ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬን ላንቺ

ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬን ላንቺ "ውድነትህን የዘነጋኸው ቀን ርካሽነትን ትቀዳጀዋለህ"
(2)

08/07/2025
እቺን ቃል ንገሯትተፈርዶብኝ እንጂመለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስልሀገሬው ምድር ላይእሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስልዞር ባለች ቁጥርአትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣትልቻለው ብዬ እንጂምሳሌ ከምሆን አ...
08/07/2025

እቺን ቃል ንገሯት
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት።

ገደል ግቢ በሏት
ይሄው ደግሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው
የእጇን አይበሉባ በቄንጥ
አኮናትራ ሰአቷን አየችው
ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው
መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና።

ማርያምን ታምራለች
ዘከርኳት በወዳች መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ
ገደል ግቢ በሏት
ልቤን ከጋረደው ወዳጅ
ከከለላት ስውር አይነጥላ
እንዲ እዳማረባት
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ

ልክ እደገላዋ ይለስልስ መንገዱ
ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት
እንደ ጥርሷ ንጣት
እያልኩኝ ፎክሬ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን
የት አባቷን እና በፀበል ካልወጣች
ትረሳለች በጅን።

ገደል ግቢ በሏት
የት አባቷን እና እንዲህ የሚያምርባት
የት እናቷን እና እንዲህ የሚደምቅባት
ገደል ግቢ በሏት
እስከ መቼ ድረስ ስቀባ
እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል
ገደል ግቢ በሏት
እኔ ገደል ስር ነኝ
ድንገት ከወደቀች እንድቀበላት።

[አስታወሰኝ ረጋሳ]

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬን ላንቺ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share