Tona Times ጦና ታይምስ

Tona Times ጦና ታይምስ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tona Times ጦና ታይምስ, Media/News Company, Addis Ababa.

ጦና ታይምስ
በወላይታ ሕዝብ ታሪክ፣ ባሕል፣ ቋንቋ፣ ማሕበር፣ ፖለቲካዊና እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሚዲያ ነው፡፡
በሚዲያው የወላይታ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ ሕጸናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አዛውንቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ይቀርባል፡፡

በቅርብ ቀን ይጠብቁ
30/09/2024

በቅርብ ቀን ይጠብቁ

ጦና ታይምስ፡- በቅርብ ቀን በዩቲዩብ እና በሁሉም ማሕበራዊ ሚዲያ ገጾች መተላለፍ ይጀምራል፡፡በቻናሉ፣ ወላይታን የተመለከቱ ዜናዎች፣ ከእንግዶች ጋር ውይይት እና ትረካዎች ይቀርባሉ፡...

98.51% ሲዳማ በክልል ይደራጅ ብሎ ድምፅ የሰጠ ሲሆን ጎጆን የመረጠው ደግሞ 1.48% መሆኑ ተገለፀ። በዚህም የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 47/2 እና 3 ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ ወይም ...
23/11/2019

98.51% ሲዳማ በክልል ይደራጅ ብሎ ድምፅ የሰጠ ሲሆን ጎጆን የመረጠው ደግሞ 1.48% መሆኑ ተገለፀ። በዚህም የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 47/2 እና 3 ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ ወይም ህዝብ የረሱ ክልል የማቋቋም መብት አለዉ በማለት በሚደነግገው መሰረት የሲዳማ ህዝበ ዉሳኔ ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተፈፅሟል ያለው ምርጫ ቦርድ የዞኑ ነዋሪዎች በነፃ ፍቃዳቸዉ በሰጡት ዉሳኔ መሠረት ሲዳማ ክልል ሆኖ መደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘቱን አረጋግጧል።

ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀአዲስ አባበ፣ ህዳር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ...
12/11/2019

ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ
አዲስ አባበ፣ ህዳር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳ እንደገለፁት፥ ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሊት ስራ ተከናውኗል።
ከኮርቻ ግድቡ ቀሪ ስራዎች መካከል 30 ሳንቲ ሜትር ሙሊት ይፈልግ የነበረው የላይኛው አርማታ ሙሊት (ፌስ ስላብ) ስራ ዛሬ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንም ገልፀዋል።
ይህም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራዎች መካከል አንዱ ወሳኝ ስራ መጠናቀቁን እንደሚያሳይ አስታውቅዋል።
በኮርቻ ግድብና በዋናው ግድብ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ስራ የኮርቻ ግድቡ በመጠናቀቁ ዋናውን ግድብ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አቶ በላቸው ተናግረዋል።
ኮርቻ ግድቡ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።via FBC

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ 384 ተማሪዎችን አስመረቀአዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎት ያሰ...
12/11/2019

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ 384 ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎት ያሰለጠናቸውን 384 ተማሪዎች አስመርቋል።
ከተመረቁት 384 ተማሪዎች ውስጥም 67 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣70 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች፣109 የበረራ አስተናጋጆች፣90 የሽያጭና 48 የምግብ ዝግጅት አገልግሎት ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።via FBC

12/11/2019

የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ በፓርቲው ውህደት ዙሪያ ውሳኔ ያሳልፋል!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ በፓርቲው ውህደት ዙሪያ ውሳኔ የሚያሳልፍ መሆኑ ተገልጿል።

ግንባርነቱን ትቶ ወደ ፓርቲነት ለማደግ ሂዳት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውህድ ፓርቲ ለመሆን ያስጠናው ሳይንሳዊ ጥናት በብሄራዊ ድርጅቶች ውይይት ሲደረግበት ቆይቷል።

አሁን ላይም አብዛኛዎቹ ብሄራዊ ድርጅቶች በጥናቱ ላይ ባደረጉት ውይይት የውህደቱ አስፈላጊነት ላይ ሙሉ እምነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የከተማ ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ካሳሁን ጎፌ ውህደቱ በፓርቲያያቸው በኩል ይሁንታ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በተደረገው የውህደት ጥናት ላይ በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ውይይት ያደረገው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በቅርቡ ውህደቱ ፍሬ እንደሚያፈራ እምነቱ መሆኑን የፓርቲው አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተናግረዋል።

ኢህአዴግ አሁን ካለበት ግንባርነት ተላቆ ወደ አንድ ሀገራዊ ፓርቲነት ማደጉም ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን በማረም ጠንካራ ፓርቲ እንዲሆን ያስችለዋል ነው ያሉት። የኦዴፓ የከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ካሳሁን ጎፌ ኢህአዴግ በተቋም እንጂ በግለሰብ ደረጃ አባልነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

ተሳትፎ ሳይኖር ዴሞክራሲ የማይኖር በመሆኑ ትክክለኛ እና እውነተኛ ዴሞክራሲ ለማስፈን ውህደቱ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑንም አክለዋል። አቶ አብርሃም አለኸኝ በበኩላቸው ውህደቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ጉዳይ ላይ በጋራ እንዲወስን የሚያስችል መሆኑን ነው የሚያብራሩት።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-12

(FBC)and@tikvahethiopia

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ በፓርቲው ውህደት ዙሪያ ውሳኔ የሚያሳልፍ መሆኑ ተገልጿል። ግንባርነቱን ትቶ ወደ ፓርቲነት ለማደ.....

ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋን በሁለት አመት ውስጥ እንዲከልሱ የሚያስገድድ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧልአዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋን ከሁለ...
11/11/2019

ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋን በሁለት አመት ውስጥ እንዲከልሱ የሚያስገድድ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋን ከሁለት አመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲከልሱ የሚያስገድድ ረቂቅ የሊዝ አዋጅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።
በሀገሪቱ ከፍተኛ የመሬት ፍላጎት እና ስርቆት መበራከቱ በ2004 ዓ.ም አዲስ የሊዝ አዋጅ እንዲወጣ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፤ ከሚታየው ፍላጎት አንፃር አዋጁ በድጋሚ መሻሻል አስፈልጎታል።
አሁን ላይም ከተሞች የሊዝ መነሻ ዋጋን ከሁለት አመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንዲከልሱ የሚያስገድድ ረቂቅ የሊዝ አዋጅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን፥ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ታዜር ገብረእግዜአብሄር ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው እንዳሉትም የሊዝ ስርአቱ የዜጎችን የመሬት አገልግሎት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስችላል።
የሊዝ ስርአቱ የዜጎችን ከመሬት አገልግሎት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ልማትን ማረጋገጥ የሚችል መሬት ማቅረብ እና የመሬት ዝርፊያን መቆጣጠርን አላማው ያደረገ ነው።
አዲሱ ረቂቅ ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት መሬት ውስጥ ከ10 እስከ 20 በመቶውን ለመኖሪያ ቤት መስሪያ አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸውም ያስገድዳል፤ ይህም የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳል ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም የሊዝ መነሻ ዋጋ ያልከለሱ ከተሞች መሬት በጨረታም ሆነ በምደባ ማስተላለፍ እንደማይችሉም አስቀምጧል።
በረቂቅ አዋጁ መሰረት አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ለተመሳሳይ አገልግሎት ከአንድ ቦታ በላይ ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ መግዛትና መወዳደር እንደማይችልም ያስቀምጣል።
በተጨማሪም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ሳያቀርብ በሁለት አመት ውስጥ ሁለት ዙር አሸንፎ ሳይዋዋል የቀረ የጨረታ አሸናፊ፥ በክልሉ ውስጥ በማንኛውም የከተማ መሬት ሊዝ ጨረታ ለሶስት ተከታታይ አመታት እንዳይሳተፍ እንደሚደረግም አስቀምጧል ነው ያሉት አቶ ታዜር።
የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ እና የመነሻ ዋጋ ዝቅተኛ መሆን እና በፍጥነት አለመከለስ የ2004ቱ አዋጅ ክፍተት እንደነበር ተገልጿል።
ይህም ተጫራቾች በቀላሉ የመሬትን ዋጋ ከፍ አድርገው በማስገባት እና ከጨረታው በመውጣት የመሬት ዋጋን እንዲለውጡ ያደርጋል።
አዋጁ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥልቀት ያለው ምክክር እንዲያደርጉበት መንግስት ፍላጎት በማሳየቱ ምክንያት እንዲዘገይ መደረጉንም ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።via FBC

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩአዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተ...
11/11/2019

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ጋር ተወያዩ።
በውይታቸውም የኢትዮጵያ እና አሜሪካን ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ውይይታቸው የሁለቱን ሃገራት አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑም በዚህ ወቅት ተገልጿል።
የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ባሳለፍነው ቅዳሜ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ከከንቲባዋ ጋርም ከ50 በላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የንግድ ማህበረሰብ አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በትናንትናው እለትም ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል።
በዛሬው እለትም ዋሽንግተን ዲሲ ከአዲስ አበባ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችላትን ስምምነት ከአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ተፈራርመዋል።via FBC

ዩኔስኮ ለሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ልማት 74 ሺህ ዶላር መደበአዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔ...
11/11/2019

ዩኔስኮ ለሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ልማት 74 ሺህ ዶላር መደበ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ልማት የሚውል 74 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መመደቡን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ፓርኩ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰበት የፓርኩ አካል መካከል 65 በመቶው ሳር ስለነበር በፍጥነት ማገገሙም ታውቋል፡፡
በተለይም ሳር በል ለሆኑ የፓርኩ እንስሳት ምቹ የሳር መኖ መውጣቱን ነው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው የተናገሩት።
የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የከፋ የሚባል አሉታዊ ተጽዕኖ አላሳደረም፤ ድርጊቱ ባልታወቀ መንገድ የተፈጸመ እና ሳይንሳዊ መንገዱን ያልተከተለ መሆኑ እንጂ ቃጠሎ በሳይንሳዊ መልኩ እንደሚመከርም ተናግረዋል።
ተፈጥሮ የነበረው ችግር ዳግም እንዳይፈጠር የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮች አስቀድሞ ለመፍታት፣ ማኅበረሰቡን በልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ለማሳተፍ፣ የአካባቢውን የፀጥታ አካላት ከፓርኩ ስካውቶች ጋር በማገናኘት በየቀጠናው ጥብቅ የቁጥጥር ሥራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሠራም አመላክተዋል።
ችግሩ በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸውን ቦታ እና ጊዜ በመለየትም 24 ሰዓት ጠበቅ ያለ ቁጥጥር እንዲደረግ ይሠራል ብለዋል አቶ አበባው።
ዩኔስኮ ብሔራዊ ፓርኩን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
ዩኔስኮ ለባለሙያዎች ስልጠና እና ለቁሳቁስ ማሟያ የሚሆን 74 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መድቧል ነው ያሉት።
ባለሙያዎች የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ውጤታማ የመቆጣጠር ሥራ ማከናወን የሚያስችል ስልጠና በኬንያ መውሰዳቸውንም አስታውቀዋል።
የሰለጠኑት ባለሙያዎችም እስከ ሕዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ ከሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በደባርቅ ከተማ የሚሰጡ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።
በፓርኩ አዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶችም ስልጠናውን ይወስዳሉ ነው የተባለው።
በተያያዘ ዜና በብሔራዊ ፓርኩ 38 ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞች በክረምቱ ተተክለዋል፤ 25 ሺህ ሄክታር የፓርኩ መሬትም በችግኞች ተሸፍኗል።
በችግኝ ተከላ ዘመቻውም የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሌሎችም አካላት ተሳትፈውበታል።
ችግኞቹ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው አቶ አበባው የተናገሩት።
የአካባቢውን ወጣቶች በማሰማራትም የማረም እና የመኮትኮት ስራ እየተከናወነ ነው ያሉት ሃላፊው፥የተተከለው ችግኝ የጽድቀት መጠን እንዲጨምር ከዘርፉ ባለሙያ ጋር ለመሥራት መታሰቡንም ጠቁመዋል።via FBC

የዛሬ ሰኞ ጥቅምት 30/2012 የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች1. የኦዴፓ የኦሮሚያ ከልል ባለሃብቶች በጋምቤላ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እንዲያገኙ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ የአማራ ...
11/11/2019

የዛሬ ሰኞ ጥቅምት 30/2012 የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1. የኦዴፓ የኦሮሚያ ከልል ባለሃብቶች በጋምቤላ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እንዲያገኙ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ የአማራ ክልሉ አዴፓም ተመሳሳይ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች ቀደም ሲል ባለሃብቶች ተረክበው ጥቅም ላይ ያላዋሏቸውን መሬቶች ለማግኘት ከጋምቤላ ክልል ጋር ሲነጋገሩ ቆይተዋል፡፡ ክልሉ ግን ጥያቄውን ገና አልተቀበለውም፡፡ ልማት ባንክ ለአዲሶቹ ባለሃብቶቹ ብድር ለመስጠት ዝግጁ ይሁን አይሁን አልታወቀም፡፡ Link- http://bit.ly/2rupVHv
2. በአማራ ክልል የሚገኘው ጥረት ኮርፖሬት ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሆን ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡ በቀጣዩ ጉባዔ ኮርፖሬቱ የእስካሁኑን ሪፖርቱን እንዲያቀርብ መታዘዙን DW ከባሕር ዳር ዘግቧል፡፡ ኮርፖሬቱ እስካሁን በቦርድ ነው ሲመራ የቆየው፡፡ አሁን በሙስና ተከሰው እስር ላይ ያሉት በረከት ስምዖንም ዘለግ ላለ ጊዜ የቦርዱ ሰብሳቢ ነበሩ፡፡
3. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ላንድ ብዙኻን መገናኛ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ማለቱን ኢትዮ ኤፍኤም 107.8 ዘግቧል፡፡ ማስጠንቀቂያው የተሰጠው ሜዲያ ሕጉን ባለመከተሉ ነው ተብሏል፡፡ የተጣሰው ሕግ ግን ምን እንደሆነና የሜዲያው የትኛው እንደሆነ ባለሥልጣኑ አልተገለጸም፡፡
4. ቅዳሜ ማታ በወልድያ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀስ ሁከት 2 ተማሪዎች ሞተው 13 ያህል ቆስለዋል፡፡ 13 ተጠርጣሪ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የግጭቱ መነሻ ምን እንደሆነ እየተጣራ መሆኑን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡ ሟቾቹ የባሌና አርሲ ልጆች እንደሆኑ ምንጮቹን ጠቅሶ የዘገበው ደሞ አዲስ ስታንዳርድ ነው፡፡
5. የሚንስትሮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመራቱን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የሀገሪቱን አንድነትና ማኅበራዊ ትስስር ከመሸርሸር ለመጠበቅ እንደተዘጋጀ ተገልጧል፡፡
6. ትናንት በድሬዳዋ በተፈጠረ ግጭት 4 ሰዎች በጦር መሳሪያ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው DW ዘግቧል፡፡ ሁለቱ በጥይት ሳይመቱ እንዳልቀረ የሆስፒታል ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ለሕይወታቸው የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ግን አይደሉም፡፡ ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ከ10 በላይ ሰዎች ታክመዋል፡፡
7. ፌደሬሽን ምክር ቤት ለ13 ዐመታት የቆየውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል እንደሻረው ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ በ1999 ዓ.ም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት፣ ለበርካታ ዐመታት ተለያይተው የሚኖሩ ባለትዳሮች ትዳራቸውን እንዳፈረሱ ይቆጠራል ሲል ወስኖ ነበር፡፡ ውሳኔው ግን የበርካታ ሴቶችን የንብረት ባለቤትነት መብት እንደጣሰ አቤቱታ ለምክር ቤቱ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ የሰበር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የቤተሰብ ሕጉን ጭምር የጣሰ ነው- በማለት ቀልብሶታል፡፡via Ethio FM

[ዋዜማ ራዲዮ] የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኦዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የሚመሯቸው ክልል ተወላጅ ባለሀብቶች በጋምቤላ ክልል ለጊዜው እየተሰራባቸው ያልሆኑ ሰፋፊ የእ.....

11/11/2019

የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ
የተበዳይን ደረት በጩቤ በመውጋት እና የተበዳይን አራት ጣቶች በመቁረጥ የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ ።
ተከሳሽ ድርሻዮ ይልማ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፊ.ዲ.ሪ የወንጀል ሀግ አንቀፅ 27/1/ እና 540 የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ተከሳሽ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ራስ ሃይሉ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ በመጠጥ በመገፋፋት ከግል ተበዳይ በሃይሉ ጌታቸው መኖርያ ቤት በመሄድ ተበዳይን በጩቤ የቀኝ ታፋው ላይ በመውጋት እና ደረቱን ሊደግመው ሲል ተበዳይም እራሱን በእጁ ሲከላከል የቀኝ እጅ አራት እጣቶችን እንዲቆረጡ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመው የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል ።
የፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲያስረዳ ሲጠይቀው ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግም የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ሊያስረዱ የሚችሉ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረቡና በማስረዳቱ ተከሳሽ ጥፋተኛ ተብሏል ።
ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ የቀደመ መልካም ባህሪው፣ የመግደል ሙከራው በሙከራ ደረጃ የቀረ በመሆኑ እና ሌሎች የቅጣት ማቅለያዎችን በመያዝ ተከሳሽ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ።via Ethio FM

የአማራ ክልል ምክር ቤት የአራት ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ*************************የአማራ ክልል ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለደ...
11/11/2019

የአማራ ክልል ምክር ቤት የአራት ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ
*************************
የአማራ ክልል ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለደብረብርሃን ቋሚ ምድብ ችሎት የሚሰሩ የ4 ዳኞች ሹመት በመስጠት ተጠናቀቀ።
ሹመቱ የተሰጣቸው በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በሥራ ልምዳቸውና በብቃታቸው ተለይተው የተመረጡ መሆናቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተወካይ ፕሬዚዳንት አቶ አብዬ ካሳሁን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።
በእዚህም የዳኝነት ሹመት የተሰጣቸው ወይዘሮ መሰረት መንግስቱ፣ አቶ ማህተመ ሰይፉ፣ አቶ ቸርነት ገብረጻዲቅና አቶ ማዕረግ ሰንደቁ ናቸው።
ምንጭ፡- ኢዜአ

በአዲስ አበባ ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ ስም አደባባይ ተሰየመ****************************የአዲስ አበባ ከተማ ከአሜሪካኗ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ጋር የእህትማማች ከተማነታቸው መታ...
11/11/2019

በአዲስ አበባ ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ ስም አደባባይ ተሰየመ
****************************
የአዲስ አበባ ከተማ ከአሜሪካኗ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ጋር የእህትማማች ከተማነታቸው መታደሱን ተከትሎ በዋሽንግተን ስም አደባባይ የተሰየመ ሲሆን በከንቲባዋ ቦውሰር ስምም መንገድ መሰየሙን የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ከተሞች የእህትማማች ከተሞች ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በትምህርት፣ በጤና እና በመሰረተ ልማት ዘርፎች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረትም በዋሽንግተን ከተማ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችና ልምዶች በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ስምምነቱን ኢ/ር ታከለ ኡማና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ተፈራርመዋል፡፡
ሁለቱ ከተሞች በኢኮኖሚ፣ ጤና፣ የባህል ልውውጥና አረንጓዴ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ተሰማምተዋል፡፡
በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ መረጃ ለመለዋወጥና በጋራ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ተስማምተዋል፡፡
ሀገራዊ የቢዝነስ ሀሳቦች ማደግ በሚችሉበት ዙሪያ በከተማ አስተዳደርና በንግድ ዘርፍ ማህበራት ደረጃ በጋራ መስራትም በስምምነቱ ውስጥ ተካቷል፡፡
በተለያዩ የፈጠራ ሀሳቦችና የቴክኖሎጂ እድገቶች ላይ በጋራ መስራት፤ የፈጠራ ሀሳቦች እንዲተገበሩ ልምድን መለዋወጥም የእህትማማች ከተማነት ስምምነት ውስጥ ተጠቅሷል፡፡
በጤና ዘርፍ ደግሞ ለዘርፉ ማደግ አስተዋጽኦ ካላቸው የጤና ፖሊሲዎች ጀምሮ በሽታን መከላከል ላይ በሚስሩ ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የሁለቱ ከተማ ነዋሪዎች ያሏቸው ባህላዊ እሴቶችን መለዋወጥና እንዲያድጉ መደጋገፍም በስምምነቱ የተካተተ ነው፡፡
በሁለቱ ከተማዎች ላይ የሚሰሩ የአረንጓዴ ፕሮጀክቶች ላይ ልምድ መለዋወጥ፣ በትራንፖርቴሽንና በኮንሽትራክሽን ዘርፉ ላይ የመፍትሄ ሀሳቦችን መለዋወጥና ድጋፍ ማድረግ በአዲስ አበባና በዋሽንግተን ዲሲ መካከል የእህትማማች ከተማነት ስምምነቱን እንደ አዲስ ለማደስ በተፈረመው ስምምነት ላይ የተካተተ ነው፡፡
በቀጣይም ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማትና ነዋሪዎች የተካተቱበት የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተል ኮሚቴ በሁለቱም በኩል የሚቋቋም ይሆናል፡፡via EBC

ኢራን 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን አሳወቀች---------------------------የኢራንን የነዳጅ መጠን በሶስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለት 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነ...
11/11/2019

ኢራን 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን አሳወቀች
---------------------------
የኢራንን የነዳጅ መጠን በሶስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለት 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን ፕሬዝደንት ሃሰን ሩሃኒ አሳወቁ።
በደቡብ ምዕራቧ ኩዝስታን አውራጃ የተገኘው ድፍድፍ ነዳጅ 2400 ስኩዌር ኪሌሜትር የሚሸፍን ነው ብለዋል ፕሬዝደንቱ።
ኢራን ከአሜሪካ በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ ነዳጅ ወደ ውጭ ልካ ለመሸጥ እየተቸገረች ትገኛለች። ማዕቀቡ የተጣለባት አምና ሲሆን አሜሪካ ከሌሎች የዓለም ኃያላን ጋር የነበራትን የኒውክሌር ስምምነት አልፈልግም ብላ ከወጣች በኋላ ነው።
«ድፍድፍ ነዳጁ 80 ሜትር ወደታች ጥልቀት ያለው ነው። የኢራን ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ብትጥሉም የሃገሪቱ ኢንጂነሮች 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ አጊንተዋል። ይህን ለኃይት ሃውስ መናገር እፈልጋለሁ» ብለዋል ሲል የዘገበው ፋርስ የዜና ወኪል ነው።
አዲስ የተገኘው ድፍድ ነዳጅ በሃገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ የነዳጅ ክምችት ያለበት ስፍራ ይሆናል ተብሎለታል። አህቫስ የተሰኘው ስፍራ በ65 ቢሊዮን በርሜል ትልቁ ነው ይላል አሶሼትድ ፕሬስ።
ኢራን በዓለም ካሉ አበይት ነዳጅ አምራች ሃገራት አንዷ ናት። ከነዳጅ ሽያጭ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢም በቢሊዮን ዶላሮች ይገመታል።
ፕሬዝደንት ሩሃኒ አሁን ላይ ሃገራቸው ያላት የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት 150 ቢሊዮን በርሜል እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ በዓለም አራተኛው ነው። ከኳታር ጋር የምታጋራው ውቅያኖስ ሥር ያለ የተፈጥሮ ጋዝ ባለቤትም ነች።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን እና ሌሎች ስድስት ሃገራት የገቡትን የኒውክሌር ስምምነት አፍርሰው ኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ የቴህራን ምጣኔ ሃብት እያሽቆለቆለ ይገኛል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።via waltainfo

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ማታ በወልድያ ዩኒቨርስቲ የተፈፀመውን ድርጊት አወገዘ********************************ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ያስተላለፈው ...
10/11/2019

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ማታ በወልድያ ዩኒቨርስቲ የተፈፀመውን ድርጊት አወገዘ
********************************
ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ያስተላለፈው መልዕክት ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፡-
በዩኒቨርስቲዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሰላማዊ መማር ማስተማር እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በወልድያ ዩኒቨርስቲ ትናንት ማታ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት አልፏል፡፡
ይሄንን ድርጊት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በፅኑ የሚያወግዘው ሲሆን አጥፊዎቹንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት እና በመለየት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ያስታውቃል፡፡
ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ጊዜ በመረጋጋት ላይ ያለ ሲሆን ከፌደራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበርም አጥፊዎቹን በአፋጣኝ ለይቶ ወደ ህግ የማቅረብና ወደፊት እንዲህ አይነት አፀያፊ ድርጊቶች በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እንዳይፈጠሩ የማድረግ ስራዎችን እየሰራን የምንገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይሄንን አውቆ የበኩሉን አስተዋፅኦና ትብብር እንዲያደርግም እንጠይቃለን፡፡
የወልደያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይደናገጡ ጥፋተኞቹን በማጋለጥ፣ በተመሳሳይ ህገወጥ እና ከሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ ድርጊቶች ላይ ባለመሳተፍና ግጭት ፈጣሪ አዝማሚያዎችን ሲመለከቱም ለሚመለከታቸው አካላት ቀድሞ ጥቆማ በማድረስ የዩኒቨርስቲያቸውን ሰላም እንዲያስከብሩ ጥሪ እናደርጋለን።
የዩኒቨርስቲው የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ክፍተት ያሳዩትን አጣርተው በአስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱም እናሳስባለን።
ሰላም ወዳድ የሆነው የወልድያ ከተማ ማህበረሰብ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ወጣቶች የዩኒቨርስቲውን ሰላም ለማስጠበቅ እያደረጉት ላለው አስተዋፅኦ እያመሰገንን እና ወደፊትም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ እያስተላለፍን ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር via EBC

የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ******************************በእውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ክለብ...
10/11/2019

የበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ
******************************
በእውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችን ጨምሮ የመንግስት እና የግል ተቋማት፣ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት፣ የተለያዩ የወጣት ማህበራት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም የክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚና የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል በክረምት የእናቶችን ቤት ላደሱ፣ ችግኝ ለተከሉ፣ የደም ልገሳ ላደረጉ፣ በተለያዩ የመንግስት ት/ቤቶች እድሳት ላይ ለተሳተፉ የከተማው ወጣቶች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ ስራ በበጋው ወቅትም እንደሚቀጥል የተናገሩት ኢ/ር ታከለ ኡማ "የበጋውን የበጎ ፈቃድ ስራ የምንጀምረው ክረምት የተከልናቸውን ችግኞች ውሃ በማጠጣት እና በመንከባከብ ነው" ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ኢ/ር ታከለ ኡማ ለክረምት የበጎ ፈቃድ ስራ መሳካት ላሳዩት ጠንካራ አመራርና ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ሽልማት እንደተበረከተላቸው ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ ነው - የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት*******************************በወልዲያ...
10/11/2019

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ ነው - የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
*******************************
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ለተከሰተው ግጭት ምክንያት የሆኑ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው ዛሬ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የአማራ ህዝብ ከየትኛውም አካባቢ የሚመጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እንደ ራሱ ቤተሰብ የሚቀበል ነው።
“ትናንት ምሽት ባልታሰበ ሁኔታ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተ ግጭት በሁለት ተማሪዎች ላይ የደረሰው ሞትና በ10 ተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ የማያሳይ ነው” ያሉት ዳይሬክተሩ በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት በደረሰው ጉዳት በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ምንጭ፡- ኢዜአ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913070430

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tona Times ጦና ታይምስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share