
18/03/2025
°ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ዋለ፡፡
ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 9/2017 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችን ያሳተፈበት ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚገኙ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያ መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በትብብርና በቅንጅት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በዓለም አቀፍ 114ኛ በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል'' በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ስኬታማ ወጣት ሴቶች ተሞክሮአቸውን ያካፈሉበት መርሀ ግብር ተከናውኗል፡፡
በዝግጅቱም የከተማችን ከፍተኛ ሴት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ጨምሮ 2000 በላይ ሴቶች የተገኙበት በተለያዩ ኪነጥበብ ክንዋኔዎች ተዘጋጅቶ ታላላቅ እንግዶች በተገኙበት የተሳተፉበት የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
ዘንድሮ በዓሉ በሀገራችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶ ተሳትፎ ይረጋገጣል " በዓለም ዓቀፍ ደረጃ For All Women And Girls Rights: Equality Empowerment!" በሚል መሪ ሀሳብ ሲከበር በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማናቸዉንም ብሎም ሴቶችን ማብቃት ከመቸዉም በላይ ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባዉ አጀንዳ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨመረሻም በዘርፍ ያሉ የክፍለ ከተማ ሰዎች በሴቶች ላይ አተኩሮ የተከረው አከባበር በነበራቸው ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡ በልዩነት ደግሞ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰርፍኬት ተረክበዋል፡፡