17/07/2025
የቴሌቪዥን ግብር‼️
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን ግብር ክፈሉ የሚል ማስጠንቀቂያ እየላከ መሆኑን የደረሰኝ ጥቆማ ያመላክታል።
ከባለፈው 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ50 ኪሎዋት በላይ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች የቴሌቪዥን አገልግሎት በየወሩ ከመብራት ጋር 10 ብር በዓመት አጠቃላይ 120 እንዲከፍሉ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን ማንኛውም ቴሌቪዥን ያለው ሰው ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት በማለት በዛሬው ዕለት ለቴሌቪዥን ባለይዞታዎች የግብር ክፈሉ ማስጠንቀቂያ እየተላከ መሆኑን ከአዲስ አበባ/ቦሌ/የደረሰኝ ጥቆማ ያመላክታል።