አልጀዚራ. Ethiopia

አልጀዚራ.  Ethiopia Oduu lolaa dhugaa fii haaraa isiniin geenya./ትኩስ የጦረነት ዜና እንድ ደርሳቹ

23/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Haji Kedir, Abdulbaari Abbamaccaa, David Covenant Man, Jemal Ilu Man

17/08/2025

Silesia DL Record!

Watch as Ethiopia’s Gudaf Tsegay stormed to victory in Silesia with a Meeting Record 3:50.62 — the 5th fastest women’s 1500m in history!

🔥🇪🇹

Fillannoon Majliisa biyyaalessaa boru eegalaFinfinnee, Hagayya 8, 2017 (AE)- Filannoon Majliisa Biyyaalessaa boru eegala...
14/08/2025

Fillannoon Majliisa biyyaalessaa boru eegala

Finfinnee, Hagayya 8, 2017 (AE)- Filannoon Majliisa Biyyaalessaa boru eegala jedhe Boordiin Raawwachiistuu Filannoo Mana Maree Dhimmoota Islaamummaa Itiyoophiyaa. Walitti Qaban Boordii Filannichaa Dooktar Abdulaaziiz Ibraahim ibsa kennaniin, Filannoo Majliisa Biyyaalessaaf galmeen filattootaa fi hojiileen filannoon duraa hojjetamuun xumuramuu himaniiru. Wayita ammaa qophii boqonnaa filannoo xumuramuun gara filannootti ce’ameera jedhan. Haaluma kanaan filannichi boru jalqabuuf akka tahu ibsaniiru.

14/08/2025

በሕገ ወጥ ተግባራት ላይ የተሳተፉ 310 የምግብ ተቋማት ታገዱ
++++++++++++++++++

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በሕገወጥ ተግባራት ላይ የተሳተፉ 310 የምግብ ተቋማት መታገዳቸውን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈፃፀም አስመልክቶ መገለጫ ሰጥቷል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በምግብ፣ በመድኃኒት፣ በሕክምና መሣሪያዎች፣ በመዋቢያ፣ በትምባሆና በአልኮል ምርቶች ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር አድርጓል።

ከክልሎች ጋር በመሆን ባካሄደው የቁጥጥር ስራ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ ባካሄው የቁጥጥር ስራ በተለይ በምግብ ዘርፍ በቁጥጥር ወቅት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ማግኘት መቻሉን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ርምጃዎች መውሰዳቸውን አሳውቀዋል፡፡

ከህገ ወጥ ተግባራቱ መካከልም፣ የመጠቀሚያ ጊዜያቸዉ ባለፈበት ጥሬ ዕቃ ምርት ማምረትና ባዕድ ነገር መጠቀም፣ ምርት ግብአትን በአግባቡ አለመያዝ፣ በነፍሳት የተበላ፣ የተበላሸ ግብአት በማምረቻ ተቋማት መገኘት፣ በደረጃ መሰረት የተሟላ ገላጭ ፅሁፍ የሌላቸዉ ምርቶች ማምረት፣ የተከለከለ ጥሬ እቃ ተጠቅሞ ምርት ማማረት እና እንደ ግብአት ያልተጠቀሙትን ግብአት ምርቱ እንዳለዉ አድርጎ በምርት ገላጭ ፅሁፍ ላይ መፃፍ እንደሚገኙበት አብራርተዋል፡፡

በመሰልና ሌሎችም ህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው በተገኙ የምግብ አምራቾች፣ አስመጪዎች እና አከፋፋዮች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደተወሰደ ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ‹‹285 የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ 384 ስረዛ፣ 39 እሸጋ እና 310 የሚሆኑት ላይ የእገዳ ርምጃዎች ተወስዷልም›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚያደርገውን ቁጥጥር በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስገነዘቡት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ህብረተሰቡም ህገ ወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለተቋሙም ሆነ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ምን እያሉን ነው? ከሁለት ሳምንት በፊት፤ ናይሮቢ የካምፓላ እንግዳዋን ከፍ ባለ ፕሮቶኮል ተቀበለች፡፡ ፍፁም አረንጓዴ አፀዱን በቀዩ ምንጣፍ ያደመቀው የናይሮቢ ስቴት ሃውስ መስተንግዶም በካም...
14/08/2025

ምን እያሉን ነው?

ከሁለት ሳምንት በፊት፤ ናይሮቢ የካምፓላ እንግዳዋን ከፍ ባለ ፕሮቶኮል ተቀበለች፡፡ ፍፁም አረንጓዴ አፀዱን በቀዩ ምንጣፍ ያደመቀው የናይሮቢ ስቴት ሃውስ መስተንግዶም በካምፓላ እንግዶች ዘንድ የተወደደ ሆነ፡፡ ከጥቅል ግቦች ውስጥ ንግድና ኢንቨስትመንትን ወደላቀ ምዕራፍ ለማሻገር ያለመው ይፋዊ ጉብኝት፤ ውይይቶችን አካሂዶና ስምምነቶችን ፈርሞ መቋጫውን የርዕሳነ ብሔሮቹ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ አድርጓል፡፡

14/08/2025

ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፡፡ 3ኛው የዕውቀት ጉባዔ “የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራዎችን በመጠቀም ለፋይናንስ ዘርፉ አዳዲስ ገበያዎችን እና ማሳያዎችን መክፈት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

14/08/2025

በአማራ ክልል ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ተሰበሰበ
++++++++++++++++++++++++++++
በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር መሰብሰቡን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሀብት አሰባሰብ አስተዳዳር እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፃም ግምገማ እና የ2108 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ የተገኙት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት እንደገለፁት፤ ማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ግቡን እንዲያሳካ ዋነኛው እና መሰረታዊው ጉዳይ ማኅበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ሀብት መሰብሰብ ነው።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ለማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት የሚሆን ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ብር መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድንን ጥቅም እና አገልግሎት ማኅብረሰቡ በሚገባ በመረዳቱ ምክንያት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ ሀብት የመሰብሰብ ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

መክፈል ለማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ መንግስት በመሸፈን የተሰበሰበውን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ቀጣይነቱንም በተገቢው ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሀብት አሰባሰብ አስተዳደር እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ ለ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን አባውራ እና አማውራዎች አገልግሎቱን መስጠት እንደተቻለ የገለፁት ደግሞ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የቢሮው ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ክሽን ወልዴ ናቸው።

የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን በክልሉ በ2003 ዓ.ም በሶስት ወረዳዎች መጀመሩን አንስተው፤ አሁን ግን በአማራ ክልል በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎቱን እየሰጡ እንደሆነ ገልፀዋል።

14/08/2025

የቼልሲ ተጫዋቾች ለዲየጎ ዦታ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉ ነው
**********

የቼልሲ ተጫዋቾች ከዓለም የክለቦች ዋንጫ ካገኙት የገንዘብ ሽልማት ግማሹን በቅርቡ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ላለፈው ለዲየጎ ዦታ እና ለወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ቤተሰቦች ለመስጠጥ መወሰናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

13/08/2025

ህፃን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ
************

የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ዕድሜ ያለውን ህፃን በማገት 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ እና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልፀዋል።

ወንጀሉ የተፈፀመው ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 1፡40 ሰዓት ገደማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ህብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

06/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tamire Fikadu Asana, Gammachuu Tolaa Margaa, Dereje Work, Situnaf Calaa, Amanuale Fikrie, Endris Abdu, Teshome Kassa, M Nur Koo, አዲሱ ውዱ, Efrem Galato, Hirpaa Baayana, Asu Siraj, Mohamed Keno, Abdalla Mahammad, Alisa Husein, Hagos Brhanu, Shushay Berhe

Address

Swaziland Street
Addis Ababa
21900

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አልጀዚራ. Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share