡ የአማራ ተወላጅ እስረኞች ከጥበቃ አባላት ጋር ግጭት መፍጠራቸውን ነው ሚዲያችን ያረጋገጠችው።

ግጭቱ የተፈጠረው በቂሊንጦ ዞን አራት ተብሎ በሚጠራው የእስረኞች ማቆያ ሲሆን የማረሚያ ቤቱን ስም አጥፍታችኋል በሚል ኢንስፔክተር ኢብራሂም የተባሉ የማረሚያ ቤቱ የእስረኞች አስተዳደር በአማራ እስረኞች ላይ መዛታቸውን ነው ያገኘነው መረጃ የሚጠቁመው።

አቶ አባይነህ ሕክምና ማገኘት ሲገባቸው በወቅቱ ባለመወሰዳቸው ምክንያ ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የብልፅግናው መንግስት በውሸት ክስ የመሰረተባቸው የአማራ ተወላጆች ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል

17/07/2025

ውርጋጡ አገዛዝ "አቶ ልደቱ ለአስር ዓመት ያህል የኖረበትን ቤት ለማሕበራዊ ፖሊስ አገልግሎት ስለምፈልገው በአስር ቀን ውስጥ ለቅቃችሁ ውጡልኝ" የሚል ማስጠንቀቂያ ለጥፏል።

17/07/2025

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኃይሎች መተባበር የማያውቁ ቀሽሞች ካልሆኑ በስተቀር የዝናሽ ባል ቀጣዩን እንቁጣጣሽ አራት ኪሎ ውስጥ እንዲያከብር ሊፈቅዱለት አይገባም።

17/07/2025

አፋሕድ የሚባል ድርጅት ከአማራ ፋኖዎች ባለፈ ጸረ አማራዎችና ብአዴኖችም ሰርገው የገቡበት እንደ መሆኑ መጠን ባልደግፈውም የአርበኛ ደረጄ በላይን ጀግንነትና ጀብደኝነት አለማድነቅ ግን አይቻልም።

17/07/2025

ከሰሞኑን በርካታ ወገኖች በዐቢይ ታጣቂ ላይ የደረሰውን ዶፍ የሚገልጹ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ልከውልኛል። እናም እነዚያ ምስሎች ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ፋኖ ወይንም ከትግራይ ኃይሎች በላይ መከላከያ ሠራዊቱን ከመጠን በላይ እንደሚጠላውና እንደሚንቀው በግልጽ አሳይተውኛል።

17/07/2025

እናት ፓርቲ በንጹሐን ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በግልጽ በመዘገብና በማውገዝ ረገድ ከሁሉም የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የተሻለ ፓርቲ ስለሆነ የፌስቡክ አካውንታቸውን ፎሎው እና ሼር በማድረግ ድጋፋችንን እንግለጽላቸው።

https://www.facebook.com/EnatParty/

Political Party

17/07/2025

አገር ሻጩ የኦሕዴድ ብልጽግና "ባንዳ" ብሎ ከፈረጀህ "አርበኛ" ነህ። "አገር ወዳድ አርበኛ" ብሎ ከጠራህ ደግሞ ተላላኪ ባን-ዳ ሆነኻል ማለት ነው።

16/07/2025

እንደ ዘ-ሀበሻ ያሉ የአገዛዙ ልሳኖች "ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ተኮሰች" ብለው ከዘገቡ ፥ ዐቢይ ወደ ኤርትራ ተኩሶ ጦርነቱን ሊጀምር ተዘጋጅቷል ማለት ነው።

16/07/2025

ዛሬ ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ሲበር የነበረ አውሮፕላን ለማረፍ ሲሞክር ተንሸራቶ ለአደጋ መጋለጡ ታውቋል። የተጎዱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

16/07/2025

ብልፅግናዊ የኣደንዛዥ እፅ ንግድ፡ የሀገር ደህንነት ስጋት!

ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው ሙስና እና የሐሺሽ ንግድ የሀገር ደህንነት ስጋት እየሆነ መጥቷል። የሐሺሽ ንግዱ በተለይም ከላቲን አሜሪካ፣ ከብራዚል ሳኦፓሎ ጋር የተሳሰረ ነው። ሐሺሹ ለአውሮፓ ገበያ መተላለፊያ ሆኖ በቦሌ በኩል ያልፋል።

ሐሺሹ ቦሌ ሲደርስ የአቪዬሽን ደህንነት ኃላፊ፣ አቶ አስራት ቀጄላ ራሱ በሚመድባቸው የራሱ ሰዎች ሐሺሹ በጥንቃቄ እንዲያልፍ ይደረጋል። በእርሱ ትዕዛዝ መሠረትም የፕሮግራም ክፍል ኃላፊው ሚክያስ በተለይም ሴንትራል C9 ላይ ወሳኝ ሰዎቻቸውን ያስቀምጣሉ። በዚህ ቦታ ብዙ ጊዜ የምትመደበው ደግሞ ሐና ተካ ነች። ሐሺሹን ለማሳለፍ የኤርፖርት ሰዎች እስከ 20 ሺህ ዶላር (ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ) ይቀበላሉ። ኃላፊዎቹ ለበታች ሰራተኞች እስከ 200,000 ብር ወይም እስከ 100,000 ብር እንደየአስተዋጽዖአቸው ያከፋፍላሉ።

የብልጽግና መንግሥት ተሳትፎ እና የሐሺሽ ንግድ ስውር ገጽታ

ረጆ ሚዲያ ያገኘችው መረጃ እንደሚያመለክተው የሐሺሽ ንግዱን በበላይነት አቶ አስራት ቀጀላ የሚመሩት ቢሆንም፣ የብልጽግና መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይህን ተግባር ያውቁታል፤ ተጠቃሚዎችም ናቸው። እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው የብልጽግና መንግሥት ይጠቀማል ሲባል ሐሺሹን ያጨሳሉ ማለት ብቻ አይደለም። እንደ መንግሥት ከሐሺሹ የሚገኘውን ገንዘብ ለሴኪዩሪቲ ሴክተሩ እየተጠቀሙበት ይገኛል።
በዝህ የሐሺሽ ንግድ ላይ ሁለት የመንግስት አካላት ንግዱን በበላይነት ለመቆጣጠር ውስጣዊ ፍትጊያ እያደረጉ እንደሆነ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንደኛው የጅማ ካባል (Jimma Cabal) ስሆን ሌለኛው ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ነው፡፡ ሁለቱም የራሳቸውን ሰዎች በሹመት ቦታው ላይ እንድኖር ከፍተኛ ሽኩቻ ያደርጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከላቲን አሜሪካ የሚመጣው ሐሺሽ ተይዞ ለኤግዝብትነት ስቀመጥ ወዲያውኑ ወስደው ጋማውን ይሉታል፡፡
መንግሥት ወደ ሀገር ውስጥ ሐሺሽ እንዲገባ በማድረግ የራሱን ሕዝብ ሱሰኛ ሲያደርገው መገመት በራሱ ከባድ እንደሚሆን ይገባናል። ነገር ግን የብልጽግና ስብስብ ገንዘብ ይገኝበታል ከተባለ እናታቸውንም ከመሸጥ ወደኃላ የሚመለሱ እንዳልሆኑ ማንነታቸው (ስብዕናቸውን) አይቶ መገመት ደግሞ አያቅትም! ከራሱ መኪና ላይ ነዳጅ ቀድቶ የሚሸጥ፣ ቁጭራ ሰፈር እየዞረ “የታጠነ ያልታጠነ” የሚልና በስሙ ፍቄ ቫያግራና ኢትዮጵያዊ ባላታዛር ያሉበት ስብስብ ይህን አያደርጉም ብሎ መከራከር ደግሞ አይቻልም፡፡
ሲአይኤ (CIA) ቢያንስ የሚደግፋቸው ቡድኖች ከሐሺሽ ንግዳቸው እንዲያተርፉ እንዳላየ ያልፍ እንደነበር ይነገራል (ለምሳሌ በአፍጋኒስታን፣ በቬትናም እንድሁን የኢራን-ኮንትራ ቅሌቶች ይጠቀሳሉ፡፡አንዳንዶች በጥቁር አሜሪካዊያን ላይ በስፋት መሰራጨቱን ይጠቅሳሉ)። ምንም እንኳ ይህ ክስ ሲአይኤ ቢያስተባብለውም፣ የብልጽግና መንግሥት ግን በራሱ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ደባና ጥፋት እየፈፀመ ይገኛል።

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአመራር ብሄራዊ ስብጥር ጥያቄ

ቀደም ሲል ኢህአዴግ በነበረበት ጊዜ ኤርፖርቱ የትግራይ ሰዎች የተሞላ ነው ይባል ነበር። አሁን ላይ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ከምንዝር እስከ አለቃ ሌላው ብሄር ዝር እንዳትሉ ተብለው በኦሮሞዎች ተሞልቷል። ለምልክት ያህል አንድ ጋሞ እና አንድ ጉራጌ ጣል ጣል ተደርጎበታል። ይህ ከዚህ በታች ያለው የአመራር ዝርዝር የብሄራዊ ስብጥር አለመመጣጠንን በግልጽ ያሳያል፦

* የአቪዬሽን ደህንነት ኃላፊ: አስራት ቀጀላ (ኦሮሞ)

* የስጋት ተንታኝ: ሀዚም (ኦሮሞ)

* የካርጎ ኃላፊ: ማስረሻ (ኦሮሞ)

* የዓለም አቀፍ ተርሚናል ኃላፊ: ሽብሩ (ኦሮሞ)

* የጽህፈት ቤት ኃላፊ: መሰረት (ኦሮሞ)

* የሥልጠና ኃላፊ: ዜና (ኦሮሞ)

* የመግቢያ ኃላፊ: አዲሱ (ኦሮሞ)

* የፕሮግራም ኃላፊ: ሚክያስ (ኦሮሞ)

* የአስተዳደር ኃላፊ: አቦነህ (ጉራጌ)

* የሀገር ውስጥ ተርሚናል ኃላፊ: ስሞን (ጋሞ)

የት አለ ህብረ-ብሄራዊነት? የብልጽግና መንግሥት ይህን እያደረገ ያለው ለአንድ ዓላማ ነው፤ “ኦሮሞዎችን ባለጊዜዎች ናችሁ” ፤”ተረኞች ናችሁ” ለማለት ነው። የሚገባውም የሚወጣውም የሚያየው ይህንኑ ነው። ሌላውና ድብቁ ዓላማው እየፈጸመ ያለውን ወንጀል በኦሮሞ ተቀጣሪዎች ለመሸፈን ነው፡፡ ሌላው ካለበት ወንጀሉ መጋለጡ አይቀርም የሚል ስጋት አለው፡፡ ነገር ግን የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የኦሮሞ መንግሥት ሊባል ፈጽሞ አይችልም። በጦርነትም ሆነ በየእስር ቤቱ እየተሰቃየ ያለው ኦሮሞ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል።
እዝህ ስማቸው የተጠቀሱት ሁሉ ሌቦች ናቸው ማለታችን እንዳልሆነም በዝሁ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ ቅን፣ ታታሪና ታማኝ ሰራተኞችም አሉበት፡፡ በዝያው ልክ ደግሞ ሌቦችና ዘራፊዎችም አሉበት!
እዝህ ጋር ለሁሉም ግልጽ እንድሆን የሚንፈልገው የብልጽግና ስብስብ ገዳይ እንጂ ጠቃሚ ስብስብ እንዳልሆነ አይቶ መፍረድ ይቻላል።

16/07/2025

ወልቃይትን ያስከበረው የአማራ ልዩሃይልና ፋኖን ትጥቅ አስፈትቶ ወደ ወልቃይት ሊገሰግስ የነበረው አገዛዝ ጎጃም፣ ወሎ፣ ሸዋና ጎንደር ዘሎ ከገባ በኋላ ሰምጦ መቅረቱ እንጂ ብርሐኑ በቀለ ጋር ተቃቅፎ ውስኪ ሲጠጣ የሚያድረው ደመቀ ዘውዱ አይደለም። በወልቃይት ላይ ዐቢይ ያሰበውን እቅድ ያከሸፈው የፋኖ አለመሸነፍ እንጂ ዳማ ሲጫወት የሚውለው የተከዜ ዘብ አይደለም።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asaye Derbie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Asaye Derbie:

Share