Iftu Anwar

Iftu Anwar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Iftu Anwar, Digital creator, Addis Ababa.

ትላንት ማህበረሰባችን "የወደፊት እጣ ፈንታዬን ይወስንልኛል፣ የነገ ማንነቴን ይቅርጽልኛል” በሚል ሙሉ እምነት በሰላማዊ መንገድ ተሰልፎ የመረጠበት ሂደት፣ ህዝብ የመንግስት ፅኑ መሰረት፣ መን...
04/06/2026

ትላንት ማህበረሰባችን "የወደፊት እጣ ፈንታዬን ይወስንልኛል፣ የነገ ማንነቴን ይቅርጽልኛል” በሚል ሙሉ እምነት በሰላማዊ መንገድ ተሰልፎ የመረጠበት ሂደት፣ ህዝብ የመንግስት ፅኑ መሰረት፣ መንግስት ደግሞ የህዝብ መጠለያ ጥላ መሆናቸውን በተግባር ያሳየበት ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ ህዝባዊ መሰረት ግን ዘላቂና የማይናወጥ ሀገርን መገንባት የሚችለው፣ ዛሬ ላይ በትውልድ ግንባታ ላይ ስልታዊና ጠንካራ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው። ምክንያቱም የትውልድ ግንባታ የዘላቂ ሀገር ግንባታ ዋና ምሰሶና ቀዳሚው መነሻ ነው! ትውልድ መገንባት ማለት የሀገርን ነገ መገንባት ነው። ትላንት ወላጆች ለሀገራቸው የወደፊት እጣ ፈንታ በምርጫ ካርዳቸው ያሳዩትን ቁርጠኝነት፣ ዛሬ በዕውቀት፣ በስነ-ምግባር፣ በሀገር ፍቅር እና በበሰለ አስተሳሰብ የተቃኘ ትውልድ በመቅረጽ ማስቀጠል ይገባል።
መንግስት የወጣቱን አቅም፣ የፈጠራ ክህሎት እና የሀሳብ ልዕልና የሚያጎለብቱ ምቹ ሁኔታዎችንና መድረኮችን በስፋት በማመቻቸት እውነተኛ ጥላነቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል፤ ማህበረሰቡም በበኩሉ ይህንን ትውልድ በቅንነትና በስራ ወዳድነት በማነጽ የመንግስትና የሀገር ፅኑ መሰረትነቱን በተግባር ሊያሳይ ይገባል።
ይህ በትውልድ ግንባታ ላይ የሚደረግ ከፍተኛ ትኩረት፣ ህዝብና መንግስትን ይበልጥ በማስተሳሰር ምክንያታዊ፣ ፈተናዎችን የሚቋቋምና ወደ መልካም አጋጣሚ የሚቀይር ሀገር ወዳድና ጠንካራ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል። ምክንያቱም ትውልድ ሲገነባ ሀገር በዘላቂነት ትገነባለች፤ መንግስትም እውነተኛ ጥላ፣ ህዝብም የማይናወጥ መሰረት ሆኖ ሀገራችንን ወደ ታላቅ ከፍታ ያሸጋግራታልና!

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ ማዕበል ተጀምሮ በስኬት መቋጫው ላይ ደርሷል። ይህ ክስተት ተራ የፖለቲካ ሂደት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ብስለትና አዲስ ሀገራዊ ማንነት ለዓለም ያስመሰ...
02/06/2026

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ ማዕበል ተጀምሮ በስኬት መቋጫው ላይ ደርሷል።
ይህ ክስተት ተራ የፖለቲካ ሂደት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ብስለትና አዲስ ሀገራዊ ማንነት ለዓለም ያስመሰከረ ታሪካዊ ዐውድ ነው።
ኢትዮጵያውያን በነፃነትና በዲሞክራሲያዊ እሴት ተቃኝተው፣ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን የሚወስነውን መሪ አካል በሉዓላዊ ስልጣናቸው መርጠዋል።
ይህ የነፃነት መግለጫ፤ የኢትዮጵያን አንድነትና መረጋጋት ለማይሹ፣ ሉዓላዊነቷን ለሚፈታተኑ የውስጥና የውጭ ሀይሎች የተሰጠ እጅግ ግልፅ፣ ጠንካራና የማያሻማ ምላሽ ሆኖ አልፏል።
ህዝቡ በምርጫ ካርዱ የጥፋትን ትረካዎች ባዶ ያስቀረበት፣ ከምንም ነገር በላይ ሰላምን፣ ልማትንና ዘላቂ የሀገር ግንባታን እንደሚመርጥ በተግባር አስመስክሯል። በአሁኑ ወቅት፣ ይህንን የህዝብ አደራ የተቀበሉ አካላት የተሰጣቸውን ሰፊ እድል ወደ ስራ በመቀየር፣ ህዝባቸውን በፍፁም ታማኝነትና በትጋት የማገልገል ታሪካዊ እዳ አለባቸው።
የህዝብን የውስጥ ስሜትና መሰረታዊ ፍላጎት ማድመጥ፣ የልማትና የሰላም ቀንዲል መሆን፣ እንዲሁም የሀገር ግንባታን ሂደት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር የህዝብ አደራን የመጠበቂያ ብቸኛው መንገድ ነው።

ዛሬ ምሽት መላው ዓለም በአንድ ድምፅ "አርሰናል" የሚለውን ስም የሚያስተጋባበት፣ የሻምፒዮንስ ሊግ የክብር ዋንጫ የአሸናፊዎቿን እጅ የምትስምበት ታላቅ ዕለት ነው። ይህ ስሜት የሁላችንም ነው...
30/05/2026

ዛሬ ምሽት መላው ዓለም በአንድ ድምፅ "አርሰናል" የሚለውን ስም የሚያስተጋባበት፣ የሻምፒዮንስ ሊግ የክብር ዋንጫ የአሸናፊዎቿን እጅ የምትስምበት ታላቅ ዕለት ነው።
ይህ ስሜት የሁላችንም ነው፤ ይህ ፍቅር የመላው መድፈኞች ነው!
ይህንን በጉጉት የምንጠብቀውን ታሪካዊ ድል ይበልጥ ልዩ ለማድረግና ደስታዬን ከእናንተ ከውድ የፌስቡክ ተከታዮቼና ጓደኞቼ ጋር ለመጋራት የዛሬውን ውጤት በትክክል ለሚገምቱ የመጀመሪያዎቹ 5 ፈጣን ኮሜንት አድራጊዎች የእያንዳንዳቸው ስልክ ላይ የ500 ብር የሞባይል ካርድ ይሞላላቸዋል!

ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ኢትዮጵያ ከታላላቅ እስከ ትናንሽ የፈተናዎች ማዕበል ውስጥ አልፋለች። ሀገራዊ አንድነታችንን ለመፈተን፣ የነገ ተስፋችንን ለማጨለምና ጉዟችንን ለማስተጓጎል የገጠ...
29/05/2026

ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ኢትዮጵያ ከታላላቅ እስከ ትናንሽ የፈተናዎች ማዕበል ውስጥ አልፋለች።

ሀገራዊ አንድነታችንን ለመፈተን፣ የነገ ተስፋችንን ለማጨለምና ጉዟችንን ለማስተጓጎል የገጠሙን ተግዳሮቶች ጥቂት አልነበሩም። ነገር ግን፣ ሀገራችን በእነዚህ ሁሉ መከራዎች መሃል ቆማ አልተንበረከከችም፤ ይልቁንም ፈተናዎችን ወደ ዕድል፣ ዕንቅፋቶችን ወደ ስኬት መሰላል በመቀየር፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሁሉም ዘርፍ የሚደነቁ ስኬቶችንና ታላላቅ ታሪካዊ ድሎችን በደማቅ ቀለም ከትባለች።

ይህንን የለውጥ ዘመን ካለፉት ሥርዓቶችና ከቀደሙት የፖለቲካ ልምዶች ፍጹም ለየት የሚያደርገው ታላቅና ህያው እውነት አለ። ቀደምት ሥርዓቶች ችግሮችን በቢሮክራሲ ማዕቀፍ ውስጥ አፍኖ በማቆየት፣ የወረቀት ሪፖርቶችን በማከማቸትና ከሥራ ይልቅ የፖለቲካ የበላይነትን በማስቀደም የሚታወቁ ነበሩ።

ፕሮጀክቶች ሳይጀመሩ የሚቀሩበት፣ ከተጀመሩም ለዘመናት የሚንጓተቱበት ሲሆን፣ የለውጡ መዋቅር ግን ይህንን ስብራት በመጠገን፣ አገር በቀል እውቀትና ብሔራዊ አቅምን ማዕከል ያደረገ አዲስ ፍልስፍና ይዞ ብቅ ብሏል። የዚህ ዘመን መዋቅር ከቃላት ባለፈ በተግባር የሚለካ፣ የፕሮጀክቶችን የማስፈጸም አቅም ወደ ላቀና ወደ ፈጣን የውጤት ምዕራፍ ያሻገረ የሥራ ክህሎት መገለጫ ነው።

ይህ የእምርታ ፍልስፍና በምድር ላይ ያሰፈራቸው አሻራዎች ዛሬ በጉልህ ይታያሉ። ከከተማ እስከ ገጠር የተዘረጉት ዘመናዊ የኮሪደር ልማቶችና መሠረተ ልማቶች የሀገራችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የዜጎችን የመኖር ክብር ከፍ አድርገዋል፤ የከተሞችን ውበት ከቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር ረገድ የቀደሙት ሥርዓቶች ጨርሶ ያላሰቡትን አዲስ መዋቅራዊ እይታ አምጥተዋል።

ግብርናውን ብናይ፣ የቀድሞዎቹ መሪዎች በዕርዳታ እህልና በጥገኝነት አስተሳሰብ ላይ ሲያተኩሩ፣ የዚህ የለውጥ ጉዞ ግን እንደ “ኢትዮጵያ ታምርት” እና "የኢትዮጵያን ይግዙ" ባሉ አገር በቀል ጥረቶች አዲስ የኢኮኖሚ ነፃነት ምዕራፍ ከፍቷል። በበጋ ስንዴ ምርታማነትና በወጪ ንግድ የታየው ተዓምር የሀገሪቱን ታሪክ ቀይሯል።

የዚህ ታላቅ የትውልድ ምንዳ ማሳያ የሆኑት ደግሞ በስትራቴጂካዊ ቁርጠኝነት የተጀመሩትና ፍሬ እያፈሩ ያሉት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ናቸው።
ለዘመናት የነበረብንን የግብርና ግብዓት ጥገኝነት ለመስበር የተጀመረው የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን አፈር በራሷ አቅም ለማበልጸግና የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተጣሉ የጽናት መሠረቶች ናቸው።

ከዚህ ጎን ለጎን፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚንና ታዳሽ ኃይልን ከእውነተኛ የገጠር ልማት ጋር ያገናኙት የባዮ ጋዝ ፕሮጀክት፣ ከትናንሽ አርሶ አደሮች ጓሮ እስከ ትላልቅ ማዕከላት የተዘረጉ የኃይልና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ምንጭ በመሆን የገጠሩን ማኅበረሰብ ሕይወት እያደሱ ይገኛሉ። እነዚህና ሌሎችም ከታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች እስከ ትናንሽ የሕዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ የሆኑት ሥራዎች ሁሉ ዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ በክብር የሚመግቡ ዘላቂ ምንዳዎች ናቸው።

ከዚህም ባሻገር፣ የትውልድ የዘመናት ህልም የሆነውና የህዝባችንን አንድነት ያጠናከረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች መነቃቃትና በዓለም አቀፍ መድረክ ያስመዘገብናቸው የዲፕሎማሲ ድሎች የኢትዮጵያን ታላቅነት ዳግም ያስመሰከሩ የክፍለ ዘመኑ ደማቅ አሻራዎች ናቸው። ቀድሞ ከነበረው ተሽኮርማሚ የዲፕሎማሲ መዋቅር የአሁኑ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ያስቀደመ፣ በልማት አጋርነትና በራሷ ሙሉ አቅም ብሎም ቁርጠኝነት ላይ የቆመ ንቁ፣ ስልታዊና ክብሯን የሚያስጠብቅ መሆኑ ልዩነቱን ጉልህ ያደርገዋል።

ሆኖም፣ እነዚህን ሁሉ

የጋራ ሀብታችን፣ የጋራ መድረሻችን ነው! የደቡቡ ውበት፣ የሰሜኑ ኩራት፣ የምስራቁ እሴትና የምዕራቡ ጥንካሬ የአንድነታችን መገለጫዎች ናቸው። ዛሬ ልዩነቶቻችንን ወደ ማራኪ ውበት፣ ባህላዊ እሴ...
26/05/2026

የጋራ ሀብታችን፣ የጋራ መድረሻችን ነው! የደቡቡ ውበት፣ የሰሜኑ ኩራት፣ የምስራቁ እሴትና የምዕራቡ ጥንካሬ የአንድነታችን መገለጫዎች ናቸው።
ዛሬ ልዩነቶቻችንን ወደ ማራኪ ውበት፣ ባህላዊ እሴቶቻችንን ደግሞ ወደ ጠንካራ ብሄራዊ ትስስር ድልድይነት የምንቀይርበት ልዩ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።
በአንድ የጋራ የብልጽግና እና የልማት ግብ ስር በቁርጠኝነት አብረን እንትጋ፣ አብረን እንደግ፤ የሀገራችንንም እምቅ አቅም በጋራ ፍሬያማ እናድርግ!

ካልተዋጠላችሁ ዳስ ጣሉ! ወጣትነት የሀገር ሉዓላዊነትና የዕድገት ማገር እንጂ፣ የዕድሜ መባከኛና የባዶ ትርክት ማስተጋቢያ አይደለም። ነገር ግን ዛሬ ላይ የምናስተውለው የወጣቱ የስነ ልቦና ስ...
25/05/2026

ካልተዋጠላችሁ ዳስ ጣሉ!

ወጣትነት የሀገር ሉዓላዊነትና የዕድገት ማገር እንጂ፣ የዕድሜ መባከኛና የባዶ ትርክት ማስተጋቢያ አይደለም። ነገር ግን ዛሬ ላይ የምናስተውለው የወጣቱ የስነ ልቦና ስብራት፣ ሀገርን ከመገንባት ይልቅ ለሀገር ሸክም ወደ መሆን እያደላ የመጣበት አስከፊ እውነታ ላይ ጥሎናል። ሀገር የምትገነባው በላብና በሥራ እንጂ በወሬና በምኞት አይደለም!
ሥራን ሳይንቁ፣ በቁርጠኝነት በትጋት በመሥራት ራስን መቀየርና ባለራዕይ መሆን ሲገባ፣የዛሬው ወጣት ግን ገና በጠዋቱ ጡረተኛ፣ በየፖለቲካው አውድማ በቀላሉ የሚነዳና የሚዘወር ሆኖ ይታያል።
ከሁሉም በላይ የሚያሳፍረው እውነታ፤ በገዛ ሀገሩ ለመሥራት የሚሸማቀቀውን ያህል፣ ስደትን መርጦ ባዕድ ሀገር ሲሄድ ኢጎውን ሰብሮና ክብሩን ጥሎ ከሁለት በላይ ፈረቃዎችን መጋፈጡ ነው። በሀገሩ ግን ዕድሎችን ከመፍጠር ይልቅ፣ ዓይኑን ጨፍኖ በጥላቻ የለውጥ ጉዞን ያጣጥላል፤ ማንሰራራቷን ይነቅፋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የብልፅግና ተምሳሌትነቷን በተግባር እያረጋገጠች ነው። ከጫፍ እስከ ጫፍ ብዙ እመርታዎች፣ ብዙ ተስፋዎችና እምቅ ምንዳዎች ከፊታችን ተደቅነዋል። ከመሠረተ-ልማት እስከ ከተማ ውበት፣ ከግብርና አብዮት እስከ ኢንዱስትሪ መነቃቃት፣ ከዲፕሎማሲ ስኬት እስከ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ የታዩ ለውጦች እውን ናቸው። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዋይታን ገታ አድርገን ዙሪያችንን መቃኘት ግድ ይለናል። ምናልባት ባለፉት ዘመናት ታሪክ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ታላቅ አሻራ አይተን ስለማናውቅ መቀበል አቅቶን እንዳይሆን? እውነታው ካልተዋጠላችሁ ደግሞ ዳስ ጣሉ!

ዓላማችን አንድ፤ግባችን ብሩህ ይሁን!

የሀገር ህልውና እና ጉዞ የሚወሰነው በገጠሟት ፈተናዎች ልክ ሳይሆን፣ ፈተናዎቹን ተሻግራ በምትገነባው የፅናት ማንነት ነው።እያንዳንዱ የፈተና ምዕራፍ አዳዲስ የጥንካሬና የብልሃት መንገዶችን ያ...
23/05/2026

የሀገር ህልውና እና ጉዞ የሚወሰነው በገጠሟት ፈተናዎች ልክ ሳይሆን፣ ፈተናዎቹን ተሻግራ በምትገነባው የፅናት ማንነት ነው።
እያንዳንዱ የፈተና ምዕራፍ አዳዲስ የጥንካሬና የብልሃት መንገዶችን ያመላክተናል። ዛሬ ላይ የምናያቸው ስትራቴጂካዊ ስኬቶችና የተጀመሩ ዘላቂ የልማት ስራዎች፣ በማዕበል መሀል ሳይናወጡ አርቆ ማየት የቻሉ ባለራዕይ እይታዎች ውጤቶች ናቸው።
እውነተኛ መሪነትና ስልታዊ ጉዞ የሚለካውም፣ ጊዜያዊ እንቅፋቶችን ወደ ትልቅ የዕድል መድረክ በመቀየር የነገን ብሩህ ተስፋ ዛሬ ላይ ማረጋገጥ ሲቻል ነው።
ይህንን የብልፅግና እና የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ የውጭ ተመልካች መሆን አንችልም።
እያንዳንዳችን በየተሰማራንበት ሙያዊ መስክ የምናሳየው ቁርጠኝነት፣ የምናመነጨው የፈጠራ ሃሳብ እና የምናበረክተው ስትራቴጂካዊ አስተዋፅኦ የሀገራችንን የነገ ታሪክ የሚቀይር ዋናው ሞተር ነው።
በትናንት ተግዳሮቶች አንገታችንን አንደፋም፤ ይልቁንም ካለፉት ስህተቶች እየተማርንና ጥንካሬዎቻችንን እያጎለበትን ወደፊት እንራመዳለን።
የእኛ መመሪያ የትናንት ጥላ ሳይሆን፣ የነገው ታላቅ የጋራ ራዕያችን ነው!

በዚህች ፈታኝ አለም ውስጥ ፅኑ ሆኖ ለመቀጠል ቀና ያለ አንገት፣ የማይናወጥ እምነትና ጠንካራ ስብዕና ይጠይቃል። የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የታሪክ ተገዢ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ፣ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳ...
22/05/2026

በዚህች ፈታኝ አለም ውስጥ ፅኑ ሆኖ ለመቀጠል ቀና ያለ አንገት፣ የማይናወጥ እምነትና ጠንካራ ስብዕና ይጠይቃል።
የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የታሪክ ተገዢ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ፣ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን ሀገር አሻጋሪ የመሆን ትልቅ እድል የገጠመው የታደለ ትውልድ ነው።
ይህ ሊሆን የቻለው፣ በታሪካችን ማህደር ውስጥ ቀደምት መሪዎች ሊደፍሩት ያልቻሉትን ደፍሮ፣ ታስቦ የማይታወቀውን አቅዶና በተግባር ፈጽሞ እውን ያደረገ፣ የሀገራችንን ገፅታ በአስደማሚ ሁኔታ የቀየረ የለውጥ አባት መሪ በማግኘታችን ነው።
ነገር ግን እኛ አሁንም ወደ ኋላ መመልከትን እናዘወትራለን፤ ወደ ፊት መሻገሩ ሲያቅተንና መንገዱ ሲጠበን እንስተዋላለን።
ነገር ግን ልብ ልንል የሚገባው፤ ኢትዮጵያ ቀና ብላ እንዳትቆም ለአርባ ዓመታት ታቅደው የተሸረቡ የሴራ ድሮችን በጣጥሶ፣ የተደራረቡ ፈተናዎችንና መዋቅራዊ እክሎችን ጥሶ ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ዛሬ ፍሬ አፍርቷል። በመሆኑም፣ በፈተናዎች መሀል ድልን እያበሰረ፣ የናፈቅነውን ተስፋ ወደ ሚጨበጥና ወደሚታይ ብርሃን ለቀየረልን መሪያችን እውነተኛ ክብርና እውቅና መስጠት፣ መልካም ስራዎችን ማበረታትና የጀመርነውን የልማት ጉዞ ማፋጠን ይገባናል።
ከፊታችን ያሉትን ፈተናዎች በጋራ ድል ለማድረግ አዕምሮና ልባችንን በቅንነት እንክፈት፤ ለዘላቂ የሀገር ግንባታም ሁላችንም የበኩላችንን ታሪካዊ ኃላፊነት እንወጣ!

ዓላማችን አንድ፣ ግባችን ብሩህ ይሁን!

ዘመኑ የከፍታ ነው” ስንል ይበልጥ ትርጉም ሊኖረው የሚችለው፣ በሀገራችን ያሉትን ነባራዊ እውነታዎች ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር እያመጣጠንን ስንጓዝ ነው። በአሁኑ ወቅት የኑሮ ውድነት ጫና እና የ...
19/05/2026

ዘመኑ የከፍታ ነው” ስንል ይበልጥ ትርጉም ሊኖረው የሚችለው፣ በሀገራችን ያሉትን ነባራዊ እውነታዎች ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር እያመጣጠንን ስንጓዝ ነው።

በአሁኑ ወቅት የኑሮ ውድነት ጫና እና የሚስተዋሉ የሰላምና ጸጥታ እጥረቶች፣ ከተመዘገቡት ስኬቶች ጎን ለጎን በትኩረት ሊታዩና ዘላቂ ምላሽ ሊሰጣቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው።

በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩት የልማት ስራዎች እጅግ የሚበረታቱና የሚደነቁ ቢሆኑም፣ ልማቱ ይበልጥ ፍሬያማ የሚሆነው የዜጎችን የእለት ተእለት ህይወት ማቅለልና ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ሲችል ነው።
በመሆኑም፣ አሁንም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በልዩ ትኩረት በመመልከት፣ የሰላም እጥረትንና የኑሮ ጫናውን በዘላቂነት መቅረፍ እንዲሁም የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን ይገባል።
የገጠሙንን ፈተናዎች በጋራ ጥረትና በግልጽነት ማለፍ የምንችለው መዋቅራዊ አሰራሮችን ይበልጥ በማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ጫናውን የሚያቃልሉ ስራዎችን በቁርጠኝነት በመስራት፣ እና የህግ የበላይነትን በማስከበር ላይ የተመሰረተ ነው።
እያንዳንዱን የሰላምና የልማት ስራ በስትራቴጂካዊ ብልሃትና በፅናት በመምራት ዘላቂ የሀገር ግንባታን ማረጋገጥ ይቻላል።

ወጣትነት የሚነድ እሳት ነው፤ ፈተና ሲበዛ የሚጠፋ ሳይሆን፣ ይበልጥ የሚቀጣጠል! እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ነገሮች አልጋ በአልጋ ሲሆኑ ሳይሆን፣ እንደ ሚኬል አርቴታ አርሰናል በፈተናዎችና በ...
18/05/2026

ወጣትነት የሚነድ እሳት ነው፤ ፈተና ሲበዛ የሚጠፋ ሳይሆን፣ ይበልጥ የሚቀጣጠል! እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ነገሮች አልጋ በአልጋ ሲሆኑ ሳይሆን፣ እንደ ሚኬል አርቴታ አርሰናል በፈተናዎችና በውድቀቶች ውስጥ አልፎ፣ በትዕግስትና በቁርጠኝነት ለአሸናፊነት መብቃት ሲቻል ነው።

አርሰናል ዛሬ ለደረሰበት የድል ማማ የበቃው በአንድ ጀምበር ሳይሆን፣ በሂደት ላይ እምነት ጥሎ፣ በትጋትና ባለመታከት በመስራቱ ነው። ወጣትነትም እንደዚሁ ነው በጉልበት መክበር፣ በእውቀት መመራመርና በተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ዓላማ መገስገስ!

ሀገርን መለወጥ በማማረር ሳይሆን፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየርና በስራ ፈጠራ የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ ላይ መሳብ ነው። ቁርጠኝነትና ትዕግስት ካለ፣ መነሻችን የትም ይሁን የት፣ መድረሻችን ታላቅ ስኬት እንደሚሆን እሙን ነው!

Team Arsenal!!
Good Luck! ⚽️

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Iftu Anwar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share